May 3, 2023
7 mins read

የህዝብ መንቃት እና መደራጀት  ለብሄራዊ አንድነት እና ደህንነት አብነት ነዉ

344693413 147241198163670 3681649681900627043 n 1 1 1

የኢትዮጵያ ህዝብ በቅንት እና በአርቆ አሳቢነት ከብሄራዊ ጥቅም እና ስም አኳያ አስቀድሞ የሚያስተባብረዉ ፣ የሚያስተሳስረዉ ፣የሚያደራጀዉ እና የሚመራዉ ኃይል ከፊት ባለመኖሩ ከዚህ ይልቅ በተቃራኒ ከጀርባ በማድፈጥ በመከራ ጊዜ የሚደበቁ ፤በፍስኃ ዘመን አገር እና ህዝብ በችግር  ወላፈን ሲፈተኑ የደረሱትን የክፉ ቀን ደራሾችን ሲያናንቁ እና ሲሳለቁ ማየት ዛሬም እንደጥንቱ ማየት የተለመደ ሆኗል ፡፡

በተለይም የዓለም ጥቁር ህዝቦች በዘረኞች እና በቅኝ ግዛት ናፋቂዎች በባርነት እና በቅኝ ግዛት ቀንበር ጫና በነበሩበት ዘመን ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት መዳፍ ለማስግባት ከሚተጉት የ9ኛዉ ክ/ዘመን ተስፋፊዎች መካከል ኢጣሊያ ለሰሜን እና ምስራቅ አፍሪካ የቅኝ ግዛት ቅርምት ሲታደላት በድጋሚ በተደረገ የ40 ዓመት ዝግጂት የቅኝ ግዛት ጦርነት እና ወረራ ዕግሬ አዉጭኝ ያሉት የዘመኑ ሹማምነት በአገኙት ቀዳዳ ወደ ድሎት እና ስደት አገር ሲኮበልሉ ከህዝብ እና አገር ጋር በፊዉታራሪነት የተዋደቁት ዕዉነተኛ ቁርጥ ቀን የህዝብ ልጆች ነበሩ ፡፡

ይሁንና ከ፭ ዓመት የነፃነት ተጋድሎ በኋላ የድል ብስራት በተነገረበት ማግስት የድል አጥቢያ ጀግና መሳይ እና የኢትዮጵያዉያንን ነፃነት እና የብሄራዊ ልዑላዊ ክብር የሽ ዘመናት ታፍሮ እና ተከብሮ መኖር የማይዋጥላቸዉ የዉጭ እና የዉሥጥ ከኃዲዎች በጨነቀ ጊዜ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከህዝብ ፊት በመሆን አገሪቷን ፣ ህዝቧን እና የዘመኑን ሹማምንት ለአገራቸዉ እንዲበቁ ያደረጉትን የዚያ ዘመን የነፃነት ፋና ወጊዎች በተለያየ ሁኔታ በደል  እና መገለል ደርሶባቸዋል ፡፡

ይህም ኢትዮጵያ ለሞቱላት  የምታቃጥል ረመጥ ዕሳት ፤ ለገደሏት በረከት ሆና እንትቀጥል እና በራስ መተማመን እንዳይኖር ከፍተኛ ሴራ ተሰርቷል፡፡

ይህም ረብ የለሽ በሆነ እና የበሬ ግንባር በማይሆን የባድመ መሬት በተደረገ የዕናት እና ልጂ ( ኢትዮጵያ እና ልጂ ( ኢትዮጵያ እና ኤርትራ)  የአንድ ህዝብ ጦርነት በትንሹ ፸ ሽ ኢትዮጵያዉያን ደም መፍሰስ እና ህይወት መጥፋት ምክነያት ሆኖ ለስልጣን ናፋቂዎች ዕድሜ ማራዘሚያ በማድረግ የዚህ ህዝብ መስዋዕት ደመ ከልብ ሆኗል ፡፡

ይህ ሳይበቃ በብሄራዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት ስሜት በዚሁ በሴራ በታጀለ ጦርነት ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉት እና ከሞት ለተረፉት  የቁርጥ ቀን ልጆች በተለይም የዓማራ ህዝብ ተወላጆች ሹመት እና ሽልማት ሲገባ ክህደት እና ዉርደት ተፈፅሟል ፡፡

ይህ ለ ፫ ጊዜ በሁለት ሽ አስራ ሶስት ዓ.ም. ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና የዓማራን ህዝብ ለመዉረር በህዎኃት የተደረገዉ የወረራ ሴራ መሰረት ከወረራ ባሻገር የህልዉና ጉዳይ ወደ መሆን በመድረሱ የዓማራ ህዝብ እና ቁርጠኛ የህዝብ  ልጆች ባደረጉት ከፍተኛ የሞት ሽረት ትግል ተደርጓል ፡፡

በዚህም ከፍተኛ የድል ዉጤት አገርን እና ትዉልድ ከጥፋት እና ሞት የማዳን ተግባር ተከናዉኖ የብዙዎች ህይወት ዕልፈት እና አካል ጉዳት ፣ የንብረት እና ሀብት ጥፋት ተስተናግዷል፡፡

ሆኖም ለአገር እና ለህዝብ ዋጋ መክፈል ወንጀል የሚሆንበት የሰሜን ምዕራብ እና መኃል ኢትዮጵያ ህዝቦች አመድ አፋሽ ሆኖ በሰላም ስም ጦርነት ተከፍቶበታል፡፡

ይህ ሁሉ በኢትዮጵያዉያን ፣ዓማራ ላይ የሚደረግ የጠላት ሴራ  ኢትዮጵያን ለጥፋት እና ህዝቡነ  ለባርነት ቀንበር ለመዳረግ ተደጋጋሚ የክህደት ተፈፅሟል፡፡

ለዚህም ኢትዮጵያን ሆነ  ኢትዮጵያዉያን ከጥፋት እና ከተደጋጋሚ ጥቃት ለመታደግ የሚያስችል ህዝባዊ እና ብሄራዊ ልባዊ አደረጃጀት እና ሁነኛ አመራር ባለመኖሩ ነዉ ፡፡

ዛሬም ቢሆን የዓማራ ህዝብ ህልዉና የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት እና የዜጎች ደህንነት  ዋስትና ሊሆን የሚችለዉ የዓማራ ህዝብ  የህልዉና እና ነፃነት ትግል የኃይል ሚዛን በዕዉን መኖር እና መረጋገጥ አለበት ፡፡

ለዚህም የኢትዮጵ የቀደመ የዘመናት ታሪክ እና ታላቅነት ለማስጠበቅ  እና ለማስቀጠል የዓማራ ህዝብ በመደረጃት ለራሱ እና ለኢትዮጵያ ህልዉና መደራጀት እና ለነፃነቱ ዘብ መቆም  አለበት ፡፡

በዚህ ረገድ የዓማራ ብሄራዊ ነፃነት ትግል ” አብነት ” መቋቋም እና መኖር በዚህም ወቅቱን የዋጀ የኃይል አሰላለፍ አስካልተፈጠረ ድረስ ላለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት የነበረዉ መከራ እና የኢትዮጵያዉያን  ሉዓላዊነት ጉዳይ ወደ ተበባሰ ደረጃ የሚያመራ መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡

ኢትዮጵያ ያለ ኢትዮጵያዉያን ባዶ እና ንብ አልባ ቀፎ እንደሆነ ስለሚቆጠር ኢትዮጵያዉያንን ማሳደድ የመጨረሻዉ የክ/ዘመናችን መከካድ ከመሆን ዉጭ ሌላ ሊሆን አይችልም ፡፡

 

Allen .A

Unity is power and Power is everything!

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop