የአማራ እና የትግራይ ክልል በመግለጫ በመጎሻሸም ቀጥለዋል

የደብረጽዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልል አስተዳደር ትናንት “የተለያዩ ኣጀንዳዎች በመቅረፅ በትግራይ ህዝብ ሰላምና ድህንነት በማወክ ዙርያ የሚደረግ ዘመቻ ኣሁንም ሳያቋርጥ እንዲቀጥል እየተደረገ ነው፡፡ በትግራይ ክልል ጉዳይ ላይ እጅን ከማስገባት በተጨማሪ ከትግራይ ጋር የሚያስተሳስሩ መንገዶች በመዝጋት እና የትግራይን መሬት በሃይል ለመውረር መፈለግ የመሳሰሉ ያረጁና ሃሏ ቀር ኣስተሳሰቦችና ክፉ ተግባራትም እየታዩ ናቸው፡፡” በሚል በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ክልል አስተዳደር ላይ መግለጫ ማውጣቱን ተከትሎ በዛሬው ዕለት የአማራ ክልል “ግጭቱን የህዝብ ለህዝብ በማስመሰል ከዚህ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ሙከራ ፍሬ አልባ እና ምንም መሠረታዊ መነሻ የሌለው ከንቱ ድካም ነው” ሲል መግለጫ አወጣ::

“በህዝቦች ትግል የመጣው ለውጥ እንዳይቀለበስ የተገኘውን ተስፋ ነፃነት እና ሠላም መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ የሚታዩ ችግሮችንም በሰከነ መንገድ የህግ የበላይነትን አስጠብቆ መፍትሄ ለመስጠት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ ሰሞኑንም በምዕራብ ጐንደር ዞን አዳኝ አገር ጨንቆ ወረዳ ምስረታ በዓልን አክብረው እየተመለሱ ባሉ ወገኖች ላይ ማንነታቸው ለጊዜው ያልታወቁ ግለሰቦች ባደረሱት ጥቃት የ4 ሠዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ በዚህ መነሻ በተፈጠረ ግጭት በዞኑ መተማ እና ሽንፋ አካባቢዎች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡” ያለው የክልሉ መግለጫ “የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልፃል፡፡ በሌላ በኩል አጋጣሚውን በመጠቀም ሁኔታውን በማባባስ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ህዝባችን ችግሮችን በውል የመረዳት አስተውሎት ያለው በመሆኑ ችግሩ ወደ ከፋ ግጭት እና ጥፋት ሳይሄድ አካባቢው እንዲረጋጋ ማድረግ ተችሏል፡” ብሏል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሳኡዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን በተመለከተ አዲስ ህግ አወጣ!

“የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፀጥታ ሀይሎች ከኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር በመሆን በአካባቢው ችግሩን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ ከአካባቢው ህዝብ ጋር በመሆን መስዋዕትነት በመክፈል ጭምር ጥፋተኞች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እየተደረገ ያለውን ጥረት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በእጅጉ ያደንቃል፡፡ በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ተሣትፎ በማድረግ ችግሩ እንዲፈጠር ያደረጉ ተጠርጣሪ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ፡፡” ካለ በኋላ መግለጫውን በመቀጠልም “ግጭቱን የህዝብ ለህዝብ በማስመሰል ከዚህ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ሙከራ ፍሬ አልባ እና ምንም መሠረታዊ መነሻ የሌለው ከንቱ ድካም መሆኑን የክልሉ መንግስት ያስታውቃል፡፡ ይህንን ዓላማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ አካላት እና የዚህ አስፈፃሚ ግለሰቦችም ትርፋቸው ኪሣራ እንደሆነ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ በክልሉ በየትኛውም አካባቢ ህግን የሚፃረሩ ተግባራትን ለማስወገድ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ የሚሠሩ ሲሆን ህዝቡ ያገኘውን ሠላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ አካላትን በማጋለጥ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡” ሲል አስጠንቅቋል::

“በቀጣይ የክልሉ ህዝብን ሠላም ለማስጠበቅ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ርብርብ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን እየገለፅን መላ የክልላችን ህዝቦችም የተገኘውን ሠላም እና ነፃነት በመጠበቅ ከመንግስት ጐን እንዲሰለፍ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪውን ያስተላልፋል፡” ሲል መግለጫውን አጠናቋል::

የደብረጽዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልል አስተዳደር ትናንት ባወጣው መግለጫው “የትግራይ ህዝብና መንግስት ደግሞ ለጥፋት ሳይሆን ለጋራ ልማትና ሰላም የቆመ በመሆኑ የሁለቱን ህዝብ ወንድማማችነት የሚያጠናክሩ እንጂ የሚያፈርሱ ስራዎች የማንሰራ መሆኑን አሁንም በድጋሜ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ይህ ማለት ግን በህዝባችን ላይ የሚፈፀሙ የጥፋት ተግባሮች ኣይተን እንዳላየን እንሆናለን ማለት ኣይደለም፡፡ በህዝባችን ንብረትና ህይወት ላይ ጉዳት ያደረሱ በሙሉ እንደ ክልል መንግስት በህግ እንዲጠየቁ ጥረት የምናደርግ ይሆናል፡፡ የኣማራ ክልል እና የፌደራል መንግስትም ህገ-መንግስቱን ያለ ማቋረጥ በተደጋጋሚ በሚጥሱ ኣካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል፡፡ ለዘመናት ኣብረው የነበሩና በብዙ መንገድ የተሳሰሩትን ህዝቦች ኣንድነታቸውና ወዳጅነታቸው ኣጠናክረው እንዲቀጥሉ ከማስቀጠል ይልቅ ማንነት ላይ መሰረት ያደረገ ጥቃት ሲፈፀም ማየት የሚያሳዝን እና የሚሳፍር ድርጊት ነው፡፡ የኣማራ ክልል ህዝብና መንግስት እንዲሁም የፈደራል መንግስት ይህ ማንነት መሰረት ኣድርጎ እየተፈፀመ ያለውን በደል ኣጥብቆ በማወገዝ ኣስቸኳይ ምላሽ በመስጠት የዜጎችን ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የወደመ ንብረታቸው እንዲተካና በተለያዩ ግዚያት በህዝብ ላይ ግፍ የሚያደርሱትን ወንጀለኞች በሙሉ እንዲሁም መንግስት በቅርብ በምህረት ለቋቸው ሲያበቃ በወንጀል ተግባር ላይ የተሰማርቱን ጨምሮ ወደ ህግ እንዲቀርቡ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል፡፡” ብሎ ነበር::
https://www.youtube.com/watch?v=LCftg3owFj4&t=4s

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኮለኔል አያናው መስፍን ቤተመንግስት ከሄዱት የወታደሮች ጀርባ አሉበት ተብለው ተጠርጥረው ታሰሩ

3 Comments

  1. የአማራ፥ክልል፥መንግስት፥ትጥቅህን፥አጥብቅ!!
    40ሚሊዪን፥የተቆጣ፥አማራ፥ከጎንህ፥ተሰልፎአል!! የሚሊሻዉ፥ስልጠና፥በጥሩ፥ሁኔታ፥
    እየተካሄደ፥ቢሆንም፥ሕዝቡን፥በስፋት፥ማስታጠቅና፥ማሰልጠን፥መቀጠል፥አለበት፥፥
    የትግሬ፥ዘራፊ፥ሽፍታ፥ድንበር፥አቋርጦ፥ከገባ፥የማያዳግም፥የመጨረሻ፥ምት፥ሊያርፍበት፥ይገባል፥፥

  2. ህዝብ የሚያውቀው ስር የሰደዱ ችግሮችና ቅሬታዎች እያሉ ለምን በሚዲያ በሚሰጥ መግለጫ ህዝብን ለማደናገር ይሞከራል፡፡
    እውነታውን ህዝብ ስለሚያውቅ ይልቅ ለህዝብና አገር የሚታሰብ ከሆነና ከጀርባው የተደበቀ አጀንዳ ከሌለ የሁለቱ ክልሎች ሊቀመንበሮችና ኃላፊነት ያለባቸው አስተዳደሮች በችግሩ አካባቢ በመገኘት ከህዝቡ ጋር በቅርብ መወያየት ያስፈልጋል፡፡ ስልጣን ላይ ተቀምጦ ጥይት ማስተኮስና በህዝብ ደም ላይ መቀለድ በኃላ አትፍረድ ይፈረድብሃል ነውና ነገሩ ከህሊና ፀፀት ነፃ የሚያደርግ ስራ ቢሰራ ጥሩ ነው፡፡

    የጠቅላይ ሚ/ሩ የጎንደር ውይይት እንኳን ለሌላው ትምህርት ሊሆነው ይገባ ነበር፡፡ ከፍ እንዳሉ መኖር የለም ነገ ዝቅ ማለት ይኖራልና፡፡

    እንደው አንዱ የሰጠውን መግለጫ አንዱ ለማፍረስና ህዝብ ለማደናገር ከማሰብ ይህን ያህል እሳት የሚያቀጣጥሉት እና ጥይት የሚተኩሱት እንዲሁም የሚያስተክሱትን ለይቶ ለመያዝ አስቸግሮ ነው? ህዝቡ ማን ከማን የሚለይ ስለሆነ ከህዝባ ጋር ቢሰራ ጥሩ ነው፡፡

    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

  3. ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ሆነን እንዴት እንደዚህ አይነት የክፋት ነገር እናስተላልፋለን? አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ሱማሌ፣ ወዘተ… ሁላችንም አንድ ነን፡፡ እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ሰላም፣ እድገት እና አንድነት የማይወደውን ጠላት ዲያብሎስን ይምታልን!!

Comments are closed.

Share