June 3, 2019
13 mins read

  <<ሁሌም ቢሆን ከእውነትና ከመርህ ጋር እናቆማለን። -  ከኢሳት ዲሲ ስቱዲዮ ጋዜጠኞች የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሊቭዥን እና ሬዲዮ /ኢሳት/ላለፉት 9 ዓመታት የሕዝብ ድምጽ፥ አይንና ጆሮ በመሆን ለነጻነት የሚደረገውን ትግል ሲደግፍና ለታፈነው ዜጋ ሁሉ መረጃ በመስጠት ወደር የለሽ አስተዋጽኦ ማድረጉ ይታወቃል።የዚህ እልህ አስጨራሽ ትግል ዋነኛ አላማም በየትኛውም ተቋም ወስጥ ግለሰቦችን ለስልጣን ማብቃት ሳይሆን በኢትዮጵያ ፍትህ፥ዲሞክራሲና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ሲባል እንደነበርም አይዘነጋም ።

በዚህ የብዙዎችን መስዋዕትነት በጠየቀው የትግል ሂደት ውስጥ ሕዝቡ የከፈለው ዋጋ ከምንም ነገር ጋር የሚመጣጠን እንዳልሆነ ቢታወቅም የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴና እና በውስጡ የምንገኝ ጋዜጠኞች ያደረግነው አስተዋጽኦና አበርክቶ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የሚረሳ ጉዳይ እንዳልሆነም እንገነዘባለን።

የሕዝባችንም ሆነ የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴዎችን እገዛ በመንተራስ እና በተቋሙ ውስጥ ስንሰራ የነበርን ጋዜጠኞች የራሳችን እና የቤተሰባችን ሕይወት በመጉዳት የሀገርንና የሕዝብ ጥቅም በማስቀደም ትልቅ ዋጋ ከፍለናል ብለን እናስባለን።

በዚህ አስቸጋሪና ዋጋ የከፈልንበት ዓላማ ውስጥ ስንገባም በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተሰቦቻችንን ሕይወት አደጋ ላይ በመጣል ጭምር እንደነበርም ለማስታወስ እንወዳለን። ይህን ሁሉ ዋጋ ስንከፈልና እስከዛሬ ድረስ በዓላማችን ጸንተን ስንቆም ግን የእናንተ የኢሳት ቤተሰቦችና ድጋፍ ሰጭዎች እገዛ ባይጨመርበት ኖሮ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ የማንችል መሆናችንን እንደምንገነዘብም በዚህ አጋጣሚ ለማሳወቅ እንፈልጋለን ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ያደረገውን መራራ ትግል ተከትሎ በአሁኑ ጊዜ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ከመጣ በኋላ ሂደቱን በመደገፍና ችግሮች ሲኖሩም በመተቸት የሚጠበቅብንን ሙያዊ እገዛ መስጠታችንን እንደቀጠልን  ሁላችሁም የምታውቁት ጉዳይ ነው። ሁሌም ስንመኘው እንደነበረው ብዙ መስዋዕትነት ከተከፈለ በኋላ በተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ በሀገራችን ኢትዮጵያ ፍትህ፥ ዲሞክራሲና ሰላም ሰፍኖ የምናይበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆንም ትልቅ ተስፋን ሰንቀን መቆየታቸንም የሚታወስ ጉዳይ ነው።

በዚህ ተስፋ ውስጥ እያለን ግን በለውጥ ሂደት ውስጥ የሕዝብ መፈናቀል፥ የግጭቶች መበራከትና ይሕንኑ ተከትሎም በርካታ ወገኖቻችን መገደላቸው በመቀጠሉና ኢፍትሐዊነት እያየለ በመምጣቱ ባለብን ሙያዊ ግዴታ መሰረት ሁኔታው እንዲስተካከል ስንጠይቅ መቆየታችንም ይታወሳል።በተለይ ደግሞ በለገጣፎና በጌዲዩ እንዲሁም በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የደረሰውን የህዝብ ሰቆቃ በኢሳት የማጋለጥ ስራ ሲጀመር የአፈና ስራ ለማከሄድ በመሞከሩ የተወሰንን ለመርህ የቆምን ሰዎች ሙያዊ ግዴታችንን ለመወጣት ስንሞክር ቀሪዎቹ ከለውጥ ሀይሉ ጋር ቆመናል የሚሉ ባለደረቦቻችን ሳይቀሩ የዘገባ ስራችንን ለማፈን ሞክረዋል።

በተለይ ደግሞ እኛ በዋሽንግተን ዲሲ የምንገኝ የኢሳት ጋዜጠኞች እነዚህ ችግሮች እንዲስተካከሉ አበክረን በመጠየቃችን ሁኔታው ያልተዋጠላቸው በቦርድ ስም የተቀመጡ የኢሳት አመራሮች   በተለይም በውጭ ሀገር ያሉትን የኢሳት ስቱዲዮዎች በእጅ አዙር የመዝጋት እርምጃ ወስጥ መግባታቸውን ለመረዳት ችለናል።ለዚህ ዓላማቸው ማስፈጸሚያም በኢሳት ባልደረቦች መካከል ክፍፍልን በመፍጠርና በተቋሙ ወስጥ የገንዘብ አቅም ተዳክሟል በሚል ሰበብ ድርጅቱን ለመዝጋት ሲንቀሳቀሱ የሕዝብን ፍላጎት እና የተቋሙን ሕልውና በማስቀደም ትግስት የተሞላበት የወስጥ ትግል በማድረግ ስንቀሳቀስ ቆይተናል።

ይህን የውስጥ ትግላችንን ወደ ሕዝብ አለመውሰዳችን እንደ ድክመት በመቁጠር ጋዜጠኞችንና መላውን ሰራተኛ ሳያማክሩ በቦርድ አባልነት ስራውን ሲመሩ የነበሩ ግለሰቦች  የኢሳትን የውጭ ስቱዲዮዎች ለመዝጋት ወስነው ሲያበቁ  ሁኔታው በእቅድ እንዲመራ የሕዝብ ጥያቄ እያየለ ቢመጣም በቸልተኝነት ወደ አዲስ አበባ በመንቀሳቀስ ድርጅቱን በሚጎዳ ተግባር ውስጥ ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም ለመረዳት ችለናል።

ያለምንም ጥናትና ዝግጁነት ሰራተኛውን ሳያሳውቁ በአዲስ አበባ ወስጥ ስራ እንዲጀመር አድርገዋል። በዚሁም በውጭ የሚገኙ ስቱዲዮዎችን ለመዝጋት ሲሉ ጋዜጠኞችን ሲከፋፍሉ ከቆዩ በኋላ በብዙዎች ዘንድ ታቃውሞ ሲገጥማቸው ሰራተኛውን ደሞዎዝ መክፈል አንችልም በማለት የማባረር እርምጃ እንደሚወስዱ ለሰራተኞች ሲያሳወቁ ሊሎች አማራጮችን እንዲያዩ እና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት እንዲመክሩበት እንዲሁም ኢሳት የሕዝብ ሆኖ እንዲቀጥል ቢጠይቁም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ይባስ ብሎም ከዚህ በፊት ባልታየ ሁኔታ የጋዜጠኞችን የሙያ ነጻነት በመጻረር ፕሮግራሞች እንዳይተላለፉ ከማገድ ጀምሮ ለውጥ አደናቃፊ በሚል ሰበብ የተለያዩ እርምጃዎችንም ሲወስዱ ቆይተዋል።

በሕዝብ ስም የተቋቋመን ሚዲያ በባለቤትነት እኛ ነን የመሰረትነው የሚል መግለጫ በመስጠት ከፖለቲካ ድርጅትነት ከስመናል ያሉ አካላትም በተዘዋዋሪ መንገድ የራሳቸውን ሰዎች በመመደብ አሁንም ኢሳትን ለመቆጣጠር በመሞከራቸው ይህም ተገቢ እንዳልሆነ በዋሽንግተን ዲሲ ጋዜጠኞች በኩል ሜይ 10/2019 ዓም ይህንኑ የሚቃወም መግለጫ ማውጣታችንም ይታወሳል።

በዚህ መግለጫ ያልተደሰቱት የኢሳት ቦርድ አመራር ነን የሚሉት እነዚሁ አካላት በገቡት ቃል መሰረት ኢሳትን ለሕዝብ እንዲያስርክቡና በድርጅቱ ስም ከተለያዩ ወገኖች የተሰባሰበው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንዳደረሱት በመጠየቃችን እንዲሁም  በፋይናንስ እጥረት ስም ሰራተኞችን እንቀንሳለን ማለታቸውም ትክክል እንዳልሆነ እና ሃላፊነታቸውን ለሕዝብ እንዲያስረክቡ ባለፈው ሀሙስ ማለትም እኢአ ሜይ 28/2019 በጻፍንላቸው ደብደቤ ብንጠይቃቸውም ለዚህ ጥያቄያችንም ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በሚከተሉት የዋሽንግተን የዲሲ ኢሳት ጋዜጠኞች ላይ በስራ ላይ እያሉ ድንገት ከስራ የማሰናበትና ለፖለቲካዊ ሴራቸው ማስፈጸሚያ እንዲረዳ የመጀመሪያ ከፋፋይ  እርምጃ ስማቸው በውል ባለተገለጹ የቦርድ አካላት ተወስዶባቸዋል።እነዚሁም፦

1.ምናላቸው ስማቸው

2.ሀብታሙ አያሌው

3.እየሩሳሌም ተክለጻዲቅ

4.ጌታቸው አብዲና

  1. ልዩ ጸጋየ እና ሌሎችንም ጨምሮ ነው።

ይሕ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ለማፈን የሚደረገው እርምጃ ኢሳትን በመዘጋት የሚደመደም እንደሚሆን   ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው ስምምነቶች ውሳኔ ማሰለፋቸውንም ለመረዳት ችለናል። ስለሆነም በተለያዩ ሰበቦች ኢሳትን የማፍረሱ እርምጃ ተጠናክሮ በመቀጠሉና ከበስተጀርባ የሚካሄዱ ሴራዎች መኖራቸውን ስለደረስንበት ይሕንኑም ለሕዝብ ማሳወቅ አስፈላጊ ሆኖ በማግኘታችን ከዚህ ቀደም በጻፍነው ደብዳቤና ባሳለፍነው ውሳኔ መሰረት እኛ ከዚህ በታች ስማችን የተገለጸውና ፊርማችንን በዚህ መግለጫ ላይ ያሰቀመጥን ጋዜጠኞች ምንም እንኳን ከኢሳት ተገፍተን ብንወጣም ተቋሙን ለመዝጋት የተያዘውን የፖለቲካ አቋም በመቃወም ስራችንን  በሌላ መንገድ አጠናክረን የምንቀጥል መሆናችንን  እንገልጻለን።በዚህ አጋጣሚም ለሕዝብ ያለንን ወገተኝነት እያረጋገጥን ቀጣዩን ሂደታችንን በተመለከተ ከሕዝብ ጋር ተመካክረን ውሳኔያችንን በተወካዮቻችን አማካኝነት የምናሳወቅ መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን።

ማስታወሻ ፦ ለኢሳት ቦርድ ከዚህ ቀደም ያቀረብነው ደብዳቤና የስም ዝርዝራችን ከዚህ መግለጫ ጋር ታያይዟል።

‘’ሁሌም ቢሆን ከእወነትና መርህ ጋር እንቆማለን’’

በዋሽንግተን ዲሲ የኢሳት ጋዜጠኞች

1.ርዕዮት ዓለሙ

2.ምናላቸው ስማቸው

3.ኤርሚያስ ለገሰ

4.ተወልደ በየነ

5.ሐብታሙ አያሌው

6.እየሩሳሌም ተክለጻዲቅ

7.ልዩ ጸጋዬ

8.ግርማ ደገፋ

9.ብሩክ ይባስ

እና ሌሎችም……………

 

 

 

7 Comments

  1. እንደተረዳሁት ጥያቄው ሁለት ነው
    1ኛ. አሜሪካን ያለው ተዘግቶ አገር ውስጥ ግቡ ተብለናል የሚል ነው፡ ፡ ይህን የሚወስነው ስልጣን የተሰተው ነው፡፡ ጥቅሙና ጉዳቱ መመዘን አለበት፡፡ ዝም ብሎ ከአሜሪካ ንቅንቅ አንልም ከሆነ አኮ ለምን እንላችኋለን፡፡
    2ኛ. የመዘገብ ነጻነታችን ተገፈናል የሚለው ነው፡፡ ይህማ ተገቢ አይደለም፡፡ እንኳን ባማኪካን እዚህም ነጻነት በሽበሽ ነው፡፡ ምርጫ ልስጣችሁ ለምን አዲስ አበባ መጥታችሁ የመሰላችሁን እንደለብ አትቦተልኩም፡፡ ዛሬ እዚህ ነጻነት በሽ ነው–ኑ ብለናል፡፡
    በናንተ ንትርክ ወያኔ እየፈነጠዘች ነው፡፡ አንዳንዴ ሳስበው በብዙ ነግር ተሳክቶላቸዋል-ወያኔዎች፡፡ ግርግሩን ከገጠር ወደ ከተማ ለማምጣት ባደረጉት ጥሪ በሃኪሞች ተጀምሮ መምህሩ ተቀላቅሏል፤ ይህው ጋዜጠኛው ተከትሏል፡፡ በርቱ ዞሮ ዞሮ ባለድሉ ህዝቡ ሳይሆን ወያኔ ነው፡፡

  2. To talk from distance and to be there on the ground in person got huge difference. When you are on the ground in person you start thinking about the role you played in the lives of your loved ones . Whether we journalists in exile know it or not, the ones that one way or the other get affected by our work are our loved ones who reside in Ethiopia.

  3. እጅጉን ያሳዝናል። ለመሆኑ በቀጥታ በስራችሁ ጣልቃ የገቡና በዉጭም ኢትዮጵያ ያሉ እነማን ናቸው ? ስማቸዉን አሳዉቁን መጥፎ ምግባራቸዉን በማር ሸፍነዉ ለቀጣይ ምርጫ እየተዘጋጁ ስለሚሆን በእንጭጩ እንድናስቀራቸዉ።

  4. There is no compromise for ESAT contribution and each devoted journalist to reach Ethiopian present history. Before reaching this climax point a lot of things should be done a head of time. Personal and idea of small group maybe worthless to continue. Before they faced serious financial problem, they should try to get other source of finance and have to be involved in business generating activities also. So far they didn’t make free their media for business promotion and Ads.

    Closing ESAT in out of Ethiopia maybe not good as nobody can be sure on the free activities of ESAT Addis only. Selling of share for public is good as it is one of source of income to continue. Those journalists who are innocent and devoted to their job should seriously discuss with board members and how such decisions goes. But those who have hidden agenda should take care as the media considered by Ethiopian people is one voice to them.

    The board members & management of ESAT should work their job in wise way; for instance why public meeting to sell ESAT for shares is conducted by Journalist Eskinder Nega and denied by police force? This job should be done by board members on free and systematic ways. Firing such well known journalist, like Ermias Legese, Rhiot Alemu,…etc not good and ESAT team should fight for this.

    Anyway ESAT team have to be smart enough on all your activities and ESAT should continue as voice of Ethiopia.

    Long live to Ethiopia!!

  5. I think if you better come to the Holy country Ethiopia you can do better. Now Ethiopia is slowly step by step coming to its Holy position that the God promised. Past 150 years the country lost that position because of devilish acts. Now every professional should be ethical including journalists. No more political criminal and no more conspiracy theory. No more, never again. Ethics is highly essential not to return to yesterday.
    I can mention only very few ethical journalists in ESAT more of you are truly spoiled. I do not know why it is so. Telling truth is very far from most of you. I appreciate young man of Amsterdam who showed radical change and discussing truth starting from past few days. What I can say to him is keep it up. On the other hand, most of you did not give any credit for example to Juar Mohammed, over 5000 sacrificed Qeros (made free of prison some of you), Fano, Ejato and sometimes including team Lema and others that were engineers to actualize this change.
    If all cooperate and work hard, devil cannot have power to dissolve Federal states of Ethiopia as well as the entire Holy land of Ethiopia in which Oromia is the center. I hope true Federation will flourish. For the presses I believe chaos acts that some journalists create should take better shape in the direction assumed by the board members.

    Bire A.F.

  6. የታማኝ ስለ ESAT መግለጫ ምን ደረሰ??????????????? ህዝብ እውነትን ይሻል፡፡ ESAT እኮ አሁን ስልጣን ላይ ለወጡት የኦዲፒ አመራራች፣ በቄሮ፣ ፋኖ ስም ሲታገሉ ለነበሩ እንዲሁም ተቀዋሚ ተብለው አገር ውስጥ በመግባት ችግር ሲፈጥሩ ለቆዩት ኦነግና አባላቶች (በሰለም ትጥቅ ፈተን እንታገላለን ቢሉምና ለብዙ የአገሪቷ ቀውሶች ተጠያቂ የሆኑት) በሙሉ ለበርካታ አመታት እውነተኛ መረጃ ለህዝብ በማቅረብና ሰቆቆውን በቆራጥ ጋዜጠኞቹ በማጋለጥና የህዝብ ዓይንና ጆሮ በመሆን ይህ ለውጥ እንዲመጣ ባደረገው እውነተኛ ትግል በህዝቡ ውስጥ ያለ ሚዲያ ነው እኮ፡፡ ይህ ይዘነጋል?

    ጥቅማቸው የተነካና በውስጥ የሚኖሩ አድር ባዮች ሁሌም ሚዲያ ተቋሙን ለማዳካም የማያደርጉት ጥረት ስለሚኖር ሁሉም ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡ መጪው ምርጫ ፍትሓዊና ዲሞክራሲያዊ እንዳይሆን የሚፈልጉ ሃይሎች ችግሮችን በመንቀስ ESAT ያጋልጥብናል በሚል ፍርሓት ከወዲሁ እያዳከሙት መሆኑንም እንዳይዘነጋ፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ESAT ያሉ ጣቢያዎች በርከት እንዲሉላት ትፈልጋልች ከአድር ባዮች ይልቅ፡፡

    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

  7. ESAT and other journalists medias know they did not report about the Ethiopian refugees who are in Ethiopia “internally displaced ” as their profession obligates them to report. For these reasons ESAT fund raisings will not be as favorable as usual because ESAT didn’t report thoroughly about Ethiopian refugees in Ethiopia “internally displaced”.
    Live coverages of the Ethiopian refugees in Ethiopia daily situations , interviews and investigative reporting to know what exactly happened has not been done as the ESAT was expected to do. Ethiopia is a failed state with ESAT falling along with the state

    Rather than Ethiopians prioritizing to volunteer caring for trees the volunteers should first take care of the countless Ethiopian displaced internal refugees in Ethiopia.

    The security apparatus first need to secure conserve humans than plant trees and conserve trees. In a country where humans are not safe how can anyone keep the trees safe.

    We talk about Ethiopian refugees suffering in Yemen and Lybia when we treat Ethiopian refugees within Ethiopia in worst dehumanizing conditions of starvation , disease and dehumanization conditions .

    The internaly Ethiopian refugees Situations in Ethiopia are worst than even Ethiopian refugees in Yemen , South Africa and Lybia.
    The human trafficker of the Arab world treat Ethiopians better than the way the tree worshiping Ethiopian government treat the Ethiopian refugees within Ethiopia.

    Ethiopia is only 0.7% water . Trees or no trees Ethiopia is poor with only 0.7% water . Very limited timber can be used for manufacturing , the rest for sure will be used for in home energy unless wind and solar energy replaces the current energy sources.
    The poor country of Ethiopia got the ever growing scarcity of electric energy due to lack of water, these trees are bound to get chopped down by the very people who planted them unless alternate energy sources such as solar wind energy development is given the much needed subsidy by the so called Federal government of Ethiopia. Before prioritizing trees or solar and wind energy the lives of the Ethiopian refugees within Ethiopia need immediate help and investigative reporting about the Ethiopian refugees in Ethiopia would force all responsible to behave humanely.

Comments are closed.

Previous Story

አዋሳ – የደቡብ ፖለቲካ መፍቻ ቁልፍ (በቦጋለ ታከለ ከአዋሳ)

Next Story

ወይ የኢሣት ነገር! ጊዜ ደጉ ስንቱን ያሳያል? – ግርማ በላይ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop