የደቡብ ክልል ምክር ቤት የሲዳማን ክልል ጥያቄ ተቀብሎ ረፈረንደም እንዲካሄድ ወሰነ

ለቀናት ጉባኤውን በሃዋሳ ሲያካሂድ የቆየው የደቡብ ክልል ምክር ቤት የየሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ሂደቱን ተከትሎ እንዲፈጸም ወሰነ።

የሲዳማ ሕዝብ የሀገሪቷ 10ኛ ክልል በመሆን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንዲቋቋም ላለፉት 27 ዓመታት ሲታገል መቆየቱን የሚገልጹ የሲዳማ ተወላጆች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ::

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የሲዳማን ክልል የመሆን ጥያቄ ጉዳይ በዛሬው ውሎው 8ኛው አጀንዳ አድርጎ በዝግ እንደመከረበት የደረሰን መረጃ ጠቆሟል:: በመጨረሻም የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ሂደቱን ተከትሎ እንዲፈጸም ውሳኔ አሳልፏል።

የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ከዚህ ቀደም የዞኑን ክልል የመሆን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መደገፉን ዘ-ሐበሻ ዘግቦ ነበር:: በዚህም መሰረት የዞኑ ምክር ቤት መደገፉን ተከትሎ ጥያቄው ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ ምክር ቤቱም በጥያቄው ላይ በዝግ ከመከረ በኋላ፥ የቀረበው ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ሂደቱን ተከትሎ እንዲፈጸም ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል::

ሲዳማ ክልል እንዲሆን ጥያቄ በማቅረብባቸው በርካታ ሰዎች ላለፉት 27 ዓመታት ሲታሰሩ; የአካል ጉዳት ሲደርሰባቸው እና ሌሎችም የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲደርስባቸው መቆየቱን የሚያስታወሱ አስተያየት ሰጪዎች ሲዳማ 10ኛው ክልል ከሆነ መታሰቢያነቱ ለነዚህ ወገኖች መሆን አለበት ይላሉ::

በሌላ በኩል ሲዳማ ክልል ከሆነ የአዋሳ ከተማ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አነጋጋሪነቱን መቀጠሉን ከሚሰጡ አስተያየቶች ለመረዳት ተችሏል::

https://www.youtube.com/watch?v=_2J0KB91Nvc

ተጨማሪ ያንብቡ:  በስጋትና በግራ መጋባት መካከል የሚገኙት ኢትዮጵያዉያን በዩክሬይን

4 Comments

 1. አስገራሚ ዜና ነው፡፡ ለመሆኑ አንድ ክልል አብሮት የነበረውን አንድ ዞን አብሬ አልኖርም ሲል በቀጥታ ክልል መሆን ትችላለህ ይህንን ግን በህዝበ ውሳኔ አስወስን ብሎ ለመወሰን ማን ስልጣን ሰጠው፡፡ ክልሎች በፌዴሬሽንና ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚቋቋሙ እንጂ አንድ የክልል ም/ቤት ስለክልል መቋቋም ምን አገባው፡፡ ክልሎች ከራሳቸው እኩል የሆነ አስተዳደር ሳይሆን መቋቋም የሚችሉት ከነሱ በታች የሆነ ዞን —የመሳሰሉትን ነው፡፡ ብች የልጅ ጨዋታ ይመስል እከሌ የሚባለው ዞን የክልል ጥያቄ ስላቀረበ ፈቅጄለታለሁ ብሎ አንድ ክልል መወሰን ፍጹም አይችልም፡፡ ክልል ለመሆን ከማንነት የዘለለ ስታንዳርድ ያለሌን መሆኑ አስተዛዛቢ ነው፡፡
  ሌላው የክልሉ ም/ቤት ም/አፈ ጉባኤ በኢቢሲ መስኮት ውሳኔው በተሰጠበት እለት ብቅ ብለው “የሲዳማ ብሄረሰብ የክልል ጥያቄ አቅርቧል ሂደት ጠብቆ እንዲፈጸም ፈቅደናል” ሲሉ ዞኑን በክልሉ ለሚኖሩ ዜጎች በሙሉ ሳይሆን ለአንድ ብሄረሰብ መስጠታቸው ሌላው አስተዛዛቢ ውሳኔ ነው፡፡ ዞኖች/ክልሎችም የሁላችንም ባለቤት እንዳልሆንን እኚህ ሰው አረጋገጡልን፡፡ ገራሚ አመራር፡፡
  በቀጣይ ይህ ውሳኔ በደቡብ ክልል ውስጥ ይዞት የሚመጣውን ውጥንቅጥ ወደፊት እናየዋለን፡፡ መዘዙ ብዙ ነው

 2. አስገራሚ ዜና ነው፡፡ ለመሆኑ አንድ ክልል አብሮት የነበረ አንድ ዞን አብሬህ አልኖርም ሲል በቀጥታ ክልል መሆን ትችላለህ ይህንን ግን በህዝበ ውሳኔ አስወስን ብሎ ለመወሰን ማን ስልጣን ሰጠው፡፡ ክልሎች በፌዴሬሽንና ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚቋቋሙ እንጂ አንድ የክልል ም/ቤት ስለክልል መቋቋም ምን አገባው፡፡ ክልሎች ከራሳቸው እኩል የሆነ አስተዳደር ሳይሆን መቋቋም የሚችሉት ከነሱ በታች የሆነ ዞን —የመሳሰሉትን ነው፡፡ ብቻ የልጅ ጨዋታ ይመስል እከሌ የሚባለው ዞን የክልል ጥያቄ ስላቀረበ ፈቅጄለታለሁ ብሎ አንድ ክልል መወሰን ፍጹም አይችልም፡፡ ክልል ለመሆን ከማንነት የዘለለ ስታንዳርድ ያለሌን መሆኑ አስተዛዛቢ ነው፡፡ የፌዴራሉ መንግስት ህግ መንግስት አንቀጽ 39 የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል ቢፈቅድም አንድ ክልል ተነስቶ ከኢትዮጵያ እገነጠላለሁ ቢል ለሚገነጠለው ክልል የአገርነት ስታተስ ኢትዮጵያ የመስጠት ስልጣን የላትም፡፡ ይህን የመወሰን ስልጣን ያላቸው ሌሎች መንግስታትና የተባበሩት መንገስታት አገር ለመሆን ያሟላ መሆኑን አይተው እውቅና ሊሰጡት ወይም ሊነፍጉት ይችላሉ፡፡ የሰሜን ሶማሊያ መገንጠል አገር የመሆን እውቅናን እስከአሁን አላስገኘላትም፡፡
  በፌዴራሉም ሆነ በክልል መንገስታት የተከተቡት ህገ-መንግስት ድርሳን ስለመገንጠል ያወራሉ እንጂ ዞኖችን ክልል ስለማድረግ፣ ወይም ከፌዴራሉ ተገንጥለው አገር ይሆናሉ የሚል መደምደሚያ የላቸውም፡፡ ታዲያ ደቡበ ክ/መንግስት ከየት አምጥቶ ነው ክልል የመሆን ጥያቄ ተቀብዬለሁ የሚለው፡፡ ከክልሉ የመገንጠል ጥያቄን እንጂ ክልል የመሆን መብትን ክልሎች የመፍቀድ፣ የመስጠት፣ የማስፈጸም ስልጣን የላቸውም፡፡ ደቡቦች የተጻፈ ህግ አለን ቢሉ እንኳን ከፌዴራሉ ህገ-መንግስት ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ውድቅ ነው፡፡ ምክንያቱም ክልልን ሌላ ክልል የማቋቋም ስልጣን የለውምና፡፡ መልሳችሁን እንጠብቃለን፡፡
  ሌላው የክልሉ ም/ቤት ም/አፈ ጉባኤ በኢቢሲ መስኮት ውሳኔው በተሰጠበት እለት ብቅ ብለው “የሲዳማ ብሄረሰብ የክልል ጥያቄ አቅርቧል ሂደት ጠብቆ እንዲፈጸም ፈቅደናል” ሲሉ ዞኑን በክልሉ ለሚኖሩ ዜጎች በሙሉ ሳይሆን ለአንድ ብሄረሰብ መስጠታቸው ሌላው አስተዛዛቢ ውሳኔ ነው፡፡ ዞኖች/ክልሎችም የሁላችንም ባለቤት እንዳልሆንን እኚህ ሰው አረጋገጡልን፡፡ ገራሚ አመራር፡፡
  በቀጣይ ይህ ውሳኔ በደቡብ ክልል ውስጥ ይዞት የሚመጣውን ውጥንቅጥ ወደፊት እናየዋለን፡፡ መዘዙ ብዙ ነው

 3. የሲዳማ ብሔር የክልልነት ጥያቄ በክልሉ ም/ቤት ተቀባይነት አግኝቶ ወደ ህዝቤ ዉሳኔ ይደረግበት አቅጣጫ ከክልሉ ህገ መንግስት አንፃር ጥሰት የለበትም፡፡ ባይሆን ሌሎችም ብሔሮች በየዞኖቻቸዉ ም/ቤት የየራሳቸዉን የክልል ምስረታ ጥያቄ እያፀደቁ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ ሲዳማ ክልል ሲሆን ሲዳማ ብቻ ሳይሆን ከ10 የማያንሱ ተጨማሪ ክልሎች መፈጠራቸዉ የማይቀር ጉዳይ ስለሆነ ነዉ፡፡ ካፋ ክልል፤ወላይታ ክልል፤ ጉራጌ ክልል፤ ሃዲያ ክልል ወ.ዘ.ተ እያለ ይቀጥላል፡፡

 4. በፌዴራሉም ሆነ በክልል መንገስታት የተከተቡት ህገ-መንግስት ድርሳናት ስለመገንጠል ያናገራሉ እንጂ ዞኖችን ክልል ስለማድረግ፣ ወይም ከፌዴራሉ ተገንጥለው አገር ይሆናሉ የሚል መደምደሚያ የላቸውም፡፡ ታዲያ የደቡበ ክ/መንግስት ከየት አምጥቶ ነው ክልል የመሆን ጥያቄ ተቀብዬለሁ የሚለው፡፡ አልቀበልም ማለት አይችልም፣ ምክንያቱም የሱ ሃላፊነት አይደለምና፡፡ ከክልሉ የመገንጠል ጥያቄን( በብሄር የተቧደነ ዞንም፣ ወረዳም፣ ቀበሌም ሊሂን ይችላል) እንጂ ክልል የመሆን መብትን ክልሎች የመፍቀድ፣ የመስጠት፣ የማስፈጸም ስልጣን ክልሎች የላቸውም፡፡ ደቡቦች የተጻፈ ህግ አለን ቢሉ እንኳን ከፌዴራሉ ህገ-መንግስት ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ውድቅ ነው፡፡ ምክንያቱም ክልልን ሌላ ክልል የማቋቋም ስልጣን የለውምና፡፡ አንድ ዞን ከክልል ተገንጥሎ ሲሻው ክልል፣ ሲፈልግ ወደ ሌላ ክልል ወይም ሌላ ጎረቤት አገር የመሄድ በኋላ በተገቢው አካል የሚወሰን እንጂ ክልል ስለጠየክ፤ ፊርማ ስለሰበሰብክ፣ ጥያቄህ አግባብ ነው ብሎ ውሳኔ ላይ መድረስ አንድም ህጋዊ መሰረት የለውም፡፡ መልሳችሁን እንጠብቃለን፡፡

  ሌላው የክልሉ ም/ቤት ም/አፈ ጉባኤ በኢቢሲ መስኮት ውሳኔው በተሰጠበት እለት ብቅ ብለው “የሲዳማ ብሄረሰብ የክልል ጥያቄ አቅርቧል ሂደት ጠብቆ እንዲፈጸም ፈቅደናል” ሲሉ የሲዳማን ዞን አስተዳደር በሲዳማ ዞን ውስጥ ለሚኖሩ ዜጎች በሙሉ ሳይሆን ለአንድ ብሄረሰብ መስጠታቸው ሌላው አስተዛዛቢ ውሳኔ ነው፡፡ ዞኖች/ክልሎችም የሁላችንም ባለቤት እንዳልሆንን እኚህ ሰው አረጋገጡልን፡፡ ገራሚ አመራር፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያዊነትን እየዘመሩ ያሉ ድንቅ መሪዎቻችንን ወደ ኋላ የሚጎትት፣ ከቀድሞው ጎጠኛ አመለካከት ያለወጣ አግላይ አመለካከት መሪ በሚባሉ ሰው መነገሩ፣ ምናልባትም አደናቃፊነት፣ ወይንም ለውጡ ወደታችኛው የአስተዳደር እርከን በሚገባው ደረጃ አለመውረዱን ማሳያ ነው፡፡ እከሌ ዞን የእከሌ ብሄረሰብ ነው የማለት አጥፊ አመለካከት፡፡ ለማንኛውም ይህ የክልሉ ውሳኔ ህገመንግስታዊ አካሄድ ሰለመሆኑ እንጂ ሲዳማ ለምን ክልል ይሆናል የሚል ደፍጣጭ ሃሳብ አለመሆኑን ልትረዱልኝ ይገባል፡፡ ሲዳማ ባለው ህገ-መንግሳታዊ ፌዴራል አወቃቀር መነሻነት ከተመዘነ ክልል መሆን መብቱ ነው፡፡ ይህ ማለት ብሄረሰባዊ የፌዴራል አወቃቀርን አደግፋለሁ ማለት አይደለም፡፡ ብዙ አማራጮች ስላሉን በጋራ መርጠን እና ተስማምተን ወደፊት የምንደርስበት ውሳኔ ይሆናል፡፡

Comments are closed.

Share