በኢትዮጵያ የተረጂዎች ቁጥር በመጨመሩ ተጨማሪ ስንዴ ሊገዛ ነው

በኢትዮጵያ እየጨመረ በመጣው የድርቅ ተጎጂዎች ቁጥር የተነሳ መንግስት ተጨማሪ ስንዴ ለመግዛት ተገደደ፡፡ ምንም እንኳን መንግስት፣ የድርቅ ተጎጂዎች ቁጥር መጨመሩን በአደባባይ ይፋ ባያደርግም፣ መረጃዎች ግን የተረጂዎች ቁጥር ማሻቀቡን እያመላከቱ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደምም የተረጂዎች ቁጥር መጨመሩን በጊዜ ይፋ ሳያደርግ የቆየው መንግስት፣ አሁንም ቁጥሩን ለመደበቅ እየጣረ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጉዳዩን በጊዜ ይፋ ማድረጉም ተገቢ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይመክራሉ፡፡

 

ድርቁ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ እንደመጣ የሚጠቁሙት መረጃዎች፣ መሻሻል የሚባል ነገር እያሳየ እንዳልሆነም መረጃዎቹ ያክላሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ተጨማሪ ስንዴ ለመግዛት ተወስኗል፡፡ ስንዴውን ለመግዛት ዓለም ዓቀፍ ጨረታ የወጣ ሲሆን፣ ከጨረታው በኋላም ወደ 700 ሺህ ኩንታል የሚጠጋ ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ታቅዷል፡፡ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ማለትም በአንድ እና በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ መንግስት ከውጭ ስንዴ አስገብቶ ነበር፡፡ አሁን ላይ የተረጂዎች ቁጥር በመጨመሩም ተጨማሪ ስንዴ ለመግዛት ዓለም ዓቀፍ ጨረታ መውጣቱ ነው የተሰማው፡፡

የተረጂዎች ቁጥር ጨምሯል አልጨመረም በሚል አልህ ድብብቆሽ እየተጫወተ የሚገኘው መንግስት፣ ጉዳዩን በአስቸኳይ ይፋ ማድረግ እንዳለበት ተመክሯል፡፡ ጉዳዩን በጊዜ ይፋ ማድረግ ለተረጂዎች በሚደረገው ዓለም ዓቀፍ እርዳታ ላይ የራሱ ጠቀሜታ እንዳለው የሚናገሩ ወገኖች፣ መንግስት ደብቆ የያዘውን የተጎጂዎች ቁጥር ጭማሪ ይፋ እንዲያደርግ እነዚሁ ወገኖች ጠይቀዋል፡፡ ቢቢኤን መረጃዎችን ጠቅሶ የተረጂዎች ቁጥር መጨመሩን መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ አፋር እና ደቡብ ክልሎች የተከሰተው ድርቅ 8 ነጥብ 5 ሚሊዬን ሰዎችን ማጥቃቱ ሲነገር ቆይቷል፡፡ አሁን ላይ ግን የተረጂዎች ቁጥር አሻቅቦ፣ ወደ ዘጠኝ ሚሊዬን ከፍ ማለቱን ከምንጮች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከግምባር!ፋኖ አስረስ ማረ ከአማራ ድምፅ ጋር!"የብልፅግና ጀምበር ጠልቃለች" The Voice of Amhara Daily News

 

BBN News November 25, 2017

2 Comments

  1. የአላሙዲን ባንክ እና ኢንሱራንስ ደንብኖች በብዛት ብራቸውን እያዘዋወሩ ነው ወደ ሌላ ባንኮች እና ኢንሱራንስ ኩባንያዎች::

    የአላሙዲን ኢንሱራንስ ኩባንያ ኢንሱራንስ ኪሳራ መመዝገብ ጀምርዋል::የአላሙዲን መታሰር ተከትሎ የአላሙዲን ኢንሱራንስ ኩባንያ ሰራተኖች የሃሰት አደጋዎች በማሳበብ ብዙ ገንዘብ በሃሰት መክፈሉም ተሰምትዋል ::

    http://www.tadias.com/06/16/2015/how-crop-insurance-is-helping-ethiopias-farmers/

    https://www.jica.go.jp/english/news/field/2014/150213_01.html

  2. ከአዙሪት ከመውጣት በፊት ሁሌም ጣር አለ ፡፡ሊያውም ከሺህ ዘመን የቡትቶ አዙሪት !!!!

Comments are closed.

Share