ሃበሻው ዶክተርና ልጁ – በአሜሪካ (ከኢየሩሳሌም አረአያ)

(በፎቶ የሚታየው ወጣት ሮቤል ..)
ዶ/ር ጳውሎስ ይባላል፤ ሃበሾችን ጨምሮ የሚያውቁት በርካታ ወገኖች ስለዶ/ር ጳውሎስ ተናግረው፣ አድናቆትና ምስጋናቸውን ሰጥተው አይጠግቡም። በዲሲ ከተዋወቅኳቸው እጅግ መልካም ሰዎች አንዱ ነው። ትብብር ለጠየቁት ሁሉ የነፃ ህክምና እርዳታ ያደርጋል። በተለይ የቁርጥማትና አጥንት ወዘተ ሕመም ለሚያሰቃያቸው በዘመናዊ መሳሪያ ፈውስ ይሰጣል። እረፍት በሆነ ቀን የህክምና መሳሪያውን እንደያዘ ነው የምታገኘው። « ገንዘብ እንክፈልህ..» የሚል ጥያቄ በጭራሽ መስማት አይፈልግም።..በአብዛኛው ከመናገር ይልቅ ማድመጥን ያዘወትራል። ለወገኖቹ አዛኝ፣ እንዲሁም አገሩን የሚወድ ሰው ነው። ንግግሩ ቁጥብ ነው፤ ከእርሱ ጋር ቁጭ ስትል ብዙ የህይወት ልምዶችን ትቀስማለህ። ዶ/ር ጳውሎስ በመደበኛ ስራው ከአሜሪካ መንግስት ጥሩ ክፍያ ያገኛል። የተቸገሩ ወገኖችን በገንዘብ ጭምር ይረዳል። በደርግ ዘመን የኢህአፓ አባል ነበር። በትግል ተፈትኗል፣ እስርና ስቃይን ቀምሷል።…የዶ/ር ጳውሎስ ልጅ ሮቤል ይባላል፤ በትግል አብራው ከነበረች የቀድሞ ፍቅረኛው በአሜሪካ ተወልዶ ያደገው የ19 አመቱ ወጣት ሮቤል ከወላጅ እናቱ ጋር በቦስተን ይኖራል። …ከ6 ወር በፊት አፕሪል 15 ቀን 2013 በቦስተን ከተማ አስደንጋጭ ነገር ይከሰታል። በእለቱ ኢትዮጲያዊያን አትሌቶች በድል አድራጊነት ያጠናቀቁበት የማራቶን ውድድር ላይ ሁለት ወንድማማቾች ቦንብ በማጥመድ ንፁሃንን ገደሉ፣ በመቶዎች አቆሰሉ።..ድርጊቱ ከተፈፀመ ከሶስት ቀን በኋላ በርካታ የF.B.I አባላት መሳሪያ ወድረው፣በጎማ የሚንቀሳቀስ ታንክ አስከትለው የነሮቤልን መኖሪያ ይከባሉ። በር ሲቆረቆር… ወላጅ እናት ባየችው ነገር ክው ብላ ትደርቃለች። ከተፈፀመው የሽብርተኝነት ድርጊት ጋር በተያያዘ ሮቤል ተጠርጥሮ እንደሚፈለግ ገልፀው ..ይዘውት ይሄዳሉ። አራት ቀን ለታሰረው ሮቤል ሶስት ታዋቂ ኢትዮጲያዊያን ጠበቆች ጥብቅና ሊቆሙለት ፈቃደኝነታቸውን አሳዩ። ..ከሁለቱ የድርጊቱ ፈፃሚ ወጣቶች አንዱ እነሮቤል መኖሪያ ቤት መጥቶ መፅሃፍ ሲቀበለው የሚያሳይ ቪዲዮ በምርመራው የቀረበ ቢሆንም፣ የሶስተኛ አመት ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነው ሮቤል ከዚህ ወጣት ጋር አብረው የሚማሩ የት/ቤት ጓደኛሞች መሆናቸውንና የሰጠውም መፅሐፍ የትምህርት እንደሆነ መፅሐፉን -ጭምር በማቅረብ ያስረዳል። ..የምርመራ ቢሮው ይህን ከተገነዘበ በኋላ ነበር – በ4ኛው ቀን እንዲፈታ ያደረገው።..ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ በመሆኑ ሮቤል በመኖሪያ ቤቱ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተደረገ። በአንዱ እግር ብቻ (እንደ እጅ ሰአት የሚታሰር አይነት) “tether ankle monitor” የሚባል ኤሌክትሮኒክስ መቆጣጠሪያ ተጠልቆለታል። ይህ መሳሪያ የሚገጠምለት ሰው ከተፈቀደለት ክልል ውጭ አልፎ ከሄደ መሳሪያው ለፖሊስ ጥቆማ ይሰጣል፣ በደቂቃዎች ውስጥ ፖሊስ ይደርሳል።…ዛሬ አርብ ኦክቶበር 18 ቀን ሮቤል ፍ/ቤት ይቀርባል።….ዝርዝር ጉዳዩን ያጫወተኝ ወላጅ አባቱ ዶ/ር ጳውሎስ፣ በመከፋት ስሜት ቅዝዝ ብሎ ፥ « አልፎ…አልፎ ልጠይቀው እሄዳለሁ፤ ተሰናብቼው ስወጣ ከቤቱ በር ማለፍ ስለማይችል አይኖቹ ውስጥ ቅሬታ አነባለሁ። እኔም ሆዴ እየተላወሰ ይከፋኛል። ትንሽ ይረብሻል። ..ሞራሉ ግን ጥሩ ነው፤ ቤት ሆኖ ትምህርቱን ያጠናል፣ ያነባል። ሮቤል ልጄ ስለሆነ ሳይሆን፣ የዚህ አይነት የሽብር ወንጀል ላለመፈፀም ኢትዮጲያዊ መሆን ብቻ በቂ ነው!! ሃበሻ አሸባሪ አይደለም!! » አለኝ።…

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ከነፃነት በኋላ በሚኖረን መንግሥት ሕዝብንና ሀገርን በቅንነት ለማገልገል ለምትመረጡ ወገኖቼ

10 Comments

  1. selam all please eghin talak sew kechnk ygelaglachw eso EGZABHIR so tilifonachewn btsetog beakbrot eteykalehu DR KECHNK YGELAGLOT

  2. I really feel sorry in this age to go through that, hope this will be a learning experience for the kid. Thank God it could be much worst.
    Jerusalem Araya, thank you for your correct informaion, neat, and clear. Keep it that way. Ensure others weak feeling doesn’t change your way.
    Nega

  3. I sympathize with the father for the situation of his son and it is likely that his son may not be involved. But as a former EPRP member who were actively involved in terroris activities in Ethiopia to invoke unnecessary generalisation is an oxymoron. Even today the governement of Ethiopia is involved in terrorist acitivities against its own citizens. Let him read the news about Ethiopia

  4. Egzeabher selzhe tenshe Lije yekumelet egha ethiopiaweyan ashebarenet weset anegebam tikikil Ethiopiawe malet SELAMAWE tehuit shekutekuit maletnew enjie kefusem lesetoin yemgeban ayedelenemena geta yawetawe.

  5. Ewunet Newu Habesha Ashebari Alneberem Zare Gin simun kibrun yemiyatefu ye Islimna akirari Wehabiyi timhirtoch gebtewu kibrun selamawinetun eyasatut be Alemim lay tetertar endihon adrgewutal eddme le Akirariiiiiiiiiii!!!!!!!!!!!!.

Comments are closed.

Share