ሌባ ተይዞ ዱላ ይጠየቃል? በሆላንድ – ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ጥቅምት 2006

በአሥራ አምስተኛው ምዕተ-ዓመት ግድም ሆላንድ የታወቀ የባሕር ኃይል ሆኖ ከደቡብ አፍሪካ እስከደቡብ አሜሪካ፣ የኔዘርላንድ የቆዳ ስፋት 41 526 ኪሜ ካሬ ወይም የትግራይ ግማሽ ነው፤ የሕዝቡም ቁጥር አሥራ ስድስት ሚልዮን ተኩል አይሞላም፤ የትግራይን ግማሽ በሚሆን መሬት ላይ የትግራይን ሦስት እጥፍ ግድም የሚያህሉ ሰዎች ይኖሩበታል፤ ሆኖም ጥንት ከደቡብ አፍሪካ እሰከደቡብ አሜሪካ፣ በእስያም ኢንዶኒዝያ ላይ የቅኝ ግዛት የዘረጋ ትንሽ አገር ነበር፤ አሁንም ትንሽ አገር ነው፤ አሁንም ሀብታም አገር ነው፤ ዋናው ሀብቱ ሕዝቡ ነው፤ አሥራ አምስት ሚልዮን ግድም የሚሆን ሕዝብ ከባሕር ጋር እየታገለ ያገኘውን መሬት ይዞ እንዲህ ያለ ሀብታም መሆኑን ሳይ እኛ በጣም ሰፊ መሬትና ስድስት ጊዜ ያህል ከኔዘርላንድ የሚበዛ ሕዝብ እያለን ቆሞ-ቀር ብቻ ሳይሆን ወደኋላ መገስገሳችን ሳይሻክረኝ አልቀረም።

ኔዘርላንድ በከፊል በባሕር ተሸፍኖ የነበረ ነው፤ በሰው ኃይልና በሰው ጥበብ ባሕሩ ተገፍቶና ተገድቦ መሬቱ ለጥቅም እንዲውል ተደርጓል፤ በዓለም ውስጥ እንደኔዘርላንድ ከባሕር ጋር ታግሎ ያሸነፈና ከባሕር ጠለል በታች የነበረውንና ረግረጉን መሬት ለጥቅም ያዋለ አገር የለም፤ በተለይ የሰሜኑ ክፍል ከባሕር የወጣ መሬት ነው።

በኔዘርላንድ ገጠርና ከተማ እየገጠሙ ናቸው፤ በየመንገዱ ላይ እርሻ፣ ላሞችና በጎች፣ አንዲሁም ፈረሶች ሲግጡ ይታያሉ፤ እዚህ ከባሕር ጋር እየታገሉ ባወጡት መሬት ላይ ቤታቸውንም ሆነ እርሻቸውን በፈለጉት ሁኔታ መጠቀም ይችላሉ።

ኔዘርላንድ በዴሞክራሲያዊ የዘውድ መንግሥት የሚተዳደር አገር ነው፤ በቅርቡ የኔዘርላንድ ንግሥት ዕድሜያቸው ስለገፋ ዘውዱን ለልጃቸው አስረክበው እሳቸው በክብር እቤታቸው ወይም እግቢያቸው ውለዋል፤ በኔዘርላንድ የመብት ጉዳይ ዋና ሥፍራን የሚይዝ ነው፤ በአምስተርዳም ከተማ ከሚኖር ከአንድ ወዳጄ ጋር ስንጫዋወት በኢትዮጵያ አንገብጋቢ ጉዳይ ስለሆነው ስለፍትሕ ጉዳይ አነሣሁ፤ በዚሁ ላይ እንዳለን አንድ ታሪክ ነገረኝ፤ በዚሁ አገር አንድ ቤተሰብ አገር ሰላም ብለው ተኝተዋል፤ ድንገት ስልክ ይደወልና የቤት እመቤቲቱ ስልኩን ለመመለስ ወደሳሎን ስትገባ የሳሎኑ በር ተከፍቶ ታያለች፤ ሁኔታው ቀፈፋትና ዘወር ስትል አንድ ጎረቤት የሆነ ሰው የእስዋን ቴሌቪዥን ይዞ እንደቆመ ዓይን ለዓይን ይጋጠማሉ፤ እየተርበደበደች ለፖሊስ ስልክ ስትደውል ጎረቤትዋ ቴሌቪዥኑን እንደያዘ ከሴትዋ ቤት ወጥቶ ወደራሱ ቤት ይገባና በሩን ቆልፎ መብራቱን አጥፍቶ ይቀመጣል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር የረታ ‹‹ይቅርታ!››

የተጠሩት ፖሊሶች ይመጣሉ፤ ሴቲቱ የደረሰባትን ትናገርና የ‹‹ሌባው››ን ቤት እያሳየች አሁን ብትገቡ ቴሌቪዥኔን ታገኛላችሁ ትላቸዋች፤ አስቲ ቴሌቪዥኑን የገዛሽበትን ደረሰኝ አሳዪን ይላሉ፤ ደረሰኝ የላትም፤ የቴሌቪዥኑን መለያ ቁጥር ይጠይቃሉ፤ ያንንም አታውቀውም፤ ፖሊሶቹ ግራ ተጋብተው ታዲያ ሰውዬውን ከመኝታው አስነሥተንና በሩን አስከፍተን ምን አድርግ ልንለው ነው፤ እዚያ ቤት ውስጥ ያለው ቴሌቪዥን የአንቺ ለመሆኑ ምንም ማስረጃ ስለሌለሽ ሰውዬውን አናሸብረውም ብለዋት ሄዱ! ይህ ትምህርት ይሆነዋል፤ ይገባዋል፤ ለምትሉት ሰው፣ በተለይ ሕግ አስከባሪ ነው ለምትሉት ንገሩ!

በዚህ ታሪክ ስደነቅ ሌላ አስደናቂ ታሪክ ነገረኝ፤ አንድ ወሮ-በላ ቢጤ አንድ ቤት ውስጥ በቀዳዳ ገብቶ ተኝቶአል፤ የቤቱ እመቤት ልታስወጣው ብትሞክር አልቻለችም፤ ቢቸግራት ለባልዋ ትነግራለች፤ አበሻ ባልዋ ይሄድና ሰውዬውን አስወጥቶ ሁለተኛ እዚህ ብትመጣ እጅህን እቆርጠዋለሁ፤ ይለዋል፤ከጥቂት ጊዜ በኋላ ባለቤቱ የቤቱን በር ደወል ሰምቶ ሲከፍት ፖሊሶች ያያል፤ ከፖሊሶቹ ጋር ቀደም ሲል እጅህን እቆርጠዋለሁ የተባለው ሰው ቆሞአል፤ ፖሊሶቹ እጅህን እቆርጥሃለሁ ያለው እሱ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ሰውዬው በዛቻው እንደተጨነቀና የዚህም ጭንቀት ምክንያት አንተ ነህ፤ ሰውዬውን አስሸበርከው! በማለት ማስፈራራቱ ማሰቃየት እንደሆነ አስረድተው እንዳይደግምህ ይሉትና ለመሆኑ ከየት ነው የመጣኸው ብለው ይጠይቁታል፤ ከአፍሪካ ሲላቸው አፍሪካ ሂድና እጅ እቆርጣለሁ እያልህ አስፈራራ፤ እዚህ ግን እንዲህ ማለት አይቻልም፤ ብለውት ይሄዳሉ፤ መለስ ዜናዊ ጣታችሁን እንቆርጣለን፤ እጃችሁን እንቆርጣለን፤ እያለ በሕዝብ ምክር ቤት ሲናገር ሁላችንም ሰምተናል፤ እሱ አሸባሪ ሳይባል እኛም ተሸበርን ብለን የምንጮህበት ሳናገኝ ተላልፈናል።

በኔዘርላንድ አንዳንድ ቦግ ብለው የሚታዩ ነገሮች አሉ፤ ለምሳሌ መንገዶቻቸው በጣም ግሩም ናቸው፤ ለቢስክሌት ልዩና ራሱን የቻለ መንገድ አላቸው፤ በኔዘርላንድ የባህል ጭቆና የሚባል ነገር የለም፤ እንዲያውም የባህል ጭቆናን የሚሽር ባህል እየገነቡ ናቸው ለማለት ይቻላል፤ እኛ የባህል ባሪያዎች ሆነን እንኖራለን፤ ብዙ ኢትዮጵያውያን ባይስማሙበትም የመክሸፋችን ዋና ምክንያት ተጨቁነን ጭቆናን አክባሪዎች መሆናችን ነው፤ የችግራችን ሁሉ መሠረት ይህ ክፉ ባህል ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአድዋ ድልና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን

2 Comments

  1. Professor Mesfin, Is it an obligation for you to write? What you wrote is silly. Are you living in your dreams? Do you think The Netherlands is better than Ethiopia (and you were surprised about it) because its policemen do not accept claim of ownership without papers proving the claim. Do you think you are living in the wildwest in Ethiopia? You can criticize the government as much as you like (because they allowed you to do so; no sacrifices!), but how can you ever think that an Ethiopian policeman would go to somebody’s house in the middle of the night, take his property, and give it to a claimant who does not have a shred of evidence to prove that it is his property? Can you say to anyone in Ethiopia “I will cut off your hands” and go away with it?

    Why did you use Tigray for comparison? If your message is the Ethiopian people then use the size of Ethiopia for the purpose. You seem to have a problem with that Region. May be they overthrew your friend Colonel Mengistu! I was admiring the way you write long before; but I am getting lost about you from the way you are putting ink on paper.

Comments are closed.

Share