April 19, 2023
10 mins read

“እውነቲም ማሞ” ማሞ ምህረቴ ባንዳ ነው ደንቆሮ? (ከ አሁንገና ዓለማየሁ)

ማሞ ምህረቴ 1 1
#image_title

ይልማ ዴሬሳ ከገንዘብ ሚንስትርነት ተነስተው ማሞ የተባሉ ሰው ተሾሙ ። በኃይለ ሥላሴ ጊዜ ነው። ታዲያ አዲሱ ተሿሚ ኦዲት አድርገው መረከብ እንዳለባቸው በመገንዘብ የቀድሞውና አዲሱ የገንዝብ ሚንስትሮች ስብሰባ ይቀመጣሉ።

ይልማ ዴሬሳ “ሁሉም ስነድ ቀረቦልዎታል። ለእያንዳንዱ ወጪና ገቢ ማስረጃው ሰነድ ተያይዟል። ነገር ግን አንድ ሚሊዮን ተኩል* ብር ንጉሡ በትእዛዝ የወሰኑበት አለ እና እሱን ታሳቢ እንዲያደርጉ” ይሏቸዋል። አቶ ማሞ ኦዲቱን ካስደረጉ በኋላ አቶ ይልማን “አንድ ችግር አለ” ይሏቸዋል።

ይልማ “የምን ችግር?”

ማሞ “የሁሉም ሰነድ ተመሳክሮ ሂሳቡም በትክክል ተወራርዷል። አንድ ተኩል ሚልዮን ብር ግን ሰነድ አልተገኘለትም። ጎድሏል ይሏቸዋል።”

ይልማ “እሱንማ ነገርኩዎት ባለፈው። ንጉሡ ያዘዙበት ነው ብዬ አስቀድሜ የገለጽኩልዎትን ዘነጉት?”

ማሞ “እኔ ማንም ይዘዝበት ብቻ ተፈርሞ የወጣበትን ሰነድ ነው የምፈልገው” ብለው ድርቅ ይላሉ።

ይልማ ዴሬሳም በመገረም እየተመለከቷቸው “እውነቲም ማሞ! ንጉሥ በቃሉ ያዛል እንጂ ከመቼ ወዲህ ነው ገንዘብ እየፈረመ የሚወስደው?” አሏቸው ይባላል።

“7ኛ ንጉሥ** ነኝ” የሚለው 3መቶ ምናምነኛ ንጉሣችንስ በፓርላማ ቀርቦ በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር የት እንዳደረስኩት ልትጠይቁኝ አትችሉም ብሎ የለም?

ወደ ዛሬው ነገሬ ልግባና ማሞ ምሕረቴ የተባለ ደንቆሮ አይሉት ባንዳ ኢትዮጵያ የምትፈራርስበትን የመጨረሻ ቁማር ከአይ ኤም ኤፍ ጋር ለመጫወት ቡድን መርቶ አሜሪካ ከርሟል። ለዚሁ ተብሎ በሲአይኤ ማሰልጠኛነት በሚታማው የሃርቫርድ ተቋሙ ‘የኬኔዲ ስኩል ኦፍ ጋቨርመንት’ ተመልምሎ የሰለጠነ እና በWorld Bank ሲሠራ የከረመው ይህ ሰው ማን ነው? ደንቆሮም ሆነ ባንዳ ማሞ ምሕረቴ የጥቃት ዒላማ ያደረጓቸውን ሀገሮች በፖለቲካ ምስቅልቅል ውስጥ አስገብተው በከፍተኛ የኑሮ ቀውስ ጫና ብትንትናቸውን ለማውጣት የብድር ተቋማታቸውን የሚጠቀሙት የምእራባውያንን አጀንዳ ለማስፈጸም ለአሻንጉሊቱ ለአቢይ አህመድ የተሰጠ ታኮ ነው። የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሲሆንም የባንኪንግም ሆነ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ሳይኖረው ነው።

ይኸው ምእራባውያን አቢይና ሕወሃትን በጦርነት አሻኩተው ካንበረከኳቸው በኋላ እጃቸውን በወንጀልና በውድመት ጫና ጠምዝዘው በአዲስ አበባ እጣ አዲሳባንም ኦሮሚያንም  ወክሎ ኦህዴድ እንደተፈራረመው፣ ማሞን ይዘው በኢትዮጵያም በአይ ኤም ኤፍ በኩልም አይ ኤም ኤፍ ተዋዋይ የሆነበት ሁኔታ ተከስቷል

ማሞ ምሕረቴ ባንዳ ካልሆነ ፊደል ቆጠር ደንቆሮ ነው። አይ ኤም ኤፍና ወርልድ ባንክ ምእራባውያን በፖለቲካ ያመስቀሏቸውን ብዙ ሀገሮችን በብድር በተለይም በዲቫልዌሽን ጫና እንዳፈረሷቸው ያላነበበ፣ ያላወቀና ያልተረዳ ፊደል ቆጣሪ መሐይም ነው ማለት ነው። ቼኮስሎቫኪያ፣ ዩጎዝላቪያ፣ ሶቪየት ዮኒየን፣ ሱዳን እና ሌሎችም ብዙ ሀገራት በነዚህ የብድር ተቋማት መሣሪያነት ነው ብትንትናቸው የወጣው ወይም ኢኮኖሚያቸው ድምጥማጡ የጠፋው።

አቢይ በሬው ሆይ ሣሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ የሚል ጨዋታ ይጫወታል። እሱን አቢይን ራሱን ግን ጌቶቹ ሣሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ ብለው ተጫውተውበት ገደል ጨምረውታል። በኖቤል ሽልማት አሞካሽተው፣ ወያኔን እንዲወጋት አበረታተው፣ ብርድ ብርድ እንዳይለው ኢሳያስን ደርበውለት በጦርና በጄኖሳይድ ወንጀል ካጨማለቁት በኋላ በወዲያ በኩል አይዞሽ ብለው ካዘመቷትና ካስወቀጧት ከሕወሃት ጋር አቆራኝተው ኤርትራን በማፍረስ ሙሉ ቀጠናውን የፈረሱ ሀገራት ክምር ለማድረጉ ዘመቻ ፊታውራሪ እያደረጉት ነው። እምቢ ቢል ደሙን ሲያጎርፈው የከረመው ሕዝብ ካልዋጠው እነሱ ራሳቸው የጦርና የጄኖሳይድ ወንጀሉን አጋልጠው ስቅላት ይፈርዱበታል። አሁን ወጥመዳቸው ውስጥ ገብቷልና እንደ ተያዘች አይጥ ቁልጭ ቁልጭ ከማለት በስተቀር ምርጫ የለውም። የሚታዘዘውን ይፈጽማል።

ተላላኪው አቢይ አህመድ ምእራባውያኑ “ሾክ ቴራፒ”*** የሚባለው የዘረፋ ኢኮኖሚክሳቸው እስኪሳካ ድረስ እለት እለት ጆሮ ጭው የሚያደርግ ቀውስ እየጠመቀ፣ ለዘረፋቸው ከለላ ይሰጣል። ሕዝብ በዚህ የማያባራ ቀውስ ተጠምዶ በሀገር ላይ የሚሠራውን የኢኮኖሚ ደባ፣ የአንጡራ ሃብት ዘረፋ፣ የሀገር ሃብት ባለቤትነት ለባእዳን መተላለፍ የሚያስተውልበት እረፍት እንዳይኖረው አበክሮ ይሠራል። ሁሉም የሕልውና አደጋ ተደቅኖበት በሞት ሽረት መካከል የሚንጠራወዝ ዐይነት ስሜት እየተሰማው ከሄደ ለጋራና ለሀገራዊ ጉዳይ ቁብ ሊሰጥ አይችልም። ቁማሩ ይሄ ነው። አዲስ የሚሞከርብን ኤክስፐሪመንት ሳይሆን ፍቱን መግደያ መሆኑ ታውቆ እንድንውጥ የተፈረደብን መርዝ ነው።

 

*አንድ ሚሊዮን ተኩል በምሳሌነት የተጠቀሰ አሓዝ እንጂ ትክክለኛው ሃምሳ ሚሊዮን ይሁን መቶ ሃምሳ ሚልዮን ጸሐፊው ዘንግቶታል።

**አቢይ አህመድ 7ኛ ንጉሥ ነኝ የሚለው በኦነጋዊው የታሪክ እና የሥነ ፍጥረት እሳቤ ስለሚመራ ነው። “መጀመሪያ እግዚአብሔር ዳግማዊ ምኒልክን ፈጠረ። ከቀኝ ጎኑም እቴጌ ጣይቱን ፈጠረለት። “ የሚለው አይነት። ከዚያ በመቁጠር ነው ከሦስት መቶ በላይ ነገሥታት ተመዝግበው በሚገኙባት ሀገር “7 ኛ ንጉሥ ነኝ” ብሎ የደነቆረው፣ የሚያደነቁረው።

***ሾክ ቴራፒ የዘረፋ ኢኮኖሚክስ ቋንቋ ነው። ሾክ ቴራፒ በሕክምና እና ሲአይኤ በሚያካሂዳቸው የወንጀል ምርመራ ሥራዎች ላይ ይውል የነበረ፣  በኤሌክትሪክ ሾክ የሰውን አእምሮ ክውታና ድንጋጤ ውስጥ በማስገባት አዲስ ትእዛዞችን እና አጠባዎችን እንዲቀበል የሚደረግበት ልማድ ነው። ከዚህ በመነሳት ሚልተን ፊሪድማን የተባለ የዘረፋ ኢኮኖሚክስ ባለሙያ ሀገራትን በመብረቃዊ የሽብርና የደንጋጤ ማእበል በመዝፈቅ ተዘራፊዎቹ በጤናማ ሁኔታ ሊቀበሉት የማይችሉትን ለዘራፊዎቹ ብቻ የሚጠቅም የኢኮኖሚ ውልና ስምምነት መጫን እና ተፈጻሚ የማድረግ ስልት ቀርጿል። ለዚህም የኢኮኖሚክስ ኖቤል ሽልማት ተሸላሚ ተደርጓል።  በዚህ ስልትም ብዙ ሀገሮች ተመዝብረዋል፣ ወድመዋል፣ ብትንትናቸው ወጥቷል።  አምስቱ አመት የአቢይ አህመድ የሽብር፣ የጦርነት፣ የተከታታይ ቀውስ ጠመቃ መርሐ ግብር በግልጽ የሚያመለክተው ያንን የሾክ ቴራፒ ኢኮኖሚክስ ትግብራ በኢትዮጵያ ላይ ተፈጻሚ የማድረግ ጉዞን ነው።

 

https://www.independent.org/news/article.asp?id=46

https://www.peoplesworld.org/article/world-bank-and-international-monetary-fu

https://www.jstor.org/stable/160829

https://tesfanews.net/how-the-world-bank-and-the-imf-destroy-africa/

http://erepository.uonbi.ac.ke/bitstream/handle/11295/60212/Githua_Th

e%20impact%20%20of%20Internat%20(IMF)%20and%20the%20World%20Bank%

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop