የቀድሞው የፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ታሠሩ | ቀድሞው የማእከላዊ ምርመራ ምክትል አዛዥ እየታደኑ ነው

November 11, 2018

ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከዘይኑ ጀማል ቀደም ብሎ ለቀናት ፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ሆነው ተሹመው የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ታሰሩ:: ትንናት የታሰሩት የጦር መኮንኖች ቁጥር ወደ 50 ያደገ ሲሆን ከሃገር ያመለጡ እንዳሉም ተዘግቧል::

ካፒታል የ እንግሊዘኛው ጋዜጣ ምንጮቼ ነገሩኝ ሲል እንደዘገበው አቶ ያሬድ ዘሪሁን ታስረው እየተመረመሩ ይገኛሉ:: አቶ ያሬድ ከተሾሙ በኋላ ወዲያውኑ ከኃላፊነታቸው ሊነሱ የቻሉት የተቋሙ አደረጃጀት ሰፊና ልዩ ቁጥጥርና ክትትል የሚፈልግ ከመሆኑ አንፃር፣ በዘርፉ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ያለው ቢመራው የተሻለ ይሆናል ከሚል መነሻ መሆኑን; በወቅቱ ከስልጣናቸው ሲነሱም; ከኃላፊነታቸው በመነሳታቸው ቅሬታም ሆነ ተቃውሞ አለማሰማታቸውን ዘ-ሐበሻ በወቅቱ ዘግቦ ነበር::

ዛሬ ዘብጥያ የወረደው ያሬድ ዘሪሁን ፌዴራል ፖሊስ ከመመደቡ በፊት ሕወሓቶች ይዘውሩት የነበረው የኢንሳ ምክትል ነበር::

ትንናት ጠዋት የታሰሩት ሰዎች ቁጥር 40 ደርሶ እንደነበር ዘግበን ሌሎች የሚያሰሩም አሉ ብለን ነበር:: በዚህም መሰረት ካፒታል ጋዜጣ የታሰሩትን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የደህንነት ሰዎች ቁጥር 50 ደርሷል ብሎታል:: እንደጋዜጣው ዘገባ የ እስር ዋራንት ከወጣላቸው መካከልም ከሃገር ጥለው የፈረጠጡም አሉ::

ዘ-ሐበሻ ከፓሊስ ዛሬ እንዳገኘነው ስብሰባ ተጠርተው ታፍሰው የተወሰዱትም ሆነ ከቤታቸው ተወስደው የታሰሩት ተጠርጣሪዎቹ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። አንዳንድ ምንጮች ፖሊስ መዝገብ የሚከፈተው እነ እነ ክንፈ ዳኘው በሚል ነው ቢሉም ጀነራል ክንፈ ዳኘው ስለመታሰራቸው ማረጋገጥ አልተቻለም::

በሌላ ዜና በርካታ የደህንነት ሠዎች ማዘዣ ወጥቶባቸው እየታደኑ ነው። በሰብአዊ መብት ጥሠትና አሸባሪነት ከሚፈለጉት ውስጥ የቀድሞው የማእከላዊ ምርመራ ምክትል አዛዥ ረታ ተስፋዬ እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ አዛዦች ይገኙበታል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞው በጠቅላይ አቃቤ ህግ የፀረ ሽብር ዳይሬክቴሮት ዳይሬክተር አቶ ብርሀኑ በቁጥጥር ስር ውለዋል::
በትናንትናው እና በዛሬው ዕለት ካሉበት እየታደኑ ከታሰሩት ዋና ዋና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት አመራሮች መካከል
1. ዶ/ር ሀሺም ተውፊቅ: የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ም/ኃላፊና የአቅም ግንባታ ዘርፍ የዳይሬክተሮች ዳይሬክተር
2. አቶ ደርበው ደመላሸ: የኢኮኖሚ ደህንነት መምሪያ ዳይሬክተር
3. አቶ ተሾመ ኃይሌ – የጥበቃና ኤርፖርቶች ደህንነት ዳይሬከተር
4. አቶ አስገለ – የውጭ ደህንነት መምሪያ ም/ዳይሬክተር የአዴኃን መስራችን ሺአለቃ ፋናዬን ያስገደለ
5. ኤርትራ ውስጥ ሰው በመላክ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ሊያስገድል የነበረ ነበር የተባለው አቶ ደረሶ አያና – የሰሜን ምዕራብ መምሪያ ኃላፊ
6. አቶ ኢዮብ ተወልደ- የደቡብ ክልል መረጃ እና ደህንነት ኃላፊ
7. አቶ አማኑኤል ኪሮስ- የአገር ውሰጥ ደህንነት መምሪያ ኃላፊ
8. አቶ አሸናፊ ተስፋሁ – የሰሜን ጎንደር የደህንነት ኃላፊ፣ ከጎንደር ማረሚያ ቤት ቃጠሎ እጁ አለበት የሚባል (ጎንደር በነበርኩ ጊዜ ሲዝትብኝ የነበረ መላጣ አጭር ሰው)
9) አቶ ነጋ ኑሩ – በምሰራቅ ወሎ የመረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአማራ ክልል የደህንነት ኃላፊ የነበረ
10) አቶ ቢኒያም ማሙሸት – በሶማሌ ክልል የደኅነነት ሥራ ሲመራ የነበረ፣ በርካታ ሰወች በእጁ ያጠፋ ጨከኝ ሰው
11) አቶ ሸዊት በላይ – የግንቦት 7 ክትትል ዴስክ ኃላፊ የነበረ እና የአፋኝ ቡድን ቁልፍ አባል
12) አቶ ተከተል – የሀረሪ ክልል የደህንነት ኃላፊ የነበረ
13) አቶ አጽበሀ ግደይ – የክትትል መምሪያ ኃላፊ የነበረ እና የአፋኝ ቡድን ቁልፍ አባል
14) አቶ ሳሙዔል: የፀረ ስለላ መምሪያ ኃላፊ የነበረ ይገኙበታል::
https://www.youtube.com/watch?v=f9ZDJjIZNkI

3 Comments

 1. አቢይ አደራህን።

  መቅደምን ሰንቀህ፣
  ብልህነት ይዘህ፤
  በትግል ጓድ ለማ፣ቅንነት ታግዘህ።
  ሊገድሉህ ያሴሩትን ስትጀምር ጉዞህን፤
  ፍቅርህ ይቅበራቸው
  አቢይ አደራህን።
  በደም እንዳትፅፍ ፍላፃ ብትይዝም፤
  እነሱ ይጋደሉ
  አንተ ግን ፀጥ ዝም።
  አለበለዚያ ግን የሞከሩት ሁሉ፤
  ከተሳካላቸው ለጠላት ነው ድሉ።
  እንኳን ላንተ ይቅርና
  ለእኛም ያሳፍራል፤
  ያሰብነው ተስፋ ሁሉ ባርነት ይቀራል።
  ስለዚህ አትናገር ጓደኛዬ ብለህ፤
  የኢትዮጵያን ተስፋ እንዳትሰጥ ተታለህ።
  እናም አትገግደላቸው የሚያሴሩብህን፤
  ፍቅርህ ይቅበራቸው
  አቢይ አደራህን።

 2. እግዚኣብሔር ሆይ ቸርነትህን ሙሉ ኣድርግልን፣ እነዚህን የኣጋንንት ሠራዊት ኣርቅልን፣ ሰብኣዊ መልእክተኞችህ ዓቢይና ለማ፣ ደመቀና ገዱ የበለጠ ልብ እንዲያገኙና የሕዝባንን እፎይታ ምሉዕ እንዲያደርጉት ኣስችልልን፣ ኣንዳች ነገር የማይሳንህ ዓምላካችን ገና ብዙ ታሳየናለህ፣ ያንተ ፈቃድ ይሁንልን፥ ኣሜን!!!!

 3. ahun ewunetim lewut limeta new malet new. yeskahunu gin keld nebber. yefeneteke yenetsanet chora alnebereme lemalet gin aydelem. kenigigir balefe yezih aynet techebach ermja ketewosede zegoch yibelit netsanet yisemachewal. be’ekonimiwum reged sabotaj yemiseruna nuron yemiakefu siwur yewoyane telalakiwoch wagachewn magegnet alebachew. lemsale mebrat hayl tarif endichemir yetederegew ahun lemn tbelo meteyek alebet. hizbun lemamarerina woyanen endinafik lemadreg bzu tiret eyetederege newuna yitasebibet.

Comments are closed.

18
Previous Story

ለ18 አመታት ያህል በትግራይ ክልል ታስሮ የቆየው ካሳሁን ሲሳይ ‹‹በትግራይ የሚታሰር አማራ የከፋ ግፍ ይፈፀምበታል›› አለ

Screen Shot 2018 11 12 at 8.44.23 AM
Next Story

የታሰሩት ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የደህንነቶች ቁጥር 126 ደረሰ | ጌታቸው አሰፋ የ እስር ማዘዣ ወጦበታል

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም
Go toTop