ስለ ተስፋዬ ገ/አብ ስለተባለው እኔ የምለው “ከዲያቆኑ የጳጳሱ” – ከዳንኤል ገዛኸኝ (ጋዜጠኛ)

ከዳንኤል ገዛኽኝ አትላንታ

ቀደም ብሎ የብርሃኑ ዳምጤ አባ መላ…ለጥቆ የዳዊት ከበደ- አውራ አምባ ከዚያም የጅዋር መሃመድ “ ፈርስት ኦሮሞ” ጉዳይ ከመዘጋቱ የተስፋዬ ገ/አብ ጉዳይ መራገብ ከጀመረ እነሆ ቀናትን እያስቆጠረ ነው። ፌስቡከኛዎች…የፓልቶክ ጉዋዳዎች ነገሩን ይቀባበሉት ጀምረዋል። የሆነው ሆኖ ግን የጀዋርን ያህል ግን ሙሉ ለሙሉ ብዙዎቹ ከሹክሹክታ ባሻገር ፊትለፊት ሊሄዱበት አልከጀሉም። ነገርን ከስሩ እንዲሉ ጉዳዩን በአግባቡ ያልተመለከቱት እንዲሁ በስሜት ያሻቸውን ማለት ጀምረዋል በተስፋዬ ጉዳይ። የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች የወያኔ ደጋፊ የሆኑ ድረ-ገጾችም “የውሻ ጥል ለቀበሮ ሰርግዋ ነው” እንዲሉ ነገሩ ጥሩ አጋጣሚን የፈጠረላቸው ሆኖዋል። ከዚህ ባሻገር ጉዳዩን በተመለከተ በግልጽ ወደ አድማጭ በማምጣት ተዋንያኖቹን ለማነጋገር ከሞከሩት ውስጥ ህብር ሬድዮ ይጠቀሳል ምንም እንኩዋን ዘገባው ሙሉ እንዳይሆን ባለጉዳዮችን ማካተት ባይቻልም። ህብር ሬድዮ መሞከሩን አውቃለሁ ባይሳካለትም። ህብር ሬድዮ ከሁሉም ቀድሞ ጉዳዩን ሊሄድበት የቻለውም… “የሃገር ጉዳይ ይቀድማል…” ከሚል እሳቤ እንደሆነ የሬድዮው ፕሮዱውሰር ነግሮኛል። ለነገሩ ከላይ የጠቀስኩዋቸውን ለ አብነቱ ለመንደርደሪያ ያህል ላንሳ። አባ መላ የወያነ ደጋፊ ቁዋሚ ተከራካሪ ነበረ። ነገር ግን ወያኔን አውግዞ በቃህ እምቢ ለወያኔ ማለት ሲጀምር እሰየሁ ከማለት ይልቅ እንዳውም የጋበዘውን ሚዲያ ማጥላላት ተጀመረ። አስታውሳለሁ ዳዊት ከበደ አውራ-አምባ በሱ መድረክ ቢጋበዝ ወጅብኝ ወረደበት እኔ እንዳውም በጊዜው መድረክ የተነፈገው ዳዊት አባ መላ ዘንድ አይደለም አባ ገዳ ዘንድ ቢቀርብ ሃጢያቱ ምኑ ላይ ነው ብዬ ተከራከርኩ በጦማሬ። የሆነው ሆኖ የዴቭ አውራ አምባ ጉዳይ የተለየ ነገር ከወደሁዋላ አመጣ እንጂ ግን ግን እንደሚዲያ የግራ ቀኙን መዘገቡ ባይከፋም ያቺ የዶክተሩ የስልክ ሚስጥራዊ ንግግር ላይ ግን ዴቭ ጭቦ ሰራ። ያም ሆነ ይህ ዴቭ ወያኔ ከሃገር አባረረኝ ካለ ወደሃገሩ ይመለስ ዘንድ ትንሳኤውን ለማምጣት የሚታገልን ድርጅት የማሪያም ጠላት ማድረጉ አልተመቸኝም በዚህ አውግዤዋለሁ ግን ዴቭ ሃሳቡን የመግለጽ ነጻነቱን ባከብርም።

የሆነው ሆኖ ግን ከሰሞኑ በተስፋዬ ዙሪያ ጽሁፋቸውን ጀባ ያሉን ጸሃፊው የተከበሩ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ በመጸሃፍ መልክ ሊያወጡት አስበው በሁዋላም ለድረገጾች ሲሳይ ያደረጉት ጉዳይ በምን መመዘኛ ለመጸሃፍ ሊሆን እንደታሰበም ለኔ ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም። እንዲያውም ጉዳዩ ተራ ግለሰባዊ ጉዳይ ሆኖ ሳለ ሃገራዊ አጀንዳ ያለው ጉዳይ እንደሆነ አድርጎ ደርዝ ለማስያዝ መሞከሩ አሳዝኖኛል። በበኩሌ የሃገር ጉዳይ ይቀድማል ትክክል ነው። ሆኖም ግን የግለሰቦችን ጉዳይ ወይንም በግልጽ ቁዋንቁዋ የግለሰቦችን ጸብ በሃገር ጉዳይ ስም ማንሳት ተገቢ አይደለም ባይ ነኝ። ባይሆን ዳኛው መጽሃፍ ሊወጣው የሚችል እርሳቸው በፍላጎት ይሁን ተገደው የሰሩዋቸው የዳኝነት ተግባሮች አሉ ከደርዘን በላይ።

ሲጀመር…

ዳኛ ወልደሚካኤል አስቀድመው በጽሁፋቸው መግቢያ ላይ ስለራሳቸው ስም እና የዳኝነት ዝና እየደረደሩ ጀብዳዊ ታሪካቸውን ሊንደረደሩበት ሞከሩ። በስተሁዋላም የደራሲ እና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገ/አብን ስብእና የሚነኩ ቃላቶች እና ግለሰባዊ ሚስጥሮችን በመደርደር የደራሲው ቀጣይ መጽሃፍ መነበብ እንደሌለበት ጥቁምታ የሚሰጥ መልዕክታቸውን አዥጎደጎዱት። ሁልጊዜም መቅደም የሚገባው ሃገራዊ አጀንዳ እና ጉዳይ እያለ ግለሰባዊ ተራ አተካሮ ውስጥ መግባት ለኔ ለዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ፋይዳው አይታየኝም። በተለይ በተለይ በዳኝነት ታሪካቸው ብቻም ሳይሆን በአንድ በአጣሪ ኮምሽነነታቸው ጉዳይ ብቻ ህሊናቸው ሞግቶዋቸው ለ እውነት መቆምን መርጠው ሃገር…ኑሮ…ቤተሰብ ምቾት ሳይሉ በስደት ስለሃገራቸው ለመቆም ወስነው በቁርጥ ቀን የተገኙን ዳኛ ወልደሚካኤልን ቀርቶ እዚህ ግባ የማይባል ፋይዳ ያልፈየደን ሁሉ የትላንት ማነነቱን ሳንፈትሽ የዛሬን ሃገራዊ አቁዋሙን በማየት ማንንም ስናከብር እና ቦታ ስንሰጥ ኖረናል። በምን ምክንያት ቢሉ በይሉኝታ። ዳኛ ወልደሚካኤል የግለሰብን ማነነት በመፈተሽ ሃገራዊ ፋይዳ ያለው ነጥብ እንዳነሱ ሁሉ ተሰምቶዎት ከሆነ ይሄ ስህተት ነው። ይሉኝታው እየሸበበን እንጂ ጥቂት የፕሬስ ክሶችን…አንድ የቅንጅትንም የፍርድ ቤት ጉዳይ…ካስፈለገም ብሄራዊ ጀግናችን ብለን የምንጠራውን እውቁን የመምህራን ማህበር ፕረዚዳንት ዶ/ር ታዬ ወልደሰማያትንም የክስ ጉዳይ አንድ ነጥብ ከወያኔ እውቅ ሹመኛ ዳኛ ጎን በመቆም ስለተወሰነው ውሳኔ እና የህግ ሂደት ብሎም በቀኝ እጅነት በወያኔ ሙሉ አይን ይታዩ እና ይጠበቁ ከነበሩ ኢትዮጲያውያን ዳኛዎች የመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኙ ሰው እንደነበሩ ለማሳየት በመረጃ በተደገፈ ከላይ የዘረዘርኩዋቸውን ጉዳዮች ማንሳት ይቻላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እየተደረገ ያለዉን በዘርኝነት ላይ የተመሠረተ የጥፋት ቃለ መሃላ ማክሸፍ የእያንዳንዱ እትዮጵያዊ ነኝ ባይ ሁሉ ግዴታ ነው ፤

ከዚህ መሰል ጉዳይ ይልቅ በርካታ እርስዎ የሚያውቁዋቸው ያልተሰሙ የወያኔ ዘመን የፍርደ-ገምድል የፍትህ ውሳኔዎችን ባስነበቡን ነበር። ከዚህ ቀደም በተለያዩ አጋጣሚዎች ያቀረቡልን እውነታዎች እንዳሉ ሆነው ማለት ነው። ግን ለኛ ለ ኢትዮጲያውያን ዳኛ ወልደሚካኤል “ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋ እለት” እንዲሉ በቁርጥ ቀን ወደ ህሊናዎ ያዘነበሉ በመሆንዎ ወደ ሁዋላ መመለስ አያስፈልግም። ይመሰገናሉ ይከበራሉ ይደነቃሉ። ወደ ተስፋዬ ጉዳይ ስመጣ ታዲያ እንደ እርስዎ ያለ የተከበረ ታላቅ ዳኛ…የህግ ሰው…ህግ አዋቂ…ከግለሰብ እስከ አለም አቀፋዊ ህግ እና ስነ-ስርእት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሰው የግለሰብን ሚስጥር በማውጣት በዚህ መልኩ ለሚዲያ ማዋል ጉዳቱም ሆነ ጥቅሙ እንዲሁም መጥፎ ጎኑ ምን እንደሆነ ሳያስቡ ቀርተው ይህንን ማድረግዎ ብቻም አይደለም በአስቸጋሪ እና ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ላለነው ኢትዮጲያውያን ምን ፋይዳ ሊያበረክቱ አስበው እንደሆነ ሳስብ በጣም ተገርሜያለሁ። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጲያውያን በሃገራዊ ጉዳይ እንዳንጠመድ እና የበኩላችንን ስራ እንዳንሰራ ከገዢዎቻችን አጀንዳ እየተመረጠ በዚያ እንድንወጠር ከምንደረግበት ሁኔታ የዘለለ ስላልሆነብኝ ነው ይህንን የምለው። እናም ለረጅም ጊዜም ጥብቅ ሚስጥር…ጥብቅ ሚስጥር ሲሉ ሲያዘግሙ ከመቆየትዎም አንጻር አርባውንም ገጽ አንድ በአንድ በመፈተሽ እጥብቁ ሚስጥር ላይ ለመድረስ እየጉዋጉዋሁ አንብቤ ምንም ውሃ የሚቁዋጥር ሚስጥር ሳላገኝ ቀርቻለሁ። ምንም እንኩዋን ተስፋዬ ከ ኤርትራ መንግስት ሰዎች ጋር ያደረገውን እና የሚያደርገውን ግንኙነት ሊጠቁሙ የሚችሉ የ እጅ ጽሁፎች ቢቀርቡም እንኩዋን። በሌላ በኩል የሚስጥሮቹ አቀባይ ማለትም የተስፋዬን ዶክመንቶች ኮፒ በማድረግ ለዳኛው ያቀበለው ግለሰብ ተስፋዬም ሆነ ወልደሚካኤል እኔም ሆንኩኝ ሌሎችም በሃገር ወዳድነቱ የምንወደው ወጣቱ አለማየሁ መሰለ በተራ የወዳጃሞች ጸብ እና አለመግባባት ሳቢያ የግለሰብን ሚስጥር ለሚዲያ ፍጆታ ከማብቃት ይልቅ አንድ ሁለት ብዬ የምዘረዝረው በአለማየሁ ላይ የተሰነዘረ በቂ ጉዳይ ነበረ ግን አለማየሁን በጠበቅኩት መንገድ ሳይሆን ባልጠበቅኩት አቅጣጫ አገኘሁት። ይህ በውስጠ-ታዋቂነት የማልፈውን ጉዳይ አለማየሁ ቢያነሳው ብዙ ሊያነጋግረን በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች በሸንጎ እና በ አደባባይ…በሚዲያ እና በሌሎችም መድረኮች የተለዩ ሃገር ወዳድ የሃገር ተቆርቁዋሪ የሚመስሉንን ሰዎች ማነነት መፈተሽ እና መረዳት በቻልን ነበረ።

ይልቅም ከዚህ ይልቅ አለማየሁ አንድ ሁለት ጉዳይ ያልኩዋቸውን ነጥቦች በማንሳት አንድ በአንድ በመረጃ አስደግፎ ቢያቀርብልን ኢትዮጲያዊ ነን እያሉ በህዝብ ሚዲያ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው የግል ጥቅማቸውን የሚያሳድዱ ግለሰቦችን መረዳት በቻልን ነበረ። ይህንን ሳስረግጥ… በሌላ በኩልም አለማየሁ መሰለ በምርጫ 97 በሱ እይታ ታይተው እና ተሰምተው የማያውቁ ግን ሌሎች ያልቃኙዋቸውን እውነታዎችንም ባስቃኘን ባስጎበኘን ነበረ።

ወደ ተስፋዬ ጉዳይ ስመለስ ከአመታት በሁዋላ ዛሬ እየተነሳ ያለው የቡርቃ ዝምታ ጉዳይ ነው። በቡርቃ ዝምታ መታተም ምክንያት በ ኦሮሞዎች እና በ አማራዎች መካከል በቀጥታ በታሪኩ አማካኝነት የተከሰተ እልቂት እና ግጭት አለ ? ይህንን የሚነግረኝ ካለ መልካም ነው። ምክንያቱም የቡርቃ ዝምታን ጦስ የመስቀል ጦርነት ልበለው የ እርስ በ እርስ ግጭት ማን ነው የሚያሳየኝ ? ይልቅስ ሃረርጌ አካባቢ በምትገኘው ጨለንቆ ከተማ በመገኘት በምኒልክ ዘመን “ሃርከ ሙራ…ሃርመ ሙራ” ብለው በሚጠሩት ዘመቻ ያኔ በዘመኑ ኢትዮጲያውያን ካልነበራቸው የህዝብ ብዛት ላይ ተበድረው መሞታቸውን እና መጨፍጨፋቸውን በማወጅ በመታሰቢያ ፕሮግራሞች ላይ አማራዎች የ ኦሮሞ ጠላት ተደርገው እንዲቆጠሩ ሲሰብኩ የነበሩ የመንግስት ባለስልጣን ዛሬ ምንም ሃጢያት እንዳልሰሩ በተቃዋሚነታቸው ብቻ ሲከበሩ ሲታፈሩ እናያለን። ትላንት ያንን አደረጉ ዛሬ ደግሞ ተጸጸቱ ይሁን። ደራሲ ተስፋዬ ገ/አብ ስዬ አብርሃን ደጋግሞ መተቸቱ እንደ ስህተት እና ለሻቢያ እንደመስራት እየተቆጠረ ከስዬ ጎን የሚሰለፉ ደጋፊዎች ማፍራት እንዲቻል ዘመቻ ከተከፈተ ከአንዳንድ ድረ ገጾች ያስተዋልነው ቢሆንም ዳኛውም ይህንኑ ጉዳይ በድጋሚ ተመላለሱበት። ስዬ አብርሃ ዛሬ ነው የፍትህ ሰው መሆኑ የታወቀው ? ወይንስ ያሳተመው መጽሃፍ ላይ ፍትህን የሚወክል ሚዛን ስለገሸረልን ? እርግጥ ነው ወያኔ በስዬ ላይ የፈጸመው የፍትህ ሂደት የሚተች ጉዳይ አለው። በአንድ ጀምበር የጸረ ሙስና ክስ ዋስ እንዲያስከለክል መቅረጹ ወያኔን እንድተቸው ያደርገኛል። ግን ስዬ በጊዜው ከነዘር ማንዘሩ እስከ አንገቱ ድረስ በሙስና ተዘፍቆ እንደነበረ እማኝ አያስፈልገውም። ሌላ…እርሱ የመከላከያ ሚኒስትር በነበረበት ዘምን አይደለም እንዴ በሃረርጌ ክፍለሃገር በደኖ እንቁፍቱ ገደል በርካታ አማራዎች ከነነፍሳቸው የተወረወሩት ብዙዎች ያለቁት ? በአርሲስ የተፈጸመውን እልቂት እንረስዋለን ? ስዬ በጊዜው የሰጠውንም ምላሽ በተለይ የነጻው ሚዲያ ልጆች ታውቁታላችሁ። ጎበዝ ልብ በሉ እኔ ሰዎች ተስፋዬ ላይ አገኘን የሚሉትን ሃጢያት እየሸፋፈንኩ አይደለም።
ተስፋዬ ገብረአብ ኢትዮጲያዊነኝ እያለ ሃገሪቱን የሚገዛው መንግስት የለም አይደለህም ብሎ ካበረረው ታዲያ የ ኤርትራን መታወቂያ መያዙ ለምን ያስገርመናል። በግድ ዜግነታችሁን ሳታጡ ገንዘብ ከፍላችሁ ለሰው ሃገር ልትሰሩ…ልትታመኑ…ቃላችሁን ልትጠብቁ እና ልታከብሩ መሃላ ገብታችሁ የሰው ሃገር ፓስፖርት ይዛችሁ እንደገና ኢትዮጲያ ኢትዮጲያ እያላችሁ የምታደነቁሩን ባለሁለት ቢላዎች አላችሁ አይደለ እንዴ ? በተጉዋዳኝ በምርጫ እጦት የሰው ሃገር ዜግነት ወስዳችሁ ከሃገር ሃገር እየተንከራተታችሁ ለ ኢትዮጲያ ቁዋሚ ጠበቃ የሆናችሁ ታማኝ ኢትዮጲያውያን እንዳላችሁ ግን ልመሰክር እፈልጋለሁ። ስለዚህ ግን አስገዳጅ ምክንያት ሳይገጥማችሁ ደግሞ የሰው ሃገር ዜግነትን የምትወስዱት ለመንቀሳቀስ ከሆነ ከነ የሚያስከፍለው ዋጋ ባላችሁበት ሃገር ትራቭል ዶክመንት ማግኘት ይቻላል። ለምን የተስፋዬ ኤርትራዊነት ይገርመናል ለምን ይደንቀናል። ተስፋዬ ቢሾፍቱን ስለተወለደባት ቀጠሮ ይዞዋል። የ እናት አባቱ ሃገር ደግሞ ኤርትራ መሆንዋን ገልጾ ቀይ አበቦችን ሊጽፍ አስቦዋል። እኔ በበኩሌ የኢትዮጲያ ተቃዋሚዎች በ ኤርትራ እየታገሉ ነው እንደግፋቸው እያላችሁ ስታበቁ ተስፋዬ የ ኤርትራ ሰላይ ነው ብላችሁ የምትነዙ ሰዎች ትገርሙኛላችሁ ከዚህ ይልቅ ልንንቀሳቀስበት እና ልንሰራበት የሚገባን ጉዳይ እያለ በግለሰባዊ ጉዳዮች እንደዚህ መሽቀዳደማችን ምን ያህል የገዢዎቻችንን እድሜ እንደሚያረዝመው ማን በነገረን። ለመሆኑ ኢትዮጲያ ውስጥ ያለው የዜግነት ህግ ምን ያህል እየተሰራበት እንደሆነ እና ዜግነት ሰጪው እና ነሺው ማን ሆኖ ነው ኢትዮጲያዊ ነኝ እያለ አታለለን ምናምን የሚል የቂላቂል አስተሳሰብ እያመጣን ለፖለቲካ ማጣፈጫ የምንጠቀምበት ምክንያቱ ምን ይሆን ?…።
ደግሞስ በአሃዳዊ የመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ የመንግስት ባለስልጣናት በደም ለተወለዱባት ሃገረ-ኤርትራ በድብቅ ሲሰልሉ በተግባር ተገኝተው የነበሩበትን ሂደት ለማንሳት ለምን አልደፈርንም ?…።
ሲጨረስ…በመጨረሻም
(የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ)ዳኛ ወልደሚካኤል የተስፋዬን የ ኤርትራን ሰላይነት መሰረት በማድረግ ቀጣዩ መጽሃፉ እንዳይነበብ እኛም ኢትዮጲያውያን እንዳናነብ ሲያስገነዝቡ በጽሁፋቸው ተመልክተዋል። ነገር ግን የ እሳቸውን የዋህነት ወይንም ሞኝነት ልበለው ያስገነዘበኝን አንድ ነጥብ እዚህ ላይ መጥቀስ ግድ ይለኛል። ለመሆኑ የተስፋየ ገ/አብ አዲስ መጽሃፍ የስደተኛው ማስታወሻ ነጻነት አሳታሚ የማን ነው ?…እርሳቸውስ በዚህ በስደት አለም በኔዘርላንድ ሲኖሩ የየትኛው የፖለቲካ ድርጅት አባል ናቸው ?…ለምታውቁ ሁሉ እና ለራሳቸው ለ ዳኛ ወልደሚካኤል እተወዋለሁ።/በ እርግጥ አሁን ነጻነት አሳታሚ እና ተስፋዬ ተፋርሰው ህትመቱ በነጻነት አሳታሚነት መታተሙ ቢቀርም/። እንዲሁም የተስፋዬን የግል መረጃዎች አሳልፎ ለዳኛ ወልደሚካኤል አቀበለ የተባለው ወጣቱ ትንታግ አለማየሁ መሰለ እርሳቸው አባል ከሆኑበት የፖለቲካ ድርጅት ጋር እና የዚሁ ድርጅት አቀንቃኝ ከሆኑ ጥቂት ጋዜጠኛ ተብዬዎች ጋር ምን እና ምንድነው ?…ይሄንንም ለ አለማየሁ እና ለራሳቸው ለዳኛ ወልደሚካኤል የምተወው ጉዳይ ይሆናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕዝብ ሆይ! እንደማመጥ እንጅ! ጋሰለ አረሩ፤ አዴፓ ብአዴን፤ ብልጽግናም ይህ አድግ ነው!  

ማንኛውም ኢትዮጲያዊ ይህንን ጽሁፍ የሚያነቡ ሁሉ ለዚህ የጽሁፍ አቅራቢ ለ እኔ እንዲገነዘቡ እና እንዲረዱ የምፈልገው ነገር ግልጽ እና ግልጽ ነው…ይፋ እና ይፋዊም ነው። ማንም ለሃገሩ እንደሚቆረቆረው እኔም ለሃገሬ እቆረቆራለሁ በተመሳሳይ ሃገሬን እና ህዝብዋን የሚከፋፍሉ ዘረኛ ተግባራትን እቃወማለሁ። በዚሁ ልክ አስመሳይ እና ሰዎችን በግለሰባዊ ተግባራቸው ያለምንም ምክንያት የሚጠሉ እና የሚዲያ ግለሰቦችን አጥብቄ አወግዛለሁ። ይህ ብቻም አይደለም ለ ሃገር ተቆርቁዋሪ መስለው ህዝቡን ሃገር ወዳዱን ህብረተሰብ የሚያደናግሩትን የተቃዋሚ አይነት ካባ የለበሱ ግን ከወያኔ ምንዳ የሚወረወርላቸው ያሉትን ፕሬሶች እንደ መሰል የሙያ ባልደረባዎቼ በቸልታ …በትውውቅ የማልፍበት ምክንያት አይታየኝም። በቀጣይ በድፍረት ከነ ሚዲያዎቹ ስም እና ድብቅ ታሪካቸው ኦ ጋዜጠኛዎች በሚለው ጽሁፌ እመለስበታለሁ በሌላ ጽሁፍ ማለት ነው። መቼም የጀመርከው ጉዳይ ሌላ ወረድ ብለህ ያነሳሕው ሌላ የሚል ሃሳብ እንደሚሰነዘር አውቃለሁ ግን ምክንያት አለኝ።

እነ ዳኛ ወልደሚካኤል ያነሱት የተስፋዬ ጉዳይ በሃገር ላይ ችግር ያመጣል ተብሎ በግልጽ ከታመነበት እኔም የሃገር ጉዳይ ያገባኛል እና ሃሳቡን እደግፋለሁ ተስፋዬንም ሆነ ማንንም አወግዛለሁ። ቁም ነገሩ ከግለሰብ ጉዳይ እንውጣ አይነተኛ በሆነ መልኩ ለለውጥ የሚታገሉ ድርጅቶችንም ሆነ ግለሰቦችን አናግዝ። በዚሁ ልክ ኢሳት የተስፋዬን ጉዳይ አላራገበም ብለው ነገር የሚጎነጉኑ በፊትለፊት የ ኢሳት ደጋፊ መስለው ሚዲያውን የሚሠልሉ ዘረኛ የሚዲያ አካላትን እረፉ ኢሳት ስራውን ይስራበት ልንላቸው ይገባል። በበኩሌ እያስመሰሉ ዳር ዳሩን እየተራመዱ አንዳንዴም መሃል ሰፋሪ ተቆርቁዋሪ መስለው የሚንቀሳቀሱ “አዛኝ ቅቤ አንጉዋቾች” ስለ ኢሳት ለመናገር ከሚዳዱት ይልቅ እኔ ለ ኢሳት ቅርብ የሆንኩ ብተችም ምክንያት ያለኝ ኢትዮጲያዊ እንደሆንክሉ ይታወቅልኝ ስል…በቅዱስ መጽሃፍ እንደተጠቀሰቸው ከጻፎች እና ፈሪሳውያን ብሎም ከቀራጮች ይልቅ መቀነትዋን ፈትታ አስር ሳንቲም አስራት እንዳበረከተችው እኔም ከስደት ሃገር እንደመበለቲቱ የአቅሜን እያደረግኩ መሆኔን ስናገር ኢሳት እንዲስተካከል ካለው ይልቅ ይበልጥ እንዲሆን ስተች በባለቤትነት መንፈስ መሆኑን አስረግጨ በዚሁ ልገልጽ እወዳለሁ። ስለዚህ ሌሎቻችሁም ይህንን ልትገነዘቡ ይገባል። እውነት አለኝ የሚል ደግሞ ተደብቆ ሳይሆን በይፋ ሃሳቡን መሰንዘር ይኖርበታል ባይ ነኝ። በነገራችን ይህንን ጽሁፍ እነ ኢትዮ ሚዲያ እንደማያወጡት አውቃለሁ እና ወደዚያ አልሰደውም። ስለሆነም የ ኢትዮጲያ ጉዳይ ያገባኛል ብለው የሚቆረቆሩ አካላትን በ ኢጎ ስሜት የለም ዓያገባችሁም ውጡ የምንልበት ጥልፍልፍ አካሄድ መቅረት አለብት ልክ “ውጻዕ አይትበሎ ከምዝወጻዕ ግበሮ” እንዲሉ ብሂል መቅረት አለበት ባይ ነኝ። ሶማሌዎች እንደሚሉት “ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም” አበቃሁ ሰላም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዐብይ አህመድ ሰለስቱ ማንነቶች  (ዐብይ ሰባኪው ፤ ዐብይ ተዋኒው እና ዐብይ አጼ በጉልበቱ) 

33 Comments

  1. ይህች አገር ከሚገባው በላይ በደል የተፈጸመባት ናት፡ ክህደት ሞልቶ የተረፈባት፣ አገርን ክዶ ግለሰብን ማወደስ የማያሳፍርባት እየሆነ የመጣባት የግፍ አገር ከሆነች ቀይ ሽብር አራት አስርት አሳለፏል። አገርን መካድ የማያስነውርም እየሆነ የመጣው ከጣሊያን ወረራ ማግስት እነ በላይ ዘለቀን፤ በአደባባይ ገሎና አንጠልጥሎ ባንዳ መሾም መሸለም በመጀመሩ ነበር። እናም ባንዳነት አያስጠይቅም ወይንም አያስነውርም።፡የግሩፕ አይነትና ብዛት አይቶ ከመንጋው መደባለቅና አገር መካድ ይሁነኝ ተብሏል። ወያኔና ሻብያ አገራችንን ገንጥለውና አስገንጥለው የባህር በር አልባ ካስደረጉን የአንድ የአንድ ሰው እድሜ ሳይቆጠር ግማሹ ከወያኔ ጉያ ሌላው ከሻቢያ እቅፍ ሊገባ ሲከጅል አይንህ ላፈር ሳይሆን አሁንም ያው ባንዳነት የሚያስመሰግንበት ጊዜ በመሆኑ አበጀህ እያልን ነው። ይህ ጸሀፊ ተስፋየ አገር ክህደት አልፈጸመም ሊለን ይከጅላል። ግን ምን እንበል አሁን ከሆነ የዘር አጥንትና ደም ተቆጥሮ ሆነ ፍርድ የሚሰጠው ያው እንደወያኔና ሻብያ ማለት ነው። አባመላ ሲመጣ ከወያኔ ወጥቶ እቅፍ ነው የተቀበለው ምን እሱ ብቻ፤ የፖለቲካ መሪ እስከመሆን የደረሱት ሁሉ ከወያኔ ተንደርድረው አርበኛ ሊሆኑ ከጀሉ። ያሳያንስ ከሻብያ ጉያ ይዘውን ሊገቡም እየተንደረደሩ ነው። አሰቦትን፤ አርባ ጉጉን፤ በደኖን ካላስታወስን ተስፋየን እንዴት ልናውቅ እንችላለን፧ ወይንም ያው እንደሻቢያና ወያኔ አማራ ነው አንድ ቁጥር ጠላታችን ካላልን ማለት ነው። ለነገሩ እኮ በውስጠ ታዋቂ እየተባለ ነው። የዚህ ጸሐፊ ድፍረት የሚገርም ነው። የቡርቃ ዝምታ የአገር ደህንነት ጉዳይ አይደለም ምክንያቱም እንደአባባሉ በአንድ ዘር ላይ የተነጣጠረ ወይንም ኦሮሞኛ ተናጋሪ ወገንን ከአማረኛ ተናጋሪ የሚያጋጭ እንጅ። ደግሞም ነፍጠኛ እንደሚለው ተስፋየ ማለት ነው። ጋዜጠኛ አለን። የገርማል የወልደአብ ወልደማሪያም ልጆች ጸረ ኢትዮጵያ ጸረ አማራ ናቸው። እነሱም ግማሾቹ አዲስ አበባ ተቀምጠው ይገዛሉ ሌሎቹ አስመራ። የሰሞኑ ውል የነፍጠኛን አከርካሪ ሰበርን። የመቶ አመት የቤት ስራ ሰጠን ከሚሉት ጋር መሆኑ ያጠያይቃል። ጋት ገፋ ቢያደርጉ እንኳን ባልከፋ። ግን ያው ከዚያው በመሆኑና ሌላ የትግሬ ድታጣቂ የዘውልን ሊመጡ መሆኑ ግን ያሳስበናል። ባጭሩ ተስፋየን ያየኽበት አይን የዘር መነጸሩን አውልቀውና ጋዜጠኛም ከሆንህ ሙያውን አጠናክረው። ያኔ የአገር ክህደትነቱ ይታይሀል።

  2. RIP, Tesfaye is gone.

    Question for the writer
    How hypocrite do you sound when you call your self a journalist while others not?

  3. Daniel
    Your Piece Is So Stupid.What is not Good about ExposIng A Guy Who Is A Spy Working To Undermine EthiopiA And Create Bloodshed In The Country. Dagna Wolde MichaeL Is A Great Patriot. He Did A Marvelous Job. YouAre Crying Becsuse Your Man Has Been Exposed And BecomE Naked.

  4. Some people can never learn. Journalist Daniel, what the hell are u talking about? We can’t trust shabia. We know what they want. As opposition it is good to get an external support. But you have to know the nature of youe external supporter and then decide the nature of support you can accept. You can accept money from shabia but you can’t base your office and military in Eriteria under shabia. SHABIA AND WEYANE ARE SOWRN ENEMIES. THEIR ULTIMATE OBJECTIVE IS TO DISMANTLE ETHIOPIA. They may let you in but I asure you you can’t leave alive the ‘father land’ if they make sure that u are for Ethiopia unity!! G7 is making a historical mistake.

    Tesfaye G/Ab is NOT an ETHIOPIAN!!! He was with weyne spying weyane and Ethiopa for shabia. His articles are aming at creating animosity between Ethiopians at large and Oromos & Amharas in particular.
    Why you try to make it personal? Personal for whom?? We know it before and we see it now with evidence.

    Now, if ESAT. is not taking this seriously then the 250000.00 USD from shabia is paying back

  5. Damtew,

    Am I sensing that the Amhara elites have lost all hopes in their dream of coming to power again? The arguments that I read these days do not seem to come from cultured group, because they are expected to act as shrewedley as they are used to. Neftegna Fukera does not have much of a space now. By the way, in the same length that you mentioned about non-investigated “Teret teret” about Bedeno, Arba Gugu you should also talk about Water, Anolle, Boru Meda… and thousands of garrison towns that history has recorded. Some times I wonder whether at the end we will really live together.

    I have due respect to the author of this article. he makes a lot of sense than Neftegna thugs and hooligans. By the way Neftegna is now a medal of honor according to Mesfin W/ Mariam. So we will be using this term with the permission of the grand mufti.

  6. egziabher ejochihn yibark ur areal journalist.negerochin yemitagenazib.egna ethiopiawuyan telatochachinin yemanak miskinoch nen.sint yemiwera neger eyale silegileseboch tabokalachihu.ande Jawar ande Tesfaye.hager mewuded ethiopia ethiopia bemalet sayihon betegibar bemasayet newu.zemenu yetegibar newu zim bilachihu afachihun atikfetubin.

  7. Tesfaye has never been a journalist nor the write of this article. Stupid is what a stupid does, and truly Daniel is very stupid.

  8. ይፋና ይፋ_አንድና አንድ በራሱ መለስን ትመስላለች፡፡ ኢትዮሚዲያን በግምት ነው የተፈራው ወይስ ያውቀኛል ብለህ ፈራህ?

  9. Daniel
    what a hypocrat and stupid journalist you are? The Judge Exposed TESFAYE with a material evidence even if the article is long it has documents showing the letters Tesfaye wrote to Eritrea Embassy and what do u need more than this????? you are a disgrace to Ethiopian journalists to attack Judge Wolde michael for expressing his view on TESFAYE based on the hard facts he found out.
    YOU MUST BE ONE OF SHABIA sponsored so called Jouranlist to go out of your way to defend TESFAYE KORIT who has been relentlessely working to incite violence and conflict between OROMOS and AMHARAS.
    it seems that you have a problem of understanding facts if not TESFAYE BOOKS will not be hard to understand for any layman
    shame on yourself for calling a journalist who defend the freedom of expression of others kkkk

  10. thankssssss denial , God bless you. totally I agree with you. if we want to go back, seye was a criminal. seye was tesfay’s boss when he wrote ye burka zemata. forget Alemahayu and judge woldemichall .

  11. What’s wrong with you the writer ? I don’t have any knowledge about you how ever, you seems like another ” tut nekashi”.

  12. Mano
    Did you see any disrespect for the author in my commentary view? You see; I did not insult any Ethiopian or group of Ethiopians as you did. Just go back to your comment, and look what you said about Amharic speaking Ethiopians. To me I dont see any difference between Tesfay Gebreab, you, and other ethnocenteric groups.you obtain the same view as Tesfaye for that matter Sebhat Nega and Isayas Afeworki. In the Ethiopian politics today, those gang-up against Amara existence are ethnic nationalists. The so-called Journalist (Daniel Gezahegn) in this writing telling to the world that instigating ethnic clash is okay. I am not a journalist or I cannot tell ethical standards of journalism; but as a lay man as I am, fueling-up hate on one group by the other is not a duty, and responsibility of journalism. It is a crime, and the person held responsible for any lose of life. on the other hand what judge Meshasha did is honorable. Mamo, anti Ethiopian forces including OLF/TPLF/EPLF never had political differences; simply they cannot stand together because of power and dominance. Woyane and Shabya have a common enemy (Ethiopian nationalism), a common vision (distraction) for our country. Just look back the 21 years history, and beyond.

  13. FROM GETACHEW REDA (Editor Ethiopian Semay)
    Before I start my comment. I like to thanks the Habesha for getting his website to be used by Ethiopians. I am not seeing now the Ethiopian enemies flags like OLF, EPLF and so on…be posted in every poisonous anti Ethiopia article that posted who claimed themselves not Ethiopians. This website was intoxicated by OLF flags. awful! But now, so far so good. How long it will continue such good Ethiopian position – wait and see. But, I give him credit for cleaning his website so good. No OLF flag so far posted on their website. Thanks Ze Habesha for let us breath Fresh Air again! The moment it change, I wil be out form here. But so far, good job.

    Let me take you to my comment on Daniel GezaHeng. Here you go. These are the journalists, who called themselves “journalists” whom I was talking about all these years. This fellow by the name Daniel GezaHeng is now ‘openly’ defending the Eritrean black snake’s poison, the black snake what we called it in Tigringa ‘MENDELAY TEMEN’. Tesfay GebreAb is a black snake delivered and installed in Ethiopia by the evil ‘Isyas Afewerki’ to poison us. Here there is a hypocrite journalist who is telling you all Ethiopians, in particular to Tesfaye GebreAb’s victim ‘the Amhara society’ to continue stand on the side of their enemy and get poisoned more.

    You might wonder how many people in this current world would happily vote for Hitler/Nazi if they get the chance to vote if the Nazi stood for government (Europe/America). In similar ways, one of the few Nazi party in the Ethiopian ground are parties called OLF- and TPLF (add to that EPLF in Eritrea). They have followers, no matter how massively these three organization involved in human atrocity and crime. Nazi followers never believe their party is criminal. These three parties followers also believe their organizations never committed ethnic cleansing or mass murder due to their policy of hate towards a given ethnic/Amhara.

    So is here a journalist defending Ye BurQa Zimita and Tesfaye G/Ab for his hateful and subversive acts against our country and our people the “Amhara”, regardless, many writers already dealt about Ye BurQa Zimita and its consequences against Amhara society who lived or still live in Oromo localities:-on which by the way the ‘Eritrean snake’ made him got an honor title of “OBOO” from the OLF for writing that ‘book of hate’. You would not have to look to far to find somebody to support Nazi type writer. Here you have one as this journalist defending Tesfaye GebreAb who loves his fiction “Ye BUrQa Zimita” (though Tesfaye told us it was not fiction- it was made from real actors” (Mein Kampf).

    As Al Mariam recently wrote on one of his weekly commentary rightly wrote “As a defense lawyer, I know all too well that there is no possible defense against ghostly lies and malicious falsehoods” . Daniel Gezaheng is now challenging Ethiopians to bring any evidence that YeburQa zemita brought or would trigger any ethnic cleansing as the result of that hate full book. Not to mention, challenging judge Weldemichael and Tintag Alemayohu for the recent document that expose Tesfaye’s love and support for the Nazi party in Eritrea ‘EPLF’ evidence gotten from his hand writings and the support he got from the Eritrean Nazi party for his love as a reward.

    The kind of journalists like Daniel Gezaheng defending Nazi authors like Tesfaye GebreAb from Eritrea who use Ethiopian citizen orally to cover up his Nazi works by undermining two Ethiopians who defend their country form band infiltrates is something serious. Daniel is telling you, being banda is benign to Ethiopia and its future. This kind of elements have the audacity to defend and a Allowing Nazi type hateful propaganda in our society as fruitful is no less to advocate or be advocate for Gay in Ethiopia. We all know that Gay society is now getting ground in Ethiopia because of TPLF and foreign subversive groups against Ethiopia in order to corrupt our Ethiopian ethics. Someone sent me via email (I for got who that journalist was) that a certain journalists stood for Gay rights in Addis Ababa. And I oppose this destructive anti Ethiopia moral and ethics subversive act who defend Gays claiming they have the right to be Gay. What right are we talking about? Those gay rights groups may make a lot of noise, but they are banda elements (some are sent from Eritrea to ruin our society). I and millions of our people who find homosexuality disgusting and immoral. Being gay is nothing to be proud of. These men have chosen a lifestyle of sexual deviance that, once you’ve crossed the line and become homosexual, soon leads to other forms of deviance. It is a short step from homosexuality to pedophilia and other forms of deviant behavior.

    So, my people, do not be soft head to be pumped easily by skilful writers. Reject those who preach you day in day out that ‘banda’ are okay. Confront those if they subvert our pride and our society as that writer above advocated for Tesfaye GebeAb as benign.

    My hat to the judge Weldemichael (though I have some reservation about his some political positions in the Diaspora) and to Tintag Alemayohu (though I have no idea who this fellow is besides he was political prisoner before in Addis). You people need to give credit to these two good Ethiopians on this particular work for exposing the poison of the EPLF ‘black Snake’ Tesfaye Ge/Ab . You will see the disunity of Ethiopia even worst than what we are now- because of such journalists defending bada elements inside us. You did not see yet. The issue of OLF/EPLF inside Ethiopian politics is the main reason for our disunity. Some want to advice us and defended their poisonous mission as benign- on the other side we the “Ethiopian Unity Force” (EUF)- who are victims of Nazi parties called EPLF , TPLF, OLF” should stand and be watchful against band intrusions in our affairs. We have to reject all banda advocate agents, writers- no matter what they temporary change of tone sounds. The reason we allow political criminals and their agents still fool our society is because, we allow them to go on with no consequences for their crime. Until society stand, confront and punish those criminals they will continue infiltrate in our affairs. The opened gate we allowed so wide for over 40 years where all kind of enemies got access to exploited our sovereignty must be shut close now! Close the door regardless their hypocrite and treacherous tones sound sweet to your ear. You can’t defeat the enemies while your door is wide open to them to exploit you and brain wash you and even murder and poison you. Spy means intelligent gathering. Tesfaye is intelligent worker for OLF and EPLF . Spies tend to come from variety background with variety of skills, that include foreign language, culture, education, computer skills, writing skills, and so on…. Unless, documents found like Tesfaye’s resnt shame- it is hard to know who is a spy among you. If you have experience, you can tell by their writings or talks or style –sugar coated advocacy. Thanks Getachew Reda (Ethiopian Semay)

  14. what a confused understanding, how come you say this personal? i think you need to clear up you mind about what is to be said personal and which is not. dinkem journalist!!!

  15. Dani Gezu The Atlanta, the writer of this article, is one a hell of messed up dude or he is in the scum bag like Tesfaye from “The Father Land”. Keep this peevish analysis to your self.

  16. Daniel….you are great and fair journalist..i adore you for you’r understandig the poletical hypocrats internet heros. The thing all about Tesfaye GAB is only to divert the poletical attention Ginbot 7 to mislead of trust armedstruggel supported by Shabiya. when this guys tell us about Tesfaye’s spy for Shabiya but they forgot to tell us that Abrhaha Belay (ethiomedia) , Dawit Kebede (Awrambatimes), are Woyanes and dont forget the judge woldemichael meshesa have a blood in his hand at the time when he served Woyane and just becouse he defected the woyne dosen’t make him hero, ( he is ferde gemdel danga ).

  17. I thank profoundly the patriot Ethiopian Getachew Reda for his enlightening comment. In the same vein I applaud Judge Woldemichael Meshesha for exposing, based on irrefutable documented evidence, the Eritrean spy Tesfaye Gebreab as a traitor

  18. >>>ተስፋዬ ገብረ እባብ(ጺም ያለው እባብ) ጺሙ ሲበር ..ዳንዔል ገዛኽኝ ከአትላንታ በቡታንታ በግልጽ መነጽር ተደብቆ መጣ በለው!ይህ እንግዲህ ከአረና ትግራይ ተወካይ ከአብርሃ ደስታ ከመቐለ ቀጥሎ …የአትላንታ እስታር ባክስን ወከወሎ የተማረረ ጋዜጠኛ መሆኑ ነው። አዎን! “አብረሃ ደስታ ገና ብዙ የሻቢያ (ሹምባሽ)ሰላይ ከውጭም፣ በፌስ ቡክም፣ በቲቪም፣በሬዲዮም በድረገፅም፣ ከውስጥም፣ በሥልጣንም ላይ፣ ስንት አለ መሰላችሁ!?ብለውናል።
    እኔም ፅሑፋቸው በተለጠፈበት ሁሉ፤ ጎልጉል…freedom 4 ethiopia..አቡጊዳ ድረገፅ መልስ ሰጥቻለሁ አንቡ! ስለሠላም፣ ስለሀገራቸው ባሕልና ክብር፣ ስለመብታቸው የሚያውቁ ሁሉ ይበርቱ!!!

    *አሁን ከጉሮኖአቸው ብቅ ብቅ አሉ። አቶ ጌታቸው ረዳ የተባሉት በአንድ ጽሑፍ ላይ በሰጡት አስተያየት ባንዶችና ወታቦአቸውንም ጠቁመዋል አዎን! ከዚያው አንገታቸውን ብቅ አደረጉ! ያዘው… የተስፋዬ ገብረአብ ጸሐፊነትና ምሁርናት የሚያንገበግባቸው “የማክዶናልድ ጠበብቶች!” ወይንም በአቶ አብርሃ ደስታ አገላላፅ “ተስፋዬ የሚጎዳ ሥልጣን የለውም አልጨነቅም ‘ባንዳና ባለሥልጣን’ ቢሆን ኖሮ እኔም እቃወም ነበር ይሉና ጎበዝ ጸሐፊ ነው ይላሉ ” ፅሑፍ የጭንቅላት ጨዋታ ነው” በማለት። ለዚህም ነው የኦሮሞን ልጆች የገዛ ወተታቸውን እየጠጣ፣ አይብና እርጎ እየመጠመጠ፣ ኤርትራ በገባችበት መቀመቅ እየገፋቸው የቡርቃ ዝምታ ሲል የአሰተሳብ አድማሳቸውን ያንቦረቀቀውና “ኦሮሞ ፈረስት ጆሌ ብሸፍቱ!”ሲል አሸፈታቸው በኤርትራውያኖቹ ወገኖቹ የኦሮሞን መሬት ያስቸበችብላቸዋል!!!

    *ሰሞኑን የመጽሐፍ ንግዱን ሊያጧጡፍ “ኢሬቻ አከባባር በዐል ላይ ተገኘሁላችሁ! ይላቸዋል ግን እሱ ኤርትራን ወከሎ ሲገኝም ባህልና አልባሳቱን ለማየት ብዙ የውጭ ዜጎችም በውሃው ዳር ተገኝተው ነበር። ጥሩ ነው። ይህ ለጆሌ ቢሸፍቱ ጥቅሙ ምንድነው? እራሱ ሲመልስ” ብዙ የማታውቁት የኦሮሞ ባሕልና ታሪክ አለ እፅፍላችኋለሁ ይልና የንግድ ማስታወቂያ ይለቃል። ዘመን መለወጫችሁ የመስቀል ቀን ይሁን ይላቸዋል!። እንግዲህ ሆ! ሆ! ይላሉ። እሱም ንግዱን ዘመዶቹም ስልጣናቸውን የሚጋራ የለም ኦሮሞና አማራ ደመኞች ናቸውና!

    **>ይ>>ቀ>>ጥ>>ላ>>ል!!!!

  19. Getachew Reda,

    You will live lonely life and die a lonely death here in the USA. Your hope of seeing EPRP in power in Ethiopia is dead. There are far more alternative power sources than your dream.

  20. dear Getachew Reda
    you did a wonderful job exposing the so called journalist DANEIL he is one of the enemies of Ethiopia who dream day in and day out about the destruction of Ethiopia , Ethiopia has a lot of enemies like SHABIA, ARTERA, OLF, TPLF, etc and these groups are out to defend TESFAYE KORIT to help him write more hate and poison that will eventually destroy Ethiopia, The so called journalist DANIEL did not even say anything about the evidence which is the hand writing of TESFAYE KORIT.
    TESAYE KORIT is taking time to come up with an idea to defend himself he is now talking to his masters SHABIA how to get out of this mess and here we go stupid journalists and enemies of ethiopia are defending TESFAYE KORIT with out saying anything about the evidence presented against him(KORIT .)

    Thank you Mr Getachew and i want you to be careful for the incoming attack from the enemies of Ethiopia and SHABIA and Ethiopian bandas and if you happen to know WOLEDMICHAEL and ALEMAHYEHU please tell them to be careful in everything they do these people can come back to them even in their private life GOD PROTECT ALEMAYEHU and the Judge from the enemies of Ethiopia

  21. Daneal you are an attention sicker (ye attention timat yanawozehe) so called gazetegna nehe.

  22. Chill out my dear fellow Ethiopians. If our beloved country Ethiopia survived the evil menacing of the tplf champion meles zenawi, it certainly can survive the genocide instigator and agitator gebreab. Do not lose focus on this wicked group called tplf. Please focus on that. Especially now when it is becoming increasingly disorganized.

  23. shumbash Daniel ante merajaa neh enji gazetegna aydelehim!!! Tesfaye endehu mutual!!! ..wodajochu ende shumbash Daniel yalachihu asra huletun arbawn…awitulet!!!!….!!!….enante banda ye banda lijoch ye Ethiopia hizib baninobachihual!!!!…wutsa atbelo kemezewtsah gibero sil yenebere zare Ethiopiawi negn le Ethiopia etagelalehu yilenal!!!!….wuguz keme arios!!!!

  24. i have a quation for you guys who hate Tesfaye or you say he is a spy. if he is spy and work Shabia that mean the time of Weyanna is finished so whats your problem ? because you guys have not done nothing against Weyana for the last 20 years just talking . Arame hula

  25. Ante lemehonu yeman neger amelalash neh?, Tesfayeko andin biher kelelaw biher yemyakeyayim were be Ethiopia lay yeneza werega sew new gazetegam aydelem mesfertun balemuyawechun yiteyku getaw!, Tesfaye yalawekew and ewneta Asmera yalu balesiltabat Kibur ATO Esayasin chemiro ye arbega lijoch ena yelig lijoch mehonachewin new ( ertiran Ke Presidantu Eskil endemiwedat yetsafew) lemeweded aymesliwetim?

  26. ዳንኤል ገዛህኝ ጥሩ ጽፈህ ኢሳትን በተመለከተ አትንኩብኝ ማለትህ እና ለኢትዮ-ሚዲያ አልክለትም ምክንያቱም ጽሁፌን ስለማያወጡልኝ ያልከው የZeHabesha websiteም ቢሆን ምንም ልዩነት የለውም። እኔ በተደጋጋሚ ጽሁፍ ልኬለት ለማውጣት ፍቃደኛ አልሞሆኑ ያንተ ሽሽት ወዴት ወዴት አንተም ያው ነህ። እንደውም አንዳንዱ ትችት ከኔ ጽሁፍ መወሰዱን ተመልክቻለሁ። ኢሳትን አትንኩብኝ ብሎ ጋዘጤኝነት” ድንቄም ዲሞክራት ጋዜጠኛ?”

    • አቶ ኤርሚያስ ሽፈራሁ፡ከላይ በሰፈረው አስተያየቴ በመጨረሻ ይቀጥላል… ብዬ ሳልመለስ እርስዎ በመምጣትዎ አመሠግናለሁ። የምመለስበት ዋና ጉዳይ ይህ ግለሰብ እዚህ ያሰፈረው ሃሳብ የራሱ እንዳልሆነ ለማስረዳት ነበር። ሰው እንዴት በግልፅ መነፅር እራሱን ይደብቃል? እዚህ ያቀረባቸው ፅሑፎች በሌሎች ቦታ የተሰጡትን አስያየቶችንም ቃርሞ ነው። ተስፋዬም ይህንኑ ሥልት ሲጠቀምበት ቆይቷል …ቡና ቤት የሰማውን ፓል ቶክ ላይ ይተፋዋል፣ በድረገፅ ያነበበውን ለጋዜጣ ይረጨዋል፣ ከተጨቆኑ ብሔሮች የሰማውን ብሶት በልብ ወለድ መልክ በመፅሐፍ ለትውልድ ማባያ ይወጠውጠዋል፤ ከጓዶች የሰማውን ሚስጥር በትንቢት መልክ ይበትነዋል፤ እየፃፈ ይረጫዋል (እያንቦረቀቀ) ምድረ ፋራዎችን ያስጓራቸዋል። ጆሌ ቢሸፍቱ! ድሮ ጋዜጣ አዟሪ የነበሩ ዘመን አልፏል ብለው ጋዜጠኝነት ከእኔ በላይ የሚሉ ሕግም ባይኖር አሰልጥኖ በላካችሁ ሻቢያና ህወአት ሥም አደብ ግዙ እንላልን።”ተስፋዬምና የሜንጫ” የእውነት ቦንብ ሲፈነዳና ማንነታቸው ሲጋለጥ ቦንብ በከተማው ማስጣል ጀምረዋል። ድሮም ህወአት ታቀፎ የፈለፈለው ሀገር በታኝ ውጤቱ እርስ በእርሱ መጠፋፋት ነው።!! አንዳንድ አስመሳዮች ጥሩ ኢትዮጵውያን ያሉበትን ድረገፅ እየሰረሰሩ መጥፎ ነገር በመፃፍ ማዳከማቸውን ባለቤቶቹ በአስተያየት ሰጭው ምላሽ ቶሎ ሊገመግሙና ሊያስወግዷቸው ይገባል። ላለፉት ፲ዓመት በተሞክሮ ያገኘሁት ልምድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊጨምርበትና ሊያጋንነው ይችላል በውሸት ሰው ይቃወማል ለማለት አልደፍርም! እንዲያውም የተተቹት ግለሰቦች ግለሰቦችን እያሳደሙ፣ ሥማቸውን እየቀያሩ፣ ራሳቸው ደጋፊና የሀሳብ ተቃዋሚ ሆነው፣ ሲሞግቱን በማስረጃ አግኝተናቸዋል።ግን ሁልግዜም “እውነት ይመነምናል እንጂ አይበጠስም!! ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት ማለት እውነት ነው በለው!። ከምስጋና ጋር በቸር ይግጠመን

  27. Dniel tebeyew,

    Demo photohen tawetaleh. Mekabereh lay photoh bitay new yemishaleh. Mut neh
    Endesew aseb.

  28. dear daneal,I have never seen such kind of attantion monger personality throughout my life. mistehe ena lelijochihe bezihe bandanetehe endet linekuhe endemichelu saseb yedenkegnal.

  29. yehonke menesha ena medresha yelelehe kebe menged dehe!!! yesamba zenetafi maneneten yemataweke yematakeber banda nehe

  30. ስማ ዳንኤል
    በናትህ እመለስበታለሁ ያልከውን ጽሁፍ አትመለስበት ይህ እራሱ ሊያስመልሰን ነው።
    ለወደፊቱ ምንም ነገር ከመጻፍህ በፊት የጽሁፍህን ዓላማና ኢላማ ለይተህ ብትነሳ ጥሩ ነው። አርባ አራት ነገር ጠቅሰሃል፤ ሁሉም ግን እርስ በእርስ የሚጣረሱ ናቸው። ለተስፋዬ ስልታዊ ድጋፍ ለመስጠት ፈልገህ ወዲያው ደግሞ ተስፍዬ በራሱ እጅ ጽሁፍ የጻፈው ክህደት ትውስ ሲልህ በኢትዮጵያዊው ወገን የሚመዘዝብህን ጎራዴ ፈርተህ፡ 90 ዲግሪ በመታጠፍ ተስፍዬ የሃገር ጠላት ከሆነ እኔም እቃወመዋለሁ ብለህ አጎነበስክ። ጠላት ነው ተቃወመው።

    አጼ ምኒሊክ ፤የቡርቃ ዝምታ፤ ስዬ አብርሃ፤ኢትዮ ሚዲያ፤ኢሳት፤ህብር ሬዲዮ፤ዳኛ ወልደ ሚካኤል፤ አለማየሁ፤ ድህረ ገጾች፤ ምን ያልነካካሀው ነገር አለ..? አንዱም ግን የተስፋዬን አንገት ቀና አላደረገልህም። በተስፋዬ ላይ የቀረበው ማስረጃ ይግባኝ የማይባልበት ያፈጠጠ ያገጠጠ ነው። በን እሩ የዋለልህን ውለታ በብዕርህ ለመመለስ ያደረከው ጥረት አልተሳካም፡ እንዲያውም ሃጢያቱን ቆሰቁሰህ ለሌላ አራጅ ብዕር አቀበልከው።አንተም ራስክን ትዝብት ውስጥ ጣልክ። እድሜ ለአለማየሁ ተስፋዬ በኢትዮጵያዊው ዘንድ ላይነሳ ወድቋል። እኛ በወደቀበት ረግጥነው አልፈናል። አንተ ባይሆን ሳትረግጠው በማለፍ ውለታህን መመለስ ትችላለህ። ከወደቀበት ለማንሳት መሞከር ግን አንተንም እንዳይጥልህ ተጠንቀቅ።
    ጋዜጠኛው!!!!!

  31. ጋዜጣው ዳንዔል ገዛኽኝ ኢቺን ተረት ከሱማሌ በስንት ገዛኸው “ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም ያለው ሱማሌ በዚሁ ሳምንት ቦንብ አቀታጥሎ እሳት እሞቃለሁ ብሎ አዲስ አባባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሞተ! እወይ…!
    *በቀለ ሞላ እንዳሉት በፈጣሪ በሱማሌው ብለህ አትመለስ! ለምን አሁን የሌቦች ወታቦ ታውቋል። እዚሁ ተቀምጣችሁ የውሸት ባንዲራ እየወጠረ ወያኔ/ኢህአደግ/ህወአት ይላል!። እንኳን የኢትዮጵያን ችግር የራሳችሁ ስንት ያልተራገፈ እከክ እረስ በእርሳችሁ ተጋብቶባችኋል!? ዲያስፖራው ተጠልፏል እንዲሁ በደረቁ ይፎልላል በለው! ጋዜጠኞች፣ ፓል ቶኮች ፣ድረገፀች፣አይነበጎዎች ተጭበረበረባቸው፡ ገና አለ ገና ይመጣል…ይቦጠልቃል…ይነፋዋል…ድንቄም ፖለቲካ!! ሜንጫ ፈረስት በተስፋዬ ገብረእባብ መፅሀፍ ስያጭ የሚረዳው አሸባሪ ቡድን! ንፁሀን ድሃ እግር ኳስ አፍቃሪ ልጆች ሳይሞቱ በመቅረታቸው እግዝሐብሔር ይረመስገን!

  32. amaroch betam tigermalachu tesfeye ewnetin new yetsafew ewnet hule amaran endemimerew yetaweke new and neger laregagitilachu gin ye wend sira kalserachu amara shintam yemilew simachu ayifakim wendinet demo FB lay aydelem yalew bereha wetachu tagelu fb lay teret ena misale siltilu ke mitwilu

Comments are closed.

Share