February 4, 2014
18 mins read

አርቆ ለማየት ግመል ጀርባ ላይ መቀመጥ ያስፈልገናል ወይ? – ከመኳንት ታዬ (ደራሲና ገጣሚ)

ከመኳንት ታዬ(ደራሲና ገጣሚ)

መሬት ከሠው ልጅ ጋር ቁርኝት ካደረገችበት የዘመን አመታት ከዚህ ግዜ ጀምሮ ሀጥዑ ነበር። ከዚህ ግዜ ጀምሮ ፃዲቅ አልነበረም ብላ ለፈጠራት ያማረረችበት ርዕስ አልተፃፈም።መሬት ከአፈር አፈር ከሰው ልጅ አለና እንዲህ ባለ የእድገት ርዝማኔ ውስጥ የትዬእለሌ የሆኑ በክንዋኔዎች ተካሂደው ዘመነ ፍዳ አልፎ ዘመነ ድህንነት ተተክቶ እንደየ ግዜው ብልጠትና ጥበት ብሎም እድገት እየተራዘመ መጥቶ ዛሬ ላይ ደርሰን። ዛሬ የሰጠንን ጨምረን ሸክፈናል።

እንደ መግቢያ ከላይ ያለውን ካልኩኝ በሗላ አርቆ ለማየት ግመል ጀርባ ላይ መቀመጥ ያስፈልገናል ወይስ በአይነ ህሊናችን ቅርቡንና እሩቁን ጅምሩንና ጭርሱን፤ እየሆነ ያለውንና መፂውን መተለም በእውኑ ከእኛ ያለ ገንዘባችን አልነበረም ወይ?የዚህ ሁሉ ጥያቄ ባለቤቱ እራሱ የእኛ ሠው ይሆናል።ፅሁፋችን አማርኛ ፀሃፊው ኢትዮጲያዊ እንደመሆኑ መጠን ጉዳዮቹ እኛን ይመለከታል። ሥለእኛም ያሳውቃል። ስለዚህ በዝርዝር አጠር በላ ዝርዝር ከተከመረው ጉዳያችን ለመቀነት የሚበቃውን ጥጥ እንፍተል።

ፖለቲካችን

ፖለቲካችን ልክነቱ በቋንቋችን በባህላችን በአጠቃላይ በኢትዬጲያዊ ስልጣኔአችን ብሎም በትውልድ መሃከል ባለ የእድሜና የአስተሳሰብ ደረጃ መሆኑ ይገመታል። የጠነከሩት ክሮች ለጋቢ ሲበቁ የነተቡት ተበጥሰው ከመንገድ እየቀሩ የሸማኔው ቆሻሻ ሆነው ተጠርገው ይወጣሉ። ይሁን እንጂ ለፈታዩ ክሮች ሆነው ቀሰሙን ሞልተው ሸማኔው ጋር ደርሰው እንደነበር ይታወሳል።ይሁንና እንዲህ ባለ ጥሎ ማለፍ ጫወታ ሸማኔው በየፈርጁ ለብሶ ውበቱን ትውልድ እንዲጠቀምበት እንዴት እና በምን ምክንያት ከትከሻ ትከሻ እንዴት መተላለፍ እንዳለበት ፖለቲካ እራሱ ገዢ መሬት አለው። ሆኖም ግን የፖለቲካው ሸማኔ ድርና ማጉን እየመረጠ ፋሽኑን እየቀየረ ለገበያ ማቅረብ ያለበትና ከባለፈው ስራውና አሁን እየሰራ ካለው ገበያተኛ የወደደውን ወይም በርከት ያለ ሸማች ያለውን ማቅረብ ግድ ሳይለው እንደማይቀር ፖለቲከኛ ሆኜ ባላየውም የማነበው አልጠፋምና ሳይበዛ የተገነዘብኩ ይመስለኛል።

ታዲያ የተከበረው የፖለቲካ ጥበብ ከምን ተነስቶ ምን መድረስ አለበት የሚለውን በሚሊዬዎን ለሚቆጠሩ አዋቂዎች ለመንገር አይዳዳኝም። ግን ለቀባሪው ማርዳት የሚለውን እንኳን ትተን፤ ሊያረዳ የሚመጣ ካለ ያልቀበረም ማስታወስ ይችል ስለመሰለኝ ነው። እንደማለዘቢያነት የእኛ ሃገር ፖለቲካ ጫወታ መንቹ ሲወረወር ብዙ ግዜ የሚያርፈው የትውልድ መስመር ላይ እየሆነ መፎረሹ አልቀነስ አለንሳ። እንደ አብነት የትላንቱ ደርግ. በኢሃፓ ሰበብ ኢትዮጲያ መቼም ቢሆን ልትተካቸው የማትችለውን ትውልድ እንዳጣች ታሪክ ይዘግብልናል። የአሁኑ ደግሞ ከዛሬ ጀምሮ አስከ ነገ የምታጣውን እየሰራ ነው ።የነገው ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚቺል መገመት ያስቸገራል። “ያልዘሩት አይበቅልም “ብዬ ለመናገር ፈራለሁ። ምንአልባት ድንጋይና ድንጋይ ሲፋጭ እሳት ይፈጥራልና እርሱም ከነደደ ከበርሃንነቱ በዘለቀ ትውልድ አብስሎ የሚበላበት ይሆን ይሆናል።የሗለኛውና የፊተኛው ድንጋዮች ታገጭተው የፈጠሩት እሳት።ወደፊት ተራምዶ የታሻለ ገመድ የማይስብበት ነገር አለ አልልም ።ይታየኛል እና።

ግን የእኛ ሓገር ፖለቲካ ፤እንደምጣዳችን ፤እንደ እንስራችን አፍ እንደ ሌማታችን ፤ክብ ክብ የመሆኑ ሚስጥር ይሆንን? ኳስ አንድ አንግል መያዝ አቅቶአት ዘመኑ እና ትላንቶቹ ተቀይረው የዛሬዎቹ ቢመጡም ትውልድ ለነገ እንደ ግብ የሚቆጥረው ያጣ ይመስላል። ዘመኑ ሲሻገር፤ ትልቅ ጉዳይና መልካም ቢሒል ይዞ መሻገር ይፈልጋል። ሂሳቡ ሲሰላ በአስተሳሰብ + የህዝብ ስልጣኔ + የህዝብ ብዛት ውጤቱ አንድ በጣም የተሻለ ነገር መሆን ነበረበት ። ግን ያ የለም። ታዲያ ምን አለ፤ “አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ “? ቦታ ቀይሮም የበቀለበት ቦታም ቢሆን “ስምና ምን አልባት ብሔር ቀይሮ ያው ያለውን መተወን። “ሺ ቢታለብ ያው በገሌ”።

ግን አስከመቼ? ሌላ ጥያቄ። ያኔ በሗለኛው ዘመን ከሚኒልክ ወደ ሐይለስላሴ ስንሸጋገር በዘመኑ ያልነበረውን ነገር በመጨመር የተሻለ እየሆነ ዛሬ የምናነሳው ነገር አገኘን። ውሕደቶቹም ከደርግ ወደ ኢሕዴግ እያለ መጣና ትውልድን እንደ ግራዋ ማጣንት በሩቅ የሚያስሉት እሴቶች የሚታዩ ይመስለናል። አበስኩ ገበርኩ አለ የሐገሬ ሰው። በዚህና በዚህ ምክንያት 1+1 በስምምነት በሚመጣ እውነት መሃከልና 1+1 ከእውነት በተገኘ አንድነት በሚነሳው ጥግ የማይስቡት ርዝመት ተከስቶ እውነት የሆነውን እምነት ትላንት የነበረው አለንጋ እጅና ደጅ ቀይሮ ስለመታው ወይም እየመታው ግርፍ ያረፈበት ሰንበሩ እየባሰ መጣ። በዚህ ሁነት የእኛ ሐገር ፖለቲካ ከየት ተነስቶ የት ሊደርስ ነው? ብሎ ዘመኑ ሲጠይቅ መላሹ ማነው?

እምነታችን

በዚህ ርዕስ ሐላፊነቱን ለመውሰድ እኔው አለሁበትን እምነት ብቻ ላንሳ። የ ኢ/ኦ/ተ/ቤ ክርስቲያንን።

መጀመሪያ ቃል ነበር ። ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር። ቃልም በእግዚያሐብሔር ዘንድ ነበር(ዮሃ1፤1) እንዲህ እያለ ሲጀመር ሲፈፅምም መያዣ ያደረገው ፈጣሪውን እንደሆነ ለምስክርነት ከገነት የተባበረረው አዳም አሁን እራሱን እያባረረ እስከሚኖርባት ዘመን ድረስ ከአምላኩ ጋር ቁርኝት ያደረገባትንና የጌታችን የመድሀኒታችን ደሙ የነጠበባትን ደጀ ሠላምን እንደ መሰላል ተጠቅሞ በቅዱስ ስራውና በንስሃው ዘውትር እየወጣና እየወረደ እየተገለገለባት ይኸው አለ። ስለዚህ በአሁኑ ሁነት የሐጢያት ደረባ ፈርሶ አከባቢውን ሲያቆሸሸ ማየት የአማኞች ፍቃድ አደለም።እርግጥ ነው አማኞቹ እኛው ከሃዲዎቹ እኛው ሥለሆንን እኛን ብቻ ማየቱ ፅሁፌን እድሜ ሥለሚያራዝምልኝ ከእኛው ጋር እየታገልኩ ላብቃ።

እንዲህ ሆነ። አለቃ ገብርሃና የታባሉ የሗለኛው ዘመን አስቂኝ (ኮመዲ) በአንድ ወቅት የሆነ ቦታ ላይ እክል እንዲገጥማቸው ተደርጎ ነበርና ያንን ለማምለጥ እንዳውራ ደሮ ጮኹ ተባለ። (ዛሬ ቢኖሩ ደሞ ግራ ሲገባቸው እንደ ሲካካ ዶሮረ ይጮኹ ነበር) በዚህ ግዜ ነገር ያዘጋጀው ሰው ከምሃከል ተነስቶ “አለቃ ምነው?”ቢላቸው “አለቃም ለዚህ ሁሉ ዶሮ አውራው እኔ አደለሁም ወይ? አሉ ይባላል ።ቕድስት ቤተክርስቲያንም እንዲሁ ናት።ለእኛ ከጥበብ ጋር የመኖር ሚስጥር፤ካባሕላችን ጋር የመኖራችን ሚስጥር አረ ስንቱ፤ ብቻ ከእኛነታችን ጋር የመኖራችን ሚስጠር ፤የኢትዮጲያውያን ከብዙ ማሸነፍ ጋር የመኖራቸው ዘዴ ቅ/ቤተክርስቲያን ናት ።በዚህ ሁሉ ሁነት ውስጥ ግን ገረገራውን ተሻግሮ መቅደሱ የገባውን ፈተናዋን ሳናነሳ አናልፍም።በጣም ጥቂት እንደው ለአሉታ ለተወሰኑ ማይክሮ ሰከንዶች የሚበቃውን እናውጋ።

የጎደላት ሳይኖር ያልጎደለባቸው ልጆቿ ያጎደሉባት እና ጎደለ ብለው አደለ አጎደልን ብለው አደል ብቻ እንዲሁ በዋል ፈስስ ሆንን። ይሄም ያልፋል አይባል ነገር ፈተናው እመቅደስ ድረስ ሰተት ብሎ ገብቶ ግራ ማጋባት ከጀመረ ቢቆይም ባሳለፍናቸው 20 አመታት ደግሞ በአይነቱ የተለየ ሆነ። መንገድ ላይ ስንመጣ ከሚገጥመን ነገር ጀምሮ ቤተ መቅደስ አስክንደርስ ድረስ ያለውን ጨምረን ልናስቀድስ ስንቆም በየልቦናችን ኪስ ገብቶ ሰው የዳቢሎስን ስም ተክቶ እከሌ እንዲህ አደረገ እንጂ ሰይጣን አሳሰተው፤ በስህተት ካልሆነ የማይባልበት ደረጃ ደረስን።ይኸም ይመስላል ዘመን አመጣሽ ወረረሸን ከሊቅ አስከ ደቂቅ ተናፍሶት አዲሱ ፕሮቴስታናዊ አካሄድ ፖለቲካን ካባ አድርጎ ቤ/ክ ይዛ የመጣቸውን መንገድ ለማቋረጥ የትውልድን አመለካከት ሲቆፍር ይስተዋላል። ይህ አካሄድ ደግሞ ወዴት ያመራናል? በእውኑ ልዩነታችን በማመንና ባለማመን ውስጥ ነው ወይስ መፍታት በሚቻልና በማይቻል ጉዳይ?። ይህ ከሆነ እሩቅ ሳንሄድ ትላንት እግዚያብሔር የለም ያሉትን አስታውሶ ዛሬ ኦርቶዶክስን ማጥፋት ግባቸው ከሆኑት ጋር ኩታ ገጠም እንሆናለን ያሰኛል። ስለ እምነታችን የሚለውን ስናነሳ ስንዱ እመቤት እንደሆነች አውግቼአችሁ ነበር። አዎ አሁንም ናት። ግንሳ ቀሚስ ለብሶ የገባውን የመንግስት መዳፍ ድምጿን ሊሰሙ የመጡትን በጎቿ በእረኛዎቿ ድክመትና ቀንዳቸው ከውበታቸው በተላለፈባቸው በጎቿ አማካይነት ከበረት የሚወጡትን ቁጥር እየጨመረ መጥቷል ።በዚህ ሁኔታ ሩጫው ወዴት ነው ?።መጨረሻውስ ምንድ ነው ? ከገረገራው አልፎ እስከ ቤተ መቅደስ በሚሠራው ስህተት አዲሱ ፕሮቴስታናዊ ፖለቲክስ እጅህ ከምን? በእውኑ እምነት ወይስ በእምነት ስም የማህበረሰብ ስብስብ። አዋጭነቱስ አስከምን ድረስ ነው? እምነት ከሆነ በመላው አለም የምንገኝ ኦርቶዶክሳዊያን (በተለይ በውጭ ሃገር)የሚወክለን የመጽሃፍ ቅዱስ ቃል ጠፋ ወይስ ዳግም ክርስቶስ እስኪመጣ እንጠብቅ?።

እርግጥ ነው በዚህ ዙሪያ የሚደረግ ንግድ ቢሆን ቢሆን “ቁርበት ነጋዴ ምን ትነግዳለህ ትርፍህ ምንድነው ዘጭ ዘጭ”ይሆናል :፡ግን ደሞ ጠላት ዳቢሎስ ሰዎችን ለመፈተን ምክንያት የሆነው ወንድም/እህት(ወገኖች) መዳን አይገባቸውም ወይ ? እነዚህን እና ሌሎቹን ጥያቄዎኦችን የሚመልስ እራሱ የተባረከ ነው። ብዬ ጥያቄው ብዙ ምላሹ ብዙ የሆነውን ጉዳይ ልቋጭ።ስጀምር መጀመሪያ ቃል ነበረ (ዮሃ1፤-1) አሁን ደግሞ ቁ14 ላይ ሄደን ቃልም ስጋ ሆነ ፀጋና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ”የሁላችንም የፀጋው ባለቤት መሆን ከሚመጣው ጥፋት ለመዳንና ከአሮጌ ደፈተራችን ላይ እያነሳን አዲስ የቤት ስራ ለትውልድ በመስጠት የዳቢሎስ ስም በእኛ እንዳይተካ መጠንቀቅ የግድ ሳይለን እንዳልቀረ መንፈሴ ያሳሰበኝን ለማለት ወድጄአለሁ።

ባህላችን

ባሕላችን እና ቋንቋችን ከሌላው አለም ትንሽ ለየት እንደሚያደርገን ሁሌም የምናወሳው ነው። በዚህም አንዳች የተለየ ነገር ሲገጥመን ምነው ኢትዮጲያዊ አደለህም/አደለሽም ወይ እንባባላለን። ታዲያ” ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ አልጠፋምና” በዚህ ምክንያት “ይሉኝታ” የሚባል ግርማ መጎስ የሆነን ቆባችን አለን። ይህን ስናወልቅ ጦሩ የተሰበረበት አዳኝ እነሆናለን። በዚህ ሁኔታ እኛንም በስህተታችንና በይሉንታ ማጣታችን ሊከሰንና ሊበላን ከሚችል የህሊና አውሬ ለመዳን መፍተሔውን ገንዘብ ብናደርግ። አውሬዎቹን ለመጥቀስ ያህል ፤እርስ በእርስ መናናቅ ዘረኘነት፤ ጎጠኝነት መከፋፈል በአሁኑ ግዜ ጥርሳቸው ከሾሉት አውሬዎች ውስጥ ናቸውና። ታዲያ እንዳይንዘላዘል አድርጎ አዝሎ መዞሩ ወዴት ያደርሰናል? ውርስስ እናድርገው ብንል ይጠቅማል ወይ? ሁሉም እራሱን ይጠይቅ። በካይነቱን እና በቶሎ መራባቱን አውቆ ተፈጥሮ እና ሐይማኖት ብሎም እናት ኢትዮጲያ ካደለችው ጥቂቱን በመጠቀም የባህላችንን ክብሩነቱን ጠቀሜታውን ከወሬ ባለፈ ብናሳይ እንዴታ የተዋበ ነው።

እውነት ነው የርዕሱ ስፋት እንዲህ በጥቂት ብለውት ወይም ተፅፎ የሚያበቃ አደለም። ለመወያየት ታህል “ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም ” ነውና ልብ እንበል።

ቸር እንሰንብት።

Latest from Blog

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop