October 6, 2013
12 mins read

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ጋዜጣዊ መግለጫቸው (ከፋሲል ግርማ)

በፋሲል ግርማ

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከአካላዊ እንቅስቃሴያቸው እና ድምፀታቸው ጀምሮ እስከ ሚቀልዷቸው ቀልዶች እና የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች በሙሉ የቀድሞውን ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሚያስታውስ መልኩ ያካሄዱት ጋዜጣዊ መግለጫ ባብዛኛው ተቃርኖ የበዛበት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም በጋዜጣዊ መግለጫቸው ከጥያቄ እና መልሱ አስቀድመው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መንግስት ያለውን መረጃ የተናገሩ ሲሆን እንዲሁ በደፈናው አሃዝ ሳይጠቅሱ የሃገሪቱ ምጣኔሃብት እያደገ መሆኑን፤ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፉ ካለፈው አመት የተሻለ መሆኑን እና በሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከጎረቤት ሃገራት ጋር ኢትዮጵያ ያላትን ግንኙነት ለማብራራት ሞክረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በስተቀር ከሌሎች ጎረቤት ሃገራት ጋር ያላት ግንኙነት ስትራቴጂካዊ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሊያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ዘርዝረዋል፡፡

እንደ እርሳቸው አገላለጽ የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊያ የፌዴራል መንግስት ከሃገሩ የክልል አስተዳደሮች ጋር ተስማምቶ እንዲሰራ ኢትዮጵያ የማደራደር ሚና እየተጫወተች እንደሆነ እና አልሸባብ የተባለውን አሸባሪ ሃይል ለማጥፋት በሶማሊያ ከሰፈረው የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር ጋር በመተባበር ጥረት በማድግ ላይ ናት በማለት ሃገሪቱ በሶማሊያ ያላትን ዘርፈብዙ ጣልቃገብነት በሚያሳብቅ መልኩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ሃይለማሪያም እንዳሉት በኢትዮጵያ ብሎም ባጠቃላዩ ምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የደህንነት ችግር አለ፤ ነገርግን የእርሳቸው አስተዳደር በሶማሊያ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት ለድህንነት ችግሩ መባባስ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ማመን የፈለጉ አይመስልም፡፡

ኤርትራን በተመለከተ በተለይ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል የመግዛት እቅድ አለን ማለታቸውን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ የኢትዮጵያ መንግስት ከዘጠኝ ዓመት በፊት ጀምሮ በሁለቱ ሃገራት መካከል ሰላም እንዲፈጠር ጽኑ አቋም እንደ ያዘ እና ጥረት እያደረገ ነው ያሉ ሲሆን፤ በኤርትራ በኩል ግን ይህ ዝግጁነት የለም ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ መብራት ከኢትዮጵያ እንገዛለን ማለታቸውን አስመልክቶ የራሳቸው ብቻ ፍላጎት ነው ያሉ ሲሆን፣ ምናልባትም አጣብቂኝ ውስጥ ስለሚገኝ ኑዛዜ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ መንግስት ጋር ሰላም መፍጠር ይፈልጋል ብለው በተናገሩበት አንደበታቸው ጠቅላሚኒስትሩ የኤርትራ መንግስት ለራሱ ሳይሆን ሌሎችን ለመርዳት እየጣረ ይገኛል በሚል ለራሷ ክንፏ ተሰብሮ ሌላ ለመደገፍ እንደምትሄድ አሞራ መስለውታል፡፡

ሃገር ቤት ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች የሚያካሂዱትን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተም ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስላቅ የተቀላቀለበት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ እንደ ሃይለማሪያም ንግግር ሃገር ውስጥ የሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች በየሳምቱ በሚያደርጓቸው ሰላማዊ ሰልፎች ተደጋጋሚ ጥያቄ ነው የሚያነሱት፡፡  እርሳቸው እንዳሉ ለጥያቄዎቹ መንግስት ቀደም ብሎ መልስ የሰጠባቸው ስለሆነ ተጨማሪ ከመንግስት የሚመጣ ነገር የለም፡፡

ሰልፎቹ በዚህ ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነም የሆነ ግዜ መንግስት ሊያስቆመው እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃገርቤት ተቃዋሚዎች የሚያሰሟቸው ጥያቄዎች የራሳቸው እንዳልሆኑ እና እንደ እርሳቸው አባባል በተለያዩ ሃገሮች ያሉ ሌሎች ሃይሎች የሰጧቸው የቤት ስራዎች ናቸው፡፡

በዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር፤ ለምሳሌ ሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ፓርቲ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች እንዲፈቱ፣ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዳይገባ፣ የኑሮ ውድነት የመሳሰሉት ጉዳዮች እንዲሻሻሉ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች መልስ አያገኙም ማለት ነው፡፡

በውጭ ካሉ የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ በተመለከተ ግንቦት ሰባት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ባጭሩ ህልም ነው፤ ማለም ይችላሉ ያሉ ሲሆን በፓርቲያቸው ውስጥ መሰንጠቅ ስለመኖሩም ለተነሳው ጥያቄ ምኞት ነው መመኘት ትችላላችሁ የሚል ድፍን ያለ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ሌላው በተቃርኖ የታጀበው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ሙስና እና ኢንቨስትመንትን በተመለከተ የቀረበላቸው ሲሆን መንግስታቸው የሙስና ቀዳዳን እያጠፋ ተወዳዳሪነት የሰፈነበት አንቨስትመንት እንዲኖር ያበረታታል ብለው የተናገሩ ሲሆን፡፡

ሙስና ውስጥ የገቡ ባለሃብቶችን መንግስት እየተከታተለ እንደሆነ እና ሙስና ጋር ያልተነካኩ ባለሃብቶች ይህ ሊያሰጋቸው እንደማይገባ የገለፁ ቢሆንም በመቀጠል ደግሞ እስካሁን ስርቆት የፈፀሙ ባለሃብቶች ካሁን በኋላ ቢያቆሙ ጥሩ ነው በማለት ከዚህ ቀደም ለተፈጸሙ ዝርፊያዎች እውቅና ሰጥተዋል፡፡

እንዲሁም የቁጠባ ቤቶችን በተመለከተ የወጣው መመሪያ የቁጠባ ቤት ተመዝጋቢዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ነው መቆጠብ የሚችሉት መባሉ የሌሎች የግል ባንኮችን ተወዳዳሪነት ይቀንሳል መባሉ የተሳሳተ ትንተና የተካሄደበት ትችት ነው ያሉ ሲሆን ባንኩ ሰዎች ከሚቆጥቡት 20 በመቶ ገንዘብ ላይ 80 በመቶ ጨምሮ ስለሚያበድራቸው  ተጎጂ እንደሆነ ለማብራራት ሙከራ አድርገዋል፡፡

ነገርግን በዚህ መልሳቸው ባንኩ 80 በመቶ ብድር ሲሰጥ ጎን ለጎን በብቸኝነት ኢንቨስትመንት እያካሄደ ስለመሆኑ የሰጠውን ብድር መልሶ ከወለድ ጋር እንደሚያገኘው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘነጉት ይመስላል፡፡

በመሰረተ ልማት ላይ ስለሚገኙ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለተጠየቁት ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ከፖለቲካዊ ችሎታቸው ይልቅ የምህንድስና ሙያ እውቀታቸውን ተጠቅመው ለማብራራት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን እዚህም ላይ ግራ አጋቢ መልሶች እና ማብራሪያዎች ሰጥተዋል፡፡

የተፋሰስ ችግር በመኖሩ የአስፋልት መንገዶችን እያበላሻቸው መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀድሞ ነገር መንገዶቹ ሲሰሩ ተፋሰሱንም አብሮ መስራት ለምን እንዳልተቻለ አልጠቆሙም፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የመብራት ችግር በተለይ በመኖሪያ አካባቢዎች መብራት የሚቋረጠው አዳዲስ ማሽን ቤቶች በብዛት ስለሚከፈቱ እና በየአካባቢው ያሉ ማከፋፋያዎች ለእነዚህ የሚሆን ሃይል የመሸከም አቅም ስለሌላቸው ነው በሚል ቴክኒካል መልስ የሰጡ ሲሆን እንደ ቃሊት አካባቢ ለሚገኙ የኢንዱስትሪ አካባቢ የሚባሉ አካባቢዎችም ችግሩ ተመሳሳይ እንደሆነ ነው ያብራሩት፡፡

የሞባይል ኔትዎርክ መጣበብ ችግርም ተጠቃሚ ከታቀደው በላይ ስለበዛ ነው ያሉ ሲሆን ይህ የእቅድ እና ነባራዊ ሁኔታ አለመጣጣም እንዲሁም በተደጋጋሚ የሚያነሱት የአፈጻፀም ችግር በቀድሞውም ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሰጥ የነበረ ሲሆን ይህ የማቀድ እና የማስፈጸም ችግር ከመንግስት ብቃት ማነስ ጋር ስለመያያዙ ማንሳት የፈለጉ አይመስሉም፡፡

ባጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ  አስተዳደራቸውን ምዕሉ በኩለሄ አይነት አድርገው የሳሉት ሲሆን ለተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ ሰበብ አስባብ ከመደርደር የዘለለ መልስ አልሰጡም፡፡

ከአጠቃላይ መግለጫው ግን አንድ ነገር በእርግጠኝነት እንድንገነዘብ አድርገውናል፤ ኢህአዴግ ሌላው ቢቀር የአቀራረብ ለውጥ እንኳ እንደማይኖረው፡፡

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop