ትንሽ ስለ ተስፋዬ ገብረአብ – አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

‘የተስፋዬ ገብረአብ ማንነት አጋለጠ’ የተባለውን ፅሑፍ አነበብኩት። ገረመኝም። ረዥም ነው። የአንድ ሰው ማንነት ለማጋለጥ አርባ ምናምን ገፅ? ተስፋዬ ገብረአብን ‘ያጋለጠ ‘ ፅሑፍ ለኔ ምንም ዓይነት ተጨማሪ መረጃ አልሰጠኝም።

ስለ ተስፋዬ ገብረአብ ትንሽ ለመፃፍ የተገደድኩት ምክንያት አንዳንድ የህወሓት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ‘የተስፋዬን መጋለጥ’ ምክንያት በማድረግ እኔ አንድ ነገር እንድልላቸው ስለወተወቱኝ ነው። አንዳንዴ’ኮ ጎበዞች ናቸው። ተፎካካሪያቸውን ማኖ ማስነካት ይችላሉ። እኔ ደግሞ ማኖ መንካት እወዳለሁ፤ (ማኖ ካልነካንላቸው ከስድብ ዉጭ ሌላ የሚያውቁት ነገር የላቸው)።

ተስፋዬ ገብረአብ ጎበዝ የስነ ፅሑፍ ሰው ነው። ፅሑፉን ለመገምገም ማንነቱና ስራው አያገባንም። የፅሑፉ ይዘትና መልእክት መገምገም በቂ ነው። እንደ የስነፅሑፍ ሰው ጥሩም መጥፎም ስራዎች ይኖሩታል። ለምሳሌ ‘የቡርቃ ዝምታ’ ፅሑፉ መጥፎ ዓላማ ያለው መሆኑ የሚያሳይ ነው።

አሁን ‘የተስፋዬ ገብረአብ ማንነት ተጋለጠ’ እያላችሁኝ ነው። የሻዕቢያ ቅጥረኛና ሰላይ መሆኑ እየነገራችሁኝ ነው። ለዚህ ማስረጃችሁም በኤርትራ መንግስት የተሰጠው ግዝያዊ መታወቅያና በማስታወሻ ደብተሩ ላይ በፃፈው መሰረት ነው። ጥሩ ነው። ግን ተስፋዬ ገብረአብ የኤርትራ ግዝያዊ መታወቅያ ማግኘቱና የሻዕቢያ ሰላይ መሆኑ ምን ይደንቃል? እንዳውም ሲያንሰው ነው።

በመጀመርያ የተስፋዬ ስራዎች የምናነበው ኤርትራዊ ስለሆነ ወይ ስላልሆነ አይደለም። የሻዕቢያ ሰላይ ስለሆነ ወይ ስላልሆነም አይደለም። ‘ኢትዮዽያዊ ነኝ’ ብሎ ስለነገረንና ስላመነውም አይደለም። ፀሓፊ ስለሆነ ነው። የፕሮፌሰር ክላምፓም፣ ፕሮፌሰር ለቪና ሌሎች ስለ ኢትዮዽያ የሚፅፉና የምናነብላቸው የኢትዮዽያ ደም ስላላቸው አይደለም። ስለ ኢትዮዽያ ለመፃፍ የግድ ኢትዮዽያዊ መሆን አይጠበቅብህም። የተፃፈ ለማንበብም የፀሓፊው ማንነት ማወቅ ግድ አይደለም። ግድ የሚለን የፅሑፍ ይዘት መገምገም ነው።

ተስፋዬ ገብረአብ የሻዕብያ ሰላይ ነው እንበል። ይሄ አይደንቅም። እንዳዉም የሚደንቀው ሰላይ ባይሆን ኑሮ ነው። የኤርትራ መንግስት በሰጠው ግዝያዊ መታወቅያ ላይ የትውልድ ሀገር ደብረዘይት ይላል። መኖርያውም ናይሮቢ። ተስፋዬ ደብረዘይት ተወልዶ እንዳደገና ኢትዮዽያዊ መሆኑ ነግሮናል። ከኤርትራውያን ቤተሰብ እንደተወለደ ግን ይታወቃል። ተስፋዬ ይህም ቢሆን ክዶ አያውቅም። ከኤርትራውያን ቤተሰብ ቢወለድም (ተስፋዬ ሲወለድ ኢትዮዽያና ኤርትራ አንድ ሀገር እንደነበሩ ይታወቃል) ኢትዮዽያ ዉስጥ ተወልዶ በማደጉ ብቻ የኢትዮዽያ ዜግነት የማግኘት ሕጋዊ መብት አለው። የኢትዮዽያ ዜግነት ተሰጥቶም የኢትዮዽያ ሬድዮና ምናምን ሓላፊ ሁኖ ሰርቷል (ዜግነት ሳይኖረው ስልጣን ተሰጥቶት ከሆነ የራሳቹ ጉዳይ)።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጭራቅ አሕመድ፤ ያማራን ሥጋ፣ የኦሮሞን ነፍስ የበላ ኦነጋዊ አውሬ

ሌላ ነጥብ ደግሞ ተስፋዬ ከኢትዮዽያ ባለስልጣናት ከተጣላ በኋላ ወደ ኬንያ መሄዱና የኢህአዴግ ባለስልጣናት የኢትዮዽያ ፓስፖርቱ እንደነጠቁት ተናግሮ ነበር። እንዴት ነው ነገሩ? ፓስፖርት መንጠቅ?! ወይስ ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ከተጣላ በኋላ ነው ኢትዮዽያዊ አለመሆኑ ያወቁ? ይህ የሚያሳየው ነገር ቢኖር የሻዕቢያ መንግስት ግዝያዊ መታወቅያ የሰጠው ከኢትይዽያ ተጣልቶ ከወጣና ናይሮቢ ከገባ በኋላ መሆኑ ነው።

አንድ ሰው ፓስፖርቱ ከተነጠቀ ዜግነቱ ተነጠቀ ማለት ነው። በሌላ ሀገር (ለምሳሌ ኬንያ) እየኖሩ ዜግነት አልባ (Stateless) መሆን እንዴት እንደሚከብድ አስቡት። ፓስፖርት ሳይኖርህ እንዴት በሌላ ሀገር መንቀሳቀስ ይቻላል? ኬንያ እያለ ፓስፖርቱ ከተነጠቀ እንዴት ብሎ ወደ ደቡብ አፍሪካ መሻገር ይችላል? (ሻዕቢያ ሌላ ፓስፖርት ሰጥቶት ይሆናል)። ለምንድነው የኢትዮዽያ ፓስፖርቱ የተነጠቀው? የኤርትራ ደም ስላለው ነው? እንዲህማ ከሆነ የኤርትራ መንግስት መታወቅያ መስጠቱ ተገቢ ነው። ምክንያቱም ብዙ ከኢትዮዽያ የተፈናቀሉ ኤርትራውያን በሻዕቢያ መታወቅያ ይሰጣቸዋል። ትክክልም ነው። ከኤርትራ የተፈናቀሉ (የተባረሩ) ኢትዮዽያውን የኢትዮዽያ መታወቅያ እንሰጥ የለም እንዴ?! የማንሰጥ ከሆነም መስጠት አለብን።

ስለዚህ ተስፋዬ የኤርትራ መታወቅያ ማግኘቱ አይደንቅም። እንዳውም ተገቢ ነው። የኢትዮዽያ ፓስፖርቱ ከተነጠቀና በናይሮቢ የኤርትራ ግዝያዊ መታወቅያ ከተሰጠው በኋላ ኤርትራዊ ሁነዋል። አሁን ‘ኢትዮዽያዊ ነኝ’ ካለ ተቀባይነት የለውም። የኤርትራ ዜግነት ካገኘ ታድያ ለሀገሩ መስራቱ ምን ይደንቃል? የሻዕቢያ ሰላይ መሆኑ ምን ይደንቃል? ኤርትራዊ አይደለምን? አዎ! ለሀገሩ መስራት አለበት፤ በሚፈልገው ዘርፍ። ስለዚህ ተስፋዬ የሻዕቢያ ሰላይ ነው መባሉ አልገረመኝም።

መርሳት የሌለብን ነገር አለ። በፖለቲካ ብዙ ዉጣ ዉረዶች አሉ። ብዙ የተጠላለፉ ስለያዎች አሉ። ብዙ ታዋቂ ሰዎች የታላላቅ የስለላ ድርጅቶች ቅጥረኞች የሆኑ አሉ።። በተስፋዬ ‘መጋለጥ’ የተደነቀ ሰው በነዚህ ሰዎች ስራማ ጨርቁ ሊጥል ነው። የሻዕቢያ መንግስት እንኳንስ ተስፋዬ ገብረአብን የመሰለ የህወሓት/ኢህአዴግ የዉስጥ አዋቂ፣ ታማኝ ሊሆን የሚችልና የኤርትራ ደም ያለው ምርጥ ፀሓፊ አግኝቶ ኢትዮዽያን ለመበታተን ያለው መሰሪ ተልእኮ ለማሳካት ለኢትዮዽያውያንምኮ በገንዘብና በጦር መሳርያ ይደልላል። ሻዕቢያ እንኳንስ ተስፋዬ ምርጥ የሀገሩ ልጅ ለአልሸባብም ኮ ያግዛል፤ መታወቅያ እየሰጠ እንዲሰልሉና እንዲያሸብሩ ይተባበራል። ታድያ ይሄ ምን ይደንቃል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰሜን ኮሪያና ወጣቱ ዝንጀሮ

ተስፋዬ ገብረአብ በሻዕቢያ የተላከ የሻዕብያ ቅጥረኛ ነው አላችሁኝ። በተመሳሳይ መንገድ የተላከ ስንት የሻዕቢያ ቅጥረኛ ባለስልጣን ይኖረን ይሆን? ህወሓት በራሱ ኮ የሻዕቢያ ተልእኮ ለማስፈፀም በሻዕቢያ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ህወሓት የመሰረተው ማነው? ሻዕቢያ ነው። ሻዕቢያ መሓሪ ተኽለ (ሙሴ) የተባለ ኤርትራዊ የሻዕቢያ አባል በትግራይ ለሻዕቢያ ሊያግዝ የሚችል ድርጅት እንዲያቋቁም ወደ ኢትዮዽያ ላከ። እነዚህ ህወሓት የመሰረቱ የሚባሉ ሰባት ሰዎች አሰባስቦ እንዲደራጁ አደረገ። ስለዚህ በተስፋዬ ስራ መደነቅ የሻዕቢያ ተግባር አለማወቅ ነው።

ተስፋዬ ገብረአብ ኤርትራዊ ከሆነ ከድሮ ጀምሮ ኤርትራዊ መሆን ነበረበት። መንግስት ሲፈልግ ዜግነትና ሓላፊነት የሚሰጥ ሲፈልግ (ከባለስልጣናት ሲጣላ) ደግሞ መንጠቅ የሚችል መሆን የለበትም። አሁን ‘ተጋለጠ’ የተባለውን ትክክል ከሆነ ተስፋዬ ኤርትራዊና የሻዕቢያ ሰላይ መሆኑ ግንዛቤ እንያዝ። ምክንያቱም መረጃ ጥሩ ነው። ሰላይ ስለሆነ መፃሕፍቶቹን አናነብም ግን አልልም። ምክንያቱም አንድ የሻዕቢያ ሰላይ የፃፈው ይቅርና የሲአይኤ (CIA) ስራ አስከያጅ የፃፈውም አነባለሁ። ሰይጣን የፃፈውም ካገኘሁ አነባለሁ። ጉዳዩ መሆን ያለበት አረዳዳችን ላይ ነው።

ተስፋዬ ስለ ፃፈው ጥሩ ወይ መጥፎ ነገር መነጋገር እንችላለን። የተስፋዬ ሁኔታ በማጋለጥ የተስፋዬን ፅሑፍና ሓሳብ ማጥቃት ግን አይቻልም። እንዳውም ህፀፅ ነው (Ad hominem Circumstantial Fallacy)። ተስፋዬ ብዙ ግዜ የሚወቀስባት መፅሓፍ ‘የቡርቃ ዝምታ’ ነች። እኔም አልወደድኳትም። አካኪ ዘራፍ ግን አላልኩም። ምክንያቱም ተስፋዬ ሓሳብ አንስተዋል። ስህተት ከሆነ ስህተት መሆኑ በፅሑፍ ማስረዳት አለብኝ እንጂ ወደ ተስፋዬ ማንነት አልሯሯጥም። ምክንያቱም ተስፋዬ ፀሓፊ እንጂ ባለስልጣን አይደለም። ፅሑፍ ሓሳብ ነው። ስልጣን ግን ተግባር አለው። ሓሳብ ሰለማዊ ነው። ስልጣን የማስገደድ ባህሪ አለው። ሓሳብ የማሳመን ስራ እስከሆነ ድረስ የጭንቅላት ጨዋታ ነው። ስልጣን ግን በሃይል የማስፈራራት እርምጃም አለው። በሓሳብ ያለመቀበል መብታችን የተጠበቀ ነው። በስልጣን ግን ያለመቀበል መብታችን ሊጣስ ይችላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እውቀት ያልሰፈረበት አንጎል ሶፍት ዌር ያልተጫነበት ኮምፒዩተር! - በበላይነህ አባተ

ስለዚህ ማንኛውያም የሓሳብ ክርክር ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። ማንኛውም የስልጣን (የሃይል) እርምጃ ለመቀበል ግን አልተነሳሁም። ተስፋዬ ፀሓፊ እስከሆነ ድረስ (ኤርትራዊ ሰላይ ጭምር) አያስፈራኝም፤ ማንነቱ ስለተጋለጠም ትኩረት የምሰጠው ጉዳይ አልሆነም። ባለስልጣን ቢሆን ኑሮ ግን (አስቡት ሰላይ ሁኖ ባለስልጣን) እቃወመው ነበር። ማንነቱ በመጋለጡም ደስ ይለኝ ነበር።

ለመረጃ እንዲሆን ግን ተስፋዬ ‘የቡርቃ ዝምታ’ የፃፈው የኢህአዴግ ባለስልጣንና የኢትዮዽያ ዜግነት ጨብጦ በነበረበት ግዜ ነው። መፅሓፉም ገዢዎቻችን እያጨበጨቡ አስመርቀውለታል። ስለዚህ ኢትዮዽያዊ እያለ የፃፈው ነው። ከድሮ ጀምሮ ሰላይ ነበር ካልን ሌላ ጉዳይ ነው። እኔ ደግሞ ለምን የሻዕቢያ ሰላይ የሚድያ ባለስልጣን አድርገን ሾምን? ብዬ እጠይቃለሁ።

እንደሚድያ ሰዎች የተስፋዬ ማንነት ማጋለጣቸው ግን ጥሩ ነው። ምክንያቱም ግዴታቸው ተወጥቷል። በዚህ መሰረት ለተስፋዬም (ላልታወቁ ሌሎችም) ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። በፌስቡክም ቢሆን ስንት ያልተደረሰባቸው ሰላዮች ይኖራሉ።

48 Comments

  1. this is nice and civilized comment. thanks Aberha. I am eager to read tesfay’s new book. I know which one is bad and good. if some body don’t chose the bad is good, don’t read any books .

  2. መልካም ጽሁፍ ::ግን, እኔ መች ስለላና የሰላዮቹ ማንነት ወይም ቁጥራቸው አስጨነቀኝ ብለህ። ቁም ነገሩ ተስፋዬ በነበረው የኢትዮጵያዊነት ዜግነት ተጠቅሞ ልቡን ከጅምሩ ላስገዛለት ለኤርትራ መንግስት ያለችንን ምስጢር ሲያባክን፣ ባገኘውም የስልጣን አጋጣሚ ሰዎችን እና አገርን የሚጎዳ በበቀል የተነሳሳ የተሳሳተ መመሪያ ሲያስፈጽም የነበረ መሆኑ አንጂ። በተለይም ደግሞ እሱ አይደለሁም ብሎ የሆነውን ከካደ፣ የሚነግረን እና የሚያደርገው እውነት ነው ብሎ ለመቀበል ያስቸግረኛል::ያነበብኩአቸውን መጽሃፍቶጭን ሁሉ የተደበቀውን ማንነት ህን ስጨምርበት ይንተን ማንነት ሲያጎሉ የጽሁፍህን አላማ ፍንትው አድርገው ያሳያሉ
    እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

  3. Realy it is a wonderful comment. A real reader reads a book to get some information whereas using or disregarding the information is solely up to his/her personal judgment.
    I read almost all books of Tesfaye. As a writer, he wrote the realities in our society and the other side of our history which we fear to confront with. Writing books about unspoken part of our history can’t justify anti-Ethiopianism of the writer as he writes the realities on the ground. For instance, what Tesfaye raised in his book entitled as “Yeburka Zemita” is a story that was orally told in Arsi area for many years concerning Oromo oppression during the Neftegna system. What Tesfaye did was retelling us the story in well articulated terms.
    Similarly, writing about positive of Ertiria can’t justify Tesfaye’s over sympathy to Eritria as writing about any subject is the right of a writer and so many foreign writers also did same about Ethiopia.
    In my opinion, we must be courageous enough to frankly discuss about our past’s good and bads without any accusation.

  4. thank you so much Abraha and i second your outstanding comment. Some stupid and naive so called worthless oppostions are crying day in and day out about tesfaye and shabia while weyane is killing and toruting our people everyday.

  5. This Abrha Desta guy is dilussional. He even went out of topic to criticize Judge W/Michael dude the point here is that we got a material evidence shows Tesfsye has been working for Shabia and unlike the stories he has been telling how he is Ethiopian the evidences shows that he is more Eritrean than Isayas.
    No body cares about how Woyanes feel about Tesfaye what maters is that Millions of Ethiopians who think he is Ethiopian learnt that he is Eritrean and working to dismantle Ethiopia and he clearly states that on his notes.
    There were millions of Ethiooians who been tricked by what he has been saying and writting now thee people had a material evidence to show them who he really is. Now it makes more sense why he hates Dr Negaso who has been working for united Ethiopia

    Abrha the documents are not worthless as u try to undermine them and I advise u to do a reality check, it seems that you have a problem of understanding facts no one care about what Woyanes will say about Tesfaye what matters is the hard evidence so that he can not play Oromos against Amharas to dismantle Ethiopia

    Abrha please sometimes think before you write something last time you were talking bulshit supporting Teacher BETTY who openly perform sex live on TV with out complete disregard about the bad precedent this teacher would set for her students

    • Daniels,seletekekelgh asteyayethe akeberhalhu endzhe deferr belew ye sentoin hasab Leazebarku yemeynatateru sewochin MESEMER YEMEYASEZEZU Ethiopiaweyan, Geta Yakumelein elalhu.thank.

  6. Thank you Abrish i respect your opinion and God bless you Sir, This is what a professional critics mean. Good job bro.

  7. እኔ ዛሬ ዳኛ ወልደ ሚካኤል መሸሻ ተስፋዬ ገብረ አብ ማነው ብ ለውበጻፉት ጽሁፍ ዙሪያ የራሴን አስተያየትና ከርእሱም ውጭ አንዳንድ ትኩረት ሊገባቸው የሚሹ በአብዛኛው በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ትግልንም ሆን የግል ህይወት ዙሪያ ጉዳትን ያስከትላሉ እና በነዚህ ጥያቄዎች ዙሪያ ሀቀኛ ኢትዮጵያውያን እውቀታችሁንና ችሎታችሁን ተጠቅማችሁእንድትረዱን ነው፣
    በመጀመሪያ ዳኛ ወልደሚካኤል መሽሻ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጅ ለህይወታቸው ሳይሳሱ በምርጫ 97 በወያኔ የተፈጸመውን ወንጀል በማጋለጥ ለሀገርና ለወገን ታላቅ ኩራት ሆነዋል፣በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንም ደም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ደመ_ከልብ ሆኖ እንዳይቀር አድርገዋል፣
    አሁን ደግሞ ይሄው ጊዜ ወስደው ከማንም በተሻለ እና በላቀ ደራሲና ሰላይ ተስፋዬ ገብረ አብ ማንነትን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጋልጥ አድርገውል፣፥በዚህ አጻጻፍዎ ለእንደኔ አይነቱ አንባቢመጽሃፍን ለየት ባለእይታና በጥልቀት እንድንገነዘብ አድርገውናል፣፥በእውነቱ ታላላቅ የስነ ጽሁፍ ሀያሲያን ቁንጮ አድርጎታል ፤፤ከዳኝነቱ ብቃትዎ ጋር ፣እኔ ሌላ የምለው የለኝም ጤናና እድሜ ይስጥዎት፣
    በዚህ ጽሁፍዎ ክፍል ሁለት ባህሪይው በሚል ርእስ ስር የተወሰኑ ጋዜጠኞችን አንስተዋል፣አበበ በለው በእኔ እይታ ከመጀመሪያ ረድፍ ነው የማስቀምጠው ካሉን ድንቅ እውነተኛ ጋዜጠኞች መካከል ፣ከእርሱበሰተቀር ክንፉ አሰፋ፥ኤልያስ፥ደረጀ ሀብተወልድ፥ፋሲል፥ከቪኦኤ አዲሱና ሰለሞን ክፍሌ፥ከጀርመን ድምጽ ነጋሽ መሃመድ ሀቀኛ ጋዜጠኞች ተጠቅሰዋል፣ምነው ከማስታወሻዎ ተቦጭቀው ቀርተው ይሁን ወይም እፍኝ አልሞላ ስለ አሉ ወያስ ሌላ ምክንያትአላውቅም የኢሳት ጋዜጠኞች እነ ሲሳይ አጌና አፈወርቅ እና ሌሎችም ለምን አልተጠቀሱም፣የእኔ እይታ የህግና የስነ ጽሁፍ ሀያሲያን እይታ አይደለም ሁልጊዜ በሚዲያ ዘወትር ስለምናያቸውና ግር ስላለኝ ነው፣፥
    ሁለተኛው ጥያቄዬ ደራሲ ተስፋዬ ገብረ አብ የደራሲው ማስታወሻ በመጽሃፉ የውጭ ሽፋን ላይ በአቶ አንዳርጋቸው ጎትጓችነት አስተያየት እንዲሰጥ ሲደረግ ያኔ እና አሁን ከተገኝው የተስፋዬ ገብረአብ ማንነት ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ምን አይነት መልስ ይሰጠናል፥አሁንስ ምን ልትለን ትችላለህ
    በሶስተኛ ደረጃ ተስፋዬ ገብረ አብ በተለያየ ጊዜ በመጽሃፉ ውስጥ ካካተታቸው ሰዎች መካከል በንድ ወቅት አስተያየት ስሰጥ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፥አንዳርጋቸው ጽጌና ገብረ መድህን አርአያና በጥሩ ሀገር ወዳድነታቸው ጠቅሼ ነበር።ከነዚህ ሁለቱ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳና ገብረ መድሀን ተዘልፈዋል።ገበረ መድህን አር አያ ከወያኔ ሸሽተው ከመጡበትና ለደርግ እጅ ከሰጡብትና ወያኔ አሁን እስካለብት ጊዜ ድረስ ማንም እውነቱን ነው የምልህ የእምነት አባቶቻችን እንኩዋን ያላደረጉትን ወይም የንስሃ አባት ጋር ቀርበን ልንናዘዝ ከምንችለው በላይ እውነትን በመናገር የኢትዮጵያን ህዝብ ከበለጠ ጥፋት የታደጉን የራሳቸውን ምቾትና ድሎት መስውእት ያደርጉልን ከማንም በላይ የምናከብራቸው ሀገር ወዳድ ጀግናችን ናቸው። ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳም ቢሆኑ አንተ ከሀገር ወጥተህ ደፍረህ ያልተናገርከውን መለስን በፓርላማ በድፍረት ተናግረው የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የተቀረውም የኢትዮጵያ ህዝብም ተበድሏል ብለው የነበራቸውን ስልጣን ትተው በአሁኑ ሰአት በንቃት እየታገሉ ያሉ ናቸው
    ከዚህ በታች ያሉት ጥያቄዎች ከተጻፈው ርእስ ውጥ ናቸው
    አንደኛ ትክክለኛ የኢትዮጵያውያን ዌብ ሳይቶች እነማን ናቸው።ለምንስ የዳኛ ወልደሚካል መሸሻ ተስፋዬ ገብረ አብ ማነው ጽሁፍ ለምን አላወጡትም
    ሁለተኛ በዚህ በውጭ ሀገር በአሜሪካ የትርጉም ስራ እንግሊዘኛን ወደ አማርኛ በስልክ የማስተርጎም ስራ የሚሰሩ አንዳንዶቹ አማርኛ ቋንቓን በደንብ መናገር አይችሉም ያዛባሉ አተረጓጎም ላ ይ የእንግሊዘኟ የቛንቓ ችሎት ባይኖረኝም ከአንድ ብሄር የመጡ ሁሉም ናቸው ብዬ ለማለት ባልደፍርም ግን ይበዛሉ ።የስለላ ስራ ይሰሩ ይሆን ለወያኔ እና ለሻቢያ አዎ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ነጻ ለማውጧት በዚህ በኩልም ትግል ማደረግ አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ
    በመጨረሻ ለዳኛ ውልደ ሚካኤል ደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚኣብሄር በአሉ ግርማን መንግስቱ ሀይለማርያም አላስገደለውም ብለውናል።እኔ ኦሮማይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲወጣ ካነበብኩት መካከል ነኝ ጠለቅ ያል ግንዛቤና እውቀት ባይኖረኝም ቄስ ባይሆኑም በነካ እጅዎ እንደዘኬ ዘክዘክ አድርጉልን ባልልም አሁንም በሱ ዙሪያ የሚያውቁት ካለ ያካፍሉን ዘንድ እጠይቃለሁ።ምክንያቱም በኦሮማይ መጽሀፍ ላይ በአሉ ግርማን ሲሳደብም ሆነ ሲያሽምር ስላላነብኩኝ እኔም የደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚኣብሄርን ሃሳብ ከሚጋሩት አንዱ ነኝ።
    በተረፈ ይሄ ባንዳ በአሉን የመሰለ ታላቅ ደራሲ ለማጣጣል መነሳቱ የሚያሳፍር ነው፤ባመነበት በሚወደው ስነ ጽሁፍ ውድ ህይወቱን የሰዋልን ደራሲ ነው።ሌሎችምበወቅቱ የታሪክ ክስተትና ሁኔታዎች ላ ይ የማይጠፋ አሻራ ያሳረፉ የማእበል የአብዮት ዋዜማ፥ማእበል የአብዮት ማግስትና የአቦዮት መባቻ ደራሲ ብርሃኑ ዘሪይሁን ማንም አይረሳም

  8. They brought misery in our country’s intentionaly other than that the aritrean people’s they are Ethiopian if they want to come to be ethiopian why not they are our brother and sister’s some narrow minded people’s who dont care to no body’s excep for themselves and agitating the people’s and make them enemy to each other’s that’s the whole problems but I thinks every thing’s clear; s to everybody we all knows people’s died for nothing they killed each other’s from both sides for nothing ; sand we need to come to our senses and leave these animosity behind didt do us no goods

  9. They brought misery in our country’s intentionaly other than that the aritrean people’s they are Ethiopian if they want to come to be ethiopian why not they are our brother and sister’s some narrow minded people’s who dont care to no body’s excep for themselves and agitating the people’s and make them enemy to each other’s that’s the whole problems but I thinks every thing’s clear; s to everybody we all knows people’s died for nothing they killed each other’s from both sides for nothing ; it, s sad we need to come to our senses and leave these animosity behind didt do us no goods shabya and woyane responsible for all these misery we shouldnot forget that

  10. I agree with your analysis. Except you should also mention the Shabiya agents in the opposition who remain unnoticed, because given the chance they will be our tomorrow’s leaders.

  11. It is not surprising being spy for foreign country for Tigres,your parents and grand parents were doing it for years. No wonder why Tigray dominated Woyane Bandas are loyal for foreigners.Mr Abraham..I don’t blame you if you are trying to down play what that snake Tesfaye did to my people and my country.Mr Abraham did you have you ever heared the Habesha saying “fes yalebet zelay ayechelem”?that is what I see here.you are also trying to down play the genocide Tesfaye insighted on that book.he is 100% responsible for that horrible crime committed againest Amara.OLF did the entire massacre in barbaric way.even though Tigre woyanes are the master minds of all the crimes.Tesfaye played big roles to inflame fighting between Amaras and Oromos and he succeeded.Amara was the victim into all that.we will never forget that.being an Apologist for that son of a bitch is a crime by its self.I hope some people will respond for your piece crap.it a crap to say the list.

  12. It is not surprising being spy for foreign country for Tigres,your parents and grand parents were doing it for years. No wonder why Tigray dominated Woyane Bandas are loyal for foreigners.Mr Abraham..I don’t blame you if you are trying to down play what that snake Tesfaye did to my people and my country.Mr Abraham,have you ever heared the Habesha saying “fes yalebet zelay ayechelem”?that is what I see here.you are also trying to down play the genocide Tesfaye insighted on that book.he is 100% responsible for that horrible crime committed againest Amara.OLF did the entire massacre in barbaric way.even though Tigre woyanes are the master minds of all the crimes.Tesfaye played big roles to inflame fighting between Amaras and Oromos and he succeeded.Amara was the victim into all that.we will never forget that.being an Apologist for that son of a bitch is a crime by its self.I hope some people will respond for your piece crap.it is a crap to say the list.

  13. Hay, let us give him another project for Gebreab. ” The sufferings of Eritrean Youth”
    Or better yet ” Why are Eritrean youth leave Eritrea en mass?” Or may be the second version of ” ye burka zemta”, but this time he gets to call it ” ye Isayas zemta”The problem is he is diving his nose in our business, while his fatherland remains an isolated African south Korea. We have to demand that he writes something about the Eritrean problems. No body can persuade me to buy his books. Books are written to inform, to educate, to bring us closer to a common destiny. Why does a writer writes to cause suffering, death, hate, genocide? Why?

  14. Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay)
    This child from Mekele is the most strikingly odd of all recent Arena cadre from Mekle City . This new born opposition fellow is simply premature to say the least, if not he is one of the obvious fools, who goes with the political predators. He dismissed Tigray never benefited by being TPLF on power. He never see that many Tigrayans as the government beneficiary. In fact he does not think Tigrayans are damaged because TPLF does not help Tigray in the economic affairs. Only the EthniQos can believe it, not me. He even does not think that the Gonder/Welkayet and the Wello fertile lands taken by force to benefit Tigray people is not for the benefit of Tigray. He is now coming with this strange “undermining new documents that expose our enemies who infiltrated us” .

    He does not have a clue what is going in the Diaspora opposition community. The Diaspora community is infiltrated by enemies because the Diaspora elites are tools for the subversive mission aimed at Ethiopia’s future. Look what Tesfaye said below about Ethiopia talking about the thinking of the Ethiopian youth about Eritrea. Efrem Madebo, Berhanu, Andargachew, Tesfaye GebreAb colaboartion with other fools clearly showed us the game of the spy is functioning well.

    OLF and Eritrean are fully using Ethiopian media covered as Ethiopians to discourage patriotic Ethiopians. Now this Tigrayan kid is fooling himself again to undermine Judge WeldemIchael and Alemayouhu’s new revelation. This child now from Mekele is coming with this new strange ego. He undermines anyone or any article or documents presented to expose or challenge spy, or enemies. He undermine those challenged Jawar Mohammod (The Islamo Fascist and OLF propagandist) by saying “Leave Jawar Mohammod alone- “YIMECHENGAL” for saying “Ethiopia out of Oromia” “I am Oromo not Ethiopian”.

    This child from Mekele is again here telling us “his readers” forced him to react about Tesfaye Gebreab. And here he goes “ why should we be surprise if Tesfaye is a spy?’ why does the writer (judge W/Michael Meshesha) need to write this long paper just to tell us Tesfaye is Eritrean spy”? You see, this child from Mekele goes on , and said “ His ID card does not show us any thing he is a spy. He dismissed every document of proof/evidence from Tesfaye’s hand writing even the part why he opposes TPLF and how he should corrupt the mind of the new Ethiopian youth (Like this child from Mekele- I am sure he is one of Tesfaye’s victim if not already) to brain wash them infiltrating among them acting as an Ethiopian- so that they will accept him as benign to our unity.

    Here is what he said (Tesfay’s hand writing )“ “መጪው የኢትዮጵያ ትውልድ የኤርትራን ታሪክ በትክክል እንዲያውቅ ያደርገዋል። ይህም በአዲሱ የኢትዮጵያ ትውልድ አእምሮ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል እንዳልነበረችና እንደማትሆንም የአመለካከት ዘር መዝራት ያስችለናል። ለዚህ ሥራም የናንተ ም/ቤትም ሆነ ህገፍ ሰነዶችን እንድመለከት በመፍቀድ ያግዘኝ ዘንድ እመኛለሁ።” በማለት ኢትዮጵያዊ
    ነው። እው ነተኛ ነው ብለው ሽንጣ ቸ ውን ገትረው ለሚ ከራከሩት ኢትዮጵያዊያን መርዶ አረዳቸው ማ ለት ነው ተስፋዬ። እው ነትና ንጋት እያደር ይጠ ራል ይሉ የለ አበው። (ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ) There, fore, this child from Mekele as Arena propagandist is now dismissing every information that tried to alert our society to be alert not to repeat the comfort and unbelievable hospitality that Ethiopians gave to that dangerous racist and anti Ethiopia mercenary any more on their community/media to anyone who acts as an Ethiopian , to carry dirty destruction in secret.

    This child from Mekele is coming with stange ego, challenging the pan Ethiopian patriots who challenged internal and external enemies of Ethiopia as mediocre documents. This are the silly future kids whom Ethiopians need to watch. This kids can be easily fooled, because they are “DEMOCRATS of THE EXTREM” who can allow any right whatever any one wants to say and do even to the extent on the sovereignty and integrity of a nation. This kind of young kids are students of Weyane Tigray- brainwashed when kids- primary Meles’s ideology who can go extreme to be easy on Ethiopia’s enemy. That is why he undermine any enemy as “so what”, “leave them alone”….. This kid and Tekle Abebe from Canada are of the same root on their Philosophy. These are dangerous to Ethiopia sovereignty who can allow any subversive mission aimed at Ethiopia’s future. They are sleepy Gurads!

    This child needs to slow down and look at our history than to Gallup with his youth fever to deny and undermine any document against spy agents. This is the child that Ethiopians need to watch not to repeat the same mistake we did before. When history repeat itself (with spy issue) , the prize goes up!
    This chiold is telling you falsely to inform you that – I will quote “ተስፋየን ለማገለጥ አርባ ምናምን ገጽ? ተስፋዬን አጋለጠ የተባለ አርባ ምናም ገጽ ምንም ዓይነት መረጃ አልሰጠኝም።” This child is undermining the amazing document that showed us many information and why he opposed TPLF and why he is infiltrating Ethiopian community and his mission.

    This child from Mekele already dismissed Jawar’s opponents and now he is dismissing and undermining this latest secret document leaked from the spy’s former roommate. This child is on denial. He is extreme DEMOCRAT that allows anti Ethiopia predators who prey on the destruction of Ethiopia. Doing so, advising so- gives him the new Young Tigrayan who allows anything to be said, infiltrate (ምን ይደንቃል!) (ምንም መረጃ አልሰጠኝም)…….

    He is trying to dismiss this valuable document dealing with the ID card given from Kenya. In fact- no one need to get ID card from Ethiopia as long as he escape from Ethiopia – or even if taken by Ethiopian authority. He can claim he is Ethiopian with explanation. Snatching passport from citizen does not meant he is denied his citizenship by TPLF and forced to change his Identity to change, unless , he is the one wants to change his Identity. We all did it with the same explanation. Tesfaye can’t be unique on this. Eritrean officials had similar situation “their passport taken by Eritrea while in exile”- but, still claimed Eritrean not Ethiopian. We immigrated empty hand. And still claim as “Ethiopian”. His Eritrean emotion was since he was a child- He was a spy when he was 26 years old supporting EPLF.

    This child even misinformed you saying “Tesfay’s ID card is reading “Tewlid Hager DEBREZEYT” no this child is lying to you. Go back and read it. It said “Lidet/Adi” that meant birth place. Not a country! Ethiopia is country Not Debrezeyt. Debrezeyt can’t be a country as this child is misreading it. Perhaps his Tigringa is reading strangely different- if that is not the case, then his lying to you. Lidet, means Birth- Adee- in the Tigringa traditional translation is county/village/locality or so on… but HAGER is the right Tigringa Translation to meaning “COUNTRY” . So he is misguiding you and himself too perhaps. I want all patriots to expose and challenge infiltrators and spy agents. So do not listen to those who wants to numb your brain not to be alert.

    Yes, you the Diaspora foolish opposition is now surprised this new revelation regardless the ECADF/Current Affairs and most opposition media flirts and allowed the Eritrean spy propaganda insulting the Amhara and Menlik and patriotic Ethiopians “unrestrictive” and other who wants to challenge intruders. Yes, The Diaspora must be surprise by this new findings. It is surprise for the Diaspora opposition- regardless we tried to alert them many times that Tesfaye is a spy not to be given a space to insult our dignity and our country to disunite us using his writing skills- unfortunately, they never listen. Because like this child who are advising our community “to leave them alone,” “do not be surprise” or “I did not get any information from 40 some pages”…… and so and so on propaganda methods of MaJAJAL.

    Many Ethiopians pledge poem for him on ECADF Tesfaye as true patriot Ethiopia (Yebisheftu LIJ) (especially there one young lady I remember- “claiming she is from Bisheftu” (She has to apologize now!)- it was shocking to me after I recorded her when she paid a tribute for him,. Many Ethiopians were eating food with their enemy. Who knows he could have poison them if it could have not cut short with this latest revelation. Keep expose those enemies and do not listen to the subversive agents. Who wants you to be JILAJIL.

  15. Abraha Desta why you went out of your way to defend Tesfaye and Criticize JUDGE WOLDEMICHAEL? of course you won’t care about the hate he has been preaching against AMHARAS pittying OROMOS, IS THIS BECAUSE YOU ARE NOT AMHARA????????? do you know OLF use Tesfaye’s book as a text book to incite hate against AMHARAS??? why this failed to worry or concern you ??? while you write everyday about every little problem facing TIGRIANS

    LAST BUT NOT LEAST WE LEARN LOTS OF ETHIOPIAN WEBSITES are run by SHABIA they refuse to post what JUDGE WOLEDMICHAEL wrote exposing TESFAYE with hard evidences and now we learnt who are real Ethiopians news media websites and we will never be fooled again about this stupid so called Ethiopian news media websites including Ethiopian review, EMF, ESAT, etc

  16. @Kolegnaw

    Your generalization indicates that you are angry and spiteful human being having some psychological problem. Focus on the substance that was brought forward than the ‘fes yalebet’ proverb. there are bad people from every tribe including some from your own family or among your friends. Such immature and arrogant argument will never help the cause or the people whom you think you are supporting. Read all what you have written and find one substance that stands against the authors argument and deal with that.

    God have mercy on you!

  17. I completely agree with Zewdu’s comment. I hope the writer of the article reads it. It seems Abraha Desta has a missing link in the over all analysis of Tesfaye G/ebab.

  18. wow! Daniels is so right. It sounds Abraham Desta is a kind of defending Tesfaye. No body misses the point of free thinking and writing for which we struggle day and night. But, when one is out and about to share his/her satanic thoughts in books or media that would instigate massacres in the disguise of free expression of thought, then one has to be stopped; at least till we get our society’s consciousness level up. Tesfaye has always been working for Shabea since the Derg times. May be, Abrha needs to dig more to understand what was at stake then.

  19. Dear abrha unlike many of your writings this piece was out of step and look like an effort to undermine the judge’s significant effort to highlight the sabotage and criminal activities of an eritrian agent who uses ethiopian identity as a cover to divide and instigate violence among ethiopia’s ethnic groups. You know well that instigating ethnic violence or genocide through your writings particularly those in the media or their books are a serious offense under international criminal court (Rwanda is a good case).The judge arguing not only about Tesfaye’s previous book but, also about his continues effort in dividing ethiopians after he left ethiopia. That is, the judge’s main point. He is an eritrian agent who continues using ethiopian identity as a cover to undermine ethiopians unity.

  20. you said it all Getachew Reda. Now, it makes me wonder that this Abraha Desta dude is also a Shabea agent.

  21. Obo Tesfaye has lost his mind. Send him to Debarawa for long vacation. I will not pay a penny for his coming trash.

  22. the book is released for free “Yesidetegnaw Mastawesha” It could not be sold. THIS IS GREAT.

    • Ayeeeee yelij neger! Aweksh, aweksh biluat hone eko negeru. Menew ante chorka Abreha wedi Desta hulum ga tilik maletu bikerebeh? Ante ye Tesfaye selaynet addis neger kalhonebehena kebefit jemero yemetawk kenebere lemen kedmeh atagaletewm neber?

      Tesfayen lemekelakel ena ebabun kemotebet afer aleseh lemasnesat new asabeh? Beakemeh metsaf yeshalehal. Seleweyane metfo yetsafe hulu yeged tsere weyane layehon yechelal. Yesfayem seleweyane bezu tsefoal. Gen Ye jegnawen Dagna Weldemichael tsehuf bedenb anbeb. Tesfaye berasu yej tsehuf keweyane menem cheger yelebegnem beloal. Selezih selewyane askefi serawoch alfeh alfeh bemetsfachew becha teshewden lela alamam kaleh zem belen yemenkebelh aymseleh.

      I hate people who all of a sudden put themselves extremely high simply because they think they are accepted as heroes. Please get back to your box and learn how to make discourse on sensitive issues.

  23. From GETACHEW REDA (Editor – Ethiopian Semay) Thanks Betti; Your idea is accepted. The problem is the website you mentioned ECADF was serving and still is serving anti Ethiopia propaganda elements. I do not expect from them to post my view what so ever. Their tent and my tent are two different antagonistic tents. የኔ እህት (ቤቲ) ልንገርሽ፡ የኢትዮጵያ አንድነትና ሕብረታችን አንዲበታተን ትልቅ ስራ የሰሩትን የመከፋፈል ስራ ውስጥ ሲከተሰማሩት ተኩላዎችና ከሃዲዎች መካካል ጥቂቶቹን ልግለጽና ከዚያ ኢካዴፍ/ካረንት አፈይርስ የተባለው ድረገጽ አንኚህን ከሃዲዎችና በራዦች አንዴዩት ሲያገለግል አንደነበር (እነ ተስፋዬ ገብራብ ማለት ነው) ልግለጽልሽ። ተኩላዎቹ መካከል ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ብርሃኑ መዋ፤ ዶክተር ገብረማርያም፤ ዳንኤል አሰፋ፤ኤልያስ ክፍሌ፤ ዳዊት ከበደ፤ የመሳሰሉት ሲገኙ የነርሱን ስራ በመስራት ደግሞ ተላላለኪዎቻቸው እንደ እነ ዶከተር አክሎግ ልመንህ፤ፈቀደ ሸዋቀና፤ግርማ ሞገስ፤ግረማ ካሳ፤ታማኝ በየነ፤ ኣበበ በለው፤ የፓልቶክ ቅጥረኞቻቸው ደግም ወርቁ ወይንም አንደ ልቡ ከባንኩቨር ካናዳ (የኢካዴፍ ዋናው አዘጋጅ) ታዬ ሚሉጌታ (ዛሬ የቃሌ ፓል ቶክ ዋነ አዘጋጅ ይመስለኛል) (ካልጋሪ ካናዳ) ፤ ወ/ሮ ሙያየ ምስክር (ትከክልኛ ስሟ ብዙ ወንድማገኘሁ (አደገኛ ዘረኛ፤ ትገሬን የምትጠላ፤በቴፕ ድመጿ የተቀረጸ; በዘረኛነቷ የምትኩራራ፤ ለዚህም ይቅርታ እንኳ ማትጠይቅበት አንደበት ያላት) የመሳሰሉት አንድነት ሃይሉን አንዲፈርስ እና አንደ እነ ተስፋዬ ገብራብ የመሳሰሉ ‘ሰላዮችም’ ሰርገው እንዲበትኑን ከሚያገለግሉ ቀንደኛው ዌብሳይት/ፓልቶክ ነው። ኦነግ/ኦብነግ/ሙጃሃዲኖች …የሆነ ቡደን ወያኔን እስከተቃወመ ድረስ ያለ ምንም ገደብ የሚያገለግሉ ግለሰቦች የተሰባሰቡበት ድረገጽና/ፓልቶክ ስለሆነ ፤ የኔን ጽሁፍ አንዲያስተናግዱ አትጠብቂ። በ ኢትዮጵያ አንድነት ላይ ብዙ ሴራ ሲጎነጎን እኛው ራሳችን ከፍተን በምንሰጠው በር ገብተው ነው አገራችነን የሚያጠቁት። አሁን ደግሞ “ኢሳያስ አፈወርቂን” የሚያሞግሱ የእነ ኤልያስ ክፍሌ እና የነ ስለሺ ተለዋጮች እነ ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው መጥተዋል። ለነዚህም “ኢካዴፍ ድረገጽና – ካረንት አፈይርስ ወይንም ቃሌ ፓልቶክ” ቀዳሚ አጋፋሪዎች ናቸው። ዕድሜ መስተዋቱ ! አውነትም እድሜ መስተዋቱ! We have to say for those banda elements “ENOGH is ENOGH!” You need to learn after 21 years of foolishness!! አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

  24. we will never forget what this so called ETHIOPIAN NEWS MEDIA WEBSITES for not saying anything against this evil SHABIA agent TESFAYE GEBERE EBAB KKKKKK dinkem ye Ethiopian website leba hulu

    ABRAHA DESTA you are ignorant and immature I stop reading you when you said Teacher BETTY has a right to perform live sex on BIG BROTHER AFRICA with little concern for the bad example she will set for her students and millions of female students, Now you are OUT TO DEFEND TESFAYE kkkkk

    If you claim you are Ethiopian try to see what Tesfye did to instigate conflict and hate against Amharas instead of wasting your time about writing only small adminstration problem happened in TIGRAY

  25. Sam.
    Is it not true our land is infested with a bunch of sale out Banda groups?was not Tesfaye G/Ab one of them?is it not true thousands of Amaras slaughter because Tesfaye’s genocide insightment in his book called Yeburka Zemeta?Tesfaye had in coditional hate to Amara.that is fact.you can not change that fact.your brother Abraha is trying to defend that devil.what substance do you want Sami boy?you deal with that reality.judgement day will come sooner or later for those tugs.are you one of them Sami boy.if that is the case,be afraid,very afraid.

  26. Correction
    Sam.
    Is it not true our land is infested with a bunch of sale out Banda groups?was not Tesfaye G/Ab one of them?is it not true thousands of Amaras were slaughter because of Tesfaye’s genocide insightment in his book called Yeburka Zemeta?Tesfaye had un conditional hate to Amara.that is fact.you can not change that reality .your brother Abraha is trying to defend that devil.what substance do you want Sami boy?you deal with that reality.judgement day will come sooner or later for those tugs.are you one of them Sami boy?if that is the case,be afraid,very afraid.

  27. Hi man? I think you are wrong at least for now. You and some other few educated guys may analyze and understand things like you did and the poison he spread in Ethiopia may not have an impact, but what about like 80 or 90% of the people of Ethiopia? I hope you know what oromo elites speared hates between this two people. I am not saying that the thing what they are saying is totally wrong, there may have some facts on which you and I generation did nothing on it and I believe that the thing they are saying is a part, even the good part of our history to have a nation . That is how most of the great country made and their new generation keep forward but we stacked instead of moving forward due to this dirty elites . Anyhow, when you comment something like this try to think about those kind but uneducated peoples who respond roghly for this kind of information because somehow, you are becoming a political figure , whatever you said will have an impact.

  28. I wish Tesfesh were not agent for eritrean government!!
    His being an eritrean has nothing to do with his book . I am reading it , it is sweet .

  29. For those of you who likes to read Gebreab’s new book, there is also another one you should read-‘Mein Kampf”, of course the writer is Adolf Hitler.

  30. …”-ተስፋዬ ገብረአብ በሻዕቢያ የተላከ የሻዕብያ ቅጥረኛ ነው አላችሁኝ። በተመሳሳይ መንገድ የተላከ ስንት የሻዕቢያ ቅጥረኛ ባለስልጣን ይኖረን ይሆን? ህወሓት በራሱ ኮ የሻዕቢያ ተልእኮ ለማስፈፀም በሻዕቢያ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ህወሓት የመሰረተው ማነው? ሻዕቢያ ነው። ሻዕቢያ መሓሪ ተኽለ (ሙሴ) የተባለ ኤርትራዊ የሻዕቢያ አባል በትግራይ ለሻዕቢያ ሊያግዝ የሚችል ድርጅት እንዲያቋቁም ወደ ኢትዮዽያ ላከ። እነዚህ ህወሓት የመሰረቱ የሚባሉ ሰባት ሰዎች አሰባስቦ እንዲደራጁ አደረገ። ስለዚህ በተስፋዬ ስራ መደነቅ የሻዕቢያ ተግባር አለማወቅ ነው።”….
    ይህ ታሪክ ሳይሆን ድርሰት ነው፥፥ ታሪክ በአንድ ሰው መልካም ፍቃድ የሚጻፍ ሳይሆን ህዝብ የሚያውቀው የሚቀበለው እውነታ ነው፥፥ አንድን ታሪክ ለማረጋገጥ ቀላል ነው፥ በቦታው የነበሩትን መጠየቅ፥፥ ይህ ሲባል አንድ ወይም ሁለት ሰው ቃለ መጠይቅ በማድረግ ሳይሆን፥ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በርካታ ሰዎችን ጠይቆ ማረጋገጥ ይቻላል፥፥ ከዛ ባለፈ እዚህ ያስቀመጥከው ልክ ተስፋይ ገብረአብ በአርሲ እንዳደረገው አብረሃ ደስታ በትግራይ ታሪክ ድርሰት ቢጽፍ አያስደንቅም፥፥

  31. For me Tesfaye has always been a shabia spook!!! what was missing so far was the tangible facts to convince the sceptics!!! Now thanks to judge Woldemichael & Alex Tesfaye is caught with the smoking gun!!!! I really appreciate judge Wolde & Alex for their patriotic deeds!!!!As to Abraha Desta although he was unduly criticizing some aspects of the judge s article he is alarming us about people out there who are worse than Tesfaye….!!!!…!!!!!

  32. ይህ በለማጅ ብዕሩ ተስፋዬን አጋለጥኩ ያለን ደነዝ ጭቃ ጭንቅላት; ስብሃትን, አበበ ባልቻን, ስንቱን ለማስዋሸት ይዳደዋል ጎበዝ!? አምዴን አምኖ ተስፋዬን መስደብ! አምዴን ራሱ የሰማው አስመስሎ ሲያወራልን ምን መሰልነው ግን? መሃይም! ስለ ኤርትራዋ ወይዘሮ ሲያወራ የተስፋዬን ሃሳብ ሳይጨርሰው ትቶ እኛን ማሞኘት የፈለገው አሳፋሪ ነው:: ተስፋዬ ያለው ግን ስሟን ሲጠይቅ “ወይዘሮ ኢትዮጵያ እባላለው” ብላለች:: እናም እትዮጵያዊነት ባህል በውስጥዋ ጥልቅ መሆኑን ነው ተስፋዬ የነገረን:: ለመሆኑ የህግ ዲግሪውን ያገኘሀው በዚህ ቀፎ ጭንቅላት ነው? ወይስ አባትህ ድሮ በዘረፈውና በወረስከው የሰው ገንዘብ ፎርጂድ አሰርተህ ነው? አንተን ብሎ ተቺ, ሃያሲ! ለመሆኑ የተስፋዬ መተወቂያ ቅጂ ነው ያልከውን ያንተን እጅስራ ከድንች ማህተም ልትሰራለት አልቻልክም ወይ? ምነው ጎበዝ? በህግ ዲግሪ ያመጣው ጭንቅላትህ ይህን ማስተዋል ተሳነው? ደነዝ ነህ! ደግሞ ለራስህ ያልሆንከው ሰውዬ የኛን አዕምሮ ለመምራት ትሞክራለህ? የቡርቃ ዝምታ ከተጻፈ ስንት ዘመኑ ነው? ዛሬ ምን አሳሰበህና በሱ ሃያሲ ሆነህ የጭቃ ጅራፍህን መዘዝክ? አባቶችህ የፈጸሙትን ጂኖሳይድ ልትክድ? ያማ ቀን ይጠብቃል:: አንተ ግን ደራሲነትን ለተስፋዬ ተውና ስርተህ ብላ ጎበዝ::

    • all you conveyed was just derogatory remarks. Such bad mouth with out substance is the true nature of morons.

  33. @Yedagnaw qtfet!!!!!…ant aganinint shaabia!!!!! ant aremenie!!!!…zim bileh hedeh worq tiris bitifelg yishalhal…enditineqlew!!!!…ant nefse bela arios kehulum yemigermew difretih naw!!!! yante Tesfaye ke engdih behula Zombi naw!!!!…

  34. TPLF was not founded by an Eritrean sent by the Shabia. False. As Aregawi Berhe – himself one of the 7 founders – clearly stated in his book ( A Political History of the TPLF) , Mussie was a Tigryan born in Eritrea who joined the EPLF in their early years of rebellion. Abraha Desta should know this better both as a Tigryan but also as an intellectual and a leader of an opposition group. Facts should not be twisted to fit your political narrative. It is true Mussie was sent by the e

  35. continued …

    Mussie was indeed sent by the EPLF at the birth of the TPLF because 1) he was an ethnic Tigryan 2) He was an experienced fighter
    Yes it’s true the EPLF was 13 years old when the TPLF came into existence and hence it was in better position to assit in setting it up and possibly influence it to its advantage but to portray the TPLF as a complete creation of the EPLF would be gross misrepresentation of the fact damaging even to those advocating this version of history.

  36. Saying that the EPLF has had much influence inside TPLF. TPLF’s sympathy to Eritrea are clear testimonies of that. And one way TPLF came under such tilted influence in favour of Eritrea is because it was infiltrated by Eritreans due in part to the geographic as well as demographic/ethnic factors that bring the two together. That Meles Zenawi was a half Eritrean explains a lot about the TPLF with out much need to tell lies about who formed TPLF.

  37. ere lemehonu yeburka zemeta zere manzeren new yasecheresew bedeno enkufetu gedel weset ayenachew tasero yetewerewerut besfay alawakenet new ahunema tegantal nkanebeh yenaten wegen ena yeabaten wegen agadelk keze belay men kereh? Oromo ena amara ande endalenebru endaltewaledu ante kehala metete abalahachew ante rash keweyane ateshalem antem weyanem shabiyam lethiopia atebejum gedel gebu leboch awerewoch kesew yaletefeterachu aremenewoch nachu antena weyane wedemu ethiopia lezelalem tenur!

Comments are closed.

Share