February 28, 2023
4 mins read

ታሪክን ለባለታሪኩ፤ በተደረገበት ቦታ፤ በተፈጠመበት ቀን!! (አሥራደው ከፈረንሳይ)

adwa 2በዚች አጭር ጽሁፌ ፤ የቀደምት የግሪክ ታሪኮች ( Classical mytology) ስለ ሔርኩል (Hercule)  በተጠቀሰች አጭርና ውስጠ ወይራ በሆነች ጥቅስ መንደርደር መረጥኩ :: 

« On ne se baigne jamais deux fois dans le même fleuve »

« በአንድ ወንዝ አንድ ጊዜ እንጂ፤ ሁለት ጊዜ አንጠመቅም  » ይላል

ይህን ጥቅስ እንድዋስ ያስገደደኝ፤ በኢትዮጵያ የዘንድሮውን የ127ኛ የአድዋ ድል በዓል አከባበር፤ በተመለከተ፤ የሚደረገውን የታሪክ ሸፍጥ፤ « ተረኞች ነን » ባዮቹን፤ ህዝብ አደብ ግዙ እንዲላቸው ለማሳሰብ ነው ::

ታሪክ፤ በአድራጊውና በተደራጊው መሃል፤ በአንድ ወቅት፤ በተወሰነ ቦታና : በተወሰነ ጊዜ፤ በበጎ ወይም በጎጂ መልኩ፤ በአሸናፊና በተሸናፊ መሃል የሚደረግ ግብ ግብ ሲሆን፤ በመጨረሻም በመኖር ወይም ባለመኖር መሃል ይቋጫል::

የአድዋ ድል፤ በእምዬ ምኒልክና እተጌ ጣይቱ  አዝማችነት፤ በኢትዮጵያ ህዝብ ጀግንነት፤ በወራሪው የጣሊያን ፋሽስት ላይ፤ የተገኘ የአብሮነታችን ድል ከመሆኑም በላይ፤ የመላው አፍሪካ የጥቁር ህዝቦች ድል እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል ::

የዘመኑ የዘርና የጎሣ ፖለቲከኞች፤ የአድዋን ድል ከኢትዮጵያዊነት ማማው ለማውረድ፤ ከመሬት ስበት በከፋ መልኩ ቁልቁል ወደታች በመጎተት፤

 

ያለ ድሉ ባለቤቶች፤ እምዬ ምንሊክ፤ እተጌ ጣይቱና ጀግኖቻችን፤

ያለ ቦታው፤ የአድዋ ድል አደባባይ  ፊት ለፊት፤

ያለ አብሮ ዘማች ታቦቱ፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን

ያለ ሰንደቅ ዓላማችን፤ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለሙ፤  እንዲከበር ወስነዋል ::

አይምሯቸው፤ በዘርና በጎሣ ከታጠረ ግለሰቦች፤ ማህበረሰ’ባዊም ሆነ አገራዊ ዕሳቤ ስለማይመነጭ፤  አብሮነትን በሚያቀጭጭ፤ ክብርን በሚያጎድፍ፤ ታሪክን በሚከልስ ሁኔታ፤ እንዲከበር የወሰኑትን አጠፊዎች፤ ህዝብ በአንድነት እንዲጠየፋቸው አደራ እላለሁ ::

እግረ መንገዴንም፤ በእስር ለሚጉላሉት :

– ጋዜጠኛና የታሪክ ምሁር፤ ጋሼ ታዲዎስ ታንቱ፤

– በአዲስ አበባ አካባቢና በአማራ ክልል፣ ለሚፈናቀሉ ወገኖቻችን፤

– የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታይ ለሆኑት ወገኖቻችን፤

– ለአርበኛ ዘመነ ካሴና፤ ለመላው የፋኖ አባላት ፍትህን እጠይቃለሁ ::

 

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

ነፃነት፤ እኩልነትና ወንድማማችነት ይለምልም !!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ !!

የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም  (28/02/2023) እኤአ

 

ባቡሩም ሰገረ ስልኩም ተናገረ
ምኒልክ መልዐክ ነው ልቤ ጠረጠረ
ምኒሊክ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ
332336598 3629627227271315 6505558082944763049 n

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop