አንዳርጋቸው ጽጌ! ከኢሳያስ ጉያ፤ ነጻነት? ወይስ ባርነት?

ቦጋለ ካሣዬ (አምስተርዳም፤19/9/2013)

1. የግንቦት-7ቱ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ወያኔን በሽፍትነት ዘመኑ በአማካሪነት፤ስልጣን ከጨበጠ በሁዋላ ደግሞ በሹመት አገልግሎታል። ግልጋሎቱን ‘በቁጭት’ መንፈስ ሲናገር፤…« ውስጡ ገብቶ ማስተካከል ይቻላል ከሚል የዋህና ምናልባትም ደደብነት ሊባል በሚችል» እምነቱ የተነሳ እንደነበር ከኢሳት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር ባዳረገው ቃለ ምልልስ ነግሮናል። ይኼን እንደ ፖለቲካ እዳ ማየት አይገባም። ዛሬ ደግሞ ጎንቦት-7 ወያኔን ማስገደድ ወይም ማስወገድ የሚል አቁዋም ያራምዳል። ይሁን እንጂ ከፍሺስትና ባርነትን አፍቃሪው ከኢሳያስ አፈወርቂ ጉያ ውስጥ በመግባት ወያኔን እንጥላለን የሚል አደገኛ የፖለቲካ ቁማር ጫወታ፤ አሳሳቢ ጉዳይ ስለሆነ በግልጽ መወያየት ያሻል። ምን? ኢሳያስን እንዴት ባሪያ ትላለህ? አዎ ኢሳያስ ባሪያ ነው። ያውም ነጻነትን የሚጠላ ባሪያና የባሮች ኮርማ። የባሪያነቱን ምክንያት ለማወቅ ከፈለክ፤ የኢታሊያንን የቅኝ ግዛት ፖለቲካ እንዴት እንደሚያፈቅር በዚህ ጽሁፍ ግርጌ ማስታወሻ ላይ የተጠቀሰውን ተመልከት። የአገርህንም እድሜ ከየት ጀምሮ እንደሚቆጥርና፤ የቆጠረበትንም ምክንያት በተራ-ቁጥር 13 ተጽፎአልና ልብ ብለህ እንብብ።
2. አንዳርጋቸው ከወያኔ ጋር ለመለያየት የቆረጠበት አንዱ ምክንያት፤የቤተመንግስት በር ጠባቂዎች ከ’ወርቅ’ ዘር ያልተወለደውን ኢትዮጵያዊ ወደ ውስጥ ለማስገባት የሚያደርጉት አድሎ አንገሽግሾት ነው። ነገሩ እንደህ ነው። የቤተ መንግስት በር ጠባቂው፤ ትግርኛ ተናጋሪ የሆነን ሰው ካለምንም ችግር ወደ ውስጥ ያስገባል። ካልሆነ ግን ጠባቂው ደጅ ጠኚውን የትግርኛ ተናጋሪ ባለስልጣን ተባባሪነት/ድጋፍ እንደሚያስፍልገው በዘረኝነት መንፈስ ይንቀባረርበታል። አንታ! ስማእኒ! ማንን ትግሬ ትፈልጣለካ? አይነት ጥየቃ!(ስለ ትግርኛ ችሎታዬ ይቅርታ)።
3. ስለ ወርቅ ካነሳን… “ሴትየዋ፤ በሎቲ፣በሃብል፣በካቴናና በአልቦ ወርቅ ተጊጠው፤ ጥላ ተይዞላቸው ከሰርግ ቤት ውለው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ። ታዲያ ልብ ብሎ አይቶ የተከተላቸው፤ሲቪል የለበሰ የፌዴራል ፖሊስ ሌባ፤ ሌሊት ቤታቸው ገባና ወርቃቸውን አንድ ሳያስቀር ሙልጭ አድርጎ ወሰደው። አሁን ይኸን ስታነቡ እሰይ! የምትሉ አንዳንድ ምቀኞች መቼም አትጠፉም። የሆኖ ሆኖ ሴትየዋ አዝነው ሲያልቅሱ ጎረቤታቸው አላቃሽም ቆሽታቸው አሮና ደብኖ ኖሮ፤ አንቺ? ዋይ! ያን ሁሉ ወርቅ ሰረቀው? አንድም ሳያስቀር? ደረታቸውን መታ! መታ! እያደረጉ፤ዋይ!ዋይ!ዋይ! “አማራ አሮጎሽ እኮ ነው የሄደው”!፤“አማራ አሮጎሽ እኮ ነው የሄደው!” አሉ ይባላል። ታዲያ አንዳርጋቸው የወርቅ ዘር ዘርኝነትና ሌሎች ነገሮችም እንዲታረሙ ደጋግሞ ቢወተውትም የሚሰማው ስለጠፋ ወያኔን ለቅቄ ወጣሁ አለ።
4. ብዙም ሳይቆይ የቀሰተ ደመና አባል ሆነ። ምንም እንኩዋን እንደ ቅንጅት መሪዎች ለረዢም ጌዜ ባይታሰርም፤በቅንጅት ድል ማግስት በተከተለው የእስርና የድብደባም ሰላባ ነበር።
ከዚያም የቅንጅት ተመራጮች በቃሊቲ በታሰሩበት ወቅት፤በስደት ቅንጅትን ከሚመሩት አንዱ ዋና ሰው ነበር። የዶ/ር ብርሃኑን መጽሀፍ በማረም፣በማሳተምና ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ እንዲሰራጭም ከፍተኛ ሚና ተጫውቶአል። የመጻሐፉ ውጣ ውረድም ዶ/ር ብርሃኑን ለማግዘፍና የቅንጅት ፕሬዝዳንት እንዲሆን ለማመቻቸት ስለመሆኑ፤ በውስጡ ኢንጀነር ኃይሉን ለመተካት ይደረግ የነበረውን የስልጣን ትግል ትርካ ስናነብ እንረዳዋለን።
5. አንዳርጋቸው እኔ ራሴ ባለፈው አመት እንዳረጋገጥኩት፤ ገና በጥዋቱ ከቅንጅትን መንፈስ በፍጹም በሚቃረን መንገድ ሄዶም፤ የቅንጅት የጦር ሰራዊት ለማቁዋቁዋም ግለሰቦች መልምሎ በኬንያ በኩል ጦር ለማዝመት ሙከራ አድርጎ ነበር። የዚህ አጉል የጀብደኝነት ሰለባ የሆነው ግለሰብ ዛሬ በኡጋንዳ ይገኛል። ለምን ተሰናከለ ይኼኛው የአንዳርጋቸው ቅንጅት ጦር? ኤርትራስ ሄደው የሰለጠኑ ሰዎች አልነበሩምን? አቶ አንዳርጋቸው?
6. የአንዳርጋቸውን የወያኔ አማካሪነትና ደጋፊነት ፋይሉን የሚያውቁ፤ ገና ከጥዋቱ በአንዳርጋቸው ወደ ተቃውሞ ጎራ መቀላቀል ደስተኛ አልነበሩም። ይሁን እንጂ አብዛኞቻችን በቅንጅት መንፈስ ተጠምደን፤ እንዳንከፋፈል እንጠነቀቅ ነበርና፤የሚነሳበትን ተቃውሞ ተከላከልን። ከግለሰቦች ጋር ተጣላን። ይህም አጋጣሚ ማለትም የቅንጅት መንፈስ፤ ለአንዳርጋቸው የፖለቲካ ማንሰራራት አዲስ ሌላ ምእራፍ ፈጠረ።
7. የቅንጅት ታሳሪዎች ተፈቱ። ወዲያውም ቅንጅት ‘በውስጥ የዴሞክራሲ ችግር ምች’ ይሰቃያል በሚል ድራማ በአሜሪካ በአደባባይ ተናደ። ይሁን እንጂ ‘የውስጥ የዴሞክራሲ ችግር ምች’ በግንቦት-7ም ተከሰተና ግንቦት-7-ዴ ደግሞ ተፈጠረ። ግንቦት-7 ከወያኔ ተጽእኖ ውጭ እየተንቀሳቀሰ እንኩዋን ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሳይሆን ቀረ። አንዳርጋቸው የዚህ ሁሉ ቁልፍ ተዋንያን ነው።
8. ግንቦት-7 ሲመሰረት፤ ብዙ አገር ወዳድ ዜጋ 500 ዶላር ወይም ኢሮ እያዋጣ ተቀላቅሎት ነበር። ይሁን እንጂ እነ አንዳርጋቸው ብራቸውን ከሰበሰቡ በሁዋላ፤ በመጀመሪያ ከአንድነት ኃይሎች ጋር ለመስራት ፍላጎታቸውን ማሳየት ጀመሩ። ቀስ ብለው ደግሞ ከቅንጅት መንፈስ በመንሽራተት፤ የኦነግንና ኦብነግን ማሽኮርመም ጀመሩ። የአንድነቱ ኃይል አጎረመረመ። እነ አንዳርጋቸው ግን ብዙም አልተጨነቁም። ኢሳታቸው ስላለ የፕሮፓጋንዳ የበላይነት አላቸውና፤የጎሳ ፖለቲካቸውን በታሪካዊ በደል ፈጻሚ(አማራ) እና ስለባ(ሌለው ጎሳ) እያመካኙ፤አሁን ኤርትራ ሽባ ሆኖ የቀረውን ከማል ገልቹን፤ እንደ የአንድነት ታጋይ በማግዘፍ ጄኔራል ከማል ገልቹ! ጄኔራል ከማል ገልቹ! እያሉ አናፉብን። በደርግ ስርአት ብዙ ሰው ገድለው በኢትዮጵያ ባንዲራ ፍቅር ስር የተደበቁ የፓልቶክ ጀሌዎቻቸውም አብረው ከበሮ ደለቁ። ኦነግ ለሁለት ተከፈለ ተባልን! የጎሳው ቡድን አረቄ ሳይጠጣ ሰከረ። ይሁን እንጂ ከግርግሩ ውጭ፤ የጎሳው መንጋ ሾፌሮች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የኦነጉ ባቲ በጀርመን ተገኝተው የተናገሩትን፤ከሚከተለው የአንድ የግንቦት-7 ደጋፊ የነበረ ግለሰብ ማስታወሻ ማየቱ፤ በመሰረቱ ኦነግ ምንም ለውጥ እንዳላደረገ ስለሚያሳይ ትዝብቱን እንዳለ አቅርቤዋለሁ፤
« በኦገስት 2012 ኑረንበርግ (ጀርመን) በግንቦት ሰባትና በኦነግ በተጠራው ስብሰባ ላይ ተሳትፌ ነበር። በወቅቱ ጥያቄም አንስቼ ባገኘሁት መልስ ስለግንቦት ሰባት የነበረኝን አመለካከት እስከወዲያኛው እንድቀይር ተገድጃለሁ። የቀዳሁትን ለመረጃነት እልክልሃለሁ። ግንቦት ሰባትን የወከሉት የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ነበሩ።
አንደበታቸው የተፈታ በመሆኑ ንግግራቸው ለአድማጭ ይጥማል። የንግግራቸው ይዘት ግን ተሰብሳቢውን ኢትዮጵያዊነት የሚጠቅመን አንድ አማራጭ ብቻ መሆኑን ለማሳመን የሚጥር ነበር።
ለኔ ግን ይህ ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ከመነሻውም እዛ ላይ ሁላችንም የማያወላውል አመለካከት ያለን መስሎኝ ነበር።
ለዚህም ነበር በአቅሜ ግንቦት-7ን የምረዳው። ይሁንና ነገርና ጭራ ከወደ ሁዋላ ነው እንዲሉ ጨዋታው የለየለት የአቶ ባቲ ተራ ሲደርስ ነው። በነገራችን ላይ የአቶ ባቲ ስም ሌላ ነው። ነገርግን በአማራ ተጽእኖ የተሰጠኝ በመሆኑ ኦሮሞነቴን የሚያንጸባርቀውን ባቲ እመርጣለሁ ብለው ባለፉት ዘመናት ኦሮሞ ኢትዮጵያ ውስጥ የደረሰበትን በደል ዘርዝረው ንግግራቸው አበቁ። ያኔ ነው ለኔ ዶ/ር ብርሃኑ ወይ የቤት ስራቸውን አልሰሩም ወይም ሌላ አጀንዳ አላቸው የሚል ስሜት ያሳደረብኝ። ከዛም በመነሳት ይህንን ጥያቄ አቀረብኩ፤ንግግራችሁን ሳዳምጥ የዶ/ር ብርሃኑ ንግግር እንደ ዘፈን ነው የሆነብኝ፤ ዘፈኑም “ አረ ባቲ ባቲ “ የሚል ነው ካልኩ በሁዋላ፤ ለመሆኑ አቶ ባቲ “ በኢትዮጵያ አንድነት ያምናሉ ወይ? ስላቸው የሰጡት መልስ “ ድል አድርገን ስንገባ የኦሮሞ ሕዝብ ትገነጠላለህ?ወይስ አብረህ ትኖራለህ?ተብሎ በሚሰጠው መልስ ይወሰናል። ለዚህ ጥያቄ መልስ በአሁን ሰዓት የለኝም ብለዋል። ከዚህ በመነሳት እዛ ስብሰባ ላይ ለኔ የሚጠቅም ነገር ለመስማት በመሰረተ ሃሳቡ ላይ “ በኢትዮጵያ አንድነት” ላይ ስምምነት ባለመኖሩ ግንቦት ሰባት በዚህ ሃሳብ ላይ የጠራ አመለካከት እንዲኖረው አስመዝግቤ የኢትዮጵያውያን የአውሮፓ ዓመታዊ እግር ኩዋሰ ለማየት ሄጃለሁ።»
9. የኦነግ የታሪክ ክህደት፣የመገንጠል አባዜ፣ጥላቻውንና ወንጀሉን ከግንዛቤ በማስገባት፤ከኦሮሞ ሕብረተሰብ አብራክ የወጡት ፕሮፌሰር ፍቃዱ ደገፌ፤ የተቃዋሚ ወገን እንዳይጠነክር አንዱ ደንቃር የሆነው ኦነግ እንደሆነ ተነግረዋል። በቅርቡ የተቁዋቁመው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ድርጅትም ኦነግ ከሚያራምደው መሰረታዊ የፖለቲካ አቁዋም ልዩነት እንደሌለው፤ ሊቀመንበሩና ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ካደረጉት ምልልስ ግንዝቤ ያገኘን ይመስለኛል። ታዲያ ግንቦት-7 አገር የማፍረስ ፖለቲካ ከሚያካሂዱ ድርጅቶች ጋር ለምን አጋር ይሆናል? ለምንስ ጀሌ ይሆናል?
10. እነ አንዳርጋቸውም ይኸን ሁሉ የሚያጡት አይመስለኝም። ታዲያ ለምን ወያኔን ለመጣል በሚል የጋራ አጀንዳ ብቻ አንዴ ከፈረሰ እንደገና ለመመስረት የማይቻለውን አገር ያህል ነገር አፋራሽና አፋራሽ ይሆናሉ? ይኽ የፖለቲካ ደደብነት ካልሆነ የኢትዮጵያ ጠላትነት ከመሆንስ ይዘላል ወይ? እንደምናውቀው ግንቦት-7 ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ስላልሆነ ብዙ ጉዳዮች በግለሰቦች ብቻ ነው የሚወሰኑት።
እነዚህ ግለሰቦች ደግሞ መላእክቶች ሳይሆኑ፤ በጥቅም ሊገዙ፣ ሊታለሉና ሊገደዱ የሚችሉ ሰዎች ስለሆኑ የተደበቀ አለማ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ አያራምዱም ብሎ መገመት በፖለቲካ ዓለም የሚቻል አይደለም።
ስለዚህ ግንቦት-7 አውቆም ሆነ በድንቁርናው ለስልጣን ጥማት ሲል፤ ከኢትዮጵያ አንድነት ጠላቶች ጋር መሰለፉ እርሱንም ከጠላት በምንም መንገድ ልዩ አያደርገውም ማለት ነው። ቀጥለን በሴፕቴምበር 5፤ ከኢሳት ሬዲዮና ቴሌቪዝን ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር አንዳርጋቸው ጽጌ ባካሄደው ቃለ ምልልስ ላይ ተመርኩዘን፤ እንወያይ።
11. አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ኢሳያሳን አፈወርቂ የሰጠው ‘በጎ’ ምስክርነት ራሱም የማያምንበት ነው። አርሱው እንዳለው ሳይሆን፤ ዛሬ በኤርትራ ምንም አይነት ነጻነት የለም። የፖለቲካ እስረኞች ሲታሰሩ እንጂ ሲፈቱ ወይም ፍርድ ቤት ሲቀርቡ አይታይም። ኢሳያስ ስለ ፖለቲካ እሰረኞች ሲጠየቅ፤ “አላውቃቸውም ነው የሚለው።” የሚያደርገውም አስቃይቶ መግደል ብቻ ነው። አለቀ። ደቀቀ።
12. የአንዳርጋቸው ቃለ ምልልስ የፈጠረው ትኩሳት ገና ሳይበርድ፤ኢሳያስ ኢትዮጵያ የሚባል አገር እንደውም የተፈጠረው ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በሁዋላ ነው ብሎ ከች አለ። አንዳርጋቸው ይኼን ይጋራ እንደሆነ አላውቅም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያው ሄዝቦላ!! ‹‹የጥቅምት 24/2013 የሽብር ጥቃት 1ኛ ዓመት መታሰቢያ›› - ክፍል 2

