ሰሞኑን የግዜ ጎርፍ የስርዐት ዝቅጠት አንከባሎ ያመጣቸው ወንጌላዊ ነን ባይ ወሮበሎች የተናገሩት ነውር ሲያነጋግር ሰንብቷል:: ይህ ዘመን ኢትዮጵያ እንደ ሃገር የዝቅጠትን ውሃ ልክ አልፉ ወርዳለች ቢባል ማጋነን አይሆንም:: ወንጀልና ወንጌል ; መንግስትና ሽፍትነት : ሌባና ፖሊሱ ተደበላልቋ:: የሃይማኖት ነጋዴው ግርግር የነብያት ነን ባዩ ግሪሳ የትንቢተኛው ሁካታ የታዳሚው ነሆለልነት በእርግጥ ለሺህ ዘመናት ሃይማኖት ከነበረባት ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ሁሉ ጉድና ነውር አለ ብሎ ለማመን ይከብዳል::
“ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች …” እንዲሉ ፓስተር ዮናታን እና ግመሬ ዝንጀሮ የመሰለው አዩ ጩፉ ተብዬዎች ከገሞራ ዋሻ ከድንቁርና አምባ ላይ ሆነው መርዛቸውን ሲረጩ ተሰምተዋል:: “መጽሃፍ ክብራቸው በነውራቸው ሆዳቸው አምላካቸው” እንዳለው ታላቋን ሃዋሪያዊና ጥንታዊቷን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ለመሳለቅ ሞክረዋል::
ፓስተር ነን ባዬቹ ምናምንቴዎች ቤተክርስቲያኗን ለመተቸት የሚያስችል እውቀትም ብቃትም ሆነ ሞራል የሌላቸው ከንቱዎች ቢሆኑም ከጀርባቸው መንግስታዊ ስልጣን የጨበጠ ጉግማንጉግ ቡድን በመኖሩ የግለሰቦቹም ሆነ ያሰሙት ስድብ ፖለቲካዊ ተልዕኮ መዋቅራዊ መሰረት እንዳለው መገንዘብ አይከብድም:: ፓስተር ዮናታን ተብዬው እንትኑን እንኳ በቅጡ የማያጸዳ መናኛ የጠቅላይ ሚንስትሩ የነብስ አባት ትውልዱን በኑፉቄ እንዲመርዝ ሽልማትን በይፉ የተቀበለ የአገዛዙ መሪ የቅርብ ሰው ነው:: የስድቡም ምንጭ ተቋማዊ ተልዕኮ ያለው ለመሆኑ መገመቱ ስህተት አይሆንም::
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያለፉት 30 አመታት በታላቅ ማዕበል ስትንገላታ ከርማለች:: በተለይም ባለፉት 4 አመታት ድንበሯ ታልፎ አድባራቷ ሲቃጠሉ ካህናቶቿ ሲታረዱ ቆይቷል:: ዛሬም በመከራና በወከባ ውስጥ ናት:: ሁሉንም ዜጋ አቅፉና ሰብስባ በምግባር አቅንታና በሃገር ፍቅር ስሜት ኮትኩታ ያሳደገች ቤተክርስቲያን ነች:: ልጆቿን ለመበተን ሃገሪቷን ለማፍረስ ለተነሱት የጥላቻና የዘር ፖለቲካው መሃንዲሶች እንቅፉት ስለሆነች እንድትጠፉ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም:: ከኢትዮጲያ ሃገር ምስረታ ጋር አያይዘው ለሚነሱት የሃሰት ተረኮች ግንባር ቀደም ተጠቂም ሆናለች:: የፖለቲካው ሰይፍ የዘረኞች ሁካታ የጨካኞች ጭፍጨፉ ጋብ ሳይል ከተማ ውስጥ በሚርመጠመጡ የጎሞራ መንገደኛ የዲያቢሎስ ግልገል በሆኑ ፓስተሮች አዲስ የግጭት ስይፍ ተመዞባታል::
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊና ቀዳማዊ ከሆኑ በአለም ካሉ ጥቂት ቤተ ዕምነቶች ግንባር ቀደምት ናት:: የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እምነቷን ስርዐቷን ዶግማና ቀኖናዋን ለሺ ዘመናት ጠብቃ ያቆየች የክርስቲያኖች ሁሉ ቀንዲል ነች:: እንደዛሬው ሃገር ሳይሰለጥን ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያውያን ትምህርት ቤት ሆስፒታል የእደጥበብና የስነጥበብ ብቸኛ አምባ ሆና ትውልድን ያሸጋገረች የታሪክና የስልጣኔ ባለቤት ነች::ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን መላው የጥቁር ሕዝብ ብችኛ መኩሪያ የሆነውን የግዕዝ/አማርኛ የስነጽሁፍ ትሩፉት ፈጥራና አዳብራ ለአለም ያበረከተች የሚስተካከላት የሌለ እጅግ ታላቅ ተቋም ነች:: እንኳን ከአራዊት ባህሪ ያልወጣ ሰው መሳይ ያልሠለጠነ የመናፍቅ መንጋና የሰዶም እጋፉሪ ቀርቶ በጥበብም በታሪክም ተራቀናል የሚሉት ጥንታዊያን ሊናገሯት የማይደፍሯት የእውቀት ማማ ነች::
በሃገራችን ከዘመነ ወያኔ ጀምሮ ቤተክርስቲያኗን በመጋፉት መንጋዋን ለመበተን በመንግስትና በፓርቲ የተመራሰፊ ዘመቻ ተካሂዶባታል:: ቤተክርስቲያኒቱ አንድ ግዜ ከቀድሞ ነገስታት ሌላ ግዜ ከአማራ ሕዝብ ማንነት ጋር በመፈረጅ የዘር ፖለቲካው ተዋናዮች የተፈራረቀ ጥቃት ተፈጽሞባታል:: በተለይ ኢትዮጵያዊው የኦሮሞ ተወላጅ በስፉት በተካሄደበት መጠነ ሰፊ የጥላቻ ቅስቀሳ ኦርቶዶክሳውነቱን እንዲለውጥ ተደርጏል:: ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን መከተል አማራ መሆን ነው?! ባርነትን በምርጫ እንደ መቀበል ተደርጎ ባልተቋረጠ መንግስታዊ የፕሮፓጋንዳ ግፊት ተሰብኳል:: ከዛም አልፎ ቤተክርስቲያኒቱ ኦሮሞ እንዲጨቆን አድርጋለች በሚል ሃሳዊ ቅስቀሳም በርካታ ምዕመናን እንዲታረዱ ገዳማቷ እንዲነዱ ተደርጏል::
ካለፈው 4 አመት ወዲህ ደግሞ የማዕከላዊ መንግስቱን የተቆጣጠረው የኦሮሞ ኤሊት ቀድሞ በክልሉ ብቻ ተወስኖ ያኪያሂድ የነበረውን ጸረ ኦርቶዶክሳዊ ጥላቻ ሃገር አቀፉዊ በማድረግ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመበተን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል:: የኦሮሞን ሕዝብ ሊናቅ በማይችል ቁጥር ከኦርቶዶክስ አማኝነት ውጪ በማድረግ አብዛኛውን ዋቄፈታ የቀረውን ፕሮቴስታንት የተረፈውም እምነት የለሽ አህዛብ እንዲሆን አድርገውታል::
ለዚህም ነው ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ሞራል የጠፉው ጭካኔ የነገሰው ስርቆት አፈናና ሽብር የተስፉፉው:: ኦሮሚያ ሰውን የሚያርዱ ጭራቆች የሰውን ስጋ ጉበትና ኩላሊት የሚበሉ በላያሰቦች የበዙት:: ኦርቶዶክስ ይሁን ካቶሊክ ፕሮቴስታንት ይሁን ጆሆቫ በብሄር አጥር ላይ የተመሰረቱ ሳይሆን የሁሉም መነሻ አንድና አንድ መጽሃፍ ቅዱስ ነው:: ሃይማኖት በብሄር ሚዛን ሲለካ በቋንቋ መነጽር ሲታይ ምናልባት ከኦሮሞ ፖለቲከኞች ሰፈር ውጪ በሌላ ቦታ ያለ አይመስለኝም::
የሰሞኑም የፓስተሮቹ ሁካታ የዚሁ የጥላቻ ፖለቲካ አራማጅ የሆኑት የኦሮሞ ልሂቃን ቅጣያ ነው የምንለው:: ፓስተር ዮናታን የሚባል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሸላሚና የነብስ አባት ከመሬት ተነስቶ በማይመለክተው በማያውቅና ባልተረዳው የኦርቶዶክስ ሃይምይኖት ቅዱሳን እና የዕምነቱ አስተምህሮ ላይ በዛ ያህል ድፍረትና ነውር በአደባባይ ለመስበክ አንዳችም ሃይማኖታዊ አምክንዮ ኖሮት አይደለም:: ሃይማኖቶች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል የሆኑት የሰዎችን የማመንና የፈለጉትን የዕምነት ተቋም የመከተል መብት መበየን የሚችል ምንም ምድራዊ ሃይል ባለመኖሩ ነው:: የግለሰቦች የማመን መብት እንደሚከበረው ሁሉ የሃይማኖት ተቋማትም እርስ በእርስ አንዱ የሌላውን መብት በማክበር እንዲመሩ ሕግ ያስገድዳል::
በእኛ ሃገር ይህንን ሕግ የሚጥሱት አንዳንድ የሃይማኖት ተቋማትና ግለሰቦች በፖለቲካና ስልጣን ላይ ባለ ወገንሲ ደገፉ ብቻ እንደሆነ ትላንትም በወያኔ እንደሆነው ሁሉ ዛሬም በኦዴፓ/ኦነግ የሚተገበረው ያው ነው:: የሃገር ውስጡ ጸረ ኦርቶዶክሳዊነት እንዳለ ሁሉ የአዲሱ የአለም ስርዐት መሪ የሆኑት ምዕራባዊያን የፕሮቴስታንቱን ዕምነት ተቋማት በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት ከፍተኛ ዕገዛ የሚያደርጉበት የእራሳቸው ፍላጎት እንዳለ በግልጽ ይታወቃል:: በዓለማችን ቀዳሚና ጥብቅ ዶግማና ቀኖና ያላቸው ጥንታዊ ሃይማኖቶች ለአዲሱ የአለም ሃይል ፍላጎት የሚመቹ በቀላሉ ብረዛና ክለሳ ለማድረግ የማይፈቅዱ በመሆናቸው ከመድረኩ እንዲገለሉ ይፈለጋል:: አዲሶቹ የዘመናችን ወንጌላዊያን ቅርብ አሳቢ ምድራዊና ጥቅም ላይ መሰረታቸውን የሚጥሉ መነሻም መድረሻም የሌላቸው በመሆኑ ውስጣዊ የፖለቲካ ሃይሎች ብቻ ሳይሆን እለማቀፉዊ ቡድኖችም ይደግፏቸዋል::
በአዲሱ የስውሩ ዓለም ሃይል የሚነዳው የሰዶም ባቡር ሃገራትን እንዲያዳርስ ከሚጫነው የኢኮኖሚ የእርዳታና የሰብዓዊ ድጋፍ በስተጀርባ ሊያራግፈው የሚፈልገውን መርገም በይበልጥ መንገድ ጠራጊ የሆኑለት በፕሮቴስታንት ሃይማኖት ሽፉን የተነሱት እንደ ፖስተር ዮናታንና እዩ ጩፉ የመሰሉትን አስመሳዮች ነው:: ፓስተሮቹ ዮናታን ጩፉ እና ነብይ ሃዋሪ የሚል መጠሪያን በድፍረት የተሸከሙት ገንዘብ አሳዳጅ መናፍቃን ኢትዮጵያ ውስጥ ትውልዱ በተሳሳት ጎዳና በመምራት ስኬታማ ሆነዋል:: ድሃውን ሕዝብ በተስፉ አስረውና በሌለ ትንቢት በማይታይ እራዕይ አደናብረው በምኞት እነሁልለው ኪሱን እያጠቡ እነሱ ግን ቅንጡ መኖሪያ ያማረ መኪና ባለ ጠባቂ ጋርድ ሆኖው የምቾት ሕይወት ያጣጥማሉ ::
በተዋበ ፉሽን አሸብርቀው ምዕራባዊነት በተጣባው ጉራማይሌ ስታይልና ቋንቋ በኑሮ ምስቅልቅል በፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ የሚናጠውን እርሃብ ያደቀቀውን ትውልድ እንደፈለጉ እንዲነዱት ተፈቅዶላቸዋል:: እነዚህ እንደ እንጉዳይ የፈሉ ሰባኪያን በሃገርና በትውልድ ላይ የሚያመጡት የከፉ አደጋ ከወዲሁ ሊታሰብበት ይገባል:: በምዕራቡ ዐለም ያሉ የፕሮቴስታንት ከፊል ተቋማት ሰዶማዊነትን ተቀብለው ከክርስቲያናዊ መንገድ በመውጣት በይፉ የሚያካሂዱት ነውር ሕጋዊና ተቋማዊ ከሆነ ውሎ አድሯል:: ይህንን መሳይ አላማ በሃገራችን ነገ እነፓስተር ዮናታን እንደማያመጡት ምንም ማረጋገጫ የለንም::
ዛሬ ላይ በምዕራቡ አለም የተንሰራፉው ነውር ትውልድን እያዳሸቀ የሞራል ልዕልናን ንዶ እርካታ ያጣ ደስታ የራቀው ቁሳዊ ትውልድ ፈጥረዋል:: ስልጣኔ መልካም እውቀትም አስፈላጊ መሆኑ ባያከራክርም በመንፈሳዊነት ካልተገራ የሞራል ልጏም ካልተበጀለት ምን እንደሚያስከትል የምዕራቡ ዓለም ትውልድ ወዴት እየሄደ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው:: ልሂቃን ለዚህ ነው “ሃይማኖት የሌለው ሰውና ልጟም የሌለው ፈረስ አንድ ነው” የሚሉት ::
በሃይማኖት ማዕከነት ይመራ የነበረው የምዕራቡ ዓለም ሕዝብ ባለፈው ምዕተ ዓመት የደረሰበት የስጣኔና የእውቀት ደረጃ ለዘመናት ሲመራበት ከኖረው ባህላዊ መንፈሳዊና ማህበራዊ ልምዶቹ እንዲነጠል አድርጎታል:: ዘመናዊነት ለአዲስና ምቹ ሕይወት የመጥቀሙን ያህል ነባር ማህበራዊና ሃይማኖታዊ ልማዶችን አፈራርሶ ልቅ የግለኝነት ባህልን ማንበሩ የአዲሱ ትውልድ ሕይወት ከባድ አድርጎታል:: ትውልዱ እራስ ወዳድ ሞራል አልባና ከሃይማኖት የተነጠለ መንፈሳዊነቱ የላላ ያደረገው ስልጣኔ ብቻ ሳይሆን ከዛም በላይ በሃይማኖት ስም የተነሱ በራዥ ከላሽ ሃሳዊ ሰባኪያን ያደረሱት ቅጥ የለሽ የሞራ ኪሳራ የባሰ በመሆኑ ነው::
ክርስትና በአጠቃላይ መንፈሳዊነት ከእራስ በላይ ለሌሎች መኖርን የሚጠይቅ ተግባር ነው:: ነገር ግን በዘመናችን ሃይማኖት ለጽድቅ መሆኑ ቀርቶ ለንግድና ለፖለቲካ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ከሆነ ሰንብቷል:: ለዚህም ነው በበጎ ተግባርና በቱሩፉት ከሌላው ልቆ በምሳሌነት ከመጠራት ይልቅ አንዱ የሌላውን መንጋ ለመቀማት የሚሯሯጠው መልካሙን ሃገራዊ እሴት አጥፍቶ አረማዊነትን የሚተክለው::
ለማጠቃለል በክርስትናም ሆነ በእስልምና ከአለም ቀዳሚዎቹ ሆነን ሳለ እንዴት ከዘመን በሗላ ሃይማኖትን ከተቀበሉ ምዕራባዊያን የመጣን ወፍዘራሽ ሃሳዊ የክርስትና እስተምህሮ በሃገራችን ተንሰራፉ:: ለመጽሃፍ ቅዱሱም ለቁራኑም ለቅዳሴው ለአዛኑም ቀዳሚ ሆነን ሳለ እምነት እንደሌለን ተቆጥረን:: በሃገር ደረጃ የሚያስብ ከጎጥ ወጥቶ ሰፊውን ሃገር የሚመለከት ከዛሬ ባሻገር ነገን በሰፊው ማሰብ የሚችል መሪ ባለማግኘታችን ነው:: የአብይ አህመድ ጉግማንጉ አካሄድ ሃገር ብቻ ሳይሆን ትውልድንም እንዳያጠፉ እስላም ክርስቲያኑ ነቅቶ መመልከት ይገባዋል:: አዲሶቹ ሰባኪያን እነ ፓስተር ዮናታን የትውልዱን የማህተብ ክር እየበጠሱ በኑፉቄ እንዳጠመቁት ሁሉ ነገ ሱሪውን አሶልቀው ጾታውን አስለውጠው: የሰዶም ሙሽራ የገሞራ መንገደኛ ከማድረግ የማይመለሱ በሃይማኖት ስም የሚነግዱ የሴጣን ወኪሎች ናቸው:: በጥላቻና በዘረኝነት ታውሮ ለነዚህ የሰይጣንፈረሶች መንገዱን የጠረገ ሁሉ ለልጆቹ እርኩሰትና የቁም ሞትን እያወረሰ መሆኑን ሊረዳ ይገባል::
እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!
ትውዱን ከጥፉት ይጠብቅልን!