ለዓመታት ኢትዮጵያ ለዜጎቿ የመከራ እና የስቃይ የደም መሬት ሆና መባጀቷ ያለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት በጥቁር ታሪክነቱ የሚዘከር መሆኑን የደረሰበት እና የሚያዉቅ ያዉቀዋል ፡፡
ያልተነካ ግልግል ሲያዉቅ የጠገበም የተራበ ስለመኖሩ አያወቅም እና እንዲሁ በቁስል ላይ እንጨት መሰግሰግ መቆም አለበት ፡፡
ዛሬ በኢትዮጵያ ዕምብርት የግዛት አካል በሆኑት ጎንደር ፣ጎጃም ፣ ወሎ እና ሸዋ ላይ እየሆነ ያለዉ የዓመታት የግፍ እና ሰቆቃ ዕባጭ የጥላቻ እና የምቀኝነት ሰንኮፍ ዉጤት ነዉ ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ አስኳል አንድ አካል የሆነዉ የኣማራ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ፣ በማንነቱ እና በልዑላዊነቱ የማይደራደር ሆኖ ሳለ በነበሩት የዘመናት ጭቆና እና መድሎ ለምን ያለ አንድም ተቋም ፣ድርጂት እና አካል አልነበረም አሁንም የለም ፡፡
ይህም ያሳሰባቸዉ ቅን የቁርጥ ቀን የችግር ጊዜ ደራሾች ኢትዮጵያዉያን በሰከነ እና ሠላማዊ መንገድ ለምን በማለታቸዉ የህይወት መስዋዕት ለህዝብ እና ለአገር ሲሉ ከፍለዋል ፡፡ ዕድለኛ የሆኑት በህይወት ከመሞት መሰንበት ብለዉ ስደትን መርጠዉ ሌሎችም በአገራቸዉ ስለ አገራቸዉ መወገናቸዉ ዕስር ቤቴ ሆነዋል ፡፡
ዕዉነት ለፍትህ እና ለዕኩልነት መናገር እና መቆም አሁን ለደረስንበት ሁኔታ የሚያበቃን ነበር ወይ ፡፡ ህዝብ እና አገር ከስርዓት እና ከአደር ባይነት ወገንተኝነት በላይ መሆናቸዉን ተረስቶ ለስርዓት እና ለአድር ባዮች ሲባል ህዝብና አገር እንዲህ ያለ መሪር ዋጋ ለዘመናት መክፈል ነበረባቸዉ ፤አለባቸዉ ወይ የሚል አንድ ከመቶ ሚሊዮን ጠፋ ብሎ የሚጠይቅ አለመኖሩ የሚያስተዛዝብ ነዉ ፡፡
ዛሬ የዓማራ ህዝብ የሚያሰማዉ ዕሮሮ የዘመናት የጭቆና እና አድሏዊ ብሶት እንጂ ድንገት አለመሆኑን አለመረዳት ያለዉን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረት የሚያወሳስብ መሆኑን መገንዘብ ነብይነት አይጠይቅም ፡፡
የህዝብን እና የአገርን ችግር ከስሩ ተርድቶ በሆደ ሠፊነት እና በአስተዋይነት ለመፍታት ስህተትን መረዳት እና ይቅር ባይነትን መቀበል ይጠይቃል፡፡
የዓማራ ህዝብ ስለ ብሄራዊ አንድነት ፣ ሠላም እና አብሮነት የሚያስተምረዉ ሳይሆን እየኖረ የሚያሳየዉ ሲጠይቅ ዘመናት ተቆጥረዋል ፡፡ ዛሬ ላይ ከሁላችን የሚጠበቀዉ ከኋላ ታሪካችን እና ስህተታችን ተምረን ከምንም ከማንም በላይ ህዝብ እና አገር ትክክል ናቸዉ በማለት ታሪካዊ እና ወቅታዊ ግዴታችንን መወጣት ብቻ ነዉ ፡፡
ከዚህ ዉጭ ለቡድን እና ለስርዓት ጥቅም እና ከንቱ ዉዳሴ አገር እና ህዝብ እንዲማቅቁ እና አንዲጨነቁ ማድረግ በበደል ላይ በደል መጨመር ይሆናል ፡፡ ለኢትዮጵያዉን የማትሆን አገር ለማንም ልትሆን አትችልም ፤አይፈቀደም ፡፡
አንድነት ኃይል ነዉ !
Allen!