February 28, 2023
5 mins read

አድዋ እና “አንድ ወጥ” አከባበር -ሸንቁጤ – ከካናዳ

Adwa 11ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር  የዘንድሮው 127 የአድዋ ድል በአል “አንድ ወጥ ”  በሆነ መልኩ እንዲከበር  በቂ ዝግጅት አድርጎ  እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አሳውቋል:: 

“አንድ ወጥ ” የሚለው  የባህልናስፖርት ሚኒስቴር ዝግጅት በትግባር ሲተረጎም-

  1. ለበአሉድምቀት በሚዘጋጀው ፖስተር  ላይ  የዳግማዊ  አፄ ምንሊክን ፎቶ አስቀርቶ  በምትኩ በትግራይ ክልል የወታደርነት ዘመኑ የሚያውቁት ጌቶቹ እንደነገሩን በኢትዮ -ኤርትራ  ጦርነት ወቅት ጏዶቹ  የተጣለባቸውን ወታደራዊ ግዳጅ ሲወጡ እርሱ ግን ከበሻሻ እስከ መቀሌ ድረስ  የዘለቀ የ ከሰል እሳት ማርገብገቢያ ሽያጭ ንግድ  ሲያጧጡፍ የከረመ  በዚህም የተነሳ  የመቀሌ ጌቶቹ”መሽረፈት” እያሉ የሚያላግጡበትን ምኩን  በምትኩ በአድዋ ድል መታሰቢያ ፖስተር ላይ ፎቶው እንዲታተም ማድረግ
  2. የዳግማዊአፄ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ  ምስሎች የታተሙባቸው አልባሳትን የሚሸጡ ሱቆችንና ማሸግ እና መዝረፍ
  3. የዳግማዊአፄ ምኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱን ምስል የሚያትሙ   ማተሚያ ቤቶችን ማስፈራሪያ እና ማስጠንቀቂያ  መስጠት እና ማሸግ
  4. የዳግማዊአፄ ምኒልክ  እቴጌ ጣይቱ እናየኢትዮጵያ  ባንዲራ  የታተመባቸውን አልባሳትም ሆነ አርማዎች ይዘው የተገኙ  ዜጎችን ማሰር…( እስካሁን ወደ 50 የሚጠጉ ታስረዋል..)
  5. የቴዲ አፍሮ  ” ጥቁር ሰው”  ሙዚቃ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንዳይጫወት ክልከላ መጣል
  6. ወደ400 የሚጠጉ  ሆድ አደር  መድረክ እና ወረት( ብር) የተጠሙ አርቲስቶችን ሰብስቦ  ምኒሊክ እና የጣይቱ ስም  እንዳይነሳ አስምለው  ቃለ ተውኔት መቼት  ገፀ ባህሪያት አልቦ ቲያትር ማሰራት  ወ.ዘ.ተ….

ጥያቄ  ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

ጋሽ  መርዳሳ  እነዚህን መፈፀም ይችሉ ይሆን

  1. የአድዋንጦርነት እና የዳግማዊ አፄ ምኒሊክ/  እቴጌ ጣይቱን ሚና  የዘገቡ  በአለም ዙሪያ የተበተኑ የታሪክ መዛግብትን ሰብስቦ ማቃጠል ይቻል ይሆን
  2. የታሪክምሁራን እና ተመራማሪዎችን አፍ መለጎም ደብዛቸውን ማጥፋትስ
  3. የዳግማዊ አፄ ምንሊክን እና እቴጌ ጣይቱን ታሪክ  ከህዝቡ ልብ መፋቅ እና ማጥፋት ይሞከር ይሆን

ጋሽ መርዳሳ እና አጋሮቻቸው ለ ኢትዮጵያ  እና  ኢትዮጵያውያን ካላቸው “ልዩ ፍቅር”  የተነሳ ይህን ከመሞከር እንደማይታክቱ አምናለሁ::

ይልቅስ ጋሽ መርዳሳን ላመስግን ! እድሜ ለርስዎ እና ለጥረትዎ  የታሪክ መፃህፍቶቻችንን ከየወሸቅንበት እና ከጣልንበት እያወጣን በወጉ አራግፈን እና ጠርዘን  ለልጆቻችን  ውርስ እንድናስቀምጥ ስላነቁን እጅግ እናመሰግናለን! እንዴ ያኛው  ሎሌዎ  እኮ “ስንሞት ኢትዮጵያ…” እያለን ሸማችንን ተከናንበን ተኝተን ነበር:: አሁን እርሶ ባይኖሩ ማን ይቀሰቅሰን ነበር?!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop