October 3, 2017
2 mins read

ሃሮማያ ከተማ በተቃውሞ እየተናጠች ነው – ሕዝብ ሕወሓቶችን ሃገራችንን ለቃችሁ ውጡ አለ

81151


(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ከ እለት ወደ እለት ወደ አስጊ ደረጃ እየደረሰ ይገኛል:: ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ግጭት በየቦታው እያስተናገደች ባለችው ኢትዮጵያ አለመረጋጋቱ አይሏል:: ዛሬ በሃሮማያ ከተማ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት የሕወሓት አስተዳደርን ሃገራችንን ለቃችሁ ውጡ በሚል ተቃውሞውን ሲያሰማ ውሏል::

በሃሮማያ በተደረገውና በርካታ ወጣቶች በተሳተፉበት በዚህ ሰልፍ “ወያኔ ሌባ” ሲሉ የተቃወሙት ወገኖች የሃገሩ ባለቤት ኦሮሞ ነው ሃገሩን ለቃችሁ ውጡ ሲል ተቃውሞውን ከፍ ባለ ድምጽ አሰምቷል::

ገንፍሎ የወጣውን የሕዝብ ቁጣ ለመቆጣጠር የሕወሓት መራሹ መንግስት በአካባቢው ወታደሮችን እንዳሰማራም ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች ሲገልጹ እስካሁን በሰውና በንብረት ላይ ስለደረሰ ጉዳት የገለጹት ነገር የለም::

በሌላ በኩል የሕወሓት ልዩ ፖሊስ በም ዕራብ ሓረርጌ ዶባ ወረዳ 3 ወገኖችን መግደሉ ተሰማ:: እንደ አካባቢው ምንጮች ገለጻ ኢብራሂም አብዲ፣ ሮባ ዳዲ እና ለጊዜው ስሙ ያልተገለጸ አንድ ወገን ናቸው በሕወሓት ልዩ ፖሊስ የተገደሉት::

በአካባቢው ውጥረት ነግሷል – ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን ተከታትላ ለመዘገብ ትሞክራለች::

6 Comments

  1. It is reasonable qeuestion by oromo people. People don’t want see such kind of evil gambler tplf. Every boday say Down Down tplf!!

  2. Tigrewoch hoy ye amarawun ye oromowen hezb eyegedelachehu lerezsem gize meqetel atchelum!!. Hezbun leqeq adergut alchalachehubetem!!

  3. ለሀገራችን አንግዳና ኣዲስ የሆነ መጤ ኣስተሳሰብን Marxist Leninist Ideology ለሀገራችን ተስማሚ ይሁን ኣይሁን ሳንመረምር በግድ ልንተገብረው በመመኮራችን በሀግራችን ተስማምቶ የሚኖረውን ደሀውን አና ኣንጻራዊ ሀብታም የሆነውን የመደብ ትግል / Class struggle /በማለት በማቃረን የተጀመረው ትግል ኣቀንቃኞቹን ጨምሮ ለብዙ ሺዎች ደም በከንቱ መፍሰሱን ታሪካችን ይመሰክራል።
    ኣሁን ደግሞ የዚሁ ርአዮተ ኣለም ተቀጥላ የሆነውን የራስን አድል በራስ የማስተዳደር በሚል- ተፋቅሮ ፣ተጋብቶ የኖረውን ህብረተሰብ ብሄር ፣ብሄረሰብ በማለት አርስ በርሱ አንዲናቆር በማድረግ አንደገና የድም ጎርፍ ድግስ አየተዘጋጀ መሆኑ በየቀኑ አያየን ነው።
    በጣም የሚያሳዝነው ተማርን ባሉት ሰዎችና ባንዳንድ Prostitute intellectuals መቀንቀኑ ነው።
    የሚያስፈልገን የማን ጎሳ ኣባል ፕሬዝደንት ወይም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ ሳይሆን ሀገራችን በነጻነት ፣ ቤኩልነት፣ ፍጹም ዲሞክራሲያዊ በሆነ accountable and transparent ኣስተዳደር ተመርታ የህዝብ ምርጫ አና ኣመኔታ ያገኘ ከየትም ጎሳ ይምጣ ያስተዳድረን ነው።
    God bless Ethiopia !

  4. Zega;
    Why does self administration – “የራስን አድል በራስ የማስተዳደር” necessarily result in “አርስ በርሱ አንዲናቆር በማድረግ አንደገና የድም ጎርፍ ድግስ” (i.e. fighting one another into a blood bath again)?? Where is the connection, unless you want to defend the unjust previledges of the few as usual to the bitter end. Is Self-determination and peaceful co-existence of nations mutually exclusive??
    How else can a “ፍጹም ዲሞክራሲያዊ በሆነ accountable and transparent ኣስተዳደር” be instituted?? Democracy does not mean that a person from my ethnie, tribe, village, etc gets the top post. This is only Abyssinian understanding of “democracy”. For the rest, democracy is power to the people, equality, justice and the rule of law, respect for individual and group rights, etc.

  5. ምርት ገበያው ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚ ተሾመለት

    Ethiopian Commodity Exchange had prooven to make the famine worst for the farmers famine victims.

    Eleni Zaude Gabre-Madhin designed ECX (Ethiopian Commodity Exchange) to benefit the Woyane TPLF voulchers and starve the majority of Ethiopians. All these conflicts between Oromo , Somali , Amara , Kimant , Tigray and many more is happening more often than usual because ECX is implementing policies that make Farmers starve by ECX exercising a command economy not market (free) economy policies towards farmers. Eleni was born in Addis Ababa, Ethiopia. She grew up in three different African countries including Kenya, Tanzania and South Africa. She speaks fluent Swahili, English, Amharic and French. She is the gold digger that would sell anything AND everything for money. She sold her soul to Meles Zenawi & Co. when she knowingly brought all these problems trhat are leading to bigger and bigger conflicts to all farmers of Ethiopia. She is not reversing her mistake or she is not saying what part ECX played in causing these dangerous situations allover in Ethiopia.

    ምርት ገበያው ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚ ተሾመለት

    ethiopianreporter. com

Comments are closed.

Previous Story

ደመራ {በሃይማኖታችን፥ በታሪካችንና በባሕላችን አንጻር} – (በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

bbn daily ethiopian news march 2
Next Story

በሀሮማያ የተካሔደውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰዎች ታሰሩ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop