May 21, 2023
18 mins read

ምን እናድርግ—?????? ፊልጶስ

346463370 602147608648078 8579688184286236842 n 1 1
#image_title

የማንኛውም መንግሥት”ሀሁ’—– የዜጎቹን ደህንነት መጠበቅ ነው።   የዜጎቹን ደህንነት መጠበቅ ያልቻል አገዛዝና  በዘረፋ ላይ የተመሰረተ ሥርዓት ስልጣኑ “የዛፍ ላይ እንቅልፍ ”  ብቻ ሳይሆን፤  ለዘመናት በደምና በአጥንት የተገነባን  የአገርና የህዝብን አንድንተን ያፈርሳል፤ ኑሮና ህይወትን ያመሰቃቅላል። ሁላችንም ይዞ ይጠፋል ።

በአንጻሩ መሰረታዊ መብቱ ከአባራኩ በወጡ ገዥዎቹ ሲደፈር፡ ከቡር ሃይማኖቱንና ማንነቱን ሲንዱበት፤ ተደራጅቶ ፤ መሪና ተመሪ ሆኖ  ታግሎ  መብቱንና ማንነቱን  ማስከበር የማይችል ዜጋ፤  ህልውናውም አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ነው።

የአገር ልዋአላዊነትና  የህዝብ ህልውና ፈተና ላይ ሲወድቅ፣ ዜጎች  በየቀኑ እደከብት ሲታረዱ፣ ተፈናቅለው መጠጊያ ሲያጡ፣   ለገዥዎች ስምን ዝና ሲባል ከደሃው አፍ በተነጠቀ ገንዝብ ቤተ-መንግሥት ለመገንባትና አዲስ ከተማ  ለመመስረት በሚል ቀልድ ቤታቸው ከላያቸው ላይ ሲፈርስ፣ በአጠቃላይ  የመኖር ዋስትና ሲጠፋ፤ ሥርዓተ አልበኝነት፣ ዘረኝነትና ዝርፊያ  የመንግሥቱ ዋና መገለጫዎች ሲሆኑ፣  አስተዳድራለሁና እመራለሁ የሚለውን መንግስት ነኝ ባይ፤  እንዴትና ለምን? ብሎ የማይጠይቅና የማይሞግት፤ ብሎም  ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ የማይረዳና ለራሱ ህልውና ተደራጅቶ የማይታገል ህዝብ መጨረሻው፤ሌዎ ቶልስቶይ እንዳለው ”–ወላጆች ልጆቻቸውን ይቀብራሉ፤ ወላጆች ደግሞ ያለ ጧሪ ይቀራሉ፤ አገርም ባለቤት አልባ ትሆናለች።—”

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ምድር እየሆነ ያለውም ይኽው ነው። ታዲያ አሁን ያለው የህልውና ጥያቄና ምስቅልቅል ችግር  የመጣው በአንድ ጀምበር  ሳይሆን፤ በሂደት መሆኑን ወደ ኋላ መለስ ብለን፤  ከትላንቱ የመማራ ክህሎት ብናገኝ   እንደሚከተለው ለማስታወስ እንሞክ።

1/ ወያኔ ወደ መቀሌ ሲኮበልልና ጠ/ሚ አብይ አህመድ ስልጣኑን በያዙ ማግስት፤ የታለመው ሥር-ነቀል ለውጥ  መሰረታዊ የሰውልጅ መብት መከበርና የጎሳ ፓለቲካን ማሰወገድ ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንደነትና በእኩልነት  የሚያስ ተናግድ ሥርዓት እንዲመጣ የተደረገው ትግል በተረኝነትና በጋጠውጥ ዘራፊ መንደርተኞች ሲተካ፤ ህዝብ ተደራጅቶ መብቱን ማስከበር ባለመቻሉና የህዝብንም ጥያቄ ያነሱ ወደ እስር ቤት ሲወረውሩ ”እንዲትና ለምን?” ባለማለታችን ፤ ኦነጋዊ ብልጽግና  በማን አልብኝነት  እንዲፈነጭ ተፈቀደለት።  ይህ ብቻ አይደልም ፤ የኦሮሚያ ብልጽግና ለኦነግ ”ኦነግ ሸኔ” የሚል የዳቦ ስም አው’ቶ ያደራጀው  አረመኔ ቡድን፤ እስከ ዚች ሰዓት ድረስ ባንኮችን ሲዘርፍ፣  ከተማን ሲያወድም፣  በመተከል፡ በሸዋ፣ በወለጋና በአፋር ምድር  ዜጋን በማንነቱ ሲያርድ፣ ሲያፍናቅልና ሲያፍን፤  እንዴትና ለምን ? ብለን መንግሥት ነኝ የሚለውን በኃላፊነት ባለመጠየቃችን ዛሬ ”ሸኔ”  የአዲስ አበባን በር እያንኳኳ ይገኛል።

2/ ገና ”ፊንፊኔ ኬኛ” ተብሎ  በአዲስ አብባ  ማንነትና የዲሞግራፊ መቀየር ዘመቻ ሲጀመር፤ ይህ ነው የሚባል ትግል አልተካሄደም።  በተለይም ተቃዎሚ ነኝ የሚሉት ”የዘመኑ  መኢሶኖች” ከብልጽግና ኪስ ገብተው፤ ምንጣፍ ጎታች ሆነው፤  እንታገልለታለን የሚልቱን የዜግነት ፓለቲካ በጎሳ ቀይረውና ለሆዳቸው አድረው ፤ ለአዲስ አበባ የሚታገሉትን ሳይቀር ከኦነጋዊ ብልጽግና ጋር ወግነው ወጉት። ታዲያ ታጋይ አልባና የተከደው የአዲስ አበባ  ህዝብ ዛሬ የምድርን ስቃይ ሁሉ ይከፍላል። ቤቱ በላዩ ላይ ይፈረሳል።  ልጅቹ በጅብ ይበላሉ። መጠጊያ አቶ፣ በገንዛ  አገሩ ስደተኛ ሆኖ ይቅበዘበዛል። የእስከ አሁኑ አልበቃ ብሎ  ወደፊት ሚሊዮኖቹን ለማፈናቀልና ቤት አልባ ለማድረግ ፍጸማዊ በሆነ መንገድ  የመዲነዋን ዲሞግራፊ ለመቀየር” የጫካ ፕሮጀክት”  የሚል እቅድ ተይዟል።

3/ ብልጽግና ከጡት አባቱ ከወያኔ ጋር ጦርነት ሲገባም ሆነ ዛሬ  ” የሰላም ስምምነት” አድርገናል ሲባል፤ ምን ኣይነት ስምምነት? በሚሊዮን ለሚጠጋ ህዝብ ማለቅና መፈናቀል ኃላፊነቱን የሚዎስድና ተጠያቂውስ ማነው?  ስምምነቱሱ  ስለ ወልቅይትና ስለ ራያ ምን ይላል?  ወያኔስ ለምን ትጥቅ አይፈታም?  ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ምን ኣይነት ተጨባጭ ‘ርምጃዎች  ተወሰደ ? ብለን ገዥዎቻችንን ባለመታገላችን ፤ ይባስ ተብሎ ሌላ ጦርነት  በወሎ፡ በጎንደር፣ በጎጃምና በሸዋ ተለኩሷል።

4/ ከአምስት ዓመት በፊት  የተደረገው የህዝብ ትግል ሲመጣና በጠ/ሚ አብይ አህመድ ቃል የተገባውና ብዙዎቹን ያወናበደው፤ ”ህገ -መንግሥቱን ማሻሻልና የጎሳ ፓለቲካን በዜግነት ፓለቲካ መቀየር” የሚል ነው። እውነቱን እንናገር  ከተባለ ጠ/ ሚሩ ገና ወር ሳይሞላቸው ነበር መንደርተኛነታቸውንና ወሮ በላ አጭበርባሪ እምባገነንነታቸውን  በአደባባይ የገለጹትና ለኢትዮጵያ ህዝብ ያላቸን ንቀት ያሳዩትና ።  ለማስታዎስ ሶስት ነገሮችን ብቻ ልግለጽ፤

1/ ”ወታደሮች መፈንቅለ-መንግሥት ሊያካሄዱብኝ ነበር” ብለው ባደረጉት ንግግር” —– እኔ  ተው ብየ እንጅ፤ ከቡራዮና ከሱልልታ በመቶ ሺ ዎች የሚቆጠሩ   መፈንቅለ መንግሥቱን ለማክሸፍ በጉዞ ላይ ነበሩ—-”’ ነው ያሉት።  ሌላው ቢቀር ለውጡን ደግፎ የወጣውን የአዲስ አበባ ህዝብ ና ራሳቸው ባስጠመዱት ቦምብ የሙቱትንና የቆሰሉትን፡ ዜጎች ከቁብ አልቆጠሯቸውም።

2/ ዘጠኝ የሚሆኑ የኦሮሞ የጎሳ ድርጅቶች፤ ጠ/ ሚሩ የሚመሩት በውቅቶ ኦህዲድን ጨምሮ ”ፊንፊኔ ኬኛ” ልዩ ጥቅም ብቻ ሳይሆን እኛ  የባለቤትነት መብት አልን ሲሉ፤  ኢትዮጵያንንም ሆነ አዲስ አበባን ወዴት አየውሰዷት  እንደሆን  የሚያሳይ ትልቅ ምልክት ነበር። ጠ/ ሚሩ በዚህ አላቁምም ፤ የአዲስ አበባን የከንቲባ ምርጫ ሰርዘውና አዲስ ህግ አውጥተው፤ የአዲስ አበባ የምክር ቤት አባል የልሆነ ምክትል ከንቲባ ሾሙ።

3/  ምርጫ  ሲቃረብና የህገ -መንግሥቱ ጉዳይ ሲነሳ  በግልጽ ህገ- መንግሥቱ ”አይነኬ” መሆኑን በተለይም ከጠቅላዩ እስከ  አቶ ሽመልስ እብዴሳ ድረስ አስረግጠው ተናግረዋል።  ተቃዎሚ ነኝ የሚሉትም ዜግነትንና ኢትዮጵያን  በማያውቅ ህገ-መንግሥት እየተመሩ ነው ለምርጫ ውድድር የገቡትና  ለፓርማ ተመራጭነትና ሚኒስተርነት ሥልጣን በገዥው በጎ ፍቃድ የተመረጡት። ታዲያ ሰሞኑን ደግሞ ማጣፊያ እያጠራቸው ሲመጠ ” ህገ-መንግሥቱ ይሻሻላል ” የምትል አዲስ ዜማ ተለቃለች። ግን ማታለልና መዋሸት አይሰለቻቸውም?

ከላይ እንደ ምሳሌ ያነሰዋቸውን ማናም  ዜጋ የሚያውቃቸን    በገሃድ እየተፈጸሙ እያለ ነው ፤ ዛሬ ጠ/ ሚ አብይ አህመድ አታለሉን የሚባለው። እንደ እውነቱ ከሆነ የተታለልነው ራሳችን ነን።  በርግጥ በዚህ ፈታኝ ወቅት ዋናው ችግር መታለላችን ወይም ማታለላቸው አየደልም። አገራችን አሁን ያለችበትና ህዝብ የሚከፈለው መሰዋአትነት እንጅ።

ከዚህ ላይ ልብ እናድርግ፤  ወያኔዎች ላለፍት ዓመታትም ሆነ ላካሄዱት ጦርነትና  የሚፈጽሙት ግፍ፤ በትግራይ ህዝብ ስም ነው። የትግራይ ወገናችን  ግን ምን አተረፈ? ብለን ቆም ብለን እንጠይቅ።  ተረኞቹ ብልጽግናዎች እነ አብይ አህመድና እነ ሽመልስ አብዴሳ   ለሚዘርፍት ገንዘብና ለሚያደርሱት ግፍና በደል፤ የቤተ – መንግሥት ግንባታና የጫካ ፕሮጀክት፣ ማፈናቀልና ማሰር የሚፈጸመው  በኦሮሞ ህዝብ ስም ነው። ግን  በወያኔ ዘመን  በህዝብ ላይ ምን ይፈጽሙ እንደነበር ለግዜውም ቢሆን እንተወውና ፤ ላለፍት አምስት ዓመታት ሰፊው ህዝብ  ከእነሱ ምን አተረፈ? ብለን እንጠይቅ።  በ”ርግጥ  ህዝብን ማፈናቀል፣ የጫካው ፕሮጀክትና ቤተመንግሥት ግንባታ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ነውን?—

—የጎረበቴ ቤት ፈርሶ በላዩ ላይ

ዙሮ እያየ ሄደ እምባውን ‘ረጭቶ አልቅሶ ለሰማይ።

እንዴት?  የት ነህ?   ብየ፣  እኔም እልጠይኩት

”ለአንተ ነው” እያሉ ነው ያፈረሱበት።

እኔን ግራ ገባኝ ፡ መች ጠየኩኝና

አገሩ-መንደሩ መች ጠበበን እና

እንኖር አልነበር በሰላም በጤና።

ሳይገባኝ -ገብቶኛል፡ ሰው ነቀሎ ለአንተ ነው

እምባ ረጭቶ ሄዷል ማነው እሚመልሰው።—–

 

በአሁኑ ሰዓት  የብልጽግና መንግግሥት ማለት ” ብልጭልጭ  ባጌጠ የሬሳ ሳጥን ውስጥ ያለ ሬሳ” ማለት ነው።

አገዛዙ ከየትኛውም ህዝብ ጋር ተለያይቷል። የኢትዮጵያ ህዝብ አንቅሮ ተፍቶታል።   የመግዛት አቅሙን ጨርሶ ለሰራተኛ እንኳን ደመወዝ መክፈል ተስኖት፡ አንድን መንግሥት  እንደ መንግሥት ሊያስቀጥለው የሚችሉት መዋቅሮች እየተበጣጠሱ፤ አዲስ አበባን የሙጥኝ ብሎ የተለመደችውን የጡት አባቱን የወያኔንን  የጎሳ ካርድ  እየተጫዎተና እያላዘነ ነው።

ታዲያ  የአሁን ጥያቄ የዘመኑ ገዥዎቻችን  አገርና ህዝብ ይዘው  ሳይጠፋና አገር አልባ ሳያደርጉን  ፤ ርስ-በርስ እያባሉ ሳያጫርሱን  እንደ ዜጋ፣ እንደ ድርጅት፣ በአጠቃላይ ከጎሳና ከመንደርተኝነት ወጥተን  እንደ ኢትዮጵያዊ ምን እናድርግ? የሚል ነው።

ልብ እናድርግ፤  ወደድንም ጠላንም ይህ  የአጭበርባሪዎቹና የዘራፊዎቹ መንደርተኛ  የብልጽግና አገዛዝ  ማስወገድ ምናልባትም እስከ አሁን የተከፈለው መሰዋአትነት ከበቂ በላይ ስለሆነ፤ ከአሁን በኃላ  ቀላል ሊሆን ይችላል።   ነገር ግን ከዚያስ? መርጊታ መስፍን ወልደ ማርያም  ”ለኢትዮጵያ ህዝብ  አገዛዝን መንቀል ቀላል ነው። ችግሩ ያለው መተካቱ  ላይ ነው።–”   ይሉን ነበር።

 

ወያኔን በህዝባዊ ማዕበል አስወግደን የተተኩትን አሁን ምን እያደረጉ እንዳለ እያያን ነው።  ይህ ሊሆን የቻለ ደግሞ የተደራጅ ኃይል ባለምኖሩ መሆኑን ትላንት ብቻ እየደለም የ1966 አብዮትም በቂ  ማሰተማሪያ ነበር።

ስለዚህም  አሁን ቅድሚያ  መስጠትና በአጣድፊ ማደረግ  ያለብን፤  ራዕይና ጽናት ያለው ፤ ከጎሳና ከዘር ፓለቲካ የጸዳ፡ ለሁሉም  ዜጋ የቆመ ታግሎ ያሚያታግል ድርጅትና  የፓለቲካ አመራር  እንዲኖረን በአገርቤትም ሆነ በውጭ የምንገኝ ዜጎች ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል።  ገዥዎቻችን  ብልጽግናዎች አሁን  ጥምረት የፈጠሩት ከወያኔ ጋር ብቻ ሳይሆን፤ ራሳቸው  ያደራጁትና የዳቦ ስም የሰጡትን ” ኦነግ ሸኔን”  ወደ አዲስ አበባ እያስጠጉ ነው።

ከወለጋ ጫካ ወ”ቶ የማያውቀው ኦነግ፤ እንዴት ዛሬ ደብረ-ዘይትና ጆሞ ደረሰ ብለን ራሳችን እንጠይቅ።ከፊት ለፊታችን የተደቀነውና የተዘጋጀልን ወጥመድ አደገኛና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን ከምንግዜውም በበለጠ መረዳትና ለማይቀረው ትግል መዘጋጀት ለራሳችን ህልውና ስንል መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።

 

በተቻለ መጠን ሁላችንም  በኢትዮጵያ ጥላ ስር በመሰባሰብ፤  ብሎም ብልጽግናዎች  ለማንም የማይበጁ መሆናቸውንና የተዘፈቁበትን የኋላ ቀር አገዛዝ እያጋለጥን፤ ከጥላቻና ከበቀል መንገድ ወጥተን ከተደራጅንና ከታገልን  እናት ኢትዮጵያችንም ሆነ ወገናችን የማንታደግበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም ። ስለዚህም እንደራጅ! እንደራጅ! እንደራጅ!

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!

 

——//—– ፊልጶስ

ግንቦት- 2015

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop