ኦዴፓ እና ኦነግ ካድሬዎቻቸውን እንዲያሳርፉ ተጠየቁ

በምዕራብ ኦሮሚያ በኦነግ ሸኔ እና በመንግስት መካከል ያለው ውጥረት ባልረገበበት ሁኔታ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር ኦዴፓ እና ኦነግ ካድሬዎቻቸውን ሊያረጋጉ እንደሚገባ ጥሪ አቀረበ::

በተለይ በደምቦዶሎ ለሰው ሕይወት ማስከፈል ምክንያት የሆነው ችግር የተፈጠረው በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ባለው የካድሬዎች ፉክክር የተነሳ ነው የሚለው ጀዋር በምዕራብ ኦሮሚያ ያለው ችግር ሊፈታ የሚችለው በመሪዎች ንግግር እንጂ በካድሬዎች ሊሆን እንደማይገባው መክሯል::

በኦዴፓና በኦነግ መካከል የመሪዎች ውይይት አድርጎ ወደ መፍትሄው መሄድ የሚሻል ነው የሚለው ጀዋር የሁለቱም ድርጅቶች ካድሬዎች በም ዕራብ ኦሮሚያ ያለውን ውጥረት እንዳባበሱት ገልጿል:: “ውይይት ተደርጎ መፍትሄውን በቶሎ ማየት እንፈልጋለን:: መሪዎቹ በራቸውን ዘግተው በቶሎ መወያየት ይኖርባቸዋል:: በ” ያለው ጀዋር ውይይቱ በቶሎ እስከሚጀመር ድረስ ድርጅቶቹ ነገር አባባሽ ያላቸውን ካድሬዎቻቸውን እንዲያስቆሙ; ሕዝብ እንዲረጋጋና ከውሸት ዜናዎች ራሱን እንዲያርቅና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪውን አቅርቧል::

ሌሎች አክቲቭስቶች “ኦሮሚያ ውስጥ ይህን ለውጥ ለማምጣት ከበቂ በላይ የቄሮ ደም ፈሷል:: ከዚህ በኋላ የኦሮሞ ሕዝብ የሚፈልገው በሰላም በመኖር ራሱን መለወጥ ብቻ በመሆኑ የለማ መገርሳ አስተዳደር በኦነግ ሸኔ ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ ይገባል” ይላሉ::

የኦነግ ሸኔ መሪ ዳኡድ ኢብሳ መሳሪያ የሚፈታም አስፈቺም የለም ማለታቸውን ተከትሎ በተለይ በአሁኑ ወቅት በምዕራብ ወለጋ እስካሁን በአለባበስም በጦር መሳሪያም የተለየ ራሱን የኦነግ ሠራዊት ነኝ ያለ ሠራዊት እየተንቀሳቀሰ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑ ይታወቃል:: ዶ/ር አብይም ፍራንክፈርት ላይ “አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ መሳሪያ ይዞ ወደ ሀገር ቤት አልገባም:: የኦነግ ሰራዊትም መሳሪያ ፈትቶ በአምባሻና በውሃ ነው የተቀበልነው” ማለታቸው ይታወሳል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጣሊያን ፖሊስ ስደተኞችን ሲቀጠቅጥ የሚያሳይ ቪድዮ (ኢትዮጵያውያንም አሉበት)

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዳኡድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ሸኔ የሚያንቀሳቅሰው ኦኤንኤን የተባለው ቴሌቭዥን ጣቢያ የሕወሓት አጀንዳ የሆነውን የአማራን ሕዝብ የመከፋፈል ፕሮግራሙን ቀጥሎ የተለያዩ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን እየሰራ በመበተን ላይ ይገኛል::
https://www.youtube.com/watch?v=_2J0KB91Nvc

1 Comment

  1. ሳቅቼ ሞትኩኝ አለች ሴትየዋ! ድርም ለስልጣን ወንበር ነው የሚራወጡት፡፡ ኦሮሞን ነጻ እናወጣለን እያሉ ህዝቡን ያላግጡበታል፡፡ እነሱ ተቧቅሰው ይዋጣላቸው፡፡ ማፈሪያዎች!

Comments are closed.

Share