የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ግርማ ዋቄ ሃላፊነታቸውን የለቀቁት በሕወሓት ሰዎች “ያልንህን ካልሠራህ” ስለተባሉ መሆኑን ገለጹ

የኢትዮጵያ አየር መንገደ ለሰባት ዓመት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት የመሩት አቶ ግርማ ያቀረቡት የሥራ መልቀቂያ ተቀባይነት አግኝቶ እ.ኤ.አ. በ2011 በጡረታ የተሰናበቱት በሚደርስባቸው የሕወሓት ባለስልጣንት ግፊት እንደነበር ዛሬ በአዲስ አበበባ ታትሞ ከወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ ገልጸዋል;;፡ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከለቀቁ በኋላ የሩዋንዳ አየር መንድ የቦርድ ሊቀመንበር፣ የሩዋንዳ የትራንስፖርት ሚኒስትር የአቪዬሽን ጉዳዮች አማካሪ በመሆን ያገለገሉት አቶ ግርማ በአሁኑ ወቅት የቶጎ ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

እንዴት እንደለቀቁ ሲያስረዱ “ኢሕአዴግ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ እ.ኤ.አ. በ1993 በአዲሱ መንግሥት አየር መንገዱ ይጠና ተባለ፡፡ ከእኛ አሠራር ጋር ይሄዳል? አይሄድም? የሚል ጥያቄ ተነሳ፡፡ አንድ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንዲጠና ተደረገ፡፡ እኔ አስተዳደሩን ወክዬ እካፈል ነበር፡፡ በጥናቱ አካሄድ ላይ ከመንግሥት አካላት ጋር ሳንስማማ ቀረን፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ፣ አቶ ተከስተ የሚባሉ ሹም ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ነበሩ፣ ሌሎችም ሚኒስትሮች ይህን እንዲያጠኑ በመንግሥት የተመደቡ ነበሩ፡፡ ከእነሱ ጋር በአካሄድ ልንስማማ አልቻልንም፡፡ አካሄዳቸው ከአየር መንገድ አሠራር ጋር የሚሄድ መስሎ ስላልታየኝ ይኼ ነገር ልክ አይደለም ብዬ እከራከራቸው ስለነበር በእኔ ደስተኛ አልነበሩም፡፡ አርፈህ የምንልህን አድርግ ይሉኝ ጀመር፡፡ እኔም የማላምንበትን ነገር አላደርግም፡፡ እናንተ ይኼ ነገር የሚያዋጣ መስሎ ከታያችሁ ቀጥሉበት፣ እኔ እዚህ ሆኜ እንቅፋት አልሆንም፡፡ እኔ የማላምንበትን ነገር አልሠራምና ልቀቁኝ አልኳቸው፡፡ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ዘንድ ተልኬ ሦስት ቀን ተሰጠኝ፡፡ የሚሰጠኝን ትዕዛዝ ተቀብዬ በስብሰባ ላይ እንድገኝ ነው፡፡ በሚደረገው ነገር ላይ እምነት ስላልነበረኝ በስብሰባው ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ እንዳልሆንኩ አስታውቄ የሥራ መልቀቂያ አስገባሁኝ፡፡ ከሥራ ወጥቼ አምስት ወራት ያለ ሥራ አዲስ አበባ ተቀመጥኩ፡፡ በኋላ ገልፍ ኤር ሥራ አገኘሁና ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አቀናሁ፡፡ ያደግኩበትንና 27 ዓመታት ያገለገልኩበትን አየር መንገድ ለቅቄ ለመሄድ ተገደድኩ፡፡ የሄድኩት ገንዘብ ፈልጌ አይደለም፡፡ የነበረው ሁኔታ የማያሠራኝ ስለነበረ ነው፡፡ እኔ ከወጣሁ ከትንሽ ጊዜ በኋላ 35 የአየር መንገድ ማኔጅመንት አባላትን ከሥራ አስወጧቸው፡፡ ከዚያ በኋላ አንተ የምትናገረው እውነት ነበር፡፡ ተመለስና ሥራ የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ቀርቦልኝ ነበር፡፡” ብለዋል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያን ከአደጋ ለመታደግ አስቸኳይ መፍትሔ ለመፈለግና ለሰላማዊ ሽግግር የሸንጎ ራእይ

https://www.youtube.com/watch?v=bG1fu3OzfzY&t=122s

2 Comments

  1. RECENTLY WE HEARD ONE OF THE 5 metec OWNED airplanes WAS LOST.The lost METEC plane was transporting contraband weapons allover Middle East SELLING ETHIOPIA’S MILITARY WEAPONS TO FOREIGNERS. Currently half Ethiopia’s military weapon that was in Tigray to protect the the border with Eritrea is not accounted for, experts suspect the expensive Ethiopia military owned arms are sold out by TPLF to YEMEN , Syria , IRAN and even beyond. Some say the imprisonment of Mohammed Alamoudi in Saudi got something to do with the illegal arms sales that TPLF was conducting in Yemen.

    SOMEHOW AFTER THE NEWS ABOUT ONE OF THE 5 METEC AIRPLANES DISAPPEARANCE WENT PUBLIC , THE LOST PLANE few nights ago was MIRACULOUSLY found parked at Bole international Airport .

    EAL Bole International Airport is guilty of covering up the crimes that this plane was committing. EAL CEO TEWOLDE AND METEC, both are under TPLF. EAL’S CEO Tewolde is CHANGING IT’S STORY SO MANY TIMES first CEO TEWOLDE gave a fake name Yohannes Megersa as the person who owns the plane not METEC . NOW ceo TEWOLDE trying to say the lost plane belongs to METEC and was parked in Bole International Airport for years while it is known it was flying in and out OF ETHIOPIA at the time. It is also known this plane transported the riches of Ethiopia to Tigray by night and was also selling contraband weapons in Yemen flying so low to the ground radar was not detecting it,whenever radar detected it in Ethiopia the TPLF symphatizers at EAL, Ethiopian AIRFORCE AND AVIATION didnot report it. METEC, which stands for Metals and Engineering Corporation, was set up in 2010. It is Ethiopia’s largest company, a military-run industrial corporation that has for years had significant influence in the economy. Though there has been some suspicion that the corporation was being used by government elites as a patronage it is in these past few days that it has become official.

    Even though METEC’s mission was to improve Ethiopia’s engineering capacity through experimentation and foreign partnerships, failures on major projects have probably cost the government 100’S OF BILLIONS of dollars. According to DW Amharic, the corruption of Ethiopia’s state-owned Metals and Engineering Corporation (METEC) extends to maritime trade. Ambassador Suleiman Dedefo who was the Ambassador of Ethiopia in Djibouti at the time said that in 2012, METEC bought two out-of-service ships called Abay and Andinet from the government’s Ethiopian Shipping Logistics and Services Enterprise .It is said that later on, METEC may have used the ships for trading arms and other contraband between Iran and Somalia. After multiple illegal voyages, the corporation sold them .

  2. Dear zehabesha website administrator,

    I’m one of your website regular reader starting from long ago. I’m really admirable & really appreciate what you’re doing to address the public all the current issues of the country on timely manner.

    But on your above report regarding the resignation of former CEO of Ethiopian Airlines(Ato Girma wake) I feel that you interpreted or may be overlooked what he said in the wrong way.He didn’t say he left Ethiopian in 2010 because their was too much pressure & interference from TPLF officials, on the contrary he mentioned their was remarkable support from the government towards his management team & the airlines.
    He mentioned about the pressure & interference from the government & his resignation(what you mentioned in the 1st paragraph of the report) from ET back in 1993 when he was a director of a marketing section not as a CEO.

    So please correct your report so that it reflects what has been said because this kind of silly mistakes may degrade the credibility & images of your website.

    Hope you will continue your effort to provide us an up-to-date information regarding current affairs of our country.

    With best regards,

    ሪፖርተር፡- በስፋት ሲወራ የምንሰማው ከሥራዎት የለቀቁት በመንግሥት ተገፍተው ወይም እርስዎን በተኩዎት በአቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ተገፍተው እንደወጡ ነው፡፡ ጡረታ እንዲወጡ የተደረገብዎ ግፊት ነበር?

    አቶ ግርማ፡- እኔን ማንም አልገፋኝም፣ ሊፈገፋኝም አይችልም፡፡ ነገር ግን ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት እኔ የመጣሁት አምስት ዓመት ለማገልገል ነበር፡፡ መስተካከል የነበረባቸውን ሁኔታዎች ከባልደረቦቼ ጋር ሁኜ አስተካክዬ ለሰባት ዓመታት ሠራሁ፡፡ በመካከል አሞኝ ስለነበር ቀዶ ሕክምና አደረግኩ፡፡ ቀዶ ጥገናውን አድርጌ ተመልሼ ሠራሁ፡፡ ከዚያ በኋላ የእኔ መቆየት የሚያስፈልግ መስሎ አልታየኝም፡፡ እንዲያውም አቶ ሥዩም ለምን ትለቃለህ? ትንሽ ቆይ ብለው ሊያግባቡኝ ብዙ ጥረዋል፡፡ እኔ ግን ከዚህ በኋላ ይበቃኛል በሚለው አቋሜ ፀናሁ፡፡ ሊተካኝ የሚችል ሰው አዘጋጅቻለሁ ስላቸው፣ ማነው የሚተካህ? ሰው ብለው ሲጠይቁኝ አቶ ተወልደ ነው ብዬ ያቀረብኩት እኔው ራሴ ነኝ፡፡

    ሪፖርተር፡- በወቅቱ ለመልቀቅዎ ዋናው ምክንያት መንግሥት በሥራዎ ላይ ተፅዕኖ ያደርግብዎ ስለነበር እንደሆነ ይነገራል፡፡ አንዳንዶች ከቦርዱ ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር የሚገልጹ አሉ፡፡ የእርስዎ ምላሽ ምንድነው?

    አቶ ግርማ፡- መንግሥትም ሆነ ቦርዱ ያሳደሩብኝ ተፅዕኖ አልነበረም፡፡ መንግሥት በሥራዬ ጣልቃ አልገባብኝም፡፡ ከቦርዱም ጋር መልካም የሥራ ግንኙነት ነበረኝ፡፡ እውነቱን መናገር አስፈላጊ ነው፡፡ አቶ ሥዩም ለአየር መንገዱ ዕድገት ከነበራቸው ምኞት ለማኔጅመንቱ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በሥራችንም ጣልቃ አይገቡም ነበር፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት በሥራ ጣልቃ እንዳይገቡ ቃል አስገብቼ ነበር የመጣሁት፡፡ እስከ መጨረሻው ቃላቸውን አክብረው ነበር አብረውን የሠሩት፡፡ ችግር እንኳን ሲፈጠር ከጎናችን ነበር የሚቆሙት፡፡ እሳቸውም መንግሥትም ቃላቸውን አክብረዋል፡፡ ሊመሠገኑ ይገባል እንጂ እኔን የጎዳኝ ሰው የለም፡፡ እንድወጣም የገፋኝ ሰው የለም፡፡ አጉል አጉል ጥያቄ የሚጠይቁ አንዳንድ የመንግሥት ኃላፊዎች ነበሩ፡፡ እነሱን እኔ በይፋ አይሆንም፣ ይኼን አላደርግም እላቸው ነበር፡፡ ያው ለጊዜው ተቀይመው ዝም ይላሉ፡፡ እኔም ብዙ አልተጨነኩበትም፣ እነሱም የግል ጉዳይ አድርገው እኔን ለማጥቃት የተነሱበት ጊዜ አልነበረም፡፡

Comments are closed.

Share