የራያ ኮረም ሕዝብ ሕወሓትን ዳግም አዋረደ

ሕወሓት ዛሬ በራያ ኮረም ከተማ የካቲት 11ን በማስመልከት የሩጫ ውድድር ጠርቶ ሕዝብ ባለመገኘቱ በድርቅ ተመቶ ተዋርዶ መመለሱ ተገለጸ::

https://www.youtube.com/watch?v=ZdkEBlHGPDA&t=1s

የራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አመራር አቶ ደጀኔ አሰፋ እንደገለጹት “በኮረም ከተማ ዛሬ ሊደረግ የታሰበው የየካቲት 11 ሩጫ ዳግም በውርደት ተደምድሟል። ከንቲባውን ጨምሮ ለሩጫው የተገኘው አጠቃላይ የሰው ብዛት ከ20 ያልበለጠ ሲሆን የተገኙትም ቢሆን በሌብነት ከተማዋን ሲግጡ የኖሩ ትግሬዎች እና የትምህርት ማስረጃ ሳይኖራቸው ትህነግን በመላላክ ብቻ እንጀራ የሚበሉ ሆድ አደሮች ብቻ ናቸው።” ብሏል::

“ህዝቡ አደጋ ያደርስብናል በሚል ስጋት ትህነግ በአንዲት ሚኒባስ አማካይነት የደህንነት ስራ ለመስራት የሞከረ ሲሆን ሩጫ ተብየውም በውጥረት ተከውኖ በቅፅበት ተበትኗል። ጭራሽ በቤተክርስቲያን የተጋቡ ተወላጆች ስለነበሩ ሩጫው ምንም ሳይታይ መቅረቱም ተሰምቷል።” ያለው ዴጀኔ “አንድም የራያ ተወላጅ ያልተገኘበት ሩጫ መሆኑ የህዝቡ የማንነት ጥያቄ ጫፍ መድረሱን እና ህዝቡ ትህነግን ምን ያህል እንደሰለቸና አንቅሮ እንደጠላው ግልፅ ማሳያ ነው ተብሏል። የኮረም ህዝብና የስበር ወጣት ኩራቶች ናችሁ!!! ኮረም ማለት እንዲህ ነው!!!! አኩሪ ህዝብ ፤ አኩሪ ወጣት!!!” ሲል አቶ ደጀኔ አሰፋ አስረድቷል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  አሸባሪው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) ድርድር እና ሰላማዊ የግጭት መፍቻ አማራጮችን በድጋሜ የጦርነት ማራመጃ እና የሽብር ማሳለጫ መሳሪያ አድርጎ እንዲጠቀም ሊፈቀድለት አይገባም

1 Comment

Comments are closed.

Share