ሰላማዊ ሰልፉ ቢታገትም ፣ የተሳካ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነበር! -ከአንድነት ፓርቲና ከ 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

 

አንድነት ፓርቲ ከ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ ጋር በመሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ ያቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ (መንግስት) ክልከላ ሠልፉ ሊደረግበት ወደነበረው መስቀል አደባባይም ሆነ በአማራጭ ነት ያቀረቡት 9 አደባባዮች እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ ከአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት እስከ ቀበና አደባባይ ባለው አስፋልት ላይ ቁጥሩ ከ80 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ተደርጓል፡፡
ለዚህ ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና ሕዝቡ የመንግሥትን ፀጥታና የፖሊስ ኃይሎች ማስፈራራት አልፎ የላቀ አዎንታዊ ምላሽ ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ አመራር ህዝቡ ለሰጠው አመርቂ ምላሽ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረቡ፣በቀጣይ ለሚደረገው ወሳኝ ትግል ታላቅ የማበረታቻ እርሾ መሆኑን ያምናል፡፡ ከዚህም ሕዝቡ አመራር ካገኘ ለመብቱና ነፃነቱ ወደ ኋላ የማይል መሆኑንና በሕዝቡ ውስጥ ከፍተኛ የለውጥ ፍላጎት መኖሩን ያረጋገጥንበት፣ ትዕይንት ሲሆን በተጨማሪ ሠላማዊ ትግል በጋራ አመራር ከተያዘ ውጤታማ መሆኑን አምነናል፡፡
ሆኖም ከዚህ ሕዝባዊ ንቅናቄ የተማርነው ሌላ ነገር ቢኖር በአገራችን ያለውን የአስተዳደርና የህግ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ መውደቁንና ገዢው ፓርቲ በየትኛውም ደረጃ በሕዝብ በሚነሱ ጥያቄዎች በከፍተኛ ሥጋት ውስጥ የወደቀ መሆኑን ነው፡፡
የአዲስ አበባ መስተዳድርና የፌዴራሉ መንግሥት ለሰልፉ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ቢልም የተለያዩ አስተዳደራዊ ደንቃራዎችን በመፍጠርና የማናውቃቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በመፍጠር የቅስቀሳ ሥራችንን በማደናቀፍና ሕዝቡ ወደ ሰልፉ እንዳይወጣ በማድረግ በተግባር ሠልፍ የማይደረግባት አገር ለመፍጠር ሣይታክት ተግቶ ሰርቷል፡፡ ቀስቃሾችና አመራሮችን አስሯል መኪናዎችን አግቷል፡፡ በዚህ ውስጥ ማለፍ የተሣካ ሕዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠራችን ከዚህ በመነሳት አንድነት ፓርቲና 33ቱ በጋራ በተጠናከረ መንገድ በመላው አገሪቱ ቀጣይና ተከታታይ ሕዝባዊ ንቅናቄ የማድረግ አስፈላጊነትን ተምረንበታል፡፡
ስለሆነም በአገር ቤትም ሆነ በውጭ አገር የምትገኙ የሠላማዊ ሕዝባዊ ንቅናቄ ደጋፊዎቻችን በሙሉ ለእስከዛሬው በድጋሚ እያመሰገንን ለቀጣዩ የጋራ ሥራችን እንደተለመደው ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
አንድነት ፓርቲና 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ
መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከፊውዳላዊ ህሳቤ እንውጣ ! ፊታውራሪ መሸሻነት ብዙ ርቀት አያሥጉዘንም !! - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

 

 

3 Comments

  1. This is what deserves for fascist TPLF. Bravo opposition forces. The time to make history and bring corrupted and racist regime officials to justice is coming.

  2. በለው! የኢህዴግ ፌደራላዊ ፖሊስና አዲስ አባባ ክልል ፖሊስ በአንድንት ለፍትህና ዲሞክራሲ ቀበና በሚገኘው ጽ/ቤት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ ይህም ሌሎች የ፴፫ ፓርቲ አባላትም ተገኝተው ነበር። ፖሊሶች እጅ ለእጅ ተያይዘው ዜጎች እንዳያልፉ መንገድ ሲዘጉ ታይቷል። ሠራዊቱ የሰለጠነና የተማረ ነው ተብሎ ሲፎከርበት ጃን ሜዳን እና መስቀል አደባባይን በቅጡ የሚለይ አይመስልም። ችግሩ ከትምህርት ጉድለት ወይንስ ማንበብና መጻፍ የማይችሉ የኢህዴግ ቅጥረኞች ናቸው? የሚለው የሥርዓቱን ደካማነት ፈሪነት፣ የሠራዊቱን ሕዝባዊነት ጥርጣሬ ውስጥ ከቶታል።
    * ለዚህም ነው ሕገመንንግስቱ የህወአት/ወያኔ ማኒፌስቶ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብመተዳዳሪያ ሕግ አይደለም” እኛ የኢትዮጵያ ህዝቦች” አይልም “እኛ የኅብር ኢትዮጵያ ዜጎች” “የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ልጆች አይልም” ብሔራዊ መዝሙሩ “የብሔር ብሄረሰቦች ሕዝቦች ሆኑ የኢትዮጵያ ልጆች ይላል” ለመዝሙር ለዘፈን ጭፋሮ ለለቅሶ አንድ ይሆኑና በህገመንግስቱ ግን ያልነበሩ፣ የማይታወቁ፣ ዛሬ የተፈጠሩ፣ ብሄር፩ ብሐረሰቦች፪ እና ሕዝቦች፫ ያደርጋቸዋል። አሁን እንግዲህ መንቀሳቀስ፣ መዘዋወር፣መሰለፍ፣መሮጥ፣ ቶሎ ቶሎ መራመድ፣ የምትሄድበትን ቦታ ማሳወቅና ከተፈቀደልህ ውጭ ብትገኝ በተራ ቁጥሩ ዜግነትህ መሠረት ልትታሰር ትችላላህ ይህ ነው ሕገመንግስቱ ይከበር የምትለው…አቶ ሼም የለው ሲያብራራ አድምጡ “መሰለፍና መጮህ፣ ሥርዓቱን በኀይል ለመናድ፣ሕገመንግስቱን ለማሸበር፣ የፍትህ ሥርዐቱን ለማርከስ ብቻ አደለም… ከተፈቀደላቸው ቦታ ስለተሰለፉም ጭምር ይቀጣሉ።

    **የጃዋር መሀመድ “ሜንጫ” ትግል የተገኘው እኩልነትና ነጻነት አስከመገንጠል፣ የማይደፈረው ፌደራሊዝም ይህንን ስለሚጨምር ነው። አንደራደርም! የሚላችሁ እናንተ የመንደር ተማሪዎቹና ደጋፊዎቹ ወይም አየር በአየር ከመማር ይልቅ የመረራችሁ ሆይ፣ – ማንነታችሁን እወቁ በኋላም ሌላውን እወቁ በለው!

    ** የሠራዊቱ አባላትም ሆነ አለቆቻቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው የሚኖሩት ለዕለት እነጀራቸው ቢሆንም እነጀራ የሚኖረው በሀገር ሠላም፣ ነጻነትና እኩልነት ሲኖር ነውና ተቀጣሪና አገልጋይነታችሁ ከግለሰቦች ፍራቻ ሳትሸበሩ ነገ ምን ይመጣ ይሆን ሳትሉ ነገ የተሻለው መሆንም ማምጣትም አለብን በሚል ቁርጠኝነት ከፍራቻ እራሳችሁን አፅድታችሁ…ተግባራችሁ ለሀገር እነጂ ለብሄር፣ ነገድ፣ ፓርቲ፣ እነዳይሆን! በህወአት አማካኝታችሁም የራሳችሁን ሕዝብና ሀገር በድላችሁ አትበልፅጉ ለዚያውስ ለየትኛው የደላ ኑሮ? ለማን ይመቸው ብላችሁ? የሞቱት ምን ተተቀሙ? ቢያንስ መልካም የሠሩ ሥማቸው አይቀበርም!። ምንም ያልሰሩ የተቀበሩበት ሳይታይ እነዲሁ በደረቅ ጩኸት ገንዘብ መሰብሰቢያ ሆነዋል። ይህ አሻጥር ለእያንዳንዱ ሠራዊት፣ ምሁር ነኝ ባይ፣ አድርባይ ፣ሁሉ ትምህርት ሊሆነው ይገባል። ሀገር ፈርሶ የተገነባ ፓርቲ፣ አንድነት፣ ሠላምና ብልጽግና የትኛውም አህጉር ላይ ሀገር የለም!!

    **ሠራዊቱ ለብቻው ከሚሰለፍ lየሌላውን ዜጋ መንቀሳቀስናበነጻነት የመዘወዘወር መብት ከሚነፍቅ አብሮ ከሕዝብ ጋር ይሰለፍና ይምራ ሠራዊት በሙያውና በቃለመሐላው ግንባር ቀደም መሆን አለበት!! ሕዝብ የመንቀሳቀስ፣ የፈለገውን የሀገሪቱን መንገድና አደባባዮች ሁሉ በመዘዋወር የመጠቀም ሙሉ የዜግነት መብት አለው።ታዲያ የቀለበትና የማሳለጫ መንገዱ የእድገት መገለጫነቱ ለጎርፍ መሄጃ፣ለእንጨት መኪናና ለአህያ ብቻ ነውን !? አዎ አሁንም ሼም ነው በለው! ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን>>>>>>>>>>>>>>>>

Comments are closed.

Share