May 11, 2019
20 mins read

የ 2012 ዓ/ም ምርጫ ፣ የሚባል ነገር ካለ፣ ከወዲሁ ፣የበለፀጉትን ሀገሮች በቅንነት ፣ምርጫው እንከን አልባ እንዲሆን አግዙን ማለት ይበጃል

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
መልካም ነገርን እንመኝና በ 2012 ዓ/ም  የሚቀጥለውን አምስት ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ ማን እንደሚያሥተዳድረው በነፃ፣በሰላማዊ፣ገለልተኛ እንዲሁም ተዓማኒ በሆነ በዴሞክራሲዊ  ምርጫ  ውሳኔውን በምርጫ ሣጥን ውሥጥ ያሥቀምጣል።
  ምርጫ 2012 ፍፁም ሰላማዊና እንከን አልባ ሆኖም ይጠናቀቃል። የዓለም ህዝብም “ጉድ!” ይላል።
   ” ጉድ! ” ያሰኘውንና ያሥደነቀውን እውነት ከታሪክና ከአፍሪካ ፖለቲካ አንፃር በዓለም ጋዜጠኞች  ይተነትናል።  እንዲህ ሲልም ያብራራል።
     “ይሄ እንደጨው ዘር ፣በዓለም ተበትኖ ፣አሜሪካዊ ነኝ።ጀርመናዊ ነኝ።እሥራኤላዊ ነኝ።ወዘተ።በማለት የምንጅላቶቹ እትብት ባልተቀበረበት ሀገር በዜግነቱ ኮርቶ እየኖረ ፣የዘር ማንዘሮቹ እትብት የተቀበረባትን ሀገሩን በስሞ መጥራት የሚቀፈው ትውልዱ ኢትዮጵያዊ …ይህ ቋንቋ ብቸኛው የሥልጣን መጨበጫዬና ከድህነት የምላቀቅበት የመታገዬ መሣሪዬ ነው የሚል …   ቋንቋን እንደ አንድ ፣የሥልጣን ማግኛና የመበልፀጊያ መሣሪያ አድርጎ ሲያብቃ ፣ እርሱ በላቀ ተዝናኖት እና በምቾት በመኖር፣ በደሃ ወጉኑ ለማላገጥ የቋመጠ… ኢትዮጵያዊው   ዜጋ በአጠቃላይ  ከድህነት አርንቋ እንዲወጣ ና ቢያንሥ አንዴ ወይም ሁለቴ ራሱን ችሎ ጠግቦ ሰርቶ እንዲበላ ከመርዳት  ይለቅ ፣ ትላንት  ” ምንጅላቶቹ  በወቅቱ የዓለም የፓለቲካ  ሥርአት  አሥገዳጅነት በበደሉት ፣ የዛሬው  ትውልድ መቀጣት አለበት ፣ እያለ ፣ዜጎች ‘ እንዲገፈታተሩ እና እንዲቋስሉ፣እንዲደሙ ና እንዲሞቱ ‘ እያደረገ  የነበረ ዛሬ ምን አይነት መድሃኒት አቅምሰውት  ነው፣ እንዲህ ዓለምን ያሥደነቀ እፁብ ድንቅ  ምርጫ እንዲደረግ ይሁንታውን የሰጠው?? ገር፣ቅን፣እና በጎ ሰው ሆኖ የተገኘው?? ” …
   ይህንን የሚሉት የበለፀጉት ሀገሮች  ፣እንደዚህ አይነቱን  ፓለቲከኛ በታሪክ አጋጣሚ አሳምረው ሥለሚያውቁት  ነወ።ሥንትና ሥንት  ለሆዱ ሟች (ባንዳ)  በታሪክ እንዳጋጠማቸው ከቶም  አይረሱም።
    እኛም ፣ ትላንት በዚች ትልቅ ሀገር ላይ በእነማን አማካኝነት አውዳሚ ና ከፋፋይ ሤራ እንደተጠነሰሰ እና ወደተግባርም እንደተሸጋገረ።ጅቡቲን እና ባህረ ነጋሽን እንዳሳጣን አንዘነጋውም። የኢትዮጵያን ሰፊ ሉአላዊ ሀገርነት እነዚህ ሥግብግቦችና ህሊና ቢሶች ፣በምቾትና ድሎት ተገዝተው ፣  ሀገሬው እርሥ በእርሱ እንዲጠፋፋ ና ሀገርንም እንዲያጠፈ  እንዳደረጉ    ከቶም አንረሳም።
    ዛሬ ደግሞ ፣” የኢትዮጵያ ብልፅግና የእኛ ድህነት ነው።”ብለው የሚያሥቡ ፣ልማታችን ጠፋታቸው እንደሆነ የሚቆጥሩ ።ዛሬም ሆዳም እና ጭፍን የሆኑ ዜጎቻችንን በምሥጢር መልምለው ረብጣ ዶላር የሚሰጡ።  ፖለቲካ ባልሆነው ፣ ” ባህል ፣ቋንቋና ኃይማኖት ” አንዱ ቋንቋ ተናጋሪ በሌላው ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ጥላቻ እንዲያድርበት የሚያደርጉ። ዓለምን ሁሉ እዚህ ደረጃ ላይ  የደረሱት የሰው ልጅ የዕድገትና የሥልጣኔ ሥርዓቶች መሆናቸውን የዘነጉ።በውሥጣችን አሉ።.( በነገራችን ላይ  የጋርዮሽ፣የባርያ አሣዳሪ ፣የፊውዷል፣የካፒታሊስት … ሥርዓተ ማህበር  ውሥጥ የሰው ልጅ ና ሀገራት ማለፋቸውን ፣ በዚህም ሂደት ውሥጥ በዓለም ህዝብ ውሥጥ የተፈፀሙ ነውረኛ ተግባራትና ለፅድቅ የበቁ አያሌ ሥራዎችን ግለሰቦችና ቡድኖች እንደፈፀሙ ይታወቃል።በዛ የሰው ልጅ ከሥልጣኔ በራቀበት ዘመን የተለያየ የሰውነት አካላትን ያመቁረጥ ሚና ሁሉም ሰው ተጫውቷል።በጦርነት፣በሥልጣን ቀናይነት፣በባህልና በኃይማኖት ሰበብ።ዛሬ ደግሞ ሰው በተራቀቀ አውዳሚ የጦር መሣሪያና ባዮሎጂካል መሣሪያ የሰው ልጅን እንደ ቅጠል ማርገፉን ቀጥሏል።)
    ዛሬም እንደባሪያ አሳዳሪ ና እንደ ፊውዶ ቡርዣ  ሥርዓተ ማህበር   ግፋ በለው በማለት፣ ሥልጣንን ለማያዝ እና ለውጪ ጌቶቻቸው ኢትዮጵያን እንደቅርጫ ሥጋ በመሸንሸን ግዳይ ለመጣል የሚቋምጡ ፣በመላው ኢትዮጵያ እንደመዠገር ተሰግሥገዋል።ለነሱ፣ሰው ህዝብ፣ዜግነትና ታሪክ ከቁጥር አይገቡም። በሥውር የሚደግፎቸውም ይህንን እኩይ ዓላማቸውን በፍጥነት እንዲተገብሩ ይፈልጋሉ። ያለአንዳች የፋይናሥ ድጋፍ ፣የሰው ልጅ ለመቀሳቀሥ አይችልምና ተከታታይነት ያለው ፀረ ዜግነት ተግባርራቸው ድጋፍ ከየት ናከነማን እንደሚያገኙ ያሳብቃል።  !!
  የሚገርመን እና ባላአዋቂነታችን  በእጅጉ እንደንቋጭ የሚያደርገን፣ የነሱ ሀገር ብልጽግና የተገኘው በጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥታቸው  መሆኑን ሆን ብለው በመሸፋፈን  የእኛን የድንቁርና የቋንቋ ሹክቻ መደገፋቸው ነው ።( እሥትራቴጂካዊ ተቀናቃኞቻችን ሳይቀሩ ።)
    ታሪካዊ ጠላቶቻችን የነበሩትን ፣ እንተዋቸው እና ሌሎች ዛሬ ደንዳና ጡንቻ ያላቸው መንግሥታት ፣ በየሥርዓቶቹ የመንግሥትን ሥልጣን በተቆጣጠሩ መሪዎቻቸው የመሪነት ብልሃት፣  ማዕከላዊው መንግሥታቸው በየጊዜው  እየተጠናከረ መሄዱ ይታወቃል ።
    እነዚህ የበለፀጉ ሀገራት፣  ያለማጋነን ፣ ሥርዓተ ህጋቸውበጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት ምሰሶነት በመዋቀሩ፣ እና ተቋማቱ ጠንካራ የአሠራር  ሥርአት ሥላላቸው  ማዕከላዊ መንግሥት ህግን ለማሥከበር የአንበሣውን ድርሻ እንዲይዝ በማድረግ ፣ሌሎች አሥተዳደራዊ ክልሎች የአናርኪዝምን መንገድ እንዳይከተሉ አድርገዋል።
   ደግሞም በተጨባጭ ፣ ለህገመንግሥታቸው እና  ለሚመሩበት የፖለቲካ፣የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲ ፍፁም ታማኝ የሆኑ መለሳለስ የማይታይባቸው ነበሯቸው።ዛሬም አላቸው።
    ዛሬም ከእሥታሊን እኩል ፑቲን፣ ለሩሲያ ይጨነቃል።ትራፕም ከጆርጅ ዋሽንግተን እኩል የአሜሪካ ቀዳሚነት ያሥጨንቀዋል።ከማኦ እኩል የዛሬው የቻይና ኮሚኒሥት ፓርቲ መሪ ዚ ጂንፒንግ የሀገራቸው መፃኢ ዕድል ያሥጨንቀቸዋል።ከሂትለር የበለጠ የጀርመኖ መሪ አንጀላ መርክል  ሥለጀርመን ይጨነቃሉ።ከሞሶሎኒ የበለጠ የዛሬው የኢጣሊያን መሪ ፣ሰርጂዮ ማታሬላ  ለሀገራቸው ታላቅነት ይጨነቃሉ።የፈረንሣዩ መሪ ኢማኑኤል ማክሮን  ከናፖሊዮን የበለጠ ለፈረንሣይ ይጨነቃሉ።የዩናይትድ ኪንግደም  የዛሬዋ መሪ ከማርጋሬት ታቸር እኩል ለሀገራቸው ይጨነቃሉ።…በነዚህ ሀገሮች ተአምር ሊሰኝ የሚበቃ ሁለንተናዊ ብልጽግና የተገኘው  የተገኘው ፣ ፣በጥንቶቹ መሪዎቻቸው ፋና ወጊነት መሆኑን ለአፋታ እንኳን አይዘነጉም።
     ይህ የእነሱ እውነት  ነው። የእኛ ደግሞ የተገላቢጦሽ ነው።ዛሬ በኢትዮጵያችን ፣” …ሁሉም ለሥልጣን ተፎካካሪ ፣ከምቾቱና ድሎት ይልቅ፣የዓለምን ጥልቅ የፓለቲካ ሂደትና ወቅታዊውን የሃያላን የጥቅም ሹክቻ ከቶም የማያውቀውን፣የዕለት ጉርሱን በመሻት ሌት ተቀን የሚለፋ፣የሚጥር ና የሚግረውን ቅን እና በጎ ሃሣቢ ዜጋ  በማሥተዋል፣ የግል ጥቅማቸውን እርግፍ አድርገው በመተው ፣በሥልጡንእነት ፣ ፍጹም ሰላማዊ ፣ነፃ፣ገለልተኛ እና ተአማኒ የሆነ ዴሞክሪያሲያዊ ምርጫ አካሄዱ። ” ቢባል ፣ እውነቱም ይሄው ቢሆን ለምዕራብውያኑ ህልም ነው የሚሆንባቸው።
 የሰውን ልጅ መብት ረግጦ ና ጭፍልቅልቅ አድርጎ  በአንድ ቋንቋ ተናጋሪነት ሥም ፣ ዘላለማዊ ላልሆነ ሥጋው ሟች በመሆን ፣ ለምቾቱና ድሏቱ ቀጣይነት፣የዘር እና የቋንቋ አቀንቋኙ እንደሚሟሟት እያወቁ ፤ ይኸ ጎጠኛ ና ሰውነቱን የዘነጋ ህሊና ቢሥ  ፣  ዜጋ በሆኑት የአንድ ሀገር ዜጎች መካከል ፣ያለመታከት ፣ልዩነትን ሲሰብክና፣ጥላቻን ሢዘራ ኖሮ፣ ዛሬ ደርሶ  ፍፁም ዴሞክራት ሆኖ ፣ ሽንፈቱን በፀጋ መቀበሉ በእጅጉ ቢያሥገርማቸው አይደንቅም።
  ብዙዎቹ ኃያላኖች የሀገራቸውን የኢኮኖሚ መዘውር የሚያሽከረክረውን ፣ ” የአንድ ፐርሰንቱን ከበርቴ ” ዘላቂ ጥቅም እና የገዛ አገራቸውን የኢኮኖሚ እና የፓለቲካ ኃያልነት እንጂ፣ ” ወርቅ ላይ፣ጥቁር እንቁ ላይ በባለቤትነት እየኖረ ” ሀብቱን ወደብልፅግና መቀየራያ ጥበብ አጥቶ  ርሃብ እየሞጨለፈው በወርቅ ላይ  ተኝቶ ሲያበቃ የነሱን የሥንዴ እርጥባን  ለሚጠብቀው ለምሥኪኑ ጥቁር ህዝብ ደንታም የላቸው።
     በኢኮኖሚ የበለፀጉት ሀገሮች  የሚያውቁት እና ወደምንፈልገው ግብ ያዘልቀናል ብለው ሁሌም የሚከተሉት ና  እሥከዛሬም የዘለቁበት  መንገድ ፣ጊዜው ላጋደለለት  ጡንቸኛ  ፣ ተቀናቃኞቹን የሚዱመሥሥበት   መሣሪያ እና ገንዘብ በእጅ አዙር ማቀበል ነው። ሥልጣን ሲይዝ በአይነት የሚከፍለው ።ይህንን ቅጥረኛ ና ባንዳ  ደጎሥ ያለ  ዶላር ለግሉ  በመሥጠት  ይሁዳ ማድረግ ነው። የኃያላኑ የኋላ ታሪክ ይህንን ይመሰክራል። በዚህ የእጆ አዙር እኩይ ተግባራቸውም  በንፁህ ወርቅ ሰሐን ላይየሀገር ሀብት ተከምሮ ተሰጥቷቸዋል።
    እነሱም ” ብሩክ ሁኑ፤ ልጆቻችን።” በማለት ፣ ጥቅማቸው እሥተጠበቀ ድረሥ የመንግሥት  ሥልጣን ከጨበጡት ቡድኖች  ጋር  ለጊዜውም ቢሆን  በወዳጅነት ዘልቀዋል። የሁልጊዜም መፈክራቸው ” ዘላቂ ጥቅም እንጂ ፣ ዘላቂ ወዳጅነት የለም። ” ነውና ጥቅም ሲያጡ ተሸብልለዋል።
      ግን እሥከ መቼ? በዚህ በሉላዊነት ዘመንስ ፣በርህራሄ ቢሥነት ፣ ለራሥ ጥቅም አድልቶ ፣  ደካማና  ንፁሐን የሆኑትን የአፍሪካ ህዝቦች  ማጎሣቀል ረጅም መንገድ በሠላም ያሠኬዳልን?? የበለፀጉት ሀገሮች ፣ቻይናንም ጨምሮ ፣ በዚህ ወቅታዊና እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ  ቆም ብለው ማሠብ ያለባቸው ወቅት  ዛሬ እና አሁን ይመሥለኛል።
    ዛሬና አሁን እኛ ኢትዮጵያዊያን ሰላምን እንፈልጋለን።ዛሬ ና አሁን ሁለንተናዊ ዕድገትን እንፈልጋለን።በዕውቀት እና በሀብት የበለፀጉት ሀገሮች ፣  ቆም ብለው በማሰብ ፣በቅንነት አግዘውን፣ እነሱ ሀገር ያለው የፍትህ ተቋማት ጥንካሬ ፣እነሱ ሀገር ያለው የህግ አሥፈፃሚ ተቋምት ጠንካሬ፣እነሱ ሀገር ያለው የህግ ተርጓሚው ተቋም ጥንካሬ፣እነሱ ሀገር ያለው የህግ አውጪው ተቋም  ጥንካሬ፣እነሱ ሀገር ያለው የፕሬስ ተቋሙ  ጥንካሬ፣እነሱ ሀገር ያለው የመከላከያ ሠራዊት ጥንካሬ፣እነሱ ሀገር ያለው የምርጫ ቦርድ ተቋም ጥንካሬ፣ እኛም ሀገር እንዲኖር ፍፁም ቸርነት የሞላበት  ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርጉልን እንሻለን።
   እነሱ ሀገር ውሥጥ ያለው ብዛ ቢል ከ7 (ከሰባት  )ፓርቲ የማይበልጠው   እና የፓርቲዎቹ በሰው፣ ና ሰው እንጂ ፣በዘር፣በቋንቋና በጎሣ ያለመከፋፈል ፣ምሥጢር  ምን እንደሆነም አሁን ላሉት መሪዎቻችን በጆሯቸው ሹክ ቢሏቸው ደሥ ይለናል።
    የሀገራቸውን ሰላምና የህዝባቸውን በሀገር የመመካት ምሥጢር ለመሪዎቻችን በግልፅ እሥካልገለፁላቸው ጊዜ  ድረሥ ፣ነገ ኢትዮጵያ ውሥጥ፣ተአማኒነት ያለው፣ነፃ፣ሠላማዊ፣ፍትሃዊ፣ገለልተኛ የሆነ የምርጫ ቦርድ የሚመራው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማየት አንችልም።
      በእኛ አገር እኮ ” ለማብነን” የተዘጋጁ እንደ “አብን”። ለጦርነት የተዘጋጁ ” ግንባራም ” ድርጅቶች። እንደ ሕወሓት  አይነቶቹ ዛሬም ከመሸፈት ና ከማመጽ ጋር የተያያዘውን የ1936 ዓ/ም “የወያኔ” ሥም ይዘው ከሚንቀሣቀሱ ፣ እና የሰው ልጅን አንድነት ሳይሆን ልዩነት ከሚሰብኩ ፣  እንከን አልባ ምርጫ መጠበቅም የዋህነት ነው።
    ምዕራባዊያኑም ሆኑ  አሜሪካ እንዲሁም  ወዳጃችን ቻይና በዚህ ረገድ አይታሙም።የዋሆችም አይደሉም።ይሁን እንጂ ሰብአዊነት ና ቅንነት ያንሳቸዋል።ሀብታሞቻቸውም ሃያ ሚሊዮን ዶላር በማውጣት በመንኳራኩር ተጉዘው ሰማይን በርግጫ የሚሉ ናቸው።ሥለማህበራዊ ፍትህ፣ሥለ ደሃ ህዝብ ብልፅግና ደንታ ያላቸው ጥቂቶች ናቸው።
    የበለፀጉት ሀገራት መንግሥታትና ቢሊዮነሮቻቸው፣ ቆም ብለው በማሰብ ፣ በዕውቀታቸው ልክ ፣ለእኛ ለአፍሪካውያን ፣ሁለንተናዊ ብልጽግና ካላሰቡልን፣ነገ ተያይዘን መጥፋታችንን መገንዘብ ይኖርባቸዋል። እነሱ ተራራ ላይ ሥላሉ የእኛ ታቹ ሜዳ ሢቃጠል የሚሥቁ ከሆነ በእጅጉ ተሣሥተዋል።የሜዳው እሣት ወደተራራው መምጣቱ አይቀርም።ይልቁንሥ ይህ እንዳይሆን፣ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ዘላቂ ሠላም ለማምጣት ፣የመንግሥት ምሰሶ የሆኑ ተቋማትን በመገንባቱ ሂደት ግልፅ ተሳትፎ በማድረግ የነገዋን የልጆቻችንን ዓለም ሰላማዊ እና ለኑሮ የተሥማማች ቢያደርጓት ይበጃል።
Previous Story

የከተሞቻችን ፅዳት እንዲህ ከሆነ መሰልጠን መገለጫው ምን ይሆን? – በ ሙሉጌታ ገዛኸኝ

Next Story

ሀገሬ ናፈቀኝ / ከግርማ ቢረጋ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop