November 19, 2018
2 mins read

በድሬዳዋ በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ፣ ቤቶች ተቃጠሉ

92597

የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ በከተማው ቅዳሜና እሁድ በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱንና ቤቶች መቃጠላቸውንም ይፋ አድርጓል፡፡ ይኸው የፖሊስ መግለጫ ህዳር 8ቀን 2011አ.ም ከሰአት በሃላ እና ህዳር 9ቀን እረፋድ ላይ በቀበሌ 09 ፖሊስ መሬትና መጋላ ጨብጡ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግጭት መፈጠሩን ይናገራል፡፡ ፖሊስ የግጭቱን መንስኤ እያጣራው እንደሆነ የገለፀው መግለጫው ጨምሮም ‹‹በዚህም ግጭት በህክምና ጭምር የተረጋገጠ በስለት ጉዳት ጉዳት ደርሶበት የ1ሰው ህይወት ሲያልፍ በ2 ቤቶች ላይ ቀጠሎ እንዲሁም በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።›› ብሏል፡፡ ግጭቱ ወደ 01 ቀበሌ

መልካ ጀብዱ የመስፋፋት አዝማሚያ ታይቶበት እንደነበረ ያስረዳው መግለጫው ይሁንና ፖሊስ ከፌደራል ፖሊስና ከመከላኪያ ጋር ምንም አይነት ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ ለመቆጣጠርም እንደተቻለ ጠቅሷል። ‹‹በአሁን ወቅት ችግሩ በተፈጠረባቸው አካባቢዎች ተገቢው ፀጥታን የማረጋገጥና ሰላምን የማስፈን ስራ እየተሰራ ነው›› ያለው መግለጫው ተፈጥሮ የነበረውን ግጭትና ሁከትም አሁን ላይ ተናግሯል። መግለጫው በመጨረሻም ‹‹መላው ህብረተሰብ ወደ ግጭት ሁከትና መረበሽ ሰዎችን እንዲያመሩ ከሚያደርጉ አንዳንድ ማህበራዊ የሚዲያ ገፆችና ያልተረጋገጠ መረጃ ከሚሰጡ ዘገባዎች እራሱን በመጠበቅ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን የማረጋገጥ ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጨምሮ ጥሪውን ያቀርባል።›› ሲል አስረድቷል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=pXfWMmUXIks

92593
Previous Story

ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የጸረ ሌብነቱ እርምጃ አቅጣጫውን እየሳተ ነው አሉ

92600
Next Story

የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት የስራ ባልደረባ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ አዲስ ክስ ተጨመረ | ፖሊስ የሜ/ጀ ክንፈ ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው በባንክ ያላቸውን ገንዘብና ንብረታቸውን ማስረጃ አቅርቦ ዋስትና ራሳቸው ያቁሙ ሲል ጠየቀ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop