የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፥ ሰሜን አሜሪካ ማኅበራት ጥምረት መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፥ ሰሜን አሜሪካ ማኅበራት ጥምረት
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, North America faithfull Union

መስከረም ፪ ቀን ፳ ፻ ዓ፲.ም፪.

“ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ዝም አንልም”

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አንድ አምላክ በሚሆን አሜን፤

የኢትያጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትናን ምዕመናን አንድነት ሕዝባዊ ትዕይንት ዓላማ

 በሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ካህናት
 በሰሜን አሜሪካ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኅብረት
 በሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ቅዱሳን ማዕከል
 በሰሜን አሜሪካ አለማቀፍ ዋልድባን እንታደግ ማኅበር
 በሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ባለወልድ

በመጪው ሐሙስ መስከረም ፰ ቀን ፳ ፻ ፲ዓ.፪ም. (September 19, 2019) የሚደረገውን ሕዝባዊ ትእይትንት/ ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

እኛ በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የምንገኝ ማኅበረ ካህናት እና ማኅበረ ምዕመናን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ክርስቲያኖች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት አጠናቀናል፡፡ በተለያዩ መንገዶች በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ክርስቲያኖች ሀገር ቤት በሚሆነው ነገር ስለሚመለከተን የድርሻችንን እድንወጣ መጠየቅ ከጀመረ የቆየ ቢሆንም ይህንን የማስተባበር ኅላፊነት በመውሰድ ከላይ በስም የዘረዘርናቸው ማኅበራት ይህንን ሕዝባዊ ሰልፍ መጠራቱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በመጪው ሐሙስ ማለትም ሐሙስ መስከረም ፰ ቀን ፳ ፻ ዓ፲. ም፪. (September 19, 2019) ከ8፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊትለፊት እንድንገናኝ ሰልፉ ተጠርቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፥ የሰሜን አሜሪካ ማኅበራት ጥምረት [1]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ክርስትናን ተቀብላ የክርስቲያን ሀገር የተባለችው በኢየሩሳሌም ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከወረደበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ጃንደረባው ባኮስ ተጠምቆ ነገሥታቱን አሳምኖ ክርስትና ተቀብለው በኦሪት እምነት የቆየውን ሕዝባችንን ወደ ሐዲስ ኪዳን አሻግረው ክርስትናን እንዲቀበል አድርገውታል፡፡ በዚህም መሠረት በዓለም ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ ክርስትና የተሰበከባት ሀገር ያደርጋታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ ሀገር የኢትዮጲያ ቤተ ክርስቲያንን ስናስብ በሁለንተናዊ መልኩ የዛሬዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት ዋናውን ድርሻና ሚና የተጫወተችውም ይህቸው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ ማስነሳት እርምጃ የመኖሪያ ቤት አልባነትን አባብሷል

ኢትዮጰያውያን በታሪካቸው፤ በቅርሳቸው በጥበባቸው፤ በጀግንነታቸው ቢታሰቡ ይህንን ሁሉ ያለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ማሰብ አይቻልም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሀገር ባለቤት ብቻ ሳትሆን በሀገር ውስጥ ያለች ሀገር ናት፡፡ ( State inside the state)

ይሁን እንጂ ካለፉት አርባ ዓመታት ወዲህ ሃይማኖት የለሽ ትውልድ ተፈጥሮ ፖለቲካ መሥርቶ ቤተ ክርስቲያንን የሥልጣኔ ተቃዋሚ አስመስሎ በመሳል ቤተ ክርስቲያንን ለምጥፋት የተሔደው ርቀት ቀላል አይደለም፡፡ በመቀጠልም በተለይ ላለፉት 28 ዓመታት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የተደረገው ግፍ ከባድና አሳዛኝ ነው፡፡ ነገር ግን በአባቶቻችን አርቆ አስተዋይነት ከዛሬ ነገ ይለወጣል በማለት በዝምታና በኅዘን ቢታለፍም በምን ታመጣላችሁ ይመስል ባሳለፍነው ዓመት ብቻ በጅጅጋ፤ በአጣዬ፤ በከሚሴ፣ በኢሎባቦር፤ በጅማ፤ በሲዳማ፣ በወለጋ ከ 33 በላይ አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ በርካታ ካህናትና ምዕመናን ታርደዋል፤ ተቃጥለዋል፡ ከቀያቸው በግፍ ተፈናቅለዋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በላይ ጉዳዩን በቸልተኝነት መመልከት አስፈላጊ ባለመሆኑ ሁለንተናዊ ሕዝባዊ ትዕይነት ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡

በመሆኑም የዚህ ሰላማዊ ትዕይንቱ አላማ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፥ የሰሜን አሜሪካ ማኅበራት ጥምረት [2]

1. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና አማኞች ምዕመናን ላይ የሚደረገውን ማንኛውንም ጥቃት ማለትም ቃጠሎ፤ ግድያ ማፈናቀል ለመቃወም፤ እንዲሁም መንግሥት ባለው ሀላፊነት የሕዝቡን ደህንነት እና በማምለኪያ ቦታዎቹ በሙሉ እንዲጠበቁ እና የተቃጣውንም ጥቃት እንዲያስቆምልን ለመጠየቅ፤

2. መንግሥት በቤተ ክርስቲያኒቱ ይዞታ በሆኑትና የአምልኮ መፈጸሚያ ስፍራዎች ማለትም የመስቀል አደባባዮችና የጥምቀተ ባህር፣ ብሎም ገዳማት እና አድባራት ይዞታዎችን በልማት እና በተለያዩ ሰበቦች ንብረቷን እየወሰደ በመሆኑ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይከበርላት ዘንድ ለመጠየቅ

ተጨማሪ ያንብቡ:  አብን፤ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት የተላለፈውን ውሳኔ እንደሚቃወም አስታወቀ

3. መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ያስደረሱትን አካላት ለሕግ እንዲያቀርብልን ለመጠየቅና ኃላፊነት ወስዶ ጥበቃ ያደርግላት ዘንድ ለማሳሰብ ፤

4. ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ባወጣው መግልጫ ላይ የጠየቃቸው ጥያቄዎች በአስቸኳይ በመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች መልስ እንዲሰጥባቸው ለመጠየቅ፤

5. ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ላይ የሚደርሰው ማስፈራሪያ በሚመከታቸው የሕግ አስከባሪ አካላት ምርመራ እንዲደረግ እና ተጠያቂ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ለሕግ እንዲቀርቡ ለመጠየቅ፤

6. ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የቤተክርስቲያን ሃላፊዎችን በተሳሳተ አመክንዮ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እና አባላት ላይ እየደረሰ ያለው እሥር ፣ እንግልትና ወከባ በአስቸኳይ እንዲቆም ለመጠየቅ፤

7. ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለማዳከም በሚመስል መልኩ፣ ፈቃድ ሰጪ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በቤተክርስቲያኒቱ ስም ለሌሎች አካላት ፈቃድ ሰጥተው እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ወንጀል ከመሆኑም ባሻገር ምዕመናንን ለመለያየት የሚደረገው ጥረት በመሆኑ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ሥራቸውን እንዲመረምሩ እና የቤተክርስቲያኒቱ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፥ የሰሜን አሜሪካ ማኅበራት ጥምረት [3]

ስም ብቸኛ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተርስቲያን ብቻ መሆኗን እንዲረጋገጥ መጠየቅ፤

ከዚህ በተጨማሪ በመጪው ሐሙስ መስከረም ፰ ቀን ፳ ፻ ዓ፲/ም፪ በውጭ ሀገር በተለይም በዋሺንግተን ዲሲ፣ በሜኖሶታ፣ በሎስ አንጀለስ እና በቶሮንቶ ያሉ የቅድስት ቤተክርስቲያን ማኅበረ ካህናትና ማኅበረ ምዕመናን ሰልፉን እያስተባበሩ ይገኛሉ፡ በዚህ በዋሺንግተን ዲሲ በሚደረገው ላይ ከአካባቢው ስቴቶች በርካታ ሰዎች ስለሚመጡ በተለይ ቦታው ብዙ የመኪና ማቆሚያ ስለማይኖረው ሰዎች የሕዝብ ትራንስፖርቴሽን እንዲጠቀሙ በተለይ በሜትሮ ትሬን ለሚይዙ ሬድ ላይን UDC ላይ በመውረድ በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ መምጣት እንደሚችሉ ለመግለጽ እንወዳለን፤ የሰልፉ ተሳታፊዎችም በአለባበስ ካህናት ልብሰ ተክህኗቸውን፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ዩኒፎርማቸውን፣ ምዕመናን ነጭ በመልበስ እለቱን በተለየ ቡኔታ እንድናከብር ተሳታፊዎችን እንጠይቃለን፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  ውጥረት በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴ በርትቷል

በቀጣይነት የማኅበራቱ ጥምረት ከምዕመናን ጋር በጋራ ልንሠራ የሚገቡንን ተግባራት ተነጋግረን ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን በሚጠቅሙ መልኩ ከውይይቶች በኃላ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጣለን ፡፡

በመጨረሻ በአጭር ጥሪ በእዚህ ቦታ በመገኘት መልዕክቱን ለመላው ዓለም ለሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ለማስተላለፍ ላደረጋችሁት ተግባር በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እያቀረብን ሥራችሁን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክ በማለት በቀጥታ ወደ ጥያቄና መልሱ እንሄዳለን፤

ወስብሃት ለእግዚአብሔር፤

ወለወላዲቱ ድንግል፤

ወለመስቀሉ ክቡር፤ አሜን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፥ የሰሜን አሜሪካ ማኅበራት ጥምረት [4]

ለተጨማሪ መረጃ: (703) 307-9478 | (202) 749-3809 | (615) 918-3720 የሰልፉ አስተባባሪዎች እና ተሳታፊዎች

 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉበኤ ሰሜን አሜሪካ
 ማኅበረ ቅዱሳን ሰሜን አሜሪካ
 ማኅበረ ካህናት ሰሜን አሜሪካ
 ዓለም አቀፍ የዋልድባን እንታደግ ማኅበር
 ማኅበረ በዓለወልድ ሰሜን አሜሪካ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፥ የሰሜን አሜሪካ ማኅበራት ጥምረት [5]

3 Comments

  1. Greek Orthodox religious leaders residing both in Greek and also here in USA are very much willing to travel to Ethiopia extending their helping hands to train the lost Dergist time generations of Ethiopian Orthodox leaders and priests how to accept the pure Orthodox way .

  2. በመካሄድ ላይ ያሉት የኦርቶዶክስ የተቃውሞ ሰልፎች በሙስሊሙ ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውን አረጋግጠናል፡፡!!! – ካየናቸው መፈክሮችም መካከል፡-
    – በአክራሪ ሙስሊሞች እየደረሰብን ያለው ጥቃት ይቁም!!!
    – የግራኝ መሐመድ የጥፋት ዘመን እንዲደገም አንፈቅድም!!!
    የሚል ሲሆን ለሰልፉ ዋናው መነሻና መንስዔ ነው ተብሎ የሚታሰበው የኦሮሚያ ቤተ ክህነትና የቀሲስ በላይ ተቃውሞ በሰልፉ ላይ ያላየነው ለምንድን ነው?

Comments are closed.

Share