October 20, 2013
7 mins read

የሕወሐት ኢሕአዴግ መንግስት በልጆቼ ለምን ዘመተ? (ከኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል)

ሁለተኛ ልጄ ክብሮም እንደ ወንድሞቹ የእስር ሰለባ ሆነ፡፡እኔ ለኢትዮፕያ ህዝብ ጠላት ሳልሆን ፍፁም ወዳጁ ነኝ መጀመርያ ደርግን 17 ኣመት በመታገል ፋሽሽታዊ ደርግ በማስውግድ ኣስተዋፅኦ ነበረኝ፡፡ ህውሃት ኢህኣደግ ስልጣን ከያዘ በሃላም ለንሮየ ለደሞወዝ ሳላስብ 17 ኣመት ሙሉ የታገልኩበት ኣላማ ስለተቀለበሰ በተጨማሪ የህውሓት መሪዎች ለኢቲዮፕያ ሉኣላዊነትና ኣንድነት ታማኝነት ስላጎደሉ የኢትዮፕያ ሕገመንግስት በሚፈቅደው መሰረት በግልም በፓርቲ ተደራጅቼ እየታገልኩ ቆይቼ ኣሁንም እታገላለው ታድያ እኔ በሃገራችን ሕ/መንግስት በሚፈቅድልኝ መሰረት መታገሌ እንደ ሃጠያት ተቆጥሮ የቂም በቀል ፖለቲካ ወደ ልጆቼ ምን ኣመጣው ይህ ለማለት የፈለጉኩት፡፡

1.የማነ ኣስገደ ልጄ ምንም ሳይፈፅም በገጠር ቤተሰብ ለመጠየቅ ሄዶ ታስሮ ብዙ ግፍ ተፈፅሞበታል በተፈፀመበት ግፍ ጠንቅ ታሞ እናቱ የመከላክያ ኣባል ስለሆነች በመከላክያ ሚኒስተር ሆስፒታል ብዙ ጥረት ተደርጎ ሊያድኑት ስላልቻሉ ወደ መቀሌ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከስልጣን በላይ ብለዉት ሂወቱ ተርፎ ኣሁንም በቤቱ ታሞ የኣልጋ ቁራኛ ሆኖ ይገኛል፡፡ በተማረው መሰረት ለሃገሩ እንዳያገለግልም እንደማይሰራ ኣካል ጉዳተኛ ኣድርገዉታል ወደ ውጪ ወስድን እንዳናሳክመው ኣቅም የለም፡፡

2.ኣሕፈሮም ኣስገደ ልጄም ከስራ ገብታው ኣፍነው ወስደው ታስሮ በፖሊስ ጣብያ 6 ወር ታስሮ ክስ ሳይመሰረትበት በቀዳማይ ወያኔ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት ከ 15 ጊዜ በላይ ቀጠሮ ጊዜ እየተባለ ሲመላለስ ከርሞ በመጨረሻ ክሱ የዋስ መብት የሚከልክለው የፀረ ሙስና ኣንቀፅ በሙስና የተከሰሰ የዋስ መብት ኣይፈቅድም የሚል ሽፋን ልጄን ከእሱር ላለማውጣት ክሱ ወደ ፀረ ሙስና ኮሚሽን በማዞር የፀረ ሙስና ጉዳይ ደግሞ በወረዳ ስለማይታይ 6 ወር ሙሉ ሲያንገላቱት ከርመው ክሱ በመቀሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደ ኣዲስ ተመስርቶ በ 28/1/2006 ዓ.ም በዞኑ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ደግሞ ሌላ ተጠርጣሪ ስላለና ስለታጣ በጋዜጣ ኣሳውጀን እስከ ምንፈልግ ኣሕፈሮም በወህኒ ቤት ይግባ በማለቱ ልጄ ያለ ፍርድ በወህኒ ቤት ተወርውሮ ይገኛል የጊዜ ቀጠሮ እየተባለ 7 ወሩ በስቃይ ይገኛል፡፡

3. ሌላ ያሁኑ ይባስ ክብሮም ኣስገደ የሚባል የ 10ኛ ክፍል ተማሪ የስብእና መሳት ስነ ኣእምሮ ችግር ያለው ይህም በሃኪም ክትትል ላይ ያለ በፍርድ ቤትም ታይቶ ያደረ በካስ ሜዳ እየተጫወተ እያለ ፖሊሶች ይዘው በእስርቤት ኣግብተው በኣንድ ጨለማ ቤት ለብቻው ኣስረው ከወላጆቹ ከሃይማኖት ኣባት ከህግ ኣማካሪ እንዳይገናኝ ኣድርገው ኣፍነዉት ይገኛሉ የምንሰጠው ምግብ ለማን እንደሚሰጥ ኣናውቅም ለፍትህ ቢሮ ፖሊስ ኣዛዞች ኣመለከትን ፍትህ ኣልተገኘም ዳኛ እንድያገናኙን በስልክ ነግሮዋቸው ፖሊሶች ኣልተቀበሉትም ኣሁን 80 ሰኣት በላይ ታስሮ ቤተሰብ ልናገኘው ኣልቻልንም ይህ ዘመቻ በእኔ የጀመረው ልጆቼም የግፍ ሰለባ ሆነዋል የኔ ጉዳይም የህውሓት የ17 ኣመት ታሪክ በመፃፌ ከኣንድ ዜግነቱ ኣሜሪካዊ ትውልድ ኢትዮፕያዊ በሰዎች የተቀናበረ ሴራ ተከስሼ 3 ኣመት ባስቆጠረ ክስ ላይ ነኝ ገና መቃጫ ኣላገኘም፡፡

ይህ ጉዳይ የእኔና የልጆቼ ብቻ ችችግር ኣይደለም ብዙ የሚናገርላቸው ያጡ ዜጎች በስቃይ ላይ ይገኛሉ ስለሆነ ሁሉም ዜጎችና ለፍትህና ለዲሞክራሲ ለሰብኣዊ መብት የምትታገሉ ያላችሁ ተቃዋሚ ሃይሎችም ዝምታ ከመምረጥ ብትነጋገሩበትና ብትቃወሙት ጥሪየን ኣቀርባለው፡፡

በተለይ በኣሁኑ ጊዜ ኣንድ ኣንድ የፖሊስ ከፍተኛ መኮነኖች በታሰረው ልጄ ኣሕፈሮም ኣስገደ ከታሰረበት የእስር ቦታ ሄደው ኣባትህ ኣስገደ ተው ኣርፈህ ተቀመጥ ትእግስት ኣድርግ እስከማለት ሄደዋል ለዚሁ አንደ ምሳሌ ኮማንደር ገ/ሂወት ካሕሳይ የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ዋና ኣዛዠ ይጠቀሳል በዛ በሰጠው ማስፈራርያ ታድያ ልጄ ኣሕፈሮም በትልቅ ስጋት ላይ ይገኛል ታድያ ከዝሂች ኣገር ኣገሬ የት ልሂድ ንፁህ ዜጋ ነኝ እና በዚህች ኣገር የዳኝነት እና የህግ የበላይነት መረጋገጥ ኣለበት ወተደራዊ ኣገዛዝ እንዳይደገም እንጠንቀቅ ፡፡

እባካችሁ የቂም በቀል ፖለቲካ ለልጆቻችን ኣናውርሳቸው ሰላም ፍትህን ዲሞክራሲን እናውርሳቸው፡፡

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop