March 27, 2023
5 mins read

ነፍሴ ቸኩላለች !!

ማሪዮ ዴ አንድራዴ- ሳኦ ፖውሎ                                                                     1893-1945 ገጣሚ፣ መጽሀፍ ደራሲና የሙዚቃ ሳይንቲስት

ትርጉም ፈቃዱ በቀለ( ዶ/ር)

እስካሁን የኖርኩበትን ዕድሜዬን ቆጠርኩኝ፤ ከእንግዲህ ወዲያ የምኖረው ጥቂት ዓመታት ብቻ እንደሆነ ተረዳሁ።

ልክ እንደህፃን ልጅ ይሰማኛል። አንድ ህፃን ልጅ አንድ ኮሮጆ ውስጥ የታሸገ ከረሜላ ካሸነፈ በኋላ የመጀመሪያውን በጉጉት ያላምጠዋል። እያላመጠ ሲሄድ አንድ ብቻ ሲቀረው የመጨረሻው የበለጠ ይጣፍጠዋል።

ከቁም ነገር ይልቅ ስለውስጥ ደንብና አሰራር፣ እንዲሁም ህግ ብቻ በሚነገርበት ትላልቅ ስብሰባዎችና ዲስኩሮች ላይ በመገኘት ጊዜዬን ማባከን በፍጹም አልፈልግም። ይህ ዐይነቱ ስብሰባ ምንም ዐይነት ውጤት ሳይታይበት የመጨረሻ መጨረሻ ይዘጋል። እንደዕድሜያቸው ልክ አዕምሮአቸው ያልበሰሉና ድርጊታቸው ሁሉ የማይረባ ሰዎችን ማየት በፍጹም አልፈልግም። እንዲሁም በጣም ዝቅተኛ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር ለመታገልና ለመጨቃጨቅ በፍጹም ጊዜ የለኝም። ለራሳቸው ጥቅም ብቻ የሚቅበጠበጡ፣ በራሳቸው ንግግር በሚረኩና ደረታቸውን ከሚነፉ ሰዎች ጋር መታየት በፍጹም አልፈልግም። አታላዮችንና አድርባዮችን እንዲሁም በውሸት ሌላውን ለማሳመን የሚፈልጉ ሰዎችን ማየት ይቀፈኛል።

የሰውን ችሎታ በመጥፎ የሚተረጉሙና፣ራሳቸውን አጉልተው ለማሳየት የሚፈልጉ፣ የዝቅተኝነት ስሜት ያላቸውንና ቀናተኞችን እሸሻለሁ። እንደነዚህ ዐይነት ሰዎችን ሳይ መንፈሴ በጣም ይረበሻል።

ውጤት በሌላቸው ትላልቅ ዲስኩሮች ላይ ለመካፈል በፍጹም አልፈልግም። ከእንግዲህ ወዲያ የምኖርበት ዕድሜዬ አጭር ስለሆነ ቁም ነገር ለማየትና ወደ ውጤት የሚመነዘር ነገር ላይ ማተኮር ያረካኛል። የምኖርበት ዕድሜዬ አጭር ስለሆነ ነፍሴ ቸኩላለች።  ብዙ ጣፋጭ ያለበትን ኮሮጆ አልፈልግም።

የሰብአዊነት ባህርይ ካላቸው ሰዎች ጋር ብቻ ለመገናኘት እመኛለሁ። በስህተታቸው የሚስቁ፣ በውጤታቸው ግን የማይፈነድቁና በስሜት የማይታወሩ ሰዎችን አደንቃለሁ።

ቀድመው ለኃላፊነት የተመረጡ ከማይመስላቸውና፣ ኃላፊነትንም ከማይሸሹ ሰዎች ጋር መሆንን እመርጣለሁ። ለሰው ልጅ ክብር ጠበቃ ሆነው የሚከራከሩ፣ ለሀቅ የቆሙና፣ ህግ እኩልነትን ማስፈን እንዳለበት የተረዱ ሰዎችን ማየት እሻለሁ። እንደዚህ ዐይነት አመለካከትና መንፈስ ብቻ ነው ለህይወት ትርጉምን የሚሰጠው።

የሰውን ልብ ረገብ ከሚያደርጉና የሌላ ሰው ብሶት ከሚሰማቸው ሰዎች ጋር መሆን በጣም ያስደስተኛል። በህይወታቸው ውስጥ ከባድ ነገር ሲደርስባቸው ይህንን እንደትምህርት የሚቆጥሩና፣ በጥሩ ምክር ደግሞ አዕምሮአቸው እየበሰለ የሚመጣ  ሰዎችን  አደንቃለሁ።

አዎ ! በጣም ቸኩያለህ። ብስለትን የሚሰጠኝ ጠለቅና ከበድ ያለ ስራን እመኛለሁ። ቶሎ እንደሚበን ነገር በጊዚያዊ ህይወት መርካትን አልፈልግም። የቀረኝን አጭር ጊዜ በከንቱ ለማባከን አልፈልግም።

እስካሁን ካሳለፍኳቸውና ካባከንኳቸው ጊዜዎች ይልቅ የመጨረሻው ጊዜዬ በጣም ጣፋጭና ጠቃሚ እንደሆነ እረዳለሁ። ዓላማዬም የመጨረሻ መጨረሻ ጥሩ ነገር ሰርቼ ይህችን ዓለም በጥሩ መንፈስ ለመለየት ብቻ ነው የምመኘው።

ሁለት ህይወቶች አሉኝ። ሁለተኛው ህይወት የሚጀምረው አንድ ህይወት ብቻ እንዳለኝ ሳውቅ ብቻ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop