በመካና መዲና እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ ቅዱስ ቦታዎችን የማስፋፋት ግንባታ ተከትሎ በያዝንው የሃጅ ተሳታፊ ምዕመናን ቁጥር ከወትሮው የቀነሰ ሆኖ ታይቷል። ዛሬ 1.3 ሚሊዮን ያህል የሚሆኑ ሃጃጅ ምዕመናን ከሙስሊማን ቅዱስ ከተማዋ ከመካ የካዕባ መስጊድ ተነስተው ወደ ሚናና ፣አረፋት እና ሙዝደሊፋ ኮርበታዎች ጸሎታቸውን በህብረት በማድረግ ጉዟቸውን ጀምረዋል።
በዘንድሮውን የሃጅ ጸሎተኞች ለመሳተፍ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የተለያዩ አለም ዜጎች ወደ ሳውዲ ገብተዋል። አብዛኛው ምዕመን በሚደላው የሰአታት ጉዞ በአየር ፣ እጅግ ባጣም ጥቂት የጎረቤት ሃገራት ሃጃጆች በየብስ ነዲዱ በርሃ በመኪናና ገምሰው ሲመጡ በጣም ጥቂቶች ደግሞ በመርከብ ቀይ ባህርን ባህር ቆርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ መግባታቸው ተመልክቷል ። የጸሎት ቦታዎችን የማስፋፈት ስራ ጅምር ተከትሎ የዘንድሮው ሃጅ ጸሎተኞች ቁጥር በቀነሰበት ሁኔታ ወደ ቅዱስ ከተማዋ መካ ከመጡት ምዕመናን መካከል አንድ ጎልማሳ ድንቅ የተባለለት የህይዎት ጉዞ መከዎኑን ሰምተናል። በሰለጠነው በዚህ ጊዜ ተፈጸመ ሊባል የሚከብድ ጉዞ አድርጎ የሃጅን የህይዎት ጉዞ ጸሎት ለመቀላቀል ሳውዲ መካ የገባው ፖኪስታናዊ ጎልማሳ ሲሆን አስገራሚ ጉዞ አድርጎ መካ የመግባቱ ዜና በአረብ መገናኛ ብዙሃን ተናኝቷል! የግልማሳው የወራት የእግር ጉዞ የብዙዎችን ቀልብ ስቧልና በማለዳ ወጌ ላስቃኛችሁ ወደድኩ …
ኸርላዝዳ ከስራት ራይ ይባላል፣ የ37 አመት ፖኪስታናዊ ጎልማሳ ነው። ከሳውዲ አልፎ የአለምን ያስደመመ የእግር ጉዞውን የጀመረው ባሳለፍነው ሰኔ ሲሆን መካ የገባው በያዝነው የጥር ወር ነው። ከስራት ከፖኪስታች ካራች ከተማ ጀምሮ ወደ ኮረብታማዋ መካ ሳውዲ አረቢያ ባደረገው የ6,387 ኪሎ ሜትር የሚገመት አሰልች የበርሃ ጉዞን በእግሩ ቆርጦ መድረሱ እውነት ነው ። ከስራት ባሳለፍነው ሰኔ የጀመረውን ጉዞ በመከወን ሳውዲ መካ ሲገባ ከፍ ያለ አቀባበል ተደርጎለታል።
ይህ ብርቱ ወጣት የቀድሞውን ወራት የሚጨርስ የሃጅ ምዕመናንን በእግራቸው በርሃውን ቆርጠው የሚመጡትን መንገድ በመከተል እንብርቱ ከተቆረጠችበት ሃገረ ፓኪስታን ካራች ተነስቶ ወደ ኢራንና የመጀመሪያ ጉዞውን በማድረግ በኢራቅ አና በዮርድያኖስ አድርጎ ሳውዲ አረቢያ መካ ለመድረስ የፈጀበት 6,387 ኪሎ ሜትር ሲሆን ከአራት ወራት በላይ የዘለቀ የእግር ጉዞ መሆኑ ብዙዎችን አስገርሞ አስደንቋል !
ከዚህ በፊት ሁለት ተመሳሳይ ረጅም የሰላም ጉዞዎችን በማድረግ የአለምን ክብረ ወሰን ለሁለት ጊዜ ያህል የሰበረው ፖኪስታናዊ ጎልማሳ ከስራት ራይ እንደ ቀደምት አባቶቹ ቀደምቱን የሃጅ የእግር ጉዞ ሲያደርግ በየደረሰባቸው ከተሞች ከፍ ያለ ድጋፍ ይደረግለት እንደነበር በኩራት አና በምስጋና ተናግሯል!
ብርቱው ፖኪስታናዊ ጎልማሳ ከስራት ረጅሙን ጉዞ አጣናቆ ትናንት የተጀመረውን የሃጅ ጉዞ 1.3 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናንን ጋር በመሆን የሃገሩን ባንዴራ በኩራት እያውለበለበ ከመካ ወደ ሚና የሚደረገውን የሃጅ ጉዞ በጸሎት ጀምሯል !
የቀድሞው ሃጅ ጉዞ ሲነሳ ኢትዮጵያውያንም ረጅሙን በርሃ እየቆረጡ ቀይ ባህርን በታንኳ ጀልባ ቀዝፈው ሃጅን ይቀላቀሉ እንደነበር ከአርብ አባቶች ተደጋጋሚ ምስክርነትን ሰምቻለሁ። ኢትዮጵያውያን በሃጅ ጸሎት ሲመጡ ባዷቸውን እነወዳልነበርና የቋጠሯትን ደረቅ ዳቦ ቆሎ ስንቅ ለዛሬ ባለጸጋ አረቦች ይታደጉ እንደነበር የጫዎቱኝ አንድ ሁለት ሳይሆኑ በርካታ አረብ አባቶችና የታሪክ ተመራማሪ ጭምር ናቸው ። ሃጅ እና ኢትዮጵያውያን ረጅም የታሪክ ትስስር አላቸው ፣ የጅማው አባጀፋር በዚህ ረገድ ስማቸው ይነሳል ፣ አባ ጅፋር ባሳዩት ትጋት በወቅቱ የሳውዲው ንጉስ ከመካ አጠገብ በስጦታ መልክ ለኢትዮጵያን ሃጃጆች ነጻ ማስተናገጃ የተሰጣቸው ትልቅ ህነጻ ይጠቀሳል ! ህንጻው መካ ካዕባ ሲስፋፋ ቦታው መቀየሩን አውቃለሁ። አሁንም ኢትዮጵያውያን ይገለገሉበታል! ስለ አገልግሎት አሰጣጡ ፣ ስላለበት ሁኔታና ስለ ባጀበት አትጠይቁኝ! በማን ይዞታ ስር ነውም ብላችሁ አትጠይቁኝ !
መነሻ መድረሻየ እና ወጌ ማጠንጠኛው ሃጅና ብርቱው ስው ናቸውና !
ብርቱ ሰው ! መልካም ጸሎት!
ነቢዩ ሲራክ