The Forum of Ethiopians Civic Organizations in the Diaspora
የኢትዮጵያዊነታዊ ድርጅቶች የጋራ መድረክ
በማርች 29፣ 2023 በሰሜን አሜሪካን የሚገኙ ስማቸዉ ከዚህ በታች የተመለከተዉ የሲቪክ ድርጅቶች እና የኢትዮጵያዋን ተቆርቋሪ ስብስቦች በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸው አካል በጋራ በመመስረት አገሪቱ ለገባችበት አደገኛ የስርዓት ቀውስ እና የህልውና አደጋ ተጠያቂ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ እና የሚያራምደው እኩይ የሆነ የአገዛዝ ስርዓትን በሰላማዊ ትግል ለመታገልና ስርአታዊ ለዉጥን ግብ አድርጎ ኢትዮጵያን ለመታደግ የሚሰራ የጋራ መድረክ መስርተዋል።
- እምቢልታ/አገር አድን ኅብረት
- ግሎባል አሊያንስ(GLOBAL ALLIANC FOR THE RIGHTS OF ETHIOPIAN
- የኢትዮጵያ የውይይት እና የመፍትሄ መድረክ(EDF)
- ቪዥን ኢትዮጵያ(VISION ETHIOPIA)
- የዲሲ ግብረ ሃይል
- የኢትዮጵያ ሴቶችመብት ማእከል(CREW)
- አለምአቀፍ የኢትዮጵያዉያን የሲቪክ ድርጅቶች ኔትዉርክ (WE CAN)
- ልዩልዩ የኢትዮጵያዋን ተቆርቋሪ ስብስቦች (concerned Ethiopians)
ድርጅቶቹ በኢትዮጵያ ሃገራችን ላይ እየተከሰተ ያለውን የአገሪቱ ህልውናን አደጋ ላይ የጣለ ሁኔታን በመገምገም የኢትዮጵያ ህዝብ ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ መብቶቹ እንዲከበሩለት ለመታገል በአራት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ የጋራ ራዕይ በመንደፍ በሚከተሉት መሰረታዊ ችግሮች ላይ አብረው ለመስራት ስምምነታቸውን አስፍረዋል።
- 1. ኢትዮጵያ ብዙ ባህል ያለባት የአንድ ህዝብ አገር ስትሆን ለረጅም ዓመታት አገረ መንግስት የመስረተች ታሪካዊት እና ታላቅ የማትከፋፈል አገር ናት። ይህ አንድነታችን የማንደራደርበት ኣቋማችን ነው።
- የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እና ልኡላዊነት የማይደፈር መሆን አለበት።
- ሁሉም ኢትዮጵያውያን ነጻ ዜጎች ሆነው በአገሪቱ በማንኛውም ስፍራ በእኩልነት የመኖር መብት ሊኖራቸው ይገባል።
- 4.ኢትዮጵያ በታላቅ የህልውና ጥያቄ ላይ ገብታለች። አገረ መንግስቱ ለሰላሳ ዓመታት በጸረ ኢትዮጵያ ጠባብ ቡድኖች አመራር በመውደቁ የተነሳ በሙስና፣ በአድልዎ እና በፍትህ አልባ አሰራር በመበከሉ ታይቶ የማይታወቅ ኢሰብአዊ ግፍ በህዝቧ ላይ እየተፈጸመ ነው። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ሰፍኖ ያለውየጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ መንግስትእና ስርዓት አገሪቱን ወደ ሰላም ዲሞክራሲ እና ብልጽግና ሊወስዳት የማይችል በመሆኑ በምንም አይነት ሁኔታ መቀጠል የለበትም። ለእነዚህ እኩይ አሰራሮች በዋናነት ተጠያቂ ስለሆነ ይህንን የጥቂት አምባገነኖች መንግስት የሚያራምደው ስርዓት መእንዲያከትም ትኩረት በመስጠት የዲሞክራሲያዊ የስርዓት ሽግግር ላይ በጋራ በአቋቋሙት መድረክ አማካይነት ለመታገል ተስማምተዋል።
በማከልም በእነዚህ አራት ነጥቦች ላይ የሚስማሙ የሲቪክ ድርጅቶች ሁሉ ይህንን ኅብረትና የጋራ መድረክ አባል እንዲሆኑ ጥሪውን ያቀርባል።
The Forum of Ethiopianist Civic Organizations in the Diaspora
የኢትዮጵያዊነታዊ ድርጅቶች የጋራ መድረክ