October 19, 2013
34 mins read

ያለም አቀፉ ወጀል ፍርድ ቤት ምስክር

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

የስሱ ብርጌድ የደቦ ፍርጠጣ ጥረት

የአፍሪካ አንድነት (እኔ ለማስረዳት የተገደድኩበት አሳፋሪው ከሮም ስምምነት ፍርጠጣ) ‹‹የደቦ የማስፈራራት ሕብረት›› ከሸፈ፡፡ ‹‹አሰቸኳዩ  ልዩ ስብሰባ›› ‹‹አ አ ከዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ችሎት ጋር ያለው ግንኙነትያከትማል ብለው ያሰቡትና ሴራውን የፈተሉት ባለስላጣናት፤ ‹‹ከተባበሩት መንግስታት የፀፅታ ካውንስል ጋር ውይይት ለማድረግ በሚል እሳቤ በኬንያው ፕሬዜዳንትና  ምክትል ፕሬዜዳንት  እንዲሁም በሱዳኑ ፕሬዜዳንት ላይ የተመሰረተውን  ክስ በተመለከተ አፍሪካ አንድነት ልዩነት አለው፤ የሮም ስምምነት አንቀጽ 16 እነሱን ተጠያቂ ሊያደርጋቸው ኣይገባም ምህረት ያድርግላቸው አይነት ውሳኔ  ይዞ  መጠናቀቁ አስገርሟቸዋል፡፡ እንደፈራሁትም ኦክቶበር 11-12  2013  ስብሰባም አሳፋሪ ሆኖ በታሪክአይኖርም፡፡ 34ቱን የሮም ስምምነትን የፈረሙትና የአፍሪካ ሃገራት አሳምኖ የፍርጠጣ ማስፈራራያውን ተግባራዊ ማድረጉ የደቦ ጥረት በጠቅላላው ከሽፏል፡፡ በብዛት የሮም ስምምነትን ጥለን እንወጣለን የሚለው ማስፈራሪያ የጨረባ ተዝካር ሆኖ ቀርቷል፡፡ የገዢው ፓርቲ አባላት ሃይለማርያምደሳለኝና ቴዎድሮስ አድሃኖም ያወናከሩት ሴራቸው ማንም ሳይቀበለውቀረ፡፡ ለዚሁም መሰናከል አድሃኖም  መገናኛዎችን መጥፎ መልእክት አዛዮች ሲል ወነጀላቸው፤ ‹‹አንዳንድ መገናኛዎች ተከፋፍለዋል ይላሉ እኛ ግን አንድም የዚያ አዝማሚያ የለንም: ያለን አንድ ምርጫ አንድነታችንን መጠበቅ ነው›› ብሎ ነበር፡፡

በአንድ ጎኑ አድሃኖም እውነት አለው፡፡ 34ቱ የሮም ስምምነት ፈራሚዎች በእነ ሃይለማርያም የተሸረበውን  የደቦ ፍርጠጣ ላለመቀበል በአንድነት ጸንተው ምርጫቸው በአንድነት መቆም መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ ብቻቸውን መሃል ሜዳ ቀርተው ከሮም ስምምነት እንውጣ ብለው ነጭ ባንዲራቸውን በማውለብለብ የባረቀባቸው መልእክታቸው ጋር የቀሩት ሃይለማርያምና አድሃኖም ብቻ ነበሩ፡፡ አንድም ፈራሚ ሃገር በአይ ሲ ሲ (ያለም አቀፉ ወጀል ፍርድ ቤት)  እንውጣ የሚለውን ሃሳብ ደግፎ የወገናቸው አልነበረም፡፡ የአፍሪካ የስምምነቱ ፈራሚ ሃገራት የሮም ስምምነት ለአፍሪካ መሪዎች እንደማይስማማና መጣሁብህ ካላረፍክ፤ ችሎትእግርሃለሁ እንጂ ሕዝብን እየበደልክ አትቀጥልም በማለት መሪዎቹን ቢያስጠ ነቅቃቸውም አይ ሲ ሲ ለአፍሪካ ሕዝቦችዋስ ጠበቃቸው እንደሆነ በሚገባ ተገንዝበዋል፡፡ በልዩ አስቸኳይ ስብሰባው የነበረው ከሕግ የመፈርጠጡ ማስፈራሪያ ከንቱ ነውና፤ የአይ ሲ ሲ ተግባር ይቀጥላል፤የሩቶና የተባባሪዎቹ ክስ መታየቱ ይቀጥላል፡፡ የኬንያታ ችሎት ሂደት በኔቬምበር 12 መሰማት ይጀምራል፤ ባሺርም ከዓለም አቀፍ ፍትህ ማስገደጃው እንደወጣበት ኮብላይነቱ ቀጣይ ይሆናል፡፡

የፍርጠጣ ሕብረት አድርባይነት፡ አደገኛ የጫጩቶች ጫጫታ
በኦክቶበር 11-12 2013  በአይ ሲ ሲ ላይ የተካሄደው የአፍሪካ አንድነት አስቸኳይ ስብሰባ ችላ ሊባልአለያም አናሳ ግምት ሊሰጠው አይገባም፡፡ ለምንነቱ ሊመሰገን ይገባዋል፡- ለፍርጠጣ ሕብረት አድርባይነቱ፡፡ ይህን አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የወተወቱት የአፍሪካ መሪዎች፤ ከሁለተኘው ዓለም ጦርነት ወዲህ የተቋቋመውን ብቸኛና ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ዓለም አቀፋዊ የፍትሕ ተቋም የጫጩ ሚጫወቱ ናቸው፡፡ሃሳባቸው34ቱን የአፍሪካ ፈራሚ ሃገራት በሽብር አውቶቡሳቸው አሳፍረው ከአይ ሲ ሲ ጋር በማጋጨት አይ ሲ ሲንለማስፈራራትና በመጨረሻዋ ሴኮንድ ላይ ፍላጎታቸውን እንደሚያሟላ እርግጠኛ ሆነው ነበር በምኞት ቅዠታቸው፡፡ደግነቱ አይ ሲ ሲ በዓላመውና በተቀበለው አደራ ጸንቶ ወይ ፍንክች ያባ ቢላ ልጅ አለ፤ አውቶቡሱም ባዶውንከአሽከርካሪው ከሃይለማርያም ደሳለኝና ከወያላው ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር ያለተሳፋሪ ቀረ፡፡ ተስፋ ቆርጠውበማሸብረክ አይ ሲ ሲ ከሰብአዊ መብትን ከሚጥሱ ወንጀለኞች፤ ከጦር ወንጀለኞች ጋር፤ በዘር ሕዝብን ከሚጨፈጭፉትጋር፤ ተጎጂውን ሕዝብ ለማስማማት የሚችል ክበብ ለማደረግ በሚል እያጉረመረሙ የማይሰማና ተቀባይ ያጣ ሙሾ ማውረድያዙ፡፡

አይ ሲን የማደናቀፉ የእልህ እሽቅድድም
የሃይለማርያምና የቴዎድሮስ አድሃኖም አይ ሲ ሲን የማደናቀፉ ጨዋታ ፕላን 34 ቱ የሮም ስምምነት ፈራሚ ሃገራትን ፊት አዞረባቸው፡፡ ሃይለማርያምና አድሃኖም በንግግራቸው ፈራሚ ሃገራትን ያሰባስብልናል ብለው ያለሟቸውን በርካታ እቅዶች አቅርበው ነበር፡፡ 1. በሥላጣን ላይ ያሉ መሪዎች (ከሕግ በላይ ይሁኑ:-ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ አንደሚባለው ሁሉ) የተጠያቂነት ከለላ ያግኙ፤ 2. ያለፈውን እንዳለፈ አርገን እንርሳው፤ 3. አይ ሲ ሲ አፍሪካና አፍሪካውያን ላይ ያተኮረ አስከፊ የፖለቲካ ተቋም አለው ፤4. 34ቱ ፈራሚ ሃገራት ስምምነቱን ሲፈርሙ የነበራቸው ግናዛቤ ተቋሙ ያለአድልዎና ፍትህን መሰረት ባደረገ መልኩ ስራውን ያከናውናል በሚል እምነት ነበር፤ (ትክክከለኛ አስተሳሰብ አልነበረም)፤  5. በኬንያታ ሩቶና በበሺር ላይ የተመሰረተው ክስ ባገር ዉስጥ ያለዉን የመቻቻሉን ሂደት ያበላሸዋል፤ 6. አይ ሲ ሲና የተባበሩት መንግስታት ሴኪውሪቲ ካውንስል ባለሁለት አድልዎ መልክ ፍትህ ነው የሚያሳዩት: አንዱ ለአፍሪካውያን ሌላው ደሞ ለሌሎች፤ 7. አይ ሲ ሲ አፍሪካውያንና አፍሪካን በዚህ ሁኔታ ሊመለከትእንደማይገባው ልናሳውቀው ይገባናል ነው:: አንድ የስምምነቱ ፈራሚ ያልሆነ ሃገር ‹‹መሪዎች›› (ማለትም ኢትዮጵያ) እንዴት አድርገው ስምምነቱን አምነውና ተቀብለው የፈረሙ ሉአላዊ  መንግስታትን  ሃገራት መሪዎችን እጅ በመጠምዘዝ ስምምንቱንና አይ ሲ ሲን አንቅራችሁ ትፉ ረግጣችሁ ዉጡ በማለት የሽብር ከበሮ ይደልቃሉ ?

በስልጣን ኮርቻ ላይ ለተፈናጠጡት የአፍሪካ መሪዎች ከወህኒ ማምለጫ ካርድ ይሰጣቸው ነው ያለው አድሃኖም በንግግሩ ላይ በሰጠው አስተያየት  ‹‹የሃገር መሪዎች የስልጣን ዘመናቸው እስኪያበቃ ድረስ ከተጠያቂነት ነጻ ሊሆኑ ይገባል::  የሃገር መሪዎችን መክሰስና መመርመር  ለኬንያና በአጠቃላይም ለአፍሪካ ትልቅ ጉዳት አለው::››  አድሃኖም ሲማጸንም ‹‹ፍትሕን ማስከበሩ ዘላቂ ማፍትሔ ለማስገኘት የሚደረገውን ጥረት በማይጎዳ መልኩ ሊሆን ይገባል›› በማለት ተረት ተረት ይለናል፡፡ አድሃኖም ምርመራንና ክስን በተመለከተ ያነሳቸው አንዳንድ ነጥቦች እውነትነት አላቸው፤  ያለአንዳች ቁጥጥር ሰብአዊ መብትን የገፈፉትን፤ የግፍ ጭፍጨፋ ያካሄዱትን፤ የዘር ግድያን የተገበሩትን፤ አፍሪካንና አፍሪካውያንን በንቀት ለመከራና ለድህነት የዳረጓትን ‹‹መሪዎች›› የአይ ሲ ሲ አካሄድ ምጥ ሊያስይዛቸው ይችላል፡፡ የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ረጂሙ የሕግ እጅ በአፍሪካ የስልጣን ወንበር ላይ የተኮፈሱትን የስብአዊ መብት ገፋፊዎች፤ በቤተ መንግስታቸው ተቀምጠው በአፍሪካና በአፍሪካውያን ላይ የግፍ ጭፍጨፋ የሚያካሂዱትን በጫካ በነጻ አውጪ ስም ተሸሽገው ያሉ ‹‹መሪዎችን›› ሽባ እንደሚያደርግ ግልጽ ነው፡፡

እርግጥ ስምምነቱን ያልፈረሙና ያልተቀበሉ እንደኢትዮጵያ ያሉት ሃገራት ያለምንም ተመልካችና ሃይ ባይ ያሻቸውን ኢሰብአዊ ተግባራት ማከናወን፤ ንጹሃናን መግደል፤ በዘር ላይ የተመሰረተ ግድያን ማካሄድ፤ እንማራለን የሚሉትን ሃገርና ሕዝብ መበዝበዝ ይችላሉ ማን አለባቸውና!  ከዚያም አልፈው የድፍረታቸው ድፍረት አይ ሲ ሲን ላማኮላሸት አይ ሲ ሲ አፍሪካውያንን ለይቶ የሚያድን ተቋም ነው በማለት የሽብር ቅጥፈታቸውን ይነዛሉ፡፡

ለመሆኑ ለምንድን ነው በሥልጣን ላያ የተቀመጡት ‹‹መሪዎች›› ሰብአዊ መብትን ከጣሱ፤ የዘር ማጥፋትን ከፈጸሙ፤የጦር ወንጀለኛ ሆነው ከተገኙ የማይከሰሱት? አድሃኖም እራሳችንንን ከክስ ለማዳን የሚል የቅብጠት መልስ ካልሆነ በቀር ሌላ መልስ አይኖረውም፡፡ሰብአዊ ጥሰትን፤ የግፍ ግድያን፤ የዘር ማጥፋትን ባስመለከተ ይከሰሱ ከተባለ መሪዎቹ ከክስ ለማምለጥ ሲሉ በምንም መልኩ ምርጫ አካሂደው መሸነፍን አይሞክሩትም:: ስለዚህም አድሃኖምና ሃይለማርያምአላማቸው በግፍ መንበረ ዙፋናቸው ላይ እስከ እለተ ሞታቸው በሕግ ሳይጠየቁ ለመወዘፍ ነው፡፡ የማይከሰሱት የማይገረሰሱትየማይደፈሩት ዘልአለማዊ ሆነው ለመኖር ነው፡፡ በጫካ ለነጻነት ታጋይ ነን የሚሉትና በቀኝ በግራ ወንጀል በመፈጠም ላይ ያሉትም በበኩላቸው እኛ የሕዝብ እንባ አድራቂ ነንና የሕዝቡ እውነተኛ ተወካዮች በመሆናችን ልንከሰስአይገባንም ቢሉስ ምን የሚያግዳቸው ደንብ አለና:: የሃይለማርያምና የአድሃኖም ሕግ እንደሆነ ወንጀለኞችከነወንጀላቸው፤ ከነጥጋባቸውና ንቀታቸው በስልጣን ላይ ሆነው አይከሰሱ ነው የሚለው፡፡በዘር ፍጅት፣ በጦር ወንጀለኛነት ወይም ህዝብን በማሰቃየት ተሳትፈው ወይም አዘው የሚያስፈጁ እነዚህ የአፍሪካ አምባገነን ገዥዎች ስለሆኑ እነሱ ቢገድሉ፣ ቢያስፈጁ መብታቸው አድርገውት መከሰስ የለብንም ብለው ሲጠይቁ ትንሽ እንኳን አለማፈራቸው ያስደንቃል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ የሚለው የፊውዳል መዝሙር ቦታ እንደሌለው እንዴት አያውቁም? በእርግጥ ሰማይ ላይታረስ ይችላል፣ በአውሮፕላን መቀዘፉ እንደ እርሻ ይቆጠራል ካልተባለ በስተቀር፡፡ ንጉስ ግን ሰው ነው፣ እንደማንኛውም ሰው ተፀንሶ ተወልዶ አድጎ ነው ለስልጣን የበቃው፡፡ እንደ ማንኛውም ሰው ደግሞ ያረጃል፣ በመጨረሻም ወደማይቀረው ዓለም ይሰናበታል፡፡ድሮ የሰው ልጅ ስልጣኔ ገና ባልዳበረበት ዘመን ንጉስ ከላይ ተቀብቶ ታዝዞ የመጣ እንደሆነ ስለሚቆጠር የፈለገውን ማድረግ ይችላል፣ አይከሰስም አይወቀስም ይባል ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ይህ ሁኔታ ያፈጀ ያረጅ ነው፡፡ የልዕለ ኃያሏ አገር መሪ ኦባም ይወቀሳል ይከሰሳል፡፡ ሰለዚህ ይህ ሀሳብ ኢትዮጵያን የምታህል ታላቅ አገር የሚመሩና የህብረቱ መቀመጫ የሆነችው አገር መሪዎች፣ መብትን ለመግፈፍና ለመጨፍለቅ ግንባር ቀደም ሆነው ይህን ማለታቸውአሳዛኝ ነው፡፡

የዘገየ ፍትሕ የተነፈገ ሕግ አለያም፤ ኢፍትሐዊ ነው፡፡
በልዩ አስቸኳይ ስበሰባው ላይ ሃይለማርያም ምስክርነት ሲሰጥ ‹‹በአይ ሲ ሲ የባሺር ክስ የተለየ ሊሆን ይገባል ምክንያቱም አስፈላጊውን ፖለቲካዊ  አመራር በመከተልና የዳርፉርን ችግር ለመፍታት ቁርጥ ውሳኔ ላይ በመድረስ ከደቡብ ሱዳንም ጋር ያለውን አለመግባባት ለመቋጨት በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡› ይላል:: በተመሳሳይም ኬንያታ እና ሩቶ ኬንያ አዲስ ሕገ መንግስት ያጸደቀች በመሆኗ የእነርሱም ክስ በተለየ ሊታይ ይገባል፤ እንዲሁም በኬንያ የነበረውን ሁሉ በመለወጥ ለሕዝቡና ለሃገሪቱ› ታይቶ የማይታወቅ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲካሄድ አድርገዋልና፤ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል ይላል፡፡

ሃይለማርያም በቀላሉ አነጋገር የሚለው አይ ሲ ሲ በሺርን፤ ኬንያታን፤ ሩቶን በነጸጻ መልቀቅ ያለበት ካለፈው ጥፋታቸው በመማር ስህተታቸውን ተረድተዋል ነው፤ ይህ አባባል፡- አንድ የወንጀል ተጠርጣሪ ከክስ ነጻ መሆን ያለበትያለፈውን ሃጢአቱን ሁሉ ተረድቶ በመተው፤ እራሱን በማስተካከል ተሃድሶ አድረጓልና፤ ተለውጦ መጾም መጸለይ፤ለተቸገሩ መቸር፤ ቤተእግዚአብሄርን፤መስጊድን፤ ሲናጎግን፤ የጸሎት ቤትን በማክበር መሳለም ጀምሮ መስረቅ ማጭበርበርን መግደልን ስለተወ  ምህረት ሊሰጠው ይገባል ነው፡: የሚያስገርም አስተያየት ነው!

ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን
እውነት ነው ይቀልዳሉ እስካሁን በግፍ የጨረሱትና ያስጨረሱት ህዘብ ደም የውሻ ደም ነው፣ ፍትህ ሊያየውአይገባም ይሉናል ፡፡ የኬንያና የሱዳን አምባገነኖችን ነጻ ለማድረግ ሲባል እስካሁን የተፈጸመው ላይጠየቅ እንስማማ ቢሉ አይደንቅም አምባገነኖች ራስ ወዳዶች ናቸውና፡፡ ዕርቅ ማለት እነሱ ያጠፉት ጥፋት እንዳይነሳ ማድረግ ብቻ ነው፣ያለዚያ ሰላም ሊኖር አይችልም፡፤ ይህ ተራ አባባል ከትዝብት ውጭ አይ ሲ ሲን ለማስፈራራት የሚፈይደው ነገር አይኖርም፡፡በአህጉሩ ውጣ ውረድ በበዛበት ግጭት ውስጥ ፍትህንና ይቅር ለእግዚአብሔርን ማመዛዘን ያስፈልጋል ይላል እራሱን ብቻ አዋቂ በማድረግ አድሃኖም ሲናገር:: በዚህ አባባል ውስጥ የሚያስገርም ምጸታዊ አነጋገር አለ፡፡

የሃይለማርያምና የቴዎድሮስ አድሃኖም ባለራዕይ እና  ኢትዮጵያን ለአለፉት አሰርት ዓመታት የገዛው የገዢው ፓርቲ ዋና መሃንዲስ፤በሞት የተለየው መለስ ዜናዊ  ሃብቱን በማካባት የበለጸገው ለፍትሕና ለይቅር ለእግዚአብሔር በልቡ ቦታ በማጣቱ ለአነስተኛ ይቅርባይነት ጨርሶ ፍላጎትና ፈቃደኝነት የሌለው ነበር፡፡ ይሄው ባለራዕይ ገዢ በኢትዮጵያ የተካሄደውን የ2005 ፓርላማ ምርጫ አስመልክቶ በባዶ እጃቸው የድምጽ መከበርን የምርጫን ሰላማዊና ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡትን ግድያ በማዘዝ 193 ዜጎች ለሞት ሲዳረጉ 763 ደግሞ በጥይት ቆስለዋል:: ፍትህን  ከይቅር ለእግዚአብሔርን ጋር የሚያመዛዝንበት መንገዱ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን የሲቪክ ማህበራት አባላትን፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን፤ጋዜጠኞችን አንዳች ማስረጃ በሌለውና በጀብደኝነት በተሞላ የሃገር ማጥፋት ክስ ለእስር መዳረግ ነው፡፡ ይሄው ባለራዕይ እየተባለ ከበሮ የሚደለቅለት በራሱ ምስል በቀረጸው የካንጋሮ (የዝንጀሮ ችሎት) በማቅረብ ፍርድ አዞባቸው በኋላ ደግሞ ተንበርክካችሁ ይቅርታ ጠይቁ በማለት ለምህረት ዋጋ ክፈሉ ያለ እኩይ ባሕሪ የተላበሰ ነበር፡፡ አሁን እንግዲህ ቴዎድሮስ አድሃኖምና ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚሉት የነዚህ ንጹሃን ዜጎችደምና በዳርፉርም የፈሰሰው የንጹሃን ዜጎች ደም በኬንያም በቅድመ ምርጫው የደረሰው ግድያና ግፍ ሁሉ ተረስቶ በሞተ ፋይል ይዘጋ ነው፡፡ አአምሮ ያለው ሰው አንደዚህ ይናገራል?!

አንደ ሃእለማርያም አስተያየት እንዴት ነው አይ ሲ ሲ አፍሪካን ነጥሎ ኢላማ ያደረገው? አይ ሲ ሲ ኢላማ ያደረገው የሰብአዊ መብት በሚደፈጥጡ አምባገነኖች ላይ ነው፡፡ እነዚህ ደግሞ በገፍ በአፍሪካ የሚገኙ ናቸው፡፡ ስለዚህ 99 በመቶ ከአፍሪካ ሆነ የሚባለው ከመብት ረገጣው ጋር በቀጥታ የተያያዘ ስለሆነ ይህም አባባል ውሀ የሚቋጥር አይሆንም፡፡የመቶኛ ድርሻው ፍትሀዊ እንዲሆን በማለት የአውሮፓ፣ የአሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ወዘተ መሪዎች በግድ ወንጀለኛ ተብለውምንም ጥፋት ሳይሰሩ መያዝ አለባቸው እንዴ? ሰብአዊ መብት ረገጣው እስከቀጠለ ድረስ 99 በመቶው አይደለም በአፍሪካ አህጉር በኢትዮጵያ ብቻም የማይሆንበት ሁኔታ የለም፡፡ድርጅቱ አፍሪካንና አፍሪካውያንን ለፖለቲካ ኢላማ ያደረገ ነው ለሚለው አሉባልታ ቅንጣት ያህል ማሳመኛ እንኳ ሊያቀርቡ አይችሉም፡፡ ምን ለማድረግ ነው የፖለቲካ ኢላማ ያደረገው? ማንን? ለምን? መቸ? እና እንዴት ለሚሉ ጥያቄዎች መልስም ሆነ ማስረጃ የላቸውም፡፡ ስለዚህ ይህም አባባል ተራ አሉባልታ ሆኖ ይቀራል፡፡ሃይለማርያምና አድሃኖም ሆን ብለው ማገናዘብ ያልፈለጉት እውነታ፤ (አስተዋይነት የጎደላቸው) በአፍሪካ ውስጥስሩን የሰደደው በቅድመ ምርጫ ወቅት በተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ በሚደረግ ተጽእኖ፤ የምርጫ መጭበርበር፤በመጨረሻውም ስልጣን ዙፋን ላይ የተኮፈሱት ጉልበተኞች ለሽንፈት ሲዳረጉ የምርጫውን ውጤት አንቀበልም የማለታቸውን ሃቅ ነው፡፡ በማያጠራጥር መልኩ በስልጣን ላይ ያሉ የአፍሪካ ገዢዎች በነጻና ፍትሃዊ  ምርጫ ማሸነፍ ስለማይችሉ ሁል ጊዜ በተቀናቃኝ ፓርቲዎች ላይ ያለውን ህግ በማዳቀል ውትፍትፍ ሕግ እያወጡ ለእስራትና ለሞት ይዳርጓቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ በ2005፤በኬንያ በ2007፤ በዝምባብዌ በ2008፤ በ2010 በኮት ዲቩዋር፤በ2011 በዴ/ ኮንጎ እና በማሊ በ2012 መፈንቅለ መንግስቱ ምርጫውን ባደናቀፈበት ጊዜ በገሃድ የታየ ነው፡፡

አዎ እርግጥ ነው ያፍሪካ መሪዎች እነርሱ በህግ የሚጠየቁ ከሆነ እንበጠብጣለን ሰላም እርቅ አይኖርም እያሉ እያስፈራሩ ነው::  እንዲህም ብሎ መሪ የለ፡፡ ራሳቸውን መምራት የማይችሉ አምባገነኖች በምን መልክ ህዝብን ያህል ነገር በሰላምና በፍቅር ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል? በምን መለኪያ ነው እነርሱ የሰላምና የዕርቅ ጠበቃ ሆነው የአዞ እንባ የሚያነቡት? ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቆዳ አንጥፉልኝ እንዳለው ነው፡፡ ለማያውቁሽ ታጠኝ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የወንጀለኞች ፍርድ ቤትና የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት አድሏዊ አሰራርነው የሚያራምዱት፣ ለአፍሪካውያን ተጠርጣሪዎች ሲሆን ከባድና አድሏዊ የሆነ ቅጣትን የሚሰጡ ሲሆን ለሌሎች ግን የተሻለ ቅጣትን ነው የሚሰጡት ይላሉ ፡፡ ተራ አሉባልታና ቅጥፈት ካልሆነ በስተቀር በማስረጃ  ቅንጣት ታህል መጥቀስ ይችላሉን? ለመሆኑ ለአድሏዊ አሰራር ቅርብና አድራጊ ማን ሆነና? ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ! የተባበሩት መንግስታት የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እራሱን ከፍ አድርጎ የሚያይ ስለሆነ  በዚህ እንዲቀጥል እኛ አፍሪካውያን መፍቀድ የለብንም፡፡ይኸ ተራ የበታችነት ስሜት መገለጫ ነው፡፡ ድርጅቱ ናቃቸው እንዳይባል በወንጀል የተዘፈቁትን አምባገነኖች እጁን አጣጥፎ በመቀመጥ ወደ ፍትህ አደባባይ ማምጣት የለበትም ማለት ነው? የበታችነትናየበላይነት ስሜት እንዴት ነው በአምባገነኖቹ የሚገለጸው? ይህም ተራ አሉባልታ ካልሆነ በስተቀር የሚፈይደው ነገርየለም፡፡

የሮም ሰምምነት ፈራሚ ሳይሆኑ ነገር ግን ድርጅቱን ለመክሰስ ግንባር ቀደም የሆኑት የእኛዎቹ ገዥዎችያቀረቧቸው 7 ነጥቦች ውሀ የሚቋጥሩ አይደሉም፡፡ በስሜት የተሞሉ ተራ አሉባልታዎች ናቸው፡፡ እንደሰብሳቢዎች አላማ ቢሆን ኖሮ ድርጅቱን እረግጠው ከሮሙ ስምምነት ሊወጡ ነበር፡፡ ነገር ግን ድጋፍ ስላላገኙ ሳይወዱ በግድ አይ ሲ ሲን እንዲለማመጡ ጊዜ በይኖባቸዋል፡፡ ዓላማቸው ሲከሽፍም እኛ ከአይ ሲ ሲ ለመውጣት አይደለም፣ዘረኛና አድሏዊ መሆኑን ለማለጥ ነው የሚል የቅጥፈት አሉባልታቸውን ለማሰማት ተገደዋል፡፡ ሂደቱም ሲስሟት ቀርቶ ሲስቧትሆኗል፡፡ የሚሰማቸው ቅሬታ ካለ በማስረጃ አስደግፈው ማቅረብ ሲገባቸው ድርጅቱን ጥሎ ለመውጣትና ለማፍረስ መወጠናቸው ከትዝብት ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም፡፡

የአፍሪካ መሪዎች አፍሪካን የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መቀበርያ አታድርጓት፡፡ የአፍሪካን ለምለም የሳር ምድር፤በረሃዋ፤ደኗ፤የአይሲ ሲ የዳግም ልደት ስፍራዋ ይሁን፡፡ አፍሪካን አይ ሲ ሲ ለዘረኝነት፤ ለፍትሕ አልባነት ከተሳለ ሰይፍነት ወደየፍትሕ ጋሻ መከታነትና ትክክለኛና ሚዛናዊ እንዲሆን አድርጉ፡፡ አይ ሲ ሲ በኦክቶበር 11-12-13 የአፍሪካ ሃገራት በአንድነት በመቆማቸው ጠንክሮ ሚዛናዊ ሆኖ በእጅጉ የበረታና ጉልበታም በመሆኑ አታሞው ይመታ፤ መለከትም ይነፋ!!

እናንት የአፍሪካ መሪዎች፡ ትክክለኛውን ተግባር ከውኑ፤‹‹ ካለያ እግዚአብሔር እና ታሪክ የዛሬውን ውሳኔያችሁን ሲያስታውሱት ይኖራሉ››የአፍሪካ አንድነት የሮምን ስምምነት እንዲቀበል እንጂ እንዳይፍቀው እማጸነዋለሁ፡፡ በተመሰቃቀለችው አፍሪካ ነገ፤በሚቀጥለው ወር፤ አለያም በሚቀጥለው ዓመት ማን ታዳኝ ማን አዳኝ እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ዛሬ በስልጣን ላይ ሆኖ የሚያድነው ነገ ከስልጣን ወርዶ ተዋርዶ ታዳኝ ሊሆን ይችላል፡፡ አይ ሲ ሲ በሌለበት የዛሬዎቹን አዳኞች ከስልጣን ሲወርዱና ሲታደኑ ማን ይቆምላቸዋል?

በመጨረሻም በ1935 ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ጊዜ ቀ ኃ ሥላሴ ለዓለማ ማሕበሩ አቤቱታ ባሰሙበት ጊዜ የሊግ ኦፍ ኔሽን ለአንዲት ደካማ አባል ሃገር ዋስትናና ድጋፍ ለመስጠት አልቻለም ነበር፡፡ ንጉሡ በዚያን ጊዜ ትዝብታዊ ማስገንዘቢያ አሰምተው ነበር:: እኔም ያንን በከፊል ለአፍሪካ አንድነት  እንደታሪክ ትምህርትነቱ አመሳስዬ አቀርባለሁ፡ ‹‹ከእግዚአብሔር መንግስት ውጪ በዚህ ምድር ላይ ማንም ሕዝብ ከማንም የሚበልጥ አይደለም፡፡ ሃያላን መንግስታት ደካማዎቹን በሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀል፤ በጦር ወንጀል፤ ሊያጠቁ በሚነሱበት ጊዜ ጉዳትየሚፈጸምባቸው ደካማ ሃገራት አቤቱታቸውን የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ሚዛናዊና በሕጉ መሰረት ፍትሕ እንዲሰጥ ይጠይቃሉ፡፡የሮምን ስምምነት የምትፍቁት ከሆነ እግዚአብሔርና ታሪክ ፍርዳችሁን ለዘልዓለም ይታዘቡታል!

ስለዚህም በኦክቶበር 11-12-13, 2013 ለዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በምስከረነት ተጠሪ  ሆኜ እማኝነት ቆሜያለሁ!

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop