November 6, 2019
6 mins read

ጥቃትን እንደ ግጭት ማቅረብ የግፉአንን ጩኸት መቀማት ነው – ያሬድ ሃይለማሪያም

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተከሰተውን ጥቃት መነሻ በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከርመው የሰጡትን መግለጫ እና በ OMN ቴሌቪዥን በተከታታይ እየተሰራጩ ያሉትን ነገሮች የተበዳይን ጩኸት መንጠቅ፣ የድርጊቱን ትርክት ማንሻፈፍ እና ከወዲሁ ፍትሕን የማዳፈን እንቅስቃሴ ስለሆነ ይህን ጉዳይ በዝምታ ማለፍ አይገባም። በሕግ አምላክ ማለት ይገባል።

+ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ ላይ ደጋግመው ክስተቱን “ግጭት” እያሉ መግለጻቸው ፍጹም አግባብነት የሌለው እና መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር የሚጣረስ ለመሆኑ ከበቂ በላይ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል። በአንዳን አካባቢዎች ሰዎች እራሳቸውን ለመከላከል ሲሉ በቡድን ተንቀሳቅሰው ለጥቃት የመጣባቸውን የተደራጀ እና ሜጫ እና ዱላ ይዞ ይንቀሳቀስ ከነበረውን ቡድን ጋር ተጋጭተዋል። ከዚያ ውጭ ግን በአብዛኛዎቹ ሥፍራዎች የተከሰተው ነገር የጅዋርን ጥሪ ሰምተው የተንቀሳቀሱ ወጣቶች በሰነዘሩት ጥቃት የደረሰ ጉዳት ነው። በዚህ ጥቃት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት የተለያዩ ብሔሮች ተወላጅ የሆኑ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባዎች ሆነዋል። ክስተቱን በሁለት ተደራጅተው ፍልሚያ በገጠሙ ቡድኖች መካከል የተደረገ ግጭት አድርጎ መግለጽ ግን እውነታውን ማዛባት ብቻ ሳይሆን የፍትህ ሂደቱንም ከወዲሁ እንዲዛባ ትርክቱን የማስተካከል ተግባር ነው።

+ በቡራዩ እልቂት የተጎዱት ሰዎችን ጩኸት ለማፈን እነ ጃዋር ልክ ዛሬ እንዳደረጉት ሁሉ የጥቃት ሰለባዎች የነበሩትን የሕብረተሰብ ክፍሎች ለክ እንደ ተፋላሚ ኃይል በመቁጠር ድርጊቱን ከማውገዝ ይልቅ በእኛ በኩል ይህን ያህል ሰው ሞቷል በማለት መንግስት ከሚያውቀው መረጃ እና የሟቾች ቁጥር ውጭ የተዛባ መግለጫም በመስጠት ፖሊስን እና የመንግስት አካላትን በአደባባይ ሲያስፈራሩ ነበር። ጉዳዩም እንደተዳፈነ ቀረ። መንግስትም ፍትሕን ከማስከበር ይልቅ በሚዲያዎቹ ጉዳዩን በጋሙ ሽማግሌዎች እና በኦሮሞ አባገዳዎች እንደተፈታ አድርጎ በማሳየት በጠራራ ጸሀይ የተፈጸመ ግፍ ተድበስብሶ ቀርቷል። ጉዳዩም ገለልተኛ በሆነ አካል እስከ አሁን አልተጣራም። ለምን?

+ ይህንኑ ተከትሎም ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት እና ጃዋር መሃመድ ዋና የአመጹ ቀጽቃሽ ስለሆነ በሕግ ይጠየቅ የሚል ሰፊ እንቅስቃሴ መከሰቱን ተከትሎ እሱ በሚመራው ሚዲያ እየተላለፈ ያለው ዘገባ ችግሩን እጅግ የሚያባብስ፣ የዘር ጥላቻን የሚያንጸባርቅ፣ ሌሎች ግጭቶችን የሚጋብዝ እና በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ለበለጠ ስጋት እና ጥቃት እንዲዳረጉ እሳት የሚያቀጣጥሉ ናቸው። የዛሬውን የOMN የቀን አማርኛ ዜና መመልከት ብቻ በቂ ነው። ሚዲያው በተለያዩ ከተሞች እየዞረ አንዳንድ የኦሮሞ ተወላጆችን እያናገረ ለቅስቀሳ እና ጥላቻ አዘል ለሆኑ ንግግሮች ሙሉ የአየር ሰዓቱን ሰጥቶ የዜና ዘገባውን ጨርሶታል። ሚዲያው በብሮድካስቲን ኤጀንሲ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ቢሆንም ማሳሰቢያውን ወደ ጎን በመተው ተመሳሳይ ቅስቀሳዎችን እያደረገ ነው።

+ በዚሁ ሚዲያም ከሁለት ቀን በፊት ጀነራል ጀማል ገልቹ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር እና እሳቸው በጥላቻ በፈረጇቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ግልጽ የሆነ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ እና ጥሪም ጭምር አስተላልፈዋል።

መንግስት እና ሕግ ባለበት አገር እንዲህ ያሉ ነገሮችን ችላ እያሉ ማለፍ ሌሎች እልቂቶችን ይጋብዛል። መንግስት አሁንም ሕግ እንዲያስከብር ሁላችንም ማሳሰብ ይኖርብናል። በተፈጸመው አሰቃቂ የጥቃት እርምጃ በቀጥተኛም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ እጃቸው ያለበት የጀዋር አይነት ሰዎች በሕግ ሊጠየቁ ይገባል።

ፍትሕ ለተገደሉ እና ጥቃት ለደረሰባቸው ሰዎች!

ያሬድ ሃይለማሪያም

6 Comments

  1. ይህ ሀሳብ እወነተኛ እና ትክክለኛ ሀቅ ነው! አሁንም ለማደናገር አና ለማደፋፈን እየተሰራ ያለው ሴራ ነገሩን ያክረዋል እንጂ መፍትሄ ሊሆን አይችልም! ሌባን ሌቤ አካፋን አካፋ ያላለ አካሄድ መጨረሻው ፍርድን በራስ መፈፀም መሄዱ አይቀርም! በተለይ እየሞተ እየተገደለ ያለ ነገር ግን ያደፈጠ አካል እንዳለ ባይረሳ ጥሩ ነው! ጫፍ መድረሱን በቅርበት እያየን ነው! ከፈነዳ በኋላ ዋይ ዋይ ሀገር ያጠፋል እንጂ አያሻግርም! የፍትህ ያለህ! የእውነተኛ ፍትህ ያለህ እያልን ነው!!! ድንገት ሚገነዘብ መንግስት በኢትዮጵያ ካለ! በጀርባ ትቶ ለህዝብ ቢሰራ ጥሩ ነው!አሸባሪ እየሸፈኑ እና በህዝብ ገንዘብ እያስጠበቁ ሰላም ሚመጣ ሚመስላቸው ካሉ እነሱም አሸባሪ መሆናቸውን መረዳት ሚያቅተው ህዝብ የለም! ሬሳ በዘር እና በእምነት መቆጠር ለምን እንደተፈለገም ከገባን ቆየን! ድብብቆሽ ካላበቃ እንደ እንስሳ ዝምብሎ ሚታረድ እና ሚገደል ሰው የለም! አሳፋሪ ስራን በቀነጨረ አስተሳሰብ መሸፈን ደሞ መጨረሻው ምን እንደሚሆን ግልፅ ነው! ጀሮ ያለው ይስማ! ህሌና ያለው ይዳኝ! መንግስት ነኝ ባይ ፍትህ ያስፍን ብለናል!

  2. Such misfortune is a lucrative business for those like you who claim themselves as “human right defenders” but do their business at the cost of the valuable human lifes.

    But for sure cheap propoganda will bring nothing. No power on earth will stop the peoples of Ethiopia from fulfilling their aspirations as a freedom loving multination to regain their human dignity and rights. It is up to you to respect the rights of all different peoples in Ethiopia for the sake of your own benefits. Let me make it clear: Your malicious politics will never work in the new Ethiopia. 

    The  persistent stubbornness and greediness of the ultra nationalists like you and your friends will help even more as a fuel in strengthening and speeding up the de-Amaharaization of the whole Ethiopian politics in order to substitute it with the politics of a true multinationalism.

    • Dear Gamewa
      What do you mean by “It is up to you to respect the rights of all different peoples in Ethiopia for the sake of your own benefits.”
      Do you mean the need for mutual respect and recognition or only to be respected by others? This is a major problem of ethnic extremists. They violate people’s dignity while demanding to be under their knees. Demanding for the rule of law without respecting the rules and regulations of the country. This is nonsense.

  3. 100% ትክክል ነህ አቻሜ። አየህው በመከራ ጊዜ 100% በሃሳብህ ስስማማ? እንዲህ ነበር አስተዳደጋችን። በአገር ጥቃት ጊዜ አንድ መሆንን ። ይህ ነገር ጭራሽ ከአስተዳደር ውጭ አርገዋቸው ካልሆነ እንደምን እነ ከማል እንዲህ ለማለት ደፈሩ ያሰኛል። እንዴት ነው ነገሩ? የጠ/ሚሩ ብቻ ሳይሆን የገረመኝ እንዴት አብረዋቸው ከተሰለፉት ጎራ ደፍሮ ይህን የተቃወመ አንድ ታዬ ደንደአ ብቻ ይሆናል? ኦዲፓን ማለቴ ነው። ዝምታው ነው እጅግ ያሳሰበኝ ከወረደው መአት በተለየ። የተገደሉትስ አልፈዋል። አገር አይናችን እያየ ስትፈርስ ኢትዮጵያዊ ሆኖ በዝምታ ለተባበርነው ነው ማልቀስ። ሰውዬው “እርዱኝ ወገኖቼ” እያሉን ነውና ። አንድ አመት ሰውዬውን ለተከታተለ የሆነ ነገር ካልሆኑ እንዴት ባንዲት ጀምበር የኢትዮጵያዊነት ጸጋቸው ይገፈፋል ከባድ የውስጥ ችግር ካልደረሰባቸው? እባካችሁ ወገኖቼ ፩)፪)፫) እያልን መፍትሄ እናቅርብ። መውጫ መንገዱን እንጠቁማቸው። ሌላው ቢቀር አቢይን በአደባባይ በነቂስ ወጥቶ የደገፈ እንኩዋ እንዴት ዝም ይባላል? በአንድ አመት ምንም መልካም ስራ አልሰሩም እኝህ ሰውዬ? አሁን ማን ይሙት አቢይ የአስከሬን ጎሳ ቆጠረ በገዛ ፍቃዱ ተጽፌ ካልተሰጠው ልትሉኝ ነው? ማን ይሙት “የወያዖ” ጽልመት አንደኛውኑ መንበሩን ባይቆጣጠሩትም ከላኛው ግቢ በታች ኢዮቤልዩ አፋፍ በደንብ ተንሰራፍተው ሁሉን እየተቆጣጠሩ አይመስላችሁም? ችግርማ አለ። ያውም የከፋ ችግር። መውጫውን ፈጣሪ ያሳያቸው እንጂ በወገንስ ተስፋ እየቆረጥኩ ነው።

  4. What happened had completely different two phases.

    Phase one was conflict not attack between security apparatus and those that went to confront the security apparatus at their pals residence. Security apparatus used lethal weapon killing a handful to disperse the crowd that was the first sign of conflict.

    Phase two is the attack when innocent unsuspecting individuals got slaughtered by literally cannibals vampires and their followers who wanted to be just like them.

Comments are closed.

Previous Story

በኢትዮጵያ ተስፋ አልቆርጥም (መሳይ መኮንን)

Next Story

” ከታሪክ ጠባሣ ለመማር ፍቃደኛ ያልሆነ ህዝብ እና መንግሥት ታሪክን ለመድገም ይገደዳል።” (ሰው ዘ -ናዝሬት)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop