ጭራቅ አሕመድ አረመኔ ብቻ ሳይሆን በግርምቢጥ (በተቃራኒ) የሚናገር ግርምቢጣም ነው። ኢትዮጵያ አትፈርስም እያለ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከጫፍ አድርሷታል፣ ሳናጣራ አናስርም እያለ አማሮችን በገፍ አስሮ ይቶርቻል (ቶርቸር ያደርጋል)፣ መግደል መሸነፍ ነው እያል፣ አማራን ገድሎ ሊያሸንፍ ቆርጦ ተነስቷል።
ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ አስር አለቃ ብርሃኑ ጁላና መሰሎቹ ከፋኖ ጋር እንደራደር የሚል ሐሳብ ሲያቀርቡለት፣ አሻፈረኝ ብሏል የሚል ዜና እንዲሰራጭለት አድርጓል። የዚህ ዜና ዓላማ ግን የዜናውን ግርምቢጥ (ተቃራኒ) ነው። ጭራቅ አሕመድ አልደራደረም ብሏል ተብሎ እንዲነገርለት የፈለገው ለመደራደር ስለፈለገ ብቻ ነው።
በመጀመርያ ደረጃ ጭራቅ አሕመድ በዙርያው ያሰባሰባቸው ሰው ተብየወች ከሱ ተቃራኒ የሆነ ሐሳብ ማቅረብ ይቅርና ፊቱን ማየት የሚፈሩ፣ የስካርና የነውር እስረኞች የሆኑ፣ ጭራቅ አሕመድ ወተቱን ጥቁር ካለ ጥቁር የሚሉ፣ አልፈው ተርፈውም ጭራቅ አሕመድ እየሱስ ነው የሚሉ፣ ሁለመናቸውን በጭራቅ አሕመድ የተሰለቡ ጃንደረባወች ናቸው። ስለዚህም እሱ አልደራደርም እያለ የጭን ገረዶቹ እነ ብርሃኑ ጁላና ተመስገን ጡሩነህ እንደራደር ሊሉት አይደፍሩም። ስለዚህም፣ ጭራቅ አሕመድ አልደራደርም የሚለው ፋኖን ለድርድር ለማግባባት ሲል ብቻ ነው።
ጭራቅ አሕመድ መደራደር የሚፈልገው ደግሞ ሊሸነፍ መሆኑን ሲረዳ ብቻ ነው። የሚደራደረው ደግሞ ሰጥቶ በመቀበል ለመስማማት ብሎ ሳይሆን፣ ሊያሽንፈው የተቃረበውን ኃይል በድርድር ሰበብ እየተለማመጠ ካዘናጋ በኋላ ድባቅ ለመምታት ሲል ብቻ ነው። ስለዚህም ማናቸውም ግለሰብም ሆነ ቡድን ከጭራቅ አሕመድ ጋር እደረደራለሁ ብሎ የተነሳ ቀን፣ ቀብሩን መማስ መጀመሩን ሊያውቅ ይገባል።
በተለይም ደግሞ ፋኖ ሆይ ከጭራቅ አሕመድ ጋር እደራደራለሁ ብልህ የተነሳህ ቀን፣ ቀብርህን መማስ መጀመርህን እወቀው። ያማራ ሕልውና ትግል አመራሮች እውነትም የሚታገሉት ላማራ ሕልውና ከሆነ፣ የሚከተሉትን ሁለት ቅድመሁኔታወች (preconditions) ባላስቀመጠ በማናቸውም ድርድር ውስጥ አንገታቸው ቢቆረጥ መሳተፍ የለባቸውም። የመጀመርያው የድርድር ቅድመሁኔታ የጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ መንግሥት ሙሉ በሙሉ መገርሰስና ሙሉ በሙሉ መፈራረስ ሲሆን፣ ሁለተኛው የድርድር ቅድመሁኔታ ደግሞ ጭራቅ አሕመድና ግብራበሮቹ (በተለይም ደግሞ ደመቀ መኮንን፣ ተመስግን ጡሩነህ፣ ስማ ጡሩነህ፣ አበባው ታደሰ፣ ይልቃል ከፋለ እና የመሳሰሉት ብአዴናዊ ግብራበሮቹ) ባማራ ሕዝብ ላይ ለፈፀሙት ወንጀል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ዘላለማዊ መቀጣጫ መሆን ነው።
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com