August 17, 2023
7 mins read

 የህዝብን  የዓማታት ዕስር እና አሳር በማሳነስ እና ማድበስበስ የኢትዮጵያን ችግር መንቀስ አይቻልም

F36jO8GW0AEVukI 1 1 1እንደ አገራችን የዘመን አቆጣጠር ግንቦት ስምንት ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አንድ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ ለራሱ እና ለአገሩ ብሄራዊ ሉዓላዊነት ካለዉ ከፍተኛ ልባዊ ፍቅር እና አክብሮት የተነሳ ዕርስ በራሱ በመደማመጥ እና በመደራጀት ያለማንም መሪ አስተባባሪ አስካዛሬ ከብዙ ዉጣ ዉረዶች ጋር አንድነቱን አስቀጥሏል፡፡

ይሁንና ከዚያች ክፉ ቀን ጀምሮ ጠላት ኢትዮጵያ አለቀላት ያለዉን በዕዉነተኛ እና ሀቀኛ ኢትዮጵያዉን ለመበተን ቋፍ በደረሰችበት እና ያለ ዕረኛ እንደተተወ የበግ መንጋ በሴራ የነበረዉ ማዕከላዊ መንግስት ሲናጋ በለስ የቀናቸዉ የዉስጥ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁኔታዉ ከጠበቁት በላይ ኢትዮጵያን ለመመዝበር እና ለማሳከር ዕድሉን በማግኘት ወደ ስልጣን ኮርቻ ወጥተዋል ፡፡

በህዝብ ተጋድሎ እና ትግል ኢትዮጵያ ጠላት እንዳሰበዉ ሳትሆን ማየት አምኖ መቀበል ያቃተዉ ኢትዮጵያን ዳግም አፍርሶ ለመስራት እና በራስ ልክ ለማድረግ ህዝብን አባር እና ገባር ማድረግ እና የታሪክ ሽሚያ መፍጠር ፣የነበሩትን መልካም ሥራዎች እና ሠሪዎች ማጣጣል እና ማግለል ዋና  የቅስቀሳ እና ወቀሳ (ፕሮፖጋንዳ) ስራ ሆኖ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ቀጠለ ፡፡

የሚሳዝነዉ ግን አሁንም በኢትዮጵያ ህዝብ  የደም እና የህይወት ዋጋ የሚከፈልባቸዉን ብሄራዊ  ትግሎች እና ጥረቶች በማሳነስ እና በማድበስበስ ዕዉነተኝነት እና ትክክለኛነት የሚመስላቸዉ ግለሰቦች በማን አለብኝነት ለህዝብ እና ለአገር ያላቸዉ ጥልቅ ጥላቻ እና ንቀት ዛሬም ሲያስተጋቡ ማየታችን በኃጢያተ እና በስህተት ጎዳና መመላለስ ለለመደ  በአገር ላይ ለሚደርስ ጥፋት እና ክህደት እንደ ልማት እና ታማኝነት መለማመዱ በተለይ በመሪ ኢህዴግ መገለጫ ጠባይ ሆኗል፡፡

ኢህአዴግ ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት በአገር እና ህዝብ ላይ ደጋግሞ ያሳየዉ  ጥፋት እና ክህደት በምድር ላይ በሰዉ ልጆች ከደረሱት ሁሉ ቢበልጥ እንጂ አያንስም ፡፡ ይህም ሆኖ “ስልጣን እና አረቄ እያደር ወደ ራስ  ” አንዲሉ  በአገር እና ህዝብ መከራ መስከሩ  ዕዉነቱን እየገለበጠ መናገሩ አዲስ አይሆንም ፡፡

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የሰሜን ምዕራብ ግዛት ያለዉ ወቅታዊ እና አሳሳቢ ሁኔታ መነሻዉ እና መድረሻዉ ዓለም የሚረዳዉ ሆኖ ከመንስዔ አስከ መፍትሄ በስክነት እና በጥልቀት ከማይት ይልቅ ዞትር እኛ ትክክል ህዝብ ስንኩል ነዉ ማለት ቀዉስ እንጂ ዘላቂ መልስ  አይሆንም ፡፡

በዓማራ ህዝብ ላይ የተዘራዉ የጥላቻ እና ማግለል ሴራ መነሻዉ በኢትዮጵያዊነትም ፤ በማንነትም ሆነ በብሄራዊ  ደረጃ የነበረ ተሳትፎ በተቀናጀ እና በተደራጀ ሁኔታ መገፋት መሆኑ ነበር ፡፡

ይህ ከሆነ ለዓመታት ሲጠየቅ እና ሲጠበቅ የነበር የፍትኃዊነት ፣ ሉዓላዊነት እና ማንነት ….ጥያቄ  ምን እንዳይሆን ብሎ ለዓማትት ማመቅ ያስከተለዉ መነቃነቅ ነበር ፤ ነዉ ፡፡

ዕኮ ለምን ይሆን ዛሬም ለብሄራዊ አብሮነት እና ደህንት የሕዝብን ብሶት እና ምሬት ከመጋራት ይልቅ የዕምየን   ላብየ  ችግሩንም ምንጩንም የተወሰኑ ፣ጥቂት ……እያሉ  ችግር ላይ ችግር መዝራት ፡፡

ለመሆኑ ጥቂት ማን ነዉ  ጥቂትስ ከየት ነዉ   ዕንኳን ብዙሃን ያለበት መሆኑ እየታወቀ  ጥቂት ከአንድ ቢጀምር አንድም ሠዉ ማንቱ እና ነፃነቱ የገሰስ አለበት ወይ ፡፡

ለመሆኑ ጥቂቶች ተነጋሪዎች ትክክል ሲሆኑ ብአዙኃን ኢትዮጵያዉያን ስለ ራሳቸዉ እና አገራቸዉ  ዕዉነተኛ እና ፍትኃዊ  የመብት እና የመኖር ነፃነት ሲሹ  ትክክል የማይሆኑት እንዴት ነዉ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል ፡፡

በመላ ኢትዮጵያም ሆነ በዓማራ ማህበረሰብ ላይ የሚነሱ መሰረታዊ የማንነት እና ሉዓላዊነት ጥያቄ ዕዉንታቸዉ በራሱ በህዝብ ሲረጋገጥ እንጂ በጥላቻ እና በእኔ ብቻ ብሎ ማድበስበስ ፣ የህዝብን እና የአገርን የረጂም ዓመታት መከራ ማሳነስ ለኢትዮጵያዉያን ቀርቶ ለጠላት የትም ያህል ርቀት ቢሄድ ዉሸት እንጂ ዕዉነት አይሆንም ( ሀሰት +ክህደት =ሐሰት ፡፡

“የኢትዮጵያም የዘመናት ችግር በማድበስበስ እና በማለባበስ(በመቅለስለስ) ሳይሆን ከዕዉነት እና ተግባር ጫፍ በመድረስ ብቻ ነዉ ፡፡”

ካለፈ ጥፋት ሆነ ስህተት አለመማር ፣ አለመመከር ፣ አለመሞከር  የንሰኃ ዕንቅፋት ፤ የፖለቲካ ክፋት ምልክት ” ለህዝብ እና ለአገር አለመኖር” ነዉ ፡፡”

 

“አንድነት ኃይል ነዉ  ”  !

 

አለን !

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop