ዛሬ እናት አገር ኢትዮጵያ ከታመመች ሶስት አስርተ ዓመታት ሆኗታል ፡፡ አገር ማቁሰል እና ህዝብ መበደል የዕለት ተዕለት ማታለል ተግባራችን ብለዉ የያዙት ያኔ ኢትዮጵያን ለማናጋት ሶስት ጠላቶች ብለዉ የሚፈርጇቸዉ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች በዉስጥ እና በዉጭ ፤ በሩቅ እና በቅርብ ሆነዉ ለዘመናት ተፈጨርጭረዋል፤ ከሞላ ጎደል የጥፋት ጅምራቸዉን አሳክተዋል ፡፡
በኢትዮጵያ ምድር ኢትዮጵያዊ ሆነዉ ተፈጥረዉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት በሶት የኢትዮጵያ መሰረት እና ዕምብርት ፤ምሰሶ የሆኑትን የኢትዮጵያ መልኮችን ኢትዮጵያዊነት ፤ ኢትዮጵያዊ ማንነት ፤ ኃይማኖት ላይ የተተከለዉ የጥፋት ዕሾክ ግማሽ ምዕተ ዓመት ተቆጥሯል፡፡
በኢትዮጵያዊነት እና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የማያቅማማዉን ሁሉ በቋንቋ እና በባህል ዓማራ፣ በኃይማኖት ክርስቲያን -የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና ፤ አገር ሲባል ክልል ማለት ኢትዮጵያን ማፅናት ሳይሆን ማግፋት እንደሆነ እኛ ኢትዮጵያን መረዳት እና መረዳዳት ተስኖን ለግማሽ ምዕተ ዓመት ለተራዘመ ጥፋት፣ ሞት እና ኃዘን ተዳርገን ዛሬም በባርነት ቀንበር ሆነን ለቁም ሞታችን እናዝናለን ፡፡
ትናንት አገር ዳር ድንበሯ እንደ ሙት ርስት በከኃዲዎች እና በተላላኪዎች ሲፈርስ፣ የሰዉ ልጆች በማንነታቸዉ እና በዕምነታቸዉ በጅምላ እና በተናጠል ሲሳደዱ ፣ ሲዋረዱ ፤ ሲታረዱ ለምን የሚል ከላካይ፤ ምነዉ የሚል አዛኝ ጠፍቶ ዛሬ ላይ እንኳ ሁነን ከትናንት ንስኃ መግባት እና መማር አቅቶን ለየግላችን ማንባት ጀመርን ፡፡
አሁንም አልገባን እንጂ ኢትዮጵያን እንደ አገር ታሪክ ለማድረግ ዕዉነትን በማዛነፍ ልብ ወለድ በማድረግ የሚደረገዉ ትንቅንቅ የጥፋት ጎርፍ የመነጨዉ ከህገ-ኢህአዴግ የስጋት መሰረት ኢትዮጵያ የምትባል አገር ፣ ኢትዮጵያዊ የሚባል ህዝብ(ዓማራ) እና የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ነበር ፤ነዉ ፡፡
ይህም ኢትዮጵያን ስሟን ለመፋቅ ካልሆነ ያልሆነ እና ያልተጀመረ አዲስ ነገር ዛሬ የለም ፡፡ ሁሉም የሰዉ ልጆች ሁሉ ሊያዉቁት የሚገባዉ በኢትዮጵያ ላይ ያለዉ ወረራ እና ምዝበራ የኃይማኖት ጉዳይ እንዳልሆነ ለዘመናት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና በህዝቦች ነፃነት ላይ የሆነዉ ግፍ እና በደል ለኢትዮጵያዉያን ቀርቶ ለመላዉ የሠዉ ልጂ ግልፅ ነዉ፡፡
ኢትዮጵያን የባህር በር በማሳጣት አስትንፋሷን መዝጋት ፍላጎት የነበራቸዉ የዉስጥ ምንደኞች ቀለሟን አጥታ ገርጥታ ፤ ልጆቿ በስድት ፣ በባርነት እና በአገራቸዉ ባይተዋር ሲሆኑ የሚደሰቱ ስለምን ኢትዮጵያን ስሟን ታሪክ እንዲሆን ለመስራት ያፈገፍጋሉ ፡፡
የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት አገር ሠርተዉ ፤ አገር ጠብቀዉ ማቆየታቸዉ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ብራና ፍቃ ፤ቀለም በጥብጣ ሆሄ በመቅረፅ፣ የአገር አስተዳደር ስርዓት በመመስረት ለዓለማዊ መንግስት መሰረት መኋኗ፣ በቋንቋ ፣በስነፅሁፍ፣ በባህል…..በዓለም ከሚገኙ ቁጥራቸዉ በጣት ከሚቆጠሩ አገሮች አንዷ መሆኗ ዕንቅልፍ የሚነሳቸዉ በምቀኝነት እና በበታችነት ጉድጓድ ገብተዉ የሚማቅቁ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማክሰም የሚችሉትን ሁሉ ቢያድርጉ የሚጠበቅ ነዉ ፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያ አገሬ ፤ መንደሬ …መቃብሬ የሚል ከኢትዮጵያዉያን ጎን ይቁም ፡፡ ኢትዮጵያ ማለት ሁሉም ናት ፡፡ ኢትዮጵያ ከኦሪት አስከ ዕለት የመረሻዉ ክህደት የሁልም አገር ናት ፣ነበረች ፡፡ ኢትዮጵያ ማለት የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ኃይማኖት ከርስትና እና ዕስልምና ምድር እና አለት ናት ፡፡ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ማወክ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተጀመረዉ የክ/ዘመኑ ኢትዮጵያን የማጥፋት ጉዞ ነዉ ፡፡
ኢትዮጵያን እና ራሳችንን ስናድን ኢትዮጵያን እናድናለን ፤ ኢትዮጵያን ስንታደግ ያኔ ዕምነታችን ፤ኃይማኖታችንን እንሆናለን ፤እንከተላለን ፡፡ ዕምነት በአገር ነዉ ፤ ዕምነት ሥራ ነዉ ፤ ሥራም በተግባር ነዉ ፡፡
በፍቅር ለመኖር አይደለም ለጥልም ለሞትም አገር ያስፈልገናል ፡፡ “ከእኔ የማይቆም ጠላቴ ነዉ” እንዲሉ ከኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ የማይቆም ኢትዮጵያዊ ሳይሆን ጠላት ነዉ ፡፡
ቤ/ክርስቲያን ባለቤቷ ክርስቶስ ነዉ ክርስቶስም የቤ/ክርስቲያን ራስ ነዉ ፤እናም ሠዉ ሆይ ክርስቲያን ሆን ዕስላም ዕምኑኝ ቤ/ክ የዓምላክ ናት ፡፡ እና ኢትዮጵያዉያን ግን ለራሳችን እና ለአገራችን እናልቅስ ፤እናንባ ፡፡ እኔ የማነባዉ ለአገሬ እና ለጥፋት መልዕክተኞች እና ለከኃዲዎች ነዉ ፡፡
“አልማዝ የሚሞረደዉም ሆነ የሚቆረጠዉ በአልማዝ እንደሆነ የኢትዮጵያም ሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ችግር ካለ የሚፈታዉ በኢትዮጵያዉያን እና በክርስቲያኖች ብቻ እና ብቻ ነዉ ፡፡ ”
እንኳን ለእናት ምድር ፤ እንኳን ለዕናት አገር ፣
ክብሯን ስትነጠቅ ዳር ድንበር ሲደፈር ፣
እንዲያዉ ይለቀሳል ሠዉ በሰዉነቱ ሠዉ ሲገባ ካፈር ፡፡
“የኢትዮጵያ አንድነት እና ሠላም የሚረጋገጠዉ በዜጎች ሞት እና ደም ሳይሆን ፤ለኢትዮጵያ አንድነት እና ሠላም መናጋት ጠንቅ የሆኑትን ታሪካዊ እና ብሄራዊ ጠላቶች ዋጋ ሲጠየቁ ብቻ ነዉ ፡፡ ”
Allen Amber!
ይኽችን ቤተ ክርስቲያን አጥፍቶ መኖር አይቻልም።”
ይኽችን ቤተ ክርስቲያን አጥፍቶ መኖር አይቻልም።”
አቡነ ሕዝቅኤል#OrthodoxUnderAttack #Ethiopian_Orthodox_Under_Attack pic.twitter.com/XwIom21VPB
— ????????????እሴተወልድ-Soስna (እሙ)???????? (@Emuye06) February 7, 2023