February 17, 2023
11 mins read

የተዋሕዶ አብዮት መቀልበስ፤ ሐይማኖትና መንግስት ወይስ ሐይማኖትና ፖለቲካ?

331289025 902102007600223 7485122687439461404 n 1

ካንድ አገር መንግስት የሚጠበቀው በሐይማኖት ጉዳይ እጁን አስገብቶ የማይፈተፍት፣ የሚደግፈውም ሆነ የሚቃወመው ሐይማኖት የሌለ ገለልተኛ መንግስት እንዲሆን ነው፡፡  መንግስት በሐይማኖት ጉዳይ እጁን አያስገባ ማለት ግን ሐይማኖት በመንግስት ጉዳይ አይግባ ማለት አይደለም፡፡

መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ የደጋፊወቹ ብቻ ሳይሆን ያገር መንግስት ስለሆነ፣ ሁሉንም ያገሪቱን ዜጎች (የመረጡትንና ያልመረጡትን) በእኩል ዓይን ማየትና ማስተናገድ ግዴታው፡፡  ዜጎቹ ግን ያገሪቱን ሕግ ማክበር እንጅ መንግስቱን መውደድ አይጠበቅባቸውም፣ የማይውዱት ከሆነ ደግሞ መንግስቱን ለማውረድ ሕጋዊ መንገዶችን መጠቅም ሙሉ መብታቸው ነው፡፡

331566378 2133929786799727 5071860936887871789 n

በተመሳሳይ መንገድ መንግስት ሁሉንም ሐይማኖቶች በእኩል ዓይን ማየት ግዴታው ቢሆንም፣ ሐይማኖቶች ግን ሐይማኖታቸውን እንደ ፖለቲካ ኃይል በመጠቀም በምግባሩ የማይወዱትን መንግስት አለመደገፍና በሕጋዊ መንገድ ለማውረድ መእምኖቻቸውን ማነሳሳት ሙሉ መብታቸው ነው፡፡  የተዋሕዶ ብፁዓን አባቶች በተለይም ደግሞ አቡነ አብርሃም እና አቡነ ጴጥሮስ ያላወቁት ወይም ደግሞ ቢያውቁትም ለመተግበር የማይፈልጉት ይህን መብታቸውን ነው፡፡  ይህን መብታቸውን ባለመተግበር ደግሞ፣ ተዋሕዶን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳውን የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት ለማውረድ የተቀሰቀሰውን የተዋሐዶን አብዮት በማስቀልበስ ራሳችውን፣ ተዋሕዶንና ጦቢያን በጭራቅ አሕመድ ቁርጥምጥም አድርገው ለማስበላት አፋፍ ላይ ደርሰዋል፡፡

ሐይማኖት ፖለቲካ ነው፣ ቅልጥ ያለ ፖለቲካ፡፡  የክርስትና ሐይማኖት አባት ራሱ እየሱስ ክርስቶስ በሐብት ክፍፍል የሚያምን (ሁለት ካለህ አንዱን ስጥ የሚል)፣ ስግብግባዊ ብልጽግናን በጽኑ የሚኮንን (ሐብታም ከሚጸድቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል የሚል)፣ 12ቱን ሐዋርያወቹን ከሐብታሞች ወይም ከምሁሮች ሳይሆን ከሠርቷደሮች (ዓሣ አጥማጆች) የመረጠ፣ ከማርክስ (Marx) የሚቀድም ከቡድሃ (Buddha) የሚከተል ሁለተኛው ያለማችን ኮሚኒስት (communist) ነው፡፡  የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ (Fidel Castro) በትክክል እንዳስቀመጡት “አዲስ ኪዳን በትክክል ቢተገበር ኖሮ ኮሚኒዝም ባላስፈለገ ነበር”።  የማርክስ ኮሚኒዝም ስብከት ከእየሱስ የትራራው ስብከት እምብዛም አይለይም፡፡

ሐይማኖት ፖለቲካ መሆኑን በትክክል ለመረዳት የዶናልደ ትራምፕን (Donald Trump) ክስተት ማጤን ብቻ ይበቃል፡፡  የዶናልድ ትራምፕ ጽንፈኛ ደጋፊወች ቁርዓን አቃጥሉ፣ ስደተኞች አትቀበሉ የሚሉ፣ አሜሪቃን በባርነትና በጅምላ ጭፍጨፋ ወደ ጨቀየው ወደ “ቀድሞ ታላቅነቷ” ለመመለስ (make America great AGAIN) ቆርጠው የተነሱ ጽንፈኛ ነጭ ብሔርተኞች (white nationalists) ናቸው፡፡  ሁሉም ተግባራቸውና ንግግራቸው ከክርስትና አስትምህሮ ጋር ፍጹም የሚቃረን፣ ባሁኗ አሜሪቃ ላይ ልክ እንደ ቀድሞዋ አሜሪቃ ነጮች አዛዥና ናዛዥ እንዲሆኑና የጌታሎሌ ግንኙነት ዳግም እንዲመሠረት የሚተጉ ነጭ ላዕልተኞች (white supremacists) ናቸው፡፡  እነዚህ ያሜሪቃ ነጭ ላዕልተኞች ራሳቸውን ወንጌላዊ ብለው የሚጠሩት፣ በክርስቶስ ወንጌል ስለሚያምኑ ሳይሆን፣ የነጭ ላዕልተኛ አጀንዳቸውን ለማራመድ የወንጌላዊነት ለምድ መልበስ ፍቱን ሆኖ ስላገኙት ብቻ ነው፡፡

ፊታችንን ወዳገራችን ወደ ጦቢያ ስንመልስ ደግሞ በኦነጋዊው በጭራቅ አሕመድ የሚመሩት ኦነጋዊ አቶ ጳጳሶች ማለትም አቶ ሳዊሮስና ጓደኞቹ ሐይማኖት ፓለቲካ መሆኑን በግልጽ የተረዱ፣ ያማራ ጥላቻቸው ከፊታቸው ላይ በግልጽ የሚነበብ፣ አዲሳባ የኦሮሞ ናት ሲሉ ዓይናቸውን የማያሹ፣ ወንጌላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን ኦሮሙማ የሆነ፣ ኦሮሚያና ብሔር ብሔረሰቦች እያሉ ስለ ኦሮሞ የበላይነት በግልጽ የሚናገሩ ኦነጋዊ ፖለቲከኞች ናቸው፡፡  እነዚህ ኦነጋዊ አቶ ጳጳሶች ተዋሕዶ ነን የሚሉት በተዋሕዶ አስትምህሮት ስለሚያምኑ ሳይሆን፣ የተዋሕዶን ለምድ መልበስ ኦነጋዊ አጀንዳቸውን ለማራመድ ፍቱን ሆኖ ስላግኙት ብቻ ነው፡፡

በፖለቲካዊ ብልጦቹ በነ አቶ ሳዊሮስ አንጻር የቆሙት አቡነ አብርሃምና አቡነ ጴጥሮስ ደግሞ ኦነጋዊው ጭራቅ አሕመድ በይሁዳው በዳንኤል ክብረት አማካኝነት እነሱንና ተዋሕዶን በልቶ ጦቢያን እንዳይበላ የሚታገሉትን ሁሉ ፓለቲካችሁን ከሐይማኖታችን ጋር አትቀላቅሉብን እያሉ የሚግስጹ፣ የሐይማኖትን ፓለቲካዊነት ያልተረዱ ፖለቲካዊ የዋሆች ናቸው፡፡  በዚሁ ፖለቲካዊ የዋህነታቸው ከቀጠሉበትና መጫወት የሚገባቸውን ፖለቲካዊ ጨዋታ ካልተጫወቱ ደግሞ፣ ጭራቅ አሕመድ በማስታረቅ ሰበብ በመኻላቸው ያስገባቸው ፖለቲከኞቹ እነ አቶ ሳዊሮስ በሚጫወቱት ፖለቲካዊ ጨዋታ በዝረራ ተሸንፈው፣ እንደ አሮጌ ቁና ተወርውረው የሚጣሉበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

በታሪካዊ አጋጣሚ ምክኒያት የቅድስት አገራችን የጦቢያ ሞት ሽረት ያለው፣ ጦቢያን ለመግደል ቆርጦ በተነሳው በጭራቅ አሕመድ እጅ ሳይሆን፣ በብፁዓን የተዋሕዶ አባቶች እጅ ላይ ነው፡፡  እነዚህ ብፁዓን አባቶች ደግሞ ጦቢያን በነጭ ጅቦች ከመበላት ለማዳን አድዋ እንደ ዘመቱት እንድ ቀድሞ አባቶቻቸው ሐይማኖት ፖለቲካ መሆኑን ተርደተው፣ መጫወት የሚገባቸውን ፖለቲካዊ ጨዋታ ባግባቡ ከተጫወቱ፣ የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት ባጭር ጊዜ ውስጥ በማስወገድ፣ ራሳቸውንም፣ ተዋሕዶንም፣ ጦቢያንም በኦነጋዊ ጅቦች ከመበላት ማዳን ይችላሉ፡፡  አልመሸም፡፡

በመጨረሻም ተዋሕዶን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳውን የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት ለማስወገድ የተቀሰቀሰው የተዋሕዶ አብዮት ባለቤት መላው የተዋሕዶ መዕምናን እንጅ ጥቂት ብፁዓን አባቶች ብቻ አይደሉም፡፡  ባለመሆናቸውም አውቀውም ሆነ ባለማወቅ፣ ባንድም በሌላም መንገድ ለዚህ አብዮት እንቅፋት በመሆን የተዋሕዶንና የልጆቿን ሞት እያፋጠኑ ያሉ የተዋሕዶ አባቶችን፣ የተዋሕዶ መዕምኖች አለመስማት ብቻ ሳይሆን ገለል ማድረግ ግዴታቸው ነው፣ ጉዳዩ የሞት ሽረት ጉዳይ ነውና፡፡

 

ድኀረ ኪታብ (postscript)  

ኦነጋዊው ጭራቅ አሕመድ አባቶችን ማስታረቅ በሚል ሰበብ በተውነው ተውኔት ላይ በግራኝ አሕመድ ዘመን የተፈጸመውን የዝዋይን ታሪክ ያነሳው በዚያ ዘመን ኦሮሞ የሚባል ብሔር በጦቢያ ውስጥ እንዳልነበር ጠፍቶት ሳይሆን፣ አዲሳባን ኬኛ ብሎ ለመሰልቅጥ እንዳሰበው፣ ተዋሕዶንም ኬኛ ብሎ ለመሰልቀጥ በነደፈው (ይልቁንም ደግሞ እነ ሌንጮ ለታ በነደፉለት) ፖለቲካዊ ጨዋታ መሠረት ብቻ ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop