November 23, 2022
26 mins read

የኦነግ ብልጽግና ጡሩምባ፣ መሬት ቀዶ ገባ!!!መሬት ለኢንቨስተሩ!!! መሬትና የመብት ማሽቆልቆል!!! – ፂዮን ዘማርያም

ግልፅ ደብዳቤ ለዶክተር አብይ አህመድ

ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

የኢትዮጵያ ገጽታ ጦርነት፣ ርሃብ፣ በሽታና ስደት በአንድ በኩል፣ ሌላዋ ገጽታዋ ደግሞ ፓርኮች፣ ፋውንቴኖች፣ ስው ሰራስ ሐይቆችና ግድቦች፣ ቤተመንግሥት፣ ወንዞችና የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት፣ ስማርት ሲቲ የጫካ ፕሮጀክት፣ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ሃያ አንድ ነጥብ ሁለት ህዝብ በችግር ላይ ይገኛሉ፡፡ ጠቅልይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፕሮጀክትዎን ከልብ በማድነቅ ለጊዜው ተውት አድርገው፣ በድርቅ ለተጎዱ አስራስድስት ሚሊዮን ህዝብና ከቀያቸው ለተፈናቀሉ አራት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ህዝብ የነፍስ ማዳን ፕሮግራም በጀቱን እንዲያውሉት በሚወዶቸው እናትዎ ስም በተጎጂው ህዝብ ስም እጠይቃለሁ፡፡ አጠገብዎ የከበቡዎት ዝንብ ሰራሽ ምሁራን ከራሳቸው ሆድ በስተቀር የሚታያቸው አንዳችም ነገር የለም፣ ስለ ህዝቡ አሰቃቂ ችግር ዞረው በማየት እራስዎ ዓይተው እንዲፈርዱ ይሁን ፡፡ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ/ም ሪፖርት መሠረት ኦነግ ሽኔ በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞንና በቤኒሻንጉል ክልል ከማሺ ዞን የዕለት ደራሺ እርዳታ ለማድረስ የተላኩ ተሸከርካሪዎች ለሦስት ወራት ማገቱን ፣ መዝረፉንና የተወሰኑትን መቃጠላቸውን ተናግረዋል፡፡……………………………………………..…………………….(1)

‹‹በኢትዮጵያ በአጠቃላይ 21.2 (ሃያ አንድ ነጥብ ሁለት) ሚሊዮን ዜጎች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ፣ ከእነዚህ ውስጥ 16 (አስራስድስት ሚሊዮን ህዝብ) በድርቅ የተጎዱ፣ እንዲሁም 4.6 (አራት ነጥብ ስድስት) ሚሊዮን የተፈናቀሉ መሆናቸው ተገልፆል፡፡ መንግሥት ለ9.4 (ዘጠኝ ነጥብ አራት) ሚሊዮን ዜጎች ዕርዳታ እያቀረበ መሆኑን፣ ለ11(አስራአንድ) ሚሊዮን ወገኖች ደግሞ በለጋሽ ድርጅቶች እንደሚሸፈን ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡ በመጪዎቹ ሁለት ወራት በመንግሥት በኩል ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 8.8 (ስምንት ነጥብ ስምንት) ሚሊዮን ዜጎች መንግሥት ስድስት ቢሊዮን ብር ያለው ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ ለማድረግ ተጨማሪ 13 (አስራሦስት) ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ አክለዋል፡፡ የፌዴራል መንግሥትና የሕወኃት ወኪሎች በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ካደረጉ በኃላ፣ 263 (ሁለት መቶ ስልሳ ሦስት) ከባድ የጭነት መኪኖች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ዕርዳታ ጭነው መጎዛቸውን አስታውቀዋል፡፡››የቌሚ ከሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ነገዎ ‹‹ኮሚሽኑ ዕርዳታ ከማመላለስ ወጥቶ፣ ዕርዳታ ፈላጊ ዜጎች ስለሚቌቌሙበት መንገድ የተሸለ ስትራቴጂ እንዲቀየስ አሳስበዋል፡፡ በመሆኑም ዕርዳታ ማድረስ ጊዜያዊ ሥራ እንጂ ቌሚ ተግባሩ ሊሆን እንደማይገባ፣የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲዎችን ጨምሮ የውች እርዳታ ድርጅቶች የምዕራባውያን የፖለቲካ ማስፈፀሚያ በመሆናቸው በተቻለ መጠን የእነዚህን ተፅዕኖ ለመቀነስ ጥገኝነትን  መቀነስ ያስፈልጋል፡፡›› ብለዋል በወያኔ በቦሌ ወጥቶ በምዕራባዊያን ሀገር ተሰዶ የኖረውና  በብልፅግና በቦሌ የገባው ዲማ ነገዎ፡፡ በእናት ኢትዮጵያ እናቱ የሞተችበትም፣ እናቱ ወንዝ የወረደችበትም ልጅ እኩል ያለቅሳል፡፡ በጦርነቱ አንድ ሚሊዮን ወጣቶች አልቅዋል፣ በመቶ ሽህ ወጣቶች አካላቸው ጎሎል፣ አራት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለው በተለያየ መጠለያ ጣቢያ ይገኛሉ፣ አስራስድስት ሚሊዮን ዜጎቻችን በድርቅና ርሃብ ቸነፈር እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡  የኢትዮጵያ ገጽታ በአንድ በኩል፣ ጦርነት፣ ርሃብ፣ በሽታና ስደት  ሲሆን ሌላዋ ገጽታዋ ደግሞ ፓርኮች፣ ፋውንቴኖች፣ ስው ሰራስ ሐይቆችና ግድቦች፣ ቤተመንግሥት፣ ወንዞችና የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት፣ ስማርት ሲቲ የጫካ ፕሮጀክት ሆኖል፡፡

 

መሬት ለኢንቨስተሩ!!! መሬትና የመብት ማሽቆልቆል!!!

yyechakaw house

አዲስ አበባ የጫካው ፕሮጀክት 3700 ሔክታር መሬት:-ዘመናዊ ሳተላይት ከተማ ሲሆን ከእንግሊዝ ኢንባሲ የሚገኙ ተራሮችን አካሎ ሱሉልታ ሸፍኖ፣ ጣፎ ደርሶ የሚመለስ የሦስት ሽህ ሰባት መቶ ሔክታር መሬት የሚሸፍን ስማርት ከተማ በውስጡም አዲስ የአብይ ቤተመንግሥት በሰማንያ ቢሊዮን ዶላር፣ ሰው ሠራሽ ግድብና ሐይቆች፣የኬብል ትራንስፖርት፣ የንግድ ማዕከላት፣ መኖሪያ ቤቶችና ኮንዶሚንየሞች ያካተተ እንደሆነ ተገልፆል፡፡ የጫኮው ፕሮጀክት ሥራ በግልጽ ጨረታ ውድድር በጋዜጣ ወጥቶ ያልታየ ሲሆን አስራአንድ ኩባንያዎች በስራው እንደተሳተፉ ግን ተገልፆል፡፡ የጫካው ፕሮጀክት የግንባታ ወጪ ከአራት መቶ ቢሊዮን እስከ አንድ ትሪሊዮን ብር ይገመታል፡፡ ከዚህ ሥፍራ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ እንደሚፈናቀል ተገምቶል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በዓመት ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኛል ተብሎል፡፡ የጫካው ፕሮጀክት ሁለት ቢሊዮኝ ዶላር ገቢ በዓመት  ያስገኛል የሚለው ጥናት የተጋነነ ይመስላል፣ዶላሩን ወደ ኢትዮጵያ ብር ስንቀይረው 105,940,000,000 (መቶ አምስት ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሚሊዮን ብር በዓመት ይሆናል ) (1 USD to ETB = 52.97የተሠላ) በቱሪዝም መስህብ ያስገኛል ብሎ መገመት ጥናቱን ኢታማኝ  ያደርገዋል፡፡ የጫካው ፕሮጀክት አንደኛ የገንዘቡ ምንጭ አለመታወቁና አለመገለፁ ግልፅነትና ታማኝነት በኢትዮጵያ መንግሥታዊ አሠራር ታሪክ ለአንዴና ለሁሌ ያጠፋዋል፡፡ ሁለተኛ የጫካው ፕሮጀክት፣ በ2015ዓ/ም በጀት የተያዘ አለመሆኑ፣ ፓርላማው፣ የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስቴር፣ ብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን  የማያውቀው  የፕሮጀክቱ ስራ በህጋዊ ጨረታ በጋዜጣ ሬዲዮና ቴሌቪዥን አለመውጣቱ ከዶክተር አብይ አህመድ ግራ ኪስ አቆማዳ በልመና ቀፈፋ የተገኘ መሆኑ በድፍረት ሲገለፅና ደላላ የሚጫወትበት መሬት የተረፈው የጫካ ፕሮጀክት  መሆኑ ስንሰማ በሃገሪቱ ህግና ሥርዓት፣ ተጠያቂነት፣ አለመኖሩን ያሳያል፡፡

ለዶክተር አብይ አህመድ በገፀ በረከት የተበረከተላቸው በጂማ 700 ሔክታር መሬት እንዲሁም በአርባ ምንጭ 400 ሔክታር መሬት የመስጠትና የመቀበል ህገ-መንግሥታዊ ሥርዓት የለም፡፡ ህጋዊና አስተዳደራዊ መመሪያ የለም!!! ሙስና ነው!!! ሙስና ማለትም ያለ ህግ የሚደረግ መስጠትና መቀበል ግንኙነት ነው፡፡ በዶክተር አብይ አህመድ ዘመን  የኦነግ ብልጽግና ጡሩምባ፣ መሬት ቀዶ ገባ!!! መሬት ለኢንቨስተሩ!!! መሬትና የመብት ማሽቆልቆል በፓርኮች፣የወንዞች ልማት፣ የጫካ ፕሮጀክቶች ስም THE GREAT LAND RUSH and LAND GRAB ድብቅ የኦሮሙማ  ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡

ከአብይ አህመድ ፓርኮች  የግንባታ ወጪዎች ውስጥ፡-አንድነት ፓርክ 5 (አምስት) ቢሊዮን ብር፣ እንጦጦ ፓርክ 2.5 (ሁለት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር፣ አደዋ ዜሮ ኪሎሜትር ፓርክ 4.6 (አራት ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ብር፣  ወዳጅነት ፓርክ 2.5 (ሁለት ነጥብ አምስት ) ቢሊዮን ብር፣ ቢተወድድ ጎሹ ወለወደፃዲቅ ፓርክ 101 (መቶ አንድ) ሚሊዮን ብር፣ አንባሳደር ፓርክ 49 (አርባ ዘጠን) ሚሊዮን ብር፣ መስቀል አደባባይ 2.6 (ሁለት ነጥብ ስድስት)ቢሊዮን ብር፣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት እድሳት 2.2 (ሁለት ነጥብ ሁለት) ቢሊዮን ብር ተገንብተዋል፡፡ በተመሳሳይ የወንጪ፣ጎርጎራና ኮይሻ ፓርኮች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡

  • ኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ የኢኮኖሚ ዘርፍ የመሬት ቅርምት በመሬት ሽሚያ ለተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መስሪያ ቦታዎች የመሠረት ድንጊያ ማስቀመጥ፣ የተለያዩ  የባህል ማዕከል ግንባታ ቦታ  በኦሮሚያ በአማራ፣ በጉራጌ ወዘተ በህዝብ ስም የመሬት ቅርምት ተጦጡፎ ይገኛል፡፡ የአዲስ አበባ የመሬት ቅርምት ፎርሙን ቀይሮና ዛሬ ፋሽኑ የአዲስ አበባ ፓርክና መናፈሻ የኢሬቻ ባህል ማክበሪያ ሰፊ ሥፍራ መቆጣጠር የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤትና የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት አዲሱ ፋሽን ሆኖል፡፡  በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በህወሓት ኢህአዴግ የተከናወኑ የመሬት ቅርምቶች ውስጥ የመለስዜናዊ አመራር አካዳሚና የመለስ ፋውንዴሽን የመሳሰሉት ተቆማት በአሁኑ ጊዜ በኦህዴድ ብልጽግና ፓርቲ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ 22 ሽህ ካሬ መሬትን ወደ  ሆስፒታልነት መቀየሩ ጎሽ የሚያስብል ቢሆንም በኦሮሙማ ማኒፌስቶ ፊንፊኔ ኬኛ የሚለውን የመስፋፋት ፖሊሲ አንዱ አካል እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከስታዲየም ከፍ ብሎ  የዋቆ ጉቱ ፋውንዴሽን ቢሮ መከፈቱን ስንቶቻችሁ አስተውላችኃል፡፡
  • ወንዞችና የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት (Rivers and Riversides Development Project)

ዶክተር አብይ አህመደ በሠላሣ ቢሊዮን ብር በላይ በአዲስ አበባ ከተማ የወንዝ ዳር መናፈሻ በመንግሥት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ (This 29 billion birr (about $1.028 billion), rivers and riversides development project is slowly making the city green as works for developing and rehabilitating the two rivers in the city launched in February 2019 progress.) የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት ከ50 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በ29 ቢሊዮን ብር (1.028 ቢሊዮን ዶላር) ወጭ የሚገነባው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት የካቲት 21ቀን 2019 እኤአ ይፋ ተደርጎል፡፡ የቤተ-መንግሥት አካባቢ የከተማ መናፈሻ ፕሮጀክት፣ ከእንጦጦ ተራራ የሚነሱ ሁለት ዋና ዋና  ወንዞችን አንደኛው 23.8  ኪሎሜትር ሌላው 27.5 ኪሎሜትር በከተማዋ ውስጥ በመጎዝ በንዋሪዎቹ ቀበና፣ግንፍሌ፣ቡልቡላ በሚል እየተጠሩ ወደ አቃቂ ወንዝ ይቀላቀላሉ፡፡ በከተማዋ ብዙ ገባር ወንዞች የሚገኙ ሲሆኑ ወንዞቹ የውሃ ብክለት ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ ከባቢ አየር ለመንከባከብ የተወጠነ ሲሆን የከተማ ቱሪዝም ለማስፋፋት ታቅዶል፡፡  በዚህ ፕሮጀክት ቤተመንግስት ጋራዝ፣ ፒያሳ፣ ውጭ ጉዳይ እያለ አቃቂ የሚደርሰው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት በይፋ ተጀምሮል፡፡

  • ‹‹አዲስ የከተማ መንደር ምሥረታ›› ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ‹‹አዲስ የከተማ መንደር ምሥረታና ግንባታ›› የአስር ሽህ ፎቆች ግንባታ የመሥሪያ ቦታ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መጠየቁን በሁሉም ሚዲያ ተሰራጭቶል፡፡ ዋና ዓላማው የኦሮሚያ ክልልን ተጠቃሚ ለማድረግ በብልፅግና ፓርቲ መንግሥት መር ግንባታ በማድረግ በኦሮሙማ ፕሮጀክት ሥም የከተማ ኮንዶሚኒየሞች ኃብትና ንብረት በተዘዋዋሪ ዘረፋ ነው፡፡ የግሉ ዘርፍ ግብርና ታክስ የሚከፍሉ ሪል ስቴት ዲቨሎፕርስ ባሉበት ሃገር፣ በአዲስ አበባ ከተማ የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሥራ ላይ የተሠማሩ ባለሃብቶች እያሉ የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት በግንባታ ሥራ ዘርፍ ላይ ምን ጥልቅ አረገው!!ኮንዶምንየም  ቤቶች፤ የኮዬ ፌጫና  ገላን የሚገኙ ሠላሣ ሶስት ሽህ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ዜጎች ከባንክ ተበድረው ገንዘብ አጠራቅመውና በባንክ ቆጥበው ኮንዶሚኒም ከሰሩ ዜጎች ተነጥቆ ለኦሮሚያ ዲያስፖራ ተመላሽ፣ ቄሮና  ኦዴፓ ካድሬዎች  እንደተሰጠና የዶክተር አብይ መንግሥት የኢትዮጵያን ህዝብ በእኩልነት ዘር ሳይለይ እንደማያስተዳድረን ተስፋችንን እንደገደለ ሁሉም ይመሰክራል፡፡ ታዲያ ‹‹የአዲስ የከተማ መንደር ምሥረታና ግንባታ›› ለማን?

 

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር የምርምርና የፖሊሲ ጥናት ዘገባ፡-

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር የምርምርና የፖሊሲ ጥናት ዳይሬክተር ዶክተር ደግዬ ጎሹ፣ለኢኮኖሚያዊ ቀውሱና ለዋጋ ንረት መባባስ ዋና ምክንያት መሬትና የመብት ማሽቆልቆል መሆኑን ገልጸዋል፡፡…………………………..(2) ማህበሩ በወቅታዊ አገራዊ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ ያጠናውን ጥናት ሰሞኑን ይፋ ባደረገበት ወቅት እንዳስታወቀው፡‹‹የመሬት አስተዳደር በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ለተከሰተው ኢኮኖሚያዊ ቀውስና ለዋጋ ንረት መባባስ በዋነኛነት ተጠቃሽ ሆኖል፡፡ የመሬት አቅርቦትና የአጠቃቀም መብት በከፍተኛ ደረጃ እያሽቆለቆለ መምጣት፣ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ለዋጋ ንረትም ዋነኛ መንስዔ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ …ለሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ቁልፍ ሚና ያለው የመሬት አቅርቦትና በመሬት መጠቀም መብት በከፍተኛ ሁኔታ መሸርሽሩ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ መሆኑ ን ማህበሩ ገልጾል፡፡ በህጋዊ መንገድ መሬት አግኝቶ ማልማት ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ችግር እየሆነ መምጣቱን ባደረገው ጥናት አረጋግጦል፡፡ከመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡››

  • ‹‹ኢትዮጵያ በአግባቡ መሬት የማቅረብና የመጠቀም መብት እኤአ በ2013 ወደ 96 በመቶ አካባቢ የነበረ ቢሆንም፣ በ2021 ግን ወደ 21 በመቶ መውረዱን ማህበሩ ያደረግኩት ባለው ጥናት ያመላክታል፡፡ ለግብርናም ሆነ ለማንኛውም ዓይነት ኢንቨስትመንት እንዲሁም ለቤት ግንባታና በአጠቃላይ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ መሬትን በአግባቡ መጠቀም ተገቢ ቢሆንም ይህንን ኃብት በአግባቡ መጠቀም ተገቢ ቢሆንም ባለመቻሉ እያስከተለው ያለው ኢኮኖሚያዊ ችግር እየጨመረ እንዲሄድ አድርጎል፡፡››
  • ‹‹ማህበሩ የችግሩን ግዝፈት ለማሳየት ሌላው የጠቀሰው አኃዛዊ መረጃ እኤአ በ2017 ከ 129 የዓለም አገሮች የመሬት አቅርቦትና የአጠቃቀም መብትን በተመለከተ የነበረው አፈፃፀም፣ ኢትዮጵያ 67ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ የነበረ ቢሆንም፣ በ2021 ግን ወደ 115ኛ ደረጃ መውረዷተጠቆሟል፡፡  መሬትን በህጋዊ መንገድ አግኝቶ ማልማት ከማይቻልበት ደረጃ መድረሱን፣ በአሁኑ ወቅት መሬት ማግኘት የሚቻለው በሁለት መንገድ ብቻ ነው፡፤ አንዱ መሬት ማግኛ ዘዴ ሙስና ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መሬትን በመውረር መውስድ ነው፡፡ አይደለም ለውጭ ኢንቨስተር ለአገር ውስጥም መሬት ማግኘት ከባድ እየሆነ መምጣቱን ፣በመሆኑም የመሬት አጠቃቀምና በመሬት የመጠቀም መብት እጅግ አሳሳቢእየሆነ ስለመጣ ማሻሻያ ሊደረግበት ይገባል፡፡››
  • ‹‹ጉዳዩ መሬት የግል ይሁን ወይም የመንግሥት የሚለው ሳይሆን ባለው የመሬት ሥሪት እንኳን በአግባቡ ቢሠራ ለውጥ ሊመጣ ይችላል፡፡ መሬትን በአግቡ መጠቀም ቢቻል የዋጋ ንረት በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስ ይችላል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ለኢንቨስትመንገት ፣ ለግብርና ፣ለቤት ግንባታም ሆነ ለመሳሰሉት መሬትን በህጋዊ መንገድ መጠቀም የማይቻልበት ደረጃ ይደርሳል የሚል ሥጋት አላቸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ መሬትን በማቅረብና በመጠቀም ረገድ ያለው አፈፃፀም ከ96 በመቶ ወደ 21 በመቶ የወረደው ፣የመሬት ሥሪቱ ተቀይሮ አይደለም፡፡ ››
  • ‹‹ኢትዮጵያ ግብርና መር ኢኮኖሚ ትከተላለች ሲባል ትልቅ መነሻ ሀብት ‹‹መሬትና ጉልበት ነው፣ አሁን ግን ትልቁ የመሬት ሀብት ታንቆ እየመከነ መገኘቱ ጉዳት እያስከተለ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ግብርናው ኢኮኖሚውን መርቶ ሊነሳ ይቅርና አሁን ባለው ሁኔታ የእለት እንጀራችንን ሊሰጠን ያልቻለበት ምክንያት በመሬት ዙሪያ ያለውን ችግር መፍታት ባለመቻሉ ነው፡፡ በጥቅል ሲታይ ደግሞ የመሬት አቅርቦትና መሬት ላይ እየታየ ያለው ችግር እየጨመረ የመጣውና ለችግሩ መባባስ መንግሥት በአብዛኛው መቆጣጠር ባለመቻሉ እንደሆነም ጥናቱ አሳይቷል፡፡ ባለፊት 25 እና 30 ዓመታት የመሬት አቅርቦትና የመጠቀምመብት ፍተኛ ሁኔታ እየወረደ መምጣት ደግሞ፣ ኮኖሚ እንቅስቃሴች ላይ ጫና ከመፍጠር ፎ፣ አሁን ለተከሰተው የኑሮ ውድነት ከፍተኛውን ድርሻ እንዲይዝመደረጉም ተጠቅሷል፡፡››

የመሬት ቅርምት!!! ….መሬት አይሸጥም አይለወጥም! መንግሥት ከመሬት ባለቤትነት ይነቀል! መሬት ከፖለቲካ ካድሬዎች የኃብት ምንጭነት ይላቀቅ!!!

 

ምንጭ

  • ኦነግ ሸኔ ስብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ ተሸከርካሪዎችን ማገቱና ማቃጠሉ ተነገረ;/ሪፖርተር ጋዜጣ ኖቨንበር 20ቀን 2022
  • ለኢኮኖሚያዊ ቀውሱና ለዋጋ ንረት መባባስ ዋና ምክንያት መሬትና የመብት ማሽቆልቆል መሆኑ ተገለጸ/ሪፖርተር ጋዜጣሜይ 1 ቀን 2022

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop