July 12, 2019
10 mins read

የሕወሓት እና የአዴፓ የቃላት ጦርነት ፣መዘዙ… – ህብር ራዲኦ

የኢሕአዲግ መስራች ድርጅቶች የሆኑት ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ሕወሓት) እና የአማራ ዲሞክራሲ
ፓርቲ (አዴፓ) ከከባድ መሳሪያ ፍልሚያ ያልተናነሰ ፣ ሙት እና ቁስለኛ ያል ያልተለቀመበት ፣ያልተቆጠረበት ፣ነገር ግን የተካረረ የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል።
ሁለቱ ፓርቲዎች የቆየ ልዪነቶች እንዳሏቸው ቢታወቅም ሰሞነኛው መሻኮት እና ተቃርኗቸው እንዲህ ገኖ እንዲወጣ ዋንኛ ምክንያት የሆነው ባለፈው ሰኔ 15 2011 ዓም በባህርዳር እና በአ/አ ከተሞች ውስጥ ለጠፋው የአምስት ከፍተኛ የክልል እና የፊደራል ባለስልጣናት ህይወት “የአዲፓ እንዝላልነት ነው” የሚለው የህዋት ማዕከላዊ ኮሚቴ ካካሄደው ስብሰባ በሁዋላ ይፋ ያደረገው የከረረ የ ወቀስ መግለጫውን ተከትሎ ነው።

እንደ ሕወሓት እምነት ለተፈጠረው የደህንነት ችግር ” አዲፓ በአማራ ክልል ውስጥ ስርአተ አልበኝነትእንዲፈጠር፣የትምክህት ሀይሎች እንዳሻቸው እንዲፈነጩ ፈቅዷል ፣ለተፈጠረው ችግሩም ህዝቡን ይቅርታ ካልጠየቀ፣አብረን የምንጓዝ አይመስለንም “ሲል ሕወሓት በመግለጫው አስፈራርቷል።

በትላንትናው እለት ባህርዳር ከተማ ውስጥ ለስብሰባ የተቀመጠው የአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ በበኩሉ ” በሰሞኑ ችግር አገራችን ኢትዬጵያ እና ሕዝቦቿ የሀዘን ማቅ ባጠለቁበት በዚህ ወቅት ፣ህዝብን እና አገርን የበደሉ እና የዘረፉ ባለስልጣናትን ከተጠያቂነት ለማሸሽ በጉያው የደበቀ፣በአገሪቱ የተጀመረው ለውጡን ለመቀልበስ ከጥፋት ኃይሎች ጋር የወገነው ሕወሓት ይህንን መሰሉ ሀላፊነት የጎደለው መግለጫን በዚህ ወቅት ማውጣቱ በእጅጉ አሳፋሪ ነው፣ድርጊቱም በሰው ቁስል እንጨት የመስደድ ያህል ነው “በማለት የአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ ከዚህ ቀደም በኢሕአዲግ እህትማማች ፓርቲዎች ታሪክ ያልታየ እጅግ ቅሬታ አዘል መግለጫውን ለህዝቡ ይፋ አድርጓል።

የ ሕወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ መግለጫ በበኩሉ ” አዴፓ ውስጣዊ ችግሮቹን ውጫዊ እና ረጃጅም እጆች እንዳሉበት በማስመሰል የሚያቀርበውን ማደናገሪያውን ሊያቆም ይገባዋል”በማለት ያስጠነቅቃል።

የሕወሓትን ውንጀላን በጭራሽ እንደማይቀበል የገለጸው የአዴፓ ማእከላው ኮሚቴ”ሕወሓት ከጅማሮው ጸረ አማራ አቋም አራማጅ ነውና ፣ለመለወጥ ያልተዘጋጀ ፣የዘመናት ወንጀሎቹን ለመሸፋፈን እና ለውጡ እንዲመጣ ከውስጥ ሆኖ የታገለው አዴፓን የሕዝቡ ጠላት አድርጎ በማቅርብ እና በማደናገር ላይ ይገኛል” ሲል ሕወሓትን በጽኑ ወቅሶታል።

የቃላት ጦርነቱ ዋንኛ መንስኤ በግርድፉ:-

የሁለቱ የኢሕአዲግ እህትማማች ድርጅቶች የሆኑት የአዴፓ እና የሕወሓት እንደዚህ በአደባባይ ወጥቶ በቃላት መቆረቋቆስ የዘር ተኮሩ ኢሕአዲጋዊ አስተዳደር ውጤት እንደሆነ፣ይዘቱም የመሰነጣጠቅ አደጋ የመጀመሪያው ምልክት እና አገሪቱን ወደ ተሻለ ስርአት አሸጋግራታለሁ ብሎ ቃል ከገባ አመት ከስድስት ወር ያልሞላው ኢሕአዲግ በአሸዋ ላይ የቆመ፣ እርሱን እንኳን መጠገን እንደተሳነው ያመላክታል የሚሉ የፓለቲካ ታዛቢዎች ብዙዎች ናቸው።

እንደ እነዚህ የፓለቲካ ተጠባቢያን ምልከታ የኢህአዲግ አባል ፓርቲዎች የሆኑት ኦዲፓ፣ሕወሓት እና ደኢህዴን ዛሬም በለውጥ ሂደቱ ወቅት ሙሉ በሙሉ ከለውጡ ጋር ያለመናበብ፣የሕዝቡን የዲሞክራሲያዊ እና የእኩልነት ፍላጎትን ባለማጤን ” ሕዋቶች በድሮ በሬ ካልታረሰ ወደ ሚል የገመድ ጉተታ እና የእጅ ጥምዘዛ ውስጥ እንደገቡ ያመላክታል “ሲሉ ይተቻሉ።

የቃላት ጦርነቱ ወዴት ያመራ ይሆን?:-

በአገሪቱ ውስጥ (በተለይ በኦሮሚያ፣በአማራ እና በትግራይ ክልሎች) ከመከላከያ ሰራዊቱ ያልተናነሰ ፣ተጠሪነቱ ለክልሎቹ ብቻ የሆነ የታጠቀ የሚሊሺያ ኃይል እንደተከማቸ የፌደራል እና የመከለከያ ባለስልጣናት በቅርቡ በአደበባይ ሲያስጠነቅቁ እና የአገሪቱ የደህንነት ሁኔታም ከአጣብቂኝ ውስጥ መውደቁን ሲያመላክቱ ተስተውለዋል። ከዚህ አኳያ በአሁኑ ወቅት የሚታየው የቃላት እና የስነልቦና ጦርነትም ቢሆን ለፓርቲዎቹ፣ለክልሎቹ ሆነ ለአጠቃላይ ለአገሪቱ አንጻራዊ የሰላም እና የደህንነት ዋስትናን ያመጣል ተብሎ አይጠበቅም፣ከተጠበቀም እጅግ የዋህነት ነው።

ምን ማድረግ ይጠበቃል?:-

ከመቀሌ እና ከባህር ዳር ከተሞች የወጡት የሕወሓት እና የአዴፓ መግለጫዎች ምንም እንኳን የገዢው የኢህአዲግ አባላት የሆኑ የሁለት ፓርቲዎች ሽኩቻ ቢመስልም የቃላት ጦርነቱ አውንታዊ ወይም አሉታዊ መልእክት የሚያርፈው በክልሉ ለሚገኙ ብሔሮች ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዬጵያዊ መሆኑ አያጠያይቅም።
ከዚህ አኳያ ከኢትዬጵያ አልፎ በጎረቤት አገራት:- በሱዳን እንዲሁም በሶማሊያ እና በኬኒያ መካከል ሳይቀር እርቅ ሰላም እናመጣለን የሚል ተስፋ የሰነቀው የጠ/ሚ/ር አብይ አሕመድ አስተዳደር ለጊዜው ወደ አጎራባች አገራት የሚያደርገው የዲፕሎማሳዊ እሩጫውን ተውት አድርጎ ያለ የሌለ ሀይሉን ወደ አገር ውስጥ ችግሮቹ በማተኮር፣ቤቱን በማጽዳት ያንጃበበውን ይውጥረት ዳመናን ቢገፈው ይመረጣል።
የሰሞነኛው የቃላት ጦርነት እና የጣት የመቀሳሰር ዘመቻው ዳፋው ከኢሕአዲግ እህት አባላቱ(የሕወሓት እና የአዴፓ) የሚዘል በመሆኑ የፓርቲ ፣ የድርጅት፣ የግንባር…ወዘተ ጭምብል ማጥለቁን፣በስሜት እና በእልህ ባህር መዋኘቱን ለጊዜው ገታ አድርጎ እየተንገዳገደ የሚገኘው ኢሕአዲግ ካለማቅማማት እና “የውስጥ ችግሮቼን ለእኔው ተዉልኝ፣ እራሴው እፈታዋለሁ “ከሚለው የሃያ ሰባት አመቱ ያረጀ እና ስንኩል አስተሳሰቡ ተላቆ ከ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ከሀይማኖት አባቶች፣ከአገር ሽማግሌዎች ከሲቪክ ማህበረሰቡ፣ከአክቲቪስቶች እና ከጋዜጠኞች …ወዘተ ጋር በአፋጣኝ ሊለወጡ ወይም ሊጠገኑ በሚገባቸው ብሔራዊ እና አገራዊ ጉዳዬች ዙሪያ መምከር ፣መመካከር የግድ ይለዋል።
ይህ አይነቱ አቀራረብ የአሽናፊነት እና የተሸናፊነት መድረክን መፍጠር ሳይሆን ለአንዲት ኢትዬጵያ እና ለልጆቿ መጻኢ እድል ሲባል የሚከፈል መስዋትነት ተደርጎ ሊቆጠር ይገባዋል።እርምጃ ውም ጊዜ የማይሰጥ፣ብልህነት እና አርቆ እስተዋይነትም ጭምር ነው።

4 Comments

  1. The Amara region’s security chief with full force must assist the Benishangul Gumuz region now , just so more refugee crisis and displacements do not happen in the Benishangul Gumuz region, which will be an irreversible migration for most.

  2. ௐௐ እነ”ኢያጎ”ን አፈላልጉን!!!ௐௐ
    ከዐቢይ ኢትዮጵያዊ

    አረመኔዎች እና ሰው-በላ የፋሺሽት-ወያኔዎች ዛሬም ታድነው ፍትህ ፊት እንዲቀርቡ ካልተደረጉ ነገ የሚብሰውን አያመጡም ለማለት አንችልም፤በአሁኑም ጊዜ የጅምላ እስርም ሰበቦቹ እነዚሁ ገዳዮች ናቸው።ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬም ሁሉንም የኢሃድግ አባላት ቢያንስ የመደመር ሥልጠና ይሰጣቸው ብንልም ሰሚ ጠፍቶ አልተፈፀመም።እንደውም ግድያውና ማፈናቀሉ እየተባባሰ ስንመለከት፦እኛ በማናውቀው መንገድ የቅነሳ ትምህርትና ሥልጠና የተሰጣቸው ይመስላል።
    ለማንኛውም በየትም አቅጣጫ ይሁን ስለኢትዮጵያ አገራችን ችግሮች ስናነሳ ዋና ዋና ከሚባሉት አበይት ችግሮቻችን መካከል አሉባልታ ዋነኛው ነው።አንዱ እና ሰው ሰራሽ የሆነው አሉባልታ ባልሰለጠነ ሕብረተሰብ መካከል ሲኖር የሚፈጥረው አደጋ ቀላል አይሆንም።በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚዛመቱት አሉባልታዎች ቢቻል ከጥፋታቸው በፊት ካልተቻለም በኋላም ቢሆን በግልፅ እንዲታወቁ ካልተደረገ እነዶክተር አምባቸውና ብ/ጄ አሳምነው ፅጌ የደረሰባቸውን የነብስ መጠፋፋት ወንጀል መፈፀሙን አውቀናል።ይህንንም ወንጀል የፈፀመው ሦስተኛው እጅ መሆኑን በሚገባ የተደረሰበት ቢሆንም፤ “ኢያጎ”ሆኖ ያቀጣጠለው መሰሪ ሸፍጠኛው ተላላኪ ቅጥረኛ ግን አልታወቀም።
    ௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐ
    አራቱ አርበኞችን እኒያ የገደሉት፤
    ፋሺሽቶቹ ናቸው
    በደም የወደሉት።
    ወገንን በሴራ ወዳጅ ተጠግተው፤
    የኛን ሰው ገድለዋል፣
    በግፍ ቀን አድብተው።
    በሸፍጥ ነው የወጉን፤
    እነ”ኢያጎ”ን ያየ ዛሬ አፈላልጉን።
    ክህደትና ሴራው፤
    ተውጠንጥኖ ባልባሌ፤
    በወዳጅ-ጠላት ሥም፣
    ላኩት ከመቀሌ።
    ችግር ተነጋግረን እንደምንፈታበት፤
    ተቀምጠን በሰላም ስንወያይበት።
    በድንገት”ኢያጎ”ን ሳናውቀው እንደነበር፤
    ሸፍጠኛው ማን ይሆን
    ሁሉም ሰው ይበርበር።
    እሱ ነው አጋዳይ ለፋሺሽት-ወያኔ፤
    መረጃ አመላላሽ በግድያው ያኔ።
    አሉባልታዎቹ አንድ በአንድ ወጥተው፤
    ወሬኛው ይጣራ በድምብ ተለይተው።
    እናም በእርግጠኛ ገዳዩን ሕዝብ ያውቃል፤
    ሦስተኛው እጅ ይያዝ አንድ መረጃ ይበቃል።
    እንመርምር ወሬውን እናጣራ ሁሉን፤
    ግርግር ፈጥረው ነው
    እኛን የገደሉን።
    አዎ እነ”ኢያጎ”ፍፁም ካልተያዙ፤
    የሚፈጥሩት ክፋት ፣
    ብዙ ነው መዘዙ።
    ፋሺሽቱ-ወያኔን
    ገዳይና አጋዳይ፤
    ይነገር በይፋ:-
    ሕዝቡ በደምብ እንዲያይ።
    የወንጀሎቹ ምንጭ አልፋና ኦሜጋ፤
    መጀመር አለበት
    በ”ኢያጎ” ፍለጋ።
    ነብስ አይካካስም በሚታይ ቁሳቁስ፤
    ደም ባይከፈልም
    ይቀራል ወይ ሃቁስ።
    ስለዚህ አንርሳ ለግፉ መጨረሻ፤
    አራት ባንዳ አያጠፋም
    ለደም ማካካሻ።
    ከእስር ቤት ተቀምጦ ሁሉን የሚያጋድል;
    እኛ ስንሞትለት ይቆጥራል እንደድል::
    እናም በሸፍጥ እኛን በድብቅ ያስወጉን፤
    እነ”ኢያጎ”ናቸው ለፍትህ አፈላልጉን።

    ወደ ሮሜ ሰዎች
    ፲፪፥፲፱ ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።

  3. EPRDF/TPLF must think Ethiopian people are all damn, TPLF honestly believes we donot know that TPLF and ADP are partners in crimes, as the rest of EPRDF are too.

    EPRDF IS PLAYING “GOOD COP/BAD COP” ON ETHIOPIANS.

    ABIY IS TRYING TO BE THE LEADER OF THE GOOD COPS (REFORMED EPRDF) AND DEBRETSION IS BEING THE LEADER OF THE BAD COPS ( NOT REFORMED EPRDF), AFTER ALL BOTH ARE TWO SIDES OF THE SAME COIN.

    AMARA REGION IS EXPECTED TO BE PUPPET FOR ABIY’S SIDE/”THE GOOD COPS” SIDE AND ADP IS ALSO EXOECTED NOT TO CREATE ANY PROBLEMS FOR TPLF/”THE BAD COPS” BY RAISING BOUNDARY AND 0THER IDENTITY ISSUES.

  4. መንቻካው የሃበሻ ፓለቲካ ምንም አይነት ሃይል አልሞት ለመዋጥ አይመችም። ትላንትም ዛሬም ያው መንቻካ ነው። የትላንቱን ከዛሬ የለየው አሰላለፋችን ብቻ ነው። ተምቦላ እንደወጣለት ሰው የደቡብ ወጣቶች በክልል ጥያቄ ዙሪያ ሲጨፍሩ ሳይ እውነትም ሃገሬ ሰክራለች ከማለት ያለፈ የምለው ነገር አጣሁ። ከለለ ማለት አጠረ ለእኔ ብቻ ይሁን አለ ማለት ነው። ምንም ቢያጣምሙት የክልል ትርጉም ከዚህ የዘለለ ነገር የለውም። ይህም የወያኔ ሴራ ከጣሊያን የወረራ የከፋፍለህ ግዛ የተቀዳ ሾተል ነው። ክልል ለማንም አይጠቅምም። በትንሽ በትልቁ ስንፋተግ ግን ዘንተ ዓለም እንኖራለን። ዛሬ በአፋርና በኦሮም አርሶ አደሮች የምናየው የክልል ፓለቲካ ስንክ ሳር ነው። ይቀጥላል…
    አሁን ከወደ ትግራይ ወያኔ አዴፓን ይቅርታ እንዲጠይቅ ሲጠይቅ ደግሞ ነገሩ ሁሉ የተገላቢጦች እንደሆነ አሳምሮ ያሳያል። የአማራን ህዝብ ወያኔ በረሃ ገብቶ ነፍጥ ካነሳበት ጊዜ ጀምሮ ፍዳውን ሲያስቆጥር የኖረ ድርጅት ተበዳይን ይቅርታ እንዲጠይቅ ካልሆነ ግን ከአዴፓ ጋር አብሮ መስራት እንደማይፈልግ ወያኔ ነግሮናል። በመሰረቱ የዛሬውና ያለፈው የሃገሪቱ ችግር በተገንጣይና ባስገንጣይ ሃይሎች የተፈጠረ መከራ ነው። የፓለቲካ ሰልፋችን በዘር ዙሪያ ከተሰመረ ወዲህ ደግሞ ጭራሽ ምድራችን ጨለማ ተላብሳለች። አሁን በትግራይ ቤቶችን በዶዘር እያፈረሰ ያለው ጨካኙ የወያኔ ክምችት ለትግራይ ህዝብ ገዶት አያውቅም። በስሙ ግን ነግዶበታል እየነገደበትም ነው። እስቲ ስብዕና አለኝ የሚል ድርጅት በክረምት የድሃ ቤት ያፈርሳል? ሰው የት እንዲገባ ነው? ዛሬም ትላንትም የድንኳን ህይወት። አይ የወያኔ ፓለቲካ አሻጥር ብቻ! ወያኔ በግፍ አፈር የመለሰባቸው የአማራ ልጆች ስፍር ቁጥር የላቸውም። ግን የተነገረን ታሞ ሞተ፤ መኪና ተጋጭቶ አለፈ፤ ጦር ሜዳ ሄዶ ከጠላት ጋር ሲፋለም ሞተ (ከህዋላ እነርሱ ገድለው) እረ ስንቱ! ይህ በመረጃ ያለ ነገር እንጂ ከሚያልፍ ወንዝ የተቀዳ የፈጠራ ወሬ አይደለም። ወያኔ የአማራ ህዝብ ጠላት ነበር አሁንም ነው። ችግሩ አሁንም በስልጣን ላይ ከወያኔ ፍትጊያ የተወለደው ልባጭ መንግሥት የአማራን ህዝብ መከራ አሁንም እያባሰው እንደሆነ ማየታችን ነው። በውሸት መፈንቅለ መንግሥት መሪ የአማራ ልጆችን እያሰረ ያለው የወያኔ ትራፊ መንግሥት ተመልሶ ወያኔን እየመሰለ ነው። በጄ/አሳምነው ጽጌ አቀናበሩት በተባለው የመንደር መፈንቅለ መንግሥት (የመንደር መፈንቅለ መንግሥት አለ እንዴ – የጄኔራሉ ቃል ነው)በማደናበር ሰዎችን ዘብጥያ የሚያወርደው የዶ/ር አብይ መንግሥት ረጋ ብሎ ነገርን ቢያስብ የተሻለ ይመስለኛል። የፈጠራ ፓለቲካ ለአሜሪካኖችም አለበጀ እንኳን ለሃበሻው ምድር። መቀሌ ላይ ይህ ነው የማይባል ወንጀል በህዝባችን ላይ ለ 27 ዓመት ያደረሱ እየተንደላቀቁ የአማራን መሪዎች በየሰበቡ ማሰሩ ተገቢ አይደለም። ለሃገራዊ አንድነት በዘረኞች የተጻፈው ህገ መንግሥት መሻሻል አለበት። አለዚያ ማቆሚያ ወደሌለው የእርስ በርስ ግጭት በመግባት ሶማሊያንና ሶሪያውያንን መቀላቀላችን አይቀሬ ነው። ሲታሰብ ክራራይሶ ያሰኛል!

Comments are closed.

Previous Story

በባህር ዳርና አዲስ አበባ በተከሰቱ ቀውሶችና በሌሎችም አካባቢዎች በሚታዩ ውጥረቶች ተሸንፈን አገራችንን አንድነት በሚፈታትን ቀውስ ውስጥ እንዳንገባ ሰከን ባለ መንፈስ  እናት ኢትዬጵያን በጋራ እንታደግ!!

Next Story

በኢትዮጵያ አሁን ለሚታየው ውጥንቅጥ መፍትሄው ፖለቲካዊ ብቻ አይደለም (ድጋፌ ደባልቄ)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop