ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የጸረ ሌብነቱ እርምጃ አቅጣጫውን እየሳተ ነው አሉ

November 19, 2018

በከፍተኛ ሌብነትና ሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ መጠናከር የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ ፍላጎት ቢሆንም በሙስና እና የሰብኣዊ መብቶች ጥሰት ስም የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ ጥረት እያደረገ ነው ሲሉ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል አስታወቁ። ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ይህንን ያስታወቁት ዛሬ ማለዳ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በትግርኛ በሰጡት መግለጫ ነው።

“መንግስት በሙስና እና የሰብኣዊ መብቶች ጥሰት የጀመረው እንቅስቃሴ አቅጣጫውን ስቷል።” ያሉት ደብረፅዮን በድርጊቱን “የውጪ እጅ ጣልቃ ገብነት እንዳለበት እናምናለን – ስለሆነም አንቀበለው” ብለዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሰሞኑን መቀሌ ድረስ በመሄድ ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር መምከራቸው ተሰምቷል።

በደህንነቱ ሃላፊ በአቶ ገታቸው አሰፋ፣ በሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና በሜ/ጀነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ ላይ ያነጠጠረው የምርመራ ውጤት በም እራብያውያን ዲፕሎማቶች ዘንድ እንደደረሰም ይነገራል። የኢትዮጵያ መንግስት በጀመረው መጠነ ሰፊ የወንጀል ምርመራ ሂደት ውስጥ የአሜሪካው የምርመራ ተቋም፣ አፍ. ቢ. አይ. ተሳትፎበታል። የአምባሳደር ማይክ የመቀሌ ጉዞ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር እንደሚያያዝ አንዳንድ ምንጮች ይተቁማሉ። መቀሌ ተጠርጣሪዎቹን አሳልፋ የማትሰጥ ከሆነ ችግሩ የከፋ እንደሚሆን በርካታ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራል::

“በቁጥጥር ስር የማዋል ስራው አፈጻጸም የህግ ልእልናን በሚያስከብር መልኩ መከናወን አበት:: የትግራይ ህዝብ ለህግ ልእልና መረጋገጥ ከሌሎች አጋሮቹ ጋር ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለና ጽኑ አቋም ያለው ነው። የህግ ልእልና ካልተረጋገጠ ግጭት ይሰፍናል” ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን፣ “የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ሌብነትና የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል ብሎ የጠረጠራቸው አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል በሜቴክና በብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤቶች የጀመረውን ስራ አጠናክሮ በሁሉም ተቋማት ሊቀጥልበት ይገባል” ብለዋል።
“የህግ ልእልና የማስከበር ስራው በተወሰኑ ተቋማት መታጠር የለበትም;; ጥፋት ፈጽመዋል የተባሉትን አካላት በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ የህግ ልእልናን የሚያረጋግጥ እንጂ የፖሊቲካ መጠቀሚያና ቁማር ሊሆን አይገባም::” ብለዋል::

“ችግር ያለበት ሰው መጠየቅ አለበት:: ሁሉም ነገር በመረጃ ላይ መመስረት አለበት:: ቅጣቱም ሌሎችን የሚያስተምር መሆን አለበት” ሲሉ በመግለጫቸው ላይ የገለጹት ዶ/ር ደብረጺዮን በጥፋት የተጠረጠሩ አካላትን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ ግልጽና ከአድልዎ የጸዳ መሆን እንዳለበትና ወደ አንድ ወገን ያዘነበለ እንዳይሆን በጥንቃቄ ሊሰራ ይገባዋል ሲሉ አሳስበዋል::

“በቁጥጥር ስር እየዋሉ ያሉት አካላት በመገናኛ ብዙኃን ጥፋተኛና ወንጀለኛ ተደርገው እየቀረቡ መሆኑ የህግ ልእልና ጉዳዮችን ለማጣራትና ለመፍረድ የተቋቋሙትን ፍርድ ቤቶችና የፖሊስ ተቋማት ተግባር ያለአግባብ እየሰሩ መሆናቸውን ያሳያል” ያሉት ዶ/ሩ “ይሔም ፍትህን ከማስከበር እሳቤ ጋር የሚጣረስና የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ መብት የሚጋፋ ነው:: አፈጻጸሙ ህግና ፖለቲካን በማቀላቀል ሳይሆን ሁለቱንም በመለያየት መሆን አለበት” ሲሉ አስጠንቅቀዋል::

ደብረፅዮን ከሳምንት በፊት በክልሉ የመሸጉ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለፌደራል መንግስት አሳልፈው እንደሚሰጡ መናገራቸው የሚታወስ ነው። አሁን ደግሞ ኢሕአዴታ በግምገማ ካስቀመጠው መርህ ውጪ እየተሠራ ነው ማለታቸው ብዙዎችን ግራ ቢያጋባም – ያለፈው ስርዓት ተጠቃሚ የነበሩ የትግራይ ብሎገሮች ተጽእኖ እንደፈጠሩባቸው ይሰማል።

በዚህ ጉዳይ ለዘ-ሐበሻ አስተያየቱን የሰጠው የኢኤም ኤፍ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ “እየጠበቀ የመጣው የአስመራ ወዳጅነትም ህወሃቶች ላይ ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረ በግልጽ ይታያል። ደብረጽዮን ስለ ውጪ እጅ ጣልቃ ገብነት እየተናገሩ ያሉት፣ የዶ/ር ዐብይ አስተዳደር በነዚህ ሁለት ሃገራት ተጽዕኖ ውስጥ ገብቷል ለማለት ይመስላል።” ካለ በኋላ “መንግስት በትግራይ ሕዝብ ውስጥ የተሸሸጉ ተጠርጣሪዎችን ወደ ሕግ የማቅረብ ግዴታ አለበት። ይህ የውጪ ሃይሎች ፍላጎት ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ ነው።” ብሏል::

ክንፉ አክሉም “የክልሉ ባለስልጣናት የህግ የበላይነት እንዲከበርና በህግ ጠለላ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች መብታቸው እንዲጠበቅ ማድረግ እንጂ አሳልፌ አልሰጥም ማለት ዋጋ ያስከፍላል። ድርጊቱ ፌደራል መንግስት በሚወስደው እርምጃ መላው የትግራይ ሕዝብን ተጠቂ ለማድረግ የታለመ እቅድ ይመስላል።” ካለ በኋላ “የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ጦርነት ላይ ነን ማለታቸው የሚታወስ ነው። የህወሃት ሰዎች ሁለት እና ሶስት ወንጀለኞችን አሳልፈን ከምንሰጥ እንዋጋለን ያሉ ይመስላል። ይህም በምስኪኑ የትግራይ ሕዝብ ስም ከኢትዮጵያ ጋር በውስጥ ጦርነት ማወጅ ያስመስላል” ሲል አስረድቷል::
https://www.youtube.com/watch?v=pXfWMmUXIks

1 Comment

 1. አማራ ሞቶ ዞምቢ ከሆነ ከ27 አመታት በላይ አሳልፍዋል:: ዞምቢ አማራ ( ZOMBIE AMARA ) ትግራይውያንን ፈርቶ ወደ ሱዳን ገባ :: November 17, 2018 በአማራና በትግራይ ተወላጆች መካካል በተከሰተ ግጭት 400 አማራውያን ወደ ሱዳን ተሰደዱ:: ሱዳን ትሪቡን የተሰኘው የሳይበር ዜና አውታር የሱዳን ስደተኞች ኮሚሽንን ጠቅሶ እንደዘገበው፦ በአማራና በትግራይ ተወላጆች መካካል በተከሰተ ግጭት ሳቢያ 400 ኢትዮጵያዊያን በምስራቃዊው የጋዳሪፍ ግዛት ገብተዋል።
  ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ሱዳን የገቡት በሁለቱ አገሮች የድንበር ከተሞች ማለትም በጋላባትና በመተማ በኩል መሆኑን የስደተኞች ኮሚሽን ኮሚሽነር ሃማድ አል ጊዞሊ ገልጸዋል ይላል ዘገባው ።
  በቀጣይ ቀናትም በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ወደ ሱዳን ሊገቡ እንደሚችሉ እንጠብቃለን ያሉት ኮሚሽነር ሃማድ ፤ ከገቡት 400 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መካከል መቶ ሰማኒያ አንድ ሕጻናትና አራስ እናቶችን ጨምሮ አንድ መቶ ሴቶች እንደሚገኙበት አስረድተዋል።
  ኮሚሽነሩ ጨምረውም ለስደተኞቹ የዕለት ደራሽ የምግብ እርዳታ ለመስጠት ከ UNHCR እና UNICEF ጋር መስማማታቸውን ገልጸዋል።
  ስደተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ለህይወታቸው እንደሚያሰጋቸውና በሱዳን አሳይለም ለመጠየቅ እንደሚፈልጉም የኮሚሽነሩ መግለጫ ያስረዳል።
  ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከሱዳን በሚያዋስነው የአማራ ክልል አካባቢ በአማራና በትግራይ ተወላጆች መካከል ግጭት ሲከሰት መሰንበቱን የሱዳን ትሪቡን ዘገባ አስታውሷል።
  ዘገባው ስለ ስደተኞቹ የብሄር ስብጥር የገለጸው ነገር የለም።

  400 Ethiopian refugees arrive in Sudan following ethnic clashes: official

  November 16, 2018 (KHARTOUM) – The Sudanese Commission of Refugees (SCR) said 400 Ethiopian refugees have arrived in the eastern state of Gedaref following ethnic clashes between Amhara and Tigray.
  Sudan’s commissioner of refugees Hamad al-Gizouli said the Ethiopian refugees have entered Sudan through Gallabat and Metemma border crossing points between the two countries.
  He expected that further influx of Ethiopian refugees would arrive in Sudan during the next days, saying among the 400 refugees there were 181 children and 100 women including pregnant and breastfeeding women.
  Al-Gizouli added they have agreed with the UNHCR and UNICEF to provide the Ethiopian refugees with ready-made meals and medical assistance.
  He pointed out that the 400 refugees have expressed a desire to stay in Sudan and apply for asylum because they are afraid to return to Ethiopia for their own safety.
  It is noteworthy that the Amhara region on the border with Sudan has witnessed violent clashes between Amhara and Tigray ethnicities since last week.(ST)

  http://quatero.net/amharic1/archives/31313

  http://www.sudantribune.com/spip.php?iframe&page=imprimable&id_article=66620

Comments are closed.

92587
Previous Story

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ግርማ ዋቄ ሃላፊነታቸውን የለቀቁት በሕወሓት ሰዎች “ያልንህን ካልሠራህ” ስለተባሉ መሆኑን ገለጹ

92597
Next Story

በድሬዳዋ በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ፣ ቤቶች ተቃጠሉ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም
Go toTop