ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ይህንን የማፊያ ቡድን በማፍረስ ታሪክ ይስሩ! በግርማ ሠይፉ ማሩ

በግርማ ሠይፉ ማሩ

ግርማ ሠይፉ ማሩ

በ2005 ዓ.ም የምክር ቤት ዘመን መጨረሻ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤቱን በሚኒስትር ደረጃ ለማዋቀር የሚረዳ አንድ አዋጅ ለምክር ቤት ቀርቦ ፀድቆዋል፡፡ ይህ አዋጅ ሲፀድቅ ከነቅሬታዬ ያለኝ ድጋፍ መስጠቴ ይታወቃል፣ ለዚህ አዋጅ ድጋፍ መስጠት የፈለኩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከበረሃ ይዘውት የመጡት ልዩ ልዩ አፋኝ ቡድን ስለማይኖራቸው እንዲሁም ቀደም ሲል የነበሩትን አፋኝ ቡድንች ወደ አንድ መዋቅር በማጠቃለል ተጠሪነቱ ከተለያዩ መዋቅሮችና ግለሰቦች ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ወደ ተገቢው ማለት ነው) ቁጥጥር በማስገባት ለዜጎች ስጋት ሳይሆን ለዜጎች እና ለሀገር ደህንነት የሚስራ ተቋም ይሆናል በሚል ተስፋ ነው፡፡ ይህ ተስፋዬም ዝም ብሎ ሳይሆን በአዋጁ አንቀፅ 3 “ይህ አዋጅ በመላው ሀገሪቱ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ በፌዴራልም ሆነ በክልል መንግስታት ደረጃ ሌላ የመረጃና ደህንነት ተቋም  ማቋቋም አይቻልም” የሚል ድንጋጌ በመያዙ ነው፡፡ በመስከረም 19 እሁድ ዕለት አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ “በሰላም” ከተጠናቀቀ በኋላ እጅግ አሰገራሚ የሆነ ተግባር አጋጥሞናል፡፡ ተስፋዬንም ስለአጨለመብኝ ይህን ጉዳይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያውቁትና የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎቱ ኃላፊውን ጠርተው ማብራሪያ እንዲጠይቁ መነሻ ለመስጠት ነው፡፡

የፓርቲያችን ወጣቶች በሰልፉ ላይ ወጣቶችን፣ ሙስሊሙን፤ ክርስቲያኑን፣ ሴቶችን እንዲሁም በግፍ የታሰሩትን ዜጎች በተመሳሌነት ለማሳየት እጃቸውን እና እግራቸውን በሰንሰለት አስረው ከፊት ሆነው ሰልፍ ላይ ሲታዩ ነበር፡፡ ማንነታቸው ያልታወቀ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ከነዚህ ወጣቶች አንዱን ጎትተው ከታክሲ በማውረድ ወደ መኪና ውስጥ ለመጫና ሲሉ በአካባቢው የነበሩ የአንድነት ወጣቶች ደርሰው መውሰድ አትችሉም በሚል ግርግር ሲፈጠር በቦታው ደረስኩ፡፡ በቦታው ደርሼ ይህን የሚፈፅሙትን ሰዎች መታወቂያ እንዲያሳዩኝ ሰጠይቅ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በአካባቢው የነበሩትን ፖሊሶች (ባለ ኮከብ ማዕረግ ያለቸው ጭምር) አስጠርቼ መታወቂያ እንዲያሰዩን እንዲያደርጉ ቢሞከርም እነዚህን ጉልበተኞች መታወቂያ ሊጠይቅ የሚችል ሞራል ያለው ፖሊስ አጣን፤ ህዝብ በተሰበሰበበት ፖሊሶችን እንዴት እንደሚያደርጓቸው ማየት በእውነት በምን ሁኔታ ላይ እንዳለን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከፖሊሶቹ አንዱ ጠርቶኝ እነዚህ እኮ ከእኛ አቅም በላይ ናቸው ሲለኝ በቅርቡ በኢሳት ቴሌቪዥን ቀርቦ ምስክርነት የሰጠው የፖሊስ መኮንን ትዝ ብሎኝ የመንግስታችን ባሕሪ አሁንም ለውጥ እያሳየ ያለመሆኑ እና ፊት ለፊት ከምናያቸው ተቋሞች ጀርባ ሌላ ስልጣን እንዳለ ፍንትው ብሎ ታየኝ፡፡ የሚገርመው በዚያው ዕለት እኔን እያወቁኝ መኪናዬን በግዳጅ አሰቁመው መንጃ ፈቃድ፣ በሚያስገርም ሁኔታ የመኪና ባለቤትነት ደብተር፣ ሰለቦሎ ዕድሳት የማያገባቸውን ሁሉ እየጠየቁ ታዘን ነው በሚል ከገዢው ፓርቲ ጋር በመተባበር ስልፉ እንዳይሳካ  ሲሰሩ የነበሩ ፖሊሶች በሰዓታት ልዩነት መታዊቂያ ያለመጠየቅ ስልጣን ያላቸው ልዩ ዜጎች እንዳሉ አስገንዝበውናል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እነዚህን ሰዎች ማንነት ማወቅ ከፈለጉ ፎቶና ቪዲዮ በእጃችን እንደሚገኝ ላረጋግጥሎት እችላለሁ፡፡ ሲቪል የለበሱ አፋኞችን ሳይሆን ዩኒፎርም የለበሱ ፖሊሶችንም ቢሆን መታወቂያ መጠየቅና ከወሮበላ ዱርዬ እራሳችን መጠበቅ መብታቸን እንደሆነ ግን ይታወቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:   የህዝብን  የዓማታት ዕስር እና አሳር በማሳነስ እና ማድበስበስ የኢትዮጵያን ችግር መንቀስ አይቻልም

በነገራችን ላይ ሰልፉ ከተጠናቀቀ በኋላ እነዚሁ ማፊያ ቡድኖች ፎቶ ይዘው ወጣቶችን በየመንገዱ እያስቆሙ እነዚህን ወጣቶች ማደን እንደያዙ ያረጋገጥን ሲሆን በዕለቱ ለደህንነታቸው ሲባል በአጀብ ወደ ቤታቸው ለማድረስ የቻልን ቢሆንም አሁንም እነዚህ ወጣቶች በምንም ዓይነት ሁኔታ ጉዳት ቢደርስባቸው ሌላ ምክንያት የሌለ እና ይህ የተደራጀ የማፊያ ቡድን የሚሰራው ስራ መሆኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲያውቁት እፈልጋለሁ፡፡ በማፊያዎቹ በመታደን ላይ ያሉት ወጣቶች ስንታየሁ ቸኮል፣ ዳንኤል ፈይሣ፣ ፋናዬ ወ/ጊዮርጊስ፣ ኤፍሬም ሰለሞን እንዲሁም አበበ ቁምላቸሁ የሚባሉ መሆናቸው እርሶም የዓለም ህብረተሰብም እንዲያውቀት መግለፅ ተገቢ መስሎ ታይቶኛል፡፡ በአደባባዩ ላይ ሲያሳዩ የነበረውም ምስል ይህንን ይመስላል፡፡ ወንጀላቸው ይህ ከሆነ ማለት ነው፡፡

 

የሰልፉ መሪዎቸ በተምሳሌታዊ አለባበስና ሁኔታ (ከስር ተቀምጠው የሚታዩት  ወጣቶች በደህንነት  ተብዬዎች የሚሳደዱት ናቸው

 

በሀገራችን የህግ ስርዓት እንዲሰፍን የምናደርገው ጥረት የሚሳካው እንደዚህ ዓይነት አፋኝ የማፊያ ቡድኖች በማሰማራት አይደለም፡፡ የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤትም እንዲህ ዓይነት የማፊያ ስራ እንዲስራ ኃላፊነት አልተሰጠውም፡፡ የተሰጡት ኃላፊነቶችና ተግባራት ከባድ በሀገር ላይ የተቃጡ ወንጀሎችን መከታተልና መረጃ መሰብሰብ ይህንንም በህግ አግባብ እንዲፈፅም ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በደርግ የመጀመሪያ ዘመን ተሰፋፍቶ የነበረውን በየቪላ ቤት እና በየመንደሩ አፍነው ወስደው ማሰቃየት በኢትዮጵያ ምድር እንዲቆም የማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት አለቦዎት፡፡ ይህን ማድረግ የሚያስችል ስልጣን ከሌለዎት ለሰብዓዊ ክብር የሚስጠውን ክርስትና እምነት እየተከተሉ ይህንን ስልጣን መያዝ ትርጉም ስለሌለው ለእኛም ተሰፋ ስለማይሆኑን ስልጣን በመልቀቅ ሌላ ታሪክ መስራት ይችላሉ፡፡ ምርጫው የእርሶ ነው፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሸንጉሊት ናቸው ከጀርባ የሚያሽከረክር ሌላ ኃይል አለ ለሚሉት ምስክርነት እየሰጡ ነው ብዬ ለመውሰድ እገደዳለሁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለመታደግ ከተፈለገ……..ፊልጶስ

ይህ በአዲስ አበባ ከተማ በአፍሪካ መዲና የደረሰውን መነሻ አድርጌ የፃፍኩት ቢሆንም በክልልም የፀጥት ክፍል የሚባል ማንነታቸው የማይታወቅ አሳሪዎች አሉ፡፡ የእነዚህን ልዩ የሚያደርገው እስረኛ በአደራ ፖሊስ ጣቢያ ስለሚያስቀምጡ ነው፡፡ ፖሊሶች በአደራ የገቡት መፍታትም ሆነ ፍርድ ቤት ማቅረብ አይችሉም፡፡ በክልል ለማስቃያ የሚሆን የቪላ ቤት እጥረት ስለአለ ሊሆን ይችላል፡፡ ከፖሊስ የበለጠ ስልጣን ግን እንዳላቸው በእርግጠኝነት እንዲያውቁት እፈልጋለሁ፡፡ አዋጁ በፍጥነት በስራ ላይ ውሎ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በአዋጁ የተሰጡትን ሀገራዊ ተግባር እንዲሰራ እንዲያደርጉ አደራ ጭምር እጠይቃለሁ፡፡

በዚህ አጋጣሚ የአንድነት ወጣቶች እነዚህን የማፊያ ቡድኖች በአደባባይ ህግን መሰረት አድርገው ሲያጋልጡዋቸው መመልከት ከምንም በላይ ኩራት የሚሰጥ መሆኑን መግልፅ ያስፈልጋል፡፡ አሁንም ቢሆን ሁላችንም በቃ ልንል ይገባል፡፡ ታክሲ ውስጥ ያለ ተሳፋሪ ሲቢል ለባሾች እንዲህ ሲያደርጉ ማንነታቸውን መጠየቅ መብቱ መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡ የደህንነት መስሪያ ቤቱ እነዚህን ቀሽሞች እንደ ሰውር ተከታታይ አሰማርቶ ከሆነ ከአሁን በኋላ እነሱ የሚስጥር ስራ ለመስራት ብቃት የሌላቸው መሆኑ ተገንዝቦ ለሆዳቸው መሙያ የሚሆን ሌላ ስራ እንዲፈልጉ ቢነግራቸው ጥሩ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ይህን የምልበት ምክንያት በልጅነታችን የማሞ ውድነህን የስለላ መፅሐፍት ለአነበብን እንዲሁም አሁን ባለው ቴክኖሎጂ የስለላ ፊልም ለሚመለከቱ ወጣቶች የሚመጥን ስአአልሆነ ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች የሚፈፅሙት ተግባር ተራ የዱርዬ ስራ ስለሆነ ነው፡፡ እኔ ለእንደዚህ ዓይነት ተቋም ላለኝ ክብር እንደዚህ ዓይነት ዱርዬዎች አይመጥኑትም፡፡ ይህ መስሪያ ቤት በእርግጥ የተጣለበትን ኃላፊነት የመወጣት ፍላጎት ካለው (ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግዴታ አለባቸው) መስሪያ ቤቱ በባለሞያ አንጂ በተራ ጆሮ ጠቢና የመንደር ወሬ ለቃሚ መሞላት የለበትም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እኔ እማልሰጣችሁ ፣ እናንተ እማትወስዱት….

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር 2006 ዓ.ም ተግባራዊ ስራ ለመስራት የሚችሉበት ዘመን እንዲሆን ምኞቴ ነው፡፡ በይፋም ባይሆን በልቦ እና በተግባር የግል አሻራዎን በዚህች ሀገር ላይ ለማኖር መልካም አጋጣሚ አግኝተዋል፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን የሚችለው ሀገራዊ መግባባት የሚፈጠርበትን እና የጠላትነት ሰሜት የሚወገድበትን ተግባር በመስራት ነው፡፡ መልካም አዲሰ ዓመት!!!!

ግርማ ሠይፉ ማሩ

5 Comments

  1. Mr. Girma,
    Hopefully your supplication does not fall into deaf ears. When PM HD came into power, I really hoped against hope that He might be the one who can bring us closer to our destiny as a nation. Wow! was I wrong! Each and every time he went against his Christian principle to serve these uneducated cruel people who hate the very people they rule with iron fist, and who hate the very country they loot. The irony is that he is brilliant and an educated person. Why is He behaving in such manner is hard to answer. Now back to his Christian principle. A few month ago, he denied visitation for those brave Ethiopians who are incarcerated in kality prison for justice, human dignity, and truth when those Europeans want to see their condition. It is unthinkable a true Christian would do that. A little more than a year ago, He gave an interview saying that He want to be like King David. He probably did not know or heard preached that King David slew the giant oppressor Goliath. That was quite a scene that a teenager taking down the most celebrated and heavily armed giant. Yea, Pm HD wants only the crown. I hope the PM would come into his senses, and try to do what is acceptable in the sight of His God. The classic example to PM HD is Moses. If Moses wanted to be with oppressors Egyptians, He could have all the privileges that comes with power. ” By faith, Moses when grown up refused to be called the son of Pharaoh, choosing to be ill-treated with oppressed people rather than the temporary enjoyment of sin” Hebrews 11:24-25. No one guaranteed the way of Christianity is easy, but if we choose to practice it, we have to do it in the manner that serves our Lord’s interest. Mr. PM HD milk shake Christianity is not acceptable, so it is time to pay attention to oppressed people. If you want to, you can help us. You can be sure that God cares about over eighty million people. Their cry has reached heaven, and God is giving you a chance to do something about it. After all, If God be with us who can be against us? Woyanne? I do not think so!

  2. I think the so called PM is a backslide Christian who is also in denial to defend himself.

  3. Wow what a powerful message. This is the reality in Ethiopia. The country is led by duriye and werobela. I hope the PM will act. May God free us from this devilish group.

  4. I want to thank Ato Girma.
    He showed us how some groups of TPLF Gangs are leading this nation illigetimately. I think it’s time to say no to this butcher regime. WOGENOCHE, ZIMITAW ALBEZAM ENDE? Eskemeche new behagerachin inde huletegna zega yeminikoterew. Ethiopiawinet yet hede? Woyane beka libal yigebawal. Aymeslachihum?

Comments are closed.

Share