አብዲ ኢሌ ለዶ/ር አብይ አህመድ ደብዳቤ ጻፉ | ስህተቴን አርሜ የለውጡ ቸርኬ ሆኜ ላገለግልህ ቃል እገባለሁ ብለዋል

በበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋትና ንብረት ማውደም ተጠርጥረው የታሰሩት የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ኢሌ ለዶ/ር አብይ አህመድ ደብዳቤ ጻፉ::

በታሰሩበት የመጀመሪያ ወራት በአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ አንደኛ ፎቅ ላይ የፖሊስ ቢሮ ተለቆላቸው ታስረው የነበሩት አብዲ ኢሌ ከቤተሰብ ጋር በየቀኑ ይገናኙ; ከባለቤታቸው ጋርም አብረው ያመጡላቸውን ምግብ በጋራ እንዲበሉ ተፈቅዶላቸው የነበረ ሲሆን ከ እስር ቤት ለማምለጥ ሞክረዋል በሚል ከቭ ኤይ ፒ እስር ቤት ወደ ሌሎች እስረኞች ወደሚገኙበት ክፍል መዘዋወራቸውን ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም ዘግቦ ነበር::

አብዲ ኢሌ ሌላው እየተደመረ እኔ ብቻ እስር ቤት የምወረወርበት ምክንያት አልገባኝም በሚል ለዶ/ር አብይ አህመድ ከ እስር ቤት በጻፉት ደብዳቤ “በማስተዳድረው ክልል የሰው ህይወት እንዳይጠፋ እና ንብረት እንዳይወድም አንተ ) የሰጠኸኝን ምክር እና ሀሳብ ችላ ብያለሁ።” ሲሉ ተናዘዋል:: ደብዳቤያቸውን ቀጥለውም ” በክልሉ እንደገናም ችግሩ ከተከሰተ በኋላም ሳትተወኝ የሰጠኸኝን ጥሩ ሀሳብ ባለመቀበሌ የለውጡ እንቅፋት ነበርኩ። ለዚህም ከልቤ ተፀፅቻለሁ።” ብለዋል አቶ አብዲ::

“አሁንም ቢሆን በደህናው ጊዜ የመከርከኝን እንዲሁም የገባህልኝን ቃልህን እንደማታጥፍ እና ፊትህን እንደማታዞርብኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ” ያሉት አብዲ ኢሌ “ከመጀመርያ ጀምሮ አመጣጥህንና እያመጣህ ያለውን አመርቂ ለውጥ በጣም አደንቃለሁ። እኔም ስህተቴን አርሜ ከህዝብ እና መንግስት ጋር በመሆን የለውጡ ቸርኬ ሆኜ እሰራለሁ።” ብለዋል በደብዳቤያቸው ሲል የኤፒ ጋዜጠኛ ኤሊያስ መሰረት ገልጿል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ አብዲ ኢሌ ከመታሰሩ በፊት ዶ/ር አብይ አህመድ በክልሉ ሰላም ለማምጣት አግባብተዋቸው እንደነበርና ስልጣናቸውን በሰላም አስረክበው ክልሉን ከብጥብጥ የሚታደጉ ከሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ እንደሚያደርጓቸው ቃል ገብተውላቸው የነበረ ቢሆንም አብዲ ኢሌ አሻፈረኝ በሚል የራሳቸውን መንገድ እንደመረጡ ዘግየት ብለን ሰምተናል::
https://www.youtube.com/watch?v=_2J0KB91Nvc

ተጨማሪ ያንብቡ:  የድምጻችን ይሰማ የኮሚቴ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ
Share