ይሁን እንጂ ኢሳያስ እንደዚህ ያለው ካለነገር አይደለም። እንደሚታወቀው ኢታሊያ ለአምስት አመታት ኢትዮጵያን በወረረች ጊዜ ወያኔ ዛሬ እንዳደረገው በጎሳ ከፋፍላት ነበር። የዚህ የፖለቲካ ግብም ትናንሽ አገሮች እንዲፈጠሩ ያለመ ነበር። የሙሶሎኒ፤ ከሂትለር ጋር መወዳጀት የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት የሃይል አስላለፍ ስለቀየረው የሞሶሎኒ እጣ ውድቀት ሆነ። ያ የተጀመረው የአገር ብተና መሰናዶ ፖለቲካም በኢትዮጵያውን አርበኞች ትግልና በእንግሊዝ ቀጥሎ በአሜሪካ እርዳታ ሊቀለበስ ቻለ። ይሁን እንጂ እስካሁን ሻእቢያ ትግራይን ከኤርትራ ጠቅልሎ እንደ ሙሶሊኒ ማስተዳደር አልጀመረም። ስዚህም ነው እንግዲህ ኢሳያስ፤ ኢትዮጵያን ሲያስብ ከሙሶሊኒ ፖለቲካ ሀ ብሎ የሚጀምረው። ኤርትራንም ሲያስብ ያው ከኢታሊያው ክርሲፒ ነው ጅማሪው። ይኼም የኢሳያስ አስተሳሰብ አዲስ አይደለም። ጉዳዩ የአፍሪካ ታሪክ የጀምረው መቼ ነው? ከሚለው ድርሰት የሚመነጭ አስተያየት ነው። ኢሳያስ ለኢትዮጵያ የሰጣት እድሜም ከዚሁ ድርሰት፤ ማለትም የአፍሪካን ታሪክ የፈጠረው የነጭ ቅኝ ገዢ ነው፤በማለት የባሪያ ፈንጋይና ተፈንጋይ አቀንቃኞች የሚያራምዱት ሃሳብ ጋር የሚስማማ ነው። የዚህ ድርሰት ጭብጥ፤ አፍሪካውያን ወይም ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ታሪክ አልሰሩም። የራሳቸው ታሪክ የላቸውም የሚል ነው። በዝርዝርም፤የዛሬዋ ኤርትራ ባሕረ ነጋሽ በሚል አትጠራም ነበር ማለት ነው። የኢትዮጵያ ንጉስ ነገስቶች ባሕረ ነጋሽን አስተዳድረው አያውቁም ማለት ነው። ለአስመራ ስም ያወጡለት አሉ አባ ነጋ አይደለም ማለት ነው።ትዮጵያም እንደ አገር ቁሙዋ አታውቅም ማለት ነው። በቃ ይኼው ነው የኢሳያስ አፈወርቂ ፖለቲካ፤ ክህደት፤ በክህደት ላይ ክደት። ለዚህም ነው ኢሳያስን ባሪያ፤የባሪያ ፈንጋይ የታሪክ አንቀቃኝ ነው የምንለው።
ሌላው በጣም ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይም፤ ኢሳያስ ኢትዮጵያ ከሁለተኛ አለም ጦርነት በሁዋላ የተፈጠረች ነች የሚለው ቅጥፈቱ፤ ትግራይ ትግሪኝ ከሚለው እቅዱ ጋር በጣም ተስማሚ መሆኑን ነው። ምክንያቱም ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ኢታሊያ ትግራይና የዛሬዋን ኤርትራ አንድ ላይ ቀልቅሎአቸው ስለነበር የሙስሎኔ ውርስ ይገባኛል ባይ ነውና። ትግራይን ገና ያልጠቀለለች ኤርትራም በተባበሩት መንግስታት እውቅና ስላገኘች፤ ኦሮሚያ፣ኦጋዲያና ሌሎችም ከተፈጠሩና እውቅና ካገኙ፤ ለትግራይ ትግሪኝ መፈጠር በተዘዋዋሪ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ኢሳያስ በከዘራውን መሬት እየቆፈረ ያስላስላል።
ወያኔን አከርካሪውን ስብሮ ትግራይን ከኤርትራ መቀላቀል የሚያልመውን የኢሳያስ ፖለቲካ ዛሬ ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሚያካሄደው ግፍ በተንገፈገፉ ወገኖች፤ እንደግልግል እንደሚያዩት ይሰማኛል። ይኸ ማለት ግን ኢትዮጵያ እንደ አገር አትኖርም ማለት ነው። ለዚህ ነው በሰላም ወይም በአመጽ የምናደርገው ትግል ከተጽእኖ ውጭ በአገራችን ውስጥ ይጠናከር የምንለው። ወያኔን በተሻለ ስርአት መተካት የሚቻለው፤ ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ብቻ የሚቆጣጠሩትና የሚመሩት ጠንካራ ድርጅት መስርተው ሲታገሉ ነው። ሻእቢያ የኢትዮጵያ ደመኛ ጠላት ነውና ቦጎዋን አይመኝም። በባርነት ደዌ የታመመና ኢትዮጵያን የሚጠላ ኢሳያስ እንዴት ብሎ የኢትዮጵያ የነጻነት አጋር ይሆናል ብሎ ግንቦት-7ና አንዳርጋቸው እንደሚያምኑ በጣም ያስደንቃል። ለኔ ይኸ ከደደብነት ውጭ፤ አገር የማፍረስ ተልእኮ እንዳለው የማይካድ ነው።
ቀጥለን በእኛም ሆነ በሌላው አገር ተጨባጭ ሁኔታ ፖለቲካን ከታጠቀ የሃይል ሚዛን ውጭ ለይቶ ማየት እንደማይቻል የአስብን ጉዳይ አንስተን እንመልከት። ግራና ቁኝን መለየት የተሳነው፤ አንዳርጋቸው በኢሳት ቃለ መጠይቁ እንዳድበሰበሰው አይደለም የኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄ ጉዳይ።
13. ስለግጭት አፈታት፤ ፕሮፌሰር ሕዝቂያስ አሰፋ ሲይስተምሩ፤በምሳሌነት ይነሳ የነበረው፤ስለ ኢትዮጵያ ምንም እውቀት ይሁን መብት የሌለው አንድ ዝቅተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን (አንዳርጋቸው ‘ያን የሚያህል ሰው’ በሚል አምልኮቱን በተዘዋዋሪነት በቃለ ምልልሱ ላይ ያንጸባርቃል)፤ ኸርማን ኮሆን ለአካባቢው ሰላም ጠንቅ ሊሆን የሚችል የፖለቲካ ውሳኔ የሰጠበት ምክንያት የራሳችንን ጉዳይ አሳልፈን ስለሰጠን ነው በማለት፤ ቅራኔን ለመፍታት ስለ ቅራኔው የጠለቀ እውቀትና የተደበቀ አጀንዳ የሌላቸው ገለልተኛ አስታራቂዎች እንደሚያስፈልጉ ያስተምራሉ።
14. በበኩሉ ኸርማን ኮሆን የሚነሳበትን ክስ ደግሞ ሲከላከል፤ ወያኔና ሻእቢያ በጦር የበላይነት ስለነበራቸው አሜሪካኖች የሚሉትን ሊቀበሉ አይችሉም ነበር፤ የአሜሪካም ሚና ተጨባጩን ሁኔታ አይቶ የተደረገ ዳኛነት እንደነበር ግንዛቤ መወሰድ ያስፈልጋል ይለናል። ይሁን እንጂ ወያኔንም ሆነ ሻእቢያን አሜሪካ ምን ያኸል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ትርዳ እንደነበርና በተቃራኒው ደርግን በተለይም የኢትዮጵያን ሰራዊት ለማፍረስ የተጫወተቺውን ሚና አያነሳም። ይኸም ብቻ አይደለም፤ ኸርማን መለስ ዜናዊን የአስብን ጉዳይ አንስቼበት አያገባኝም ብለኦል በሚል፤ ለኢትዮጵያም አሳቢ እንደነበር አንጀታችንን ለመብላት ይዳዳዋል። ይሁን እንጂ ኸርማን ያልነገረን ወይም ያልገባው ነገር ቢኖር፤ አሜሪካ ወያኔና ሻእቢያ እንዲሁም ደርግን በገለልተኝነት/ካላድሎ ማደራደር ያቃታት የደርግ መዳከም ወይሞ የነወያኔ ጥንካሬ ከሆነ፤ መለስ ዜናዊስ ቢሆን ገና ያልጠና ስልጣኑ አደጋ ላይ እንዳይወድቅበት፤ በአስብ ጉዳይ አያገባኝም ያለው ወደብ ጠልቶ ሳይሆን የሻእቢያን ሃይል ፈርቶ ላለመሆኑ ማረጋገጫው ምንድን ነው? የሚለውን ነው። እንደውም ከዊኪሊክስ እንዳነበብበው፤ ኢሳያስ ወደ ኬንያ እረፍት በሄደበት ጌዜ መለስ አውሮፕላን አዞላት አዲስ አበባ ከአስመጣው በሁዋላ፤ ወደ አስመራ በሚመለስበት ጊዜ በአውሮፕላኑ ላይ አደጋ አድርሶ ከኢሳያስ ለመገላገል ያደረገው የመጀመሪያው የከሽፈ ሙከራ ፤መለስ የሚፈራውን ተቀናቃኝ ለማስወገድ አንዱ እርምጃ መሄዱን ያሳያል።
ይሁን እንጂ በኤርትራና በኢትዮጵያ ጦርነት ጊዜ የኢትዮጵያ ጦር ኢሳያስ ከአንድ ሆቴል ሆኖ ትእዛዝ መስጠቱን ደርሶበት፤ ኢሳያስን ለመግደል ፍቃድ ጠይቆ ይሁንታ ቢያገኝም ኢሳያስ ቀደም ሲል መረጃ አግኝቶ እንደወጣ እየሩሳሌም አርአያ ባደረገው ቃለ ምልልስ መናገሩ ትዝ ይለኛል።
እንደ እየሩሳሌም ከሆነ አቶ ስዬ አብርሃ ይሄን ለሕዝብ ባለመናገራቸው ሊወቀሱ ይገባል ባይ ነው። የሆኖ ሆኖ ኢሳያስ እንዳይገደሉ ያከሸፈው መለስ ቢሆንም፤ ከጦርነቱ በሁዋላ ግን የድንበሩን አወሳሰን ጉዳይ አልቀበልም ያለውም መለስ ነበር።
አሁን ደግሞ በቅርብ በዊኪሊክስ እንደተጋለጠው፤ መለስ የልብ ልብ ስለተሰማው፤ ‘የድንበሩን’ ችግር ለመወሰን፤ የወያኔ ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ተዳርሶት እንዲኖራት መፈለጉን እንማራለን። ይኸንንም ደግሞ እውን ለማድረግ ወያኔ እንደ ማካካሻ ለኤርትራ መሬት ለመስጠት እንደሚፈልግና ይኸ ሳይደረግ ግን በድንበሩ ክለላ ስምምነት ላይ ለመድረስ አለመፈለጉን ስነዱ አጋልጦአል።
ለነገሩ የዚህን ፍንጭ የዛሬው የይስሙላ ጠ/ሚርም ምክትል በነበሩበት ጊዜ ስለ አሰብ ተጠይቀው፤ ኢሃዴጋቸው ‘ወደብ ቢያገኝ እንደማይጠላና’፤ የአስብን ጉዳይ በሚመለከት ግን ስለጥያቄው አንስቶ እንደማውቅ ነገርውናል።
አንድ ጊዜ መለስ ዜናዊም የኤርትራና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ግንኙነት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፤ የጥባቴነት (parasitic) ጠባይ ያለው ነው ማለቱ አይዘነጋም።
ስለዚህ የጅቡቲው ወደብ ክፍያ እየናረ ስለመጣ፤ ለኢፈርት ኢኮኖሚም ቢሆን መለስ የራሱ ወደብ ያስፈልገኛል ብሎ የተነሳው፤ የወታደራዊ ሃይሉ፤ በማንኛውም ወቅት ቢሆን ኤርትራን አፈርመሬት ያስግጣል ብሎ ካመነ በሁዋላ ነው። መለስ ለሱዳን መሬትም የሰጠውም በዚያ በኩል ክፉኛ ተቃዋሚ እንዳይመጣበት ለመከላከል ነው። መለስ ዜናዊ ስልጣኑን ለመያዝ የማይወስደው እርምጃ አልነበረም። ሥላሴ ባይጠራልን ኖሮ ምናልባት ሌላ 20 አመታት ሊገዛን ይችል ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኤርትራን በአቋራጭ (ከኤፍሬም እሸቴ)

15. የሆኖ ሆኖ ዛሬ ኽርማን ኮህን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያላቸው አስተያየት በጣም ተቀይሮአል። ደሞ እንዴት? ማለት ጥሩ ነው። ባለፈው በጋ ወር በአሜሪካ በተደረገው የኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት አመስራረት ጉባኤ ላይ ምሁራን፣ ምርጥና ምላጭ ጭንቅላት ያላቸው ዲፕሎማቶችና የቀድሞ ባለስልጣናት ተሳትፈው ነበር። ከጉባኤው እንደተረዳነው ኸርማን ኮህን፤ ትናንት ኢትዮጵያ አስብን አጣች ብለው የአንዞ እንባ ቢያልቅሱም፤ ዛሬ ግን ኢትዮጵያን እንደ አገር ማየት አቁመዋል። ከዶ/ር ካሳ ከበደ የንግግር ጭብጥ እንደምንረዳው፤ ኮህን ‘ኢትዮጵያዊነትን በማይፈልጉ’ ቡድኖች (ኦንግና አብነግን ማለታቸው ለመሆኑ ጥርጥር የለውም) ላይ በግድ መጫን አያስፈልግም የሚል አቁዋም ይዘዋል። ክፉ አትበሉኝና፤ እንግዲህ የዛሬውን የኮህን አቁዋምና በኢሳት ላይ ደግሞ አንዳርጋቸው የለገሳቸውን ሙገሳ ስናጤን፤ አንዳርጋቸው/ግንቦት-7፣ኮሆንና ኢሳይስ አፈወርቂ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በአንድ መስመር ላይ እንደተሰለፉ ለማረጋገጥ ጠንቁዋይ መቀለብ ይሻን ይሆን? ፈዛዛ ጭንቅላት የሌለው ሰው ካልሆነ ይህን አደጋ ማየት የሚከብድ አይመስለኝም። በነገራችን ላይ በጉባኤው ላይ ግንቦት-7ን ወክሎ የነበረው፤ ነዓምን ዘለቀ፤ የኢሳት ዋና ስራ አስኪያጅ ነው። አሳት የግንቦት-7 አይደለም ይባል የነበረውን ማደንቆሪያ ለማጋለጥ ከዚህ የበለጠ መረጃ የለም።
16. በተጨማሪም አቶ አንዳርጋቸው አስብ በመሄዱ በቃለ ምልልሱ ላይ ቢቆጭም ሲል ስለ አስብ ያነሳነው ግን ከላይ የጠቀስነውን የሃይል ሚዛን ያላገናዘበ ነው። ደግሞሞ አስብ ከሄደ በሁውላ 2 አመታትት ወያኔን በማገልገሉ ብቻ በኤርትራም መገንጠልም ሆነ በአስብ መሄድ ማንንም የመክሰስ የሞራል ብቃት የለውም። ስለዚህ አቶ አንዳርጋቸው ሊገነዘበው የሚገባው አላህ የተጠራልንን መለስ ሺህ ጊዜ ማውገዝ ፋይዳ የሌለው ከመሆኑ ሌላ፤ጀሌዎችን እንጂ ሌላውን አድማጭ መሽንገል የማይቻል መሆኑን ነው።
17. ለነገሩ ኢሳያስ በቅርቡ እንደተናገረው ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመግዛትና በአስብ ጉዳይ ላይም ውይይት መጀመሩን አልደበቀም። የሚደንቀው ግን አንዳርጋቸው ‘ጫካ ለጫካ ሲንከራተት’ ኢሳይስ እንኩዋን ስለ አሰብ የተዋዋለውን ውል አለመስማቱ ነው። ጫካ ያደድባል ይል ነበር፤ አብርሃም ያየህ!!
ደግሞም እኛ ነጻነት አፍቃሪና በታሪካችን የምንመካ ኢትዮጵያውያን አስብ! አሰብ! የምንለው 1.5 ቢሊዮን ዶላር ለመቆጠብ ብቻ ሳይሆን፤ በሰላማዊ መንገድ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ግንኙነቶች በማጠናከር የቅኝ ግዛትን መርዝ፤ ቀሰ በቀስ አምክነን፤ የመረብ ምላሴ ትውልድም (የዛሬዋ የባርነት አሻራ ኤርትራ ተፍቃ፤በባሕረ-ነጋሽ ተተክታ ማለት ነው) ሆነ የተቀረው ኢትዮጵያዊ ትውልድ ታላቁዋን ኢትዮጵያ ገንብቶ፤ በታሪኩ ኮርቶ በሰላምና በዲሞክራሲ ስርአት በልጽጎ የማየት የነበረውን የቅድመ አያቶቻችንና አያቶቻችን ራእይ ስለምንጋራና ለአዲሱ ትውልድ እንዲተላለፍ የማድረግም ሃላፊነት ስላለብን ነው። ለሚያልፍ ዓለም የማያልፍ ስምና ስራ ተክቶ ማለፍ የተማርነው ከአያቶቻችን ነውና።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እኛም የሚሊዮኖች አካል ነን። የአንድነት ጉዳይ ያገባናል - ግርማ ካሳ

ማጠቃለያ፤
18. ከላይ ዘርዝር አድርገን እንዳየነው፤ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ በወያኔ አገልግሎት፣ በቅንጅት ምስረታ፣ ቅንጅት ውስጥ ደግሞ ብዙም ባልገፋ ‘የሚደቅሳ’ ፖለቲካ ጫወታ፣ በቅንጅት መንፈስ የተላበሰ መሳይ ግንቦት-7 ምስረታ፣ ከጎሳ ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በመሳሳብና ዛሬ ደግሞ በአደባባይ እንደሚነግረን በኤርትራ የተሰበሰቡትን የኢሳያስ የጎሳ ጦሮች፤ በሻእቢያ ፍቃድ፤ ‘ፖለቲካ’ እያስተማረ ይገኛል። እንግዲህ ቀንቶት ለሁለተኛ ጊዜ የጎሳ ጦር አጅቦ አዲስ አበባ ከገባ፤ ኢትዮጵያ እንደ አገር ትቀጥል? ወይም ትፍረስ? የሚለውን የኦነግን ሪፈረንደም ወደደም ጠላም ለማስፈጸም ይገደዳል ማለት ነው። አንዳርጋቸው በቃለ ምልልሱ ላይ እንደ ፈጣሪ ለማየት የዳዳው ኸርማን ኮሆንም፤ አስታራቂ ይሆንና ኦጋዴንም እንዲሁ እንደ ኦሮሚያ ልገንጠል? ወይስ ከኢትዮጵያ ጋር ልኑር? የሚል ምርጫ እንዲያካሄድ አጋጣሚው ይመቻቻል ማለት ነው። ባይ! ባይ! ደህና ሁኝ አገሪ! ይሉሃል ይኼ ነው!
እንግዲህ ግንቦት-7 አስቸጋሪ ለሆነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አስተማማኝ አቅጣጫ ለማመላከት አልቻለም። እንደውም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ወደ ተሸረበው ሁለተኛው ዙር ታላቁ ሴራ ዘው በማለት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ከኢሳያስ ጉያ ውስጥ ገብቶአል። ግንቦት-7 የማይታረቁ ጉዳዮችን፤ ጎሳና የግለሰብ ነጻነትን በማምታትና በመቀላቀል ከጠላት ጋር ወግኖ ነጻነትን ለማምጣት በመቃዠትና እንደ ኢሳት ያሉ የመረጃ አገልግሎቶችን እንኩዋን ነጻነት በመንፈግ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የጭቆና ዘመን ማሳጠር ሲገባው እያራዘመው ይገኛል።
ዶ/ር ብርሃኑ ግንቦት-7ን ሲመሰርት፤ “እኛ እንጀምራለን። ካቃተን ግን እናቆማለን ብሎ ነበር።” አሁን ከልህ ወጥቶ ቆም ብሎ የማሰቡ ጊዜ የደረሰ ይመስለኛል። በግል አንዳርጋቸውም ሆነ ዶ/ር ብርሃኑ በወያኔ ተጠቅመዋል። ግፍም ደርሶባቸዋል። ይሁን እንጂ ከኢሳያስ ጉያ ገብቶ በአገር ጉዳይ ቁማር መጫወት አደገኛ እንደሆነ ሌላ ተልእኮ ከሌላቸው ቁጭ ብለው ሊያስቡበትና፤ ትግሉ በመሃል አገር ብቻ እንዲጠናከር ሊሰሩ ይገባል። ኢሳትም እንደልቡ እንዲሰራ ድርጅታዊ ጭቆናቸውን ቢያቆሙ ይበጃቸዋል።
19. ደፋሩ የእነ አበበ ገላው ትውልድም ዳር ቆሞ ከሚያይ፤ የሰላማዊ ትግሉ በአገር ቤት እንዳይዳፈን ተጨባጭ አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅበታል።

21 Comments

  1. እናመሰግናለን::G7 ከኤርትራ ይውጣ::ከተገንጣይ ቡድኖች ራሱን ያግልል::ካልሆነ ዳግማዊ ወያኔ ነው::

  2. ante enklfam zemblh tegna weyane gena gelbto ygerfhal were kemawrat zem maletu yshalal enkfat anhn mot leweyane dell legnbot 7 !!!

  3. Yodit lemekebater amel yalet eko mimintam silehone arfo aytegnamna atdareki. Yemiasazinew zehabesha yemimintam bota mehonu new.

  4. Mr.wrighter i read your article very carefully one of my sens organ tells me you have a very good woyane/tplf test please stay out of what you don’t even know about it let them do there job i understand they knows what they are doing don’t west there time.

  5. Yehenene yemedere ware tetethe ende wendochu werde wede chakawe, G7 lemjemeria geze bachere gezi weyane yarebedbede ena amerore weyane lemedemese zegejutune yecherese yemeselale, yanetem weyanwei ferhte kezhu yemeta newe. Issayas endate le ande kene enquane sele gelesbe kuche belo yedela bate weste tere segana weski eyeteta sezelabede alnore gn Huletune ye negusune ena yemengestune serawite demeseso endhume yantene weyane be tanke ajebo menlike betemengeste yasegebana ye Eritrean bandera U,N laye yeskele jegena newe

    • Nice Joke matit, kkk

      Yet chaka yihon G7 yeweredew. Eskahun sint wereda ena awraja netsa awtitew yihon? enkuan ye G7 10 yemaymolu tagayoch, 350,000 wetaderoch yeneberut shabia enkuan woyanen meququam alchalem.

      ye hono hon keldehen (joke) wedejelehalehu!!

  6. ከምንም ነገር በላይ ወያኔን የሚያክል ከእርቅ በላይ የሆነ የኢትዮጽያ ጠላት ተቅመጦ ባቅሙ የዘላለም ጠላት ወያኔን (እንደ ዲያብሎስ ያለ ማለት ነው) ሊያጠቃ የተነሳን ሃይል ለማውገዝ ይሄን ያህል መድከም እጅግ የማይርሳ ክህደት ነው። “አባይ የሚያድርበት የለው፤ ግንድ ይዞ ይሄዳል” የተባለውም ይሄንኑ ነው።

    ሁሉም በየፊናው ባመነበት መንግድ እንደ ደቡብ አፍሪካ ታጋዮች አንዱ አንዱን ሳያሳጣ የዘላለም የኢትዮጽያ ጠላት የሆነው ወያኔን ከምድር ላይ ለማጠፋት ብቻ ገንዘቡን፤ ጉልበቱን፤ እውቀቱን፤ ህሊናውን መስዋእት ለማድረግ ያለተንሳ ሁሉ እሱ እራሱ እኩል የኢትዮጽያ ጠላት ነው። በተለይ በአሁን ሰዓት ሃገራችን ኢትዮጽያ ያለችበትን ሁኔታ እያወቀ በተቃዋሚ ኃይሎች ላይ ብዓዕሩን የሚያንሳ ሁሉ እሱም እራሱ እኩል የኢትዮጽያ ጠላት ነው።

    መቼም ለሱም አልታዘዝንለትም እንጂ፤ እንደኔ እንደኔ 11ኛው የፈጣሪ ትዕዛዝ “የምትወዳትን ኢትዮጽያ ሃገረህን ለመቅበር የተነሳውን ጠላትህ እስኪ ወድቅ ድረስ፤ ባቅማቸው ሊያድንዋት የተነሱትን ሁሉ ስማቸውን በክፉ አትንሳ” ቢባል በእውነት እንዴት ደስ ባለኝ ነበር።

    ኢትዮጽያ ለዘላለም ትኑር! ዓሜን

  7. ከምንም ነገር በላይ ወያኔን የሚያክል ከእርቅ በላይ የሆነ የኢትዮጽያ ጠላት ተቅመጦ ባቅሙ የዘላለም ጠላት ወያኔን (እንደ ዲያብሎስ ያለ ማለት ነው) ሊያጠቃን የተነሳን ሃይል ለማውገዝ ይሄን ያህል መድከም እጅግ የማይርሳ ክህደት ነው። “አባይ የሚያድርበት የለው፤ ግንድ ይዞ ይሄዳል” የተባለውም ይሄንኑ ነው።

    ሁሉም በየፊናው ባመነበት መንግድ እንደ ደቡብ አፍሪካ ታጋዮች አንዱ አንዱን ሳያሳጣ የዘላለም የኢትዮጽያ ጠላት የሆነው ወያኔን ከምድር ላይ ለማጠፋት ብቻ ገንዘቡን፤ ጉልበቱን፤ እውቀቱን፤ ህሊናውን መስዋእት ለማድረግ ያለተንሳ ሁሉ እሱ እራሱ እኩል የኢትዮጽያ ጠላት ነው። በተለይ በአሁን ሰዓት ሃገራችን ኢትዮጽያ ያለችበትን ሁኔታ እያወቀ በተቃዋሚ ኃይሎች ላይ ብዓዕሩን የሚያንሳ ሁሉ እሱም እራሱ እኩል የኢትዮጽያ ጠላት ነው።

    መቼም ለሱም አልታዘዝንለትም እንጂ፤ እንደኔ እንደኔ 11ኛው የፈጣሪ ትዕዛዝ “የምትወዳትን ኢትዮጽያ ሃገረህን ለመቅበር የተነሳው ጠላትህን እስኪ ወድቅ ድረስ፤ ባቅማቸው ሊያድንዋት የተነሱትን ሁሉ ስማቸውን በክፉ አትንሳ” ቢባል በእውነት እንዴት ደስ ባለኝ ነበር።

    ኢትዮጽያ ለዘላለም ትኑር! ዓሜን

  8. Thank you for taking your time writing this article. Some of your negative comment about these individuals or g7 may make sense. But I have one important question for you. Do you have any other alternate solution you can offer us beside opposing what they are doing? At list they are doing something!

  9. it’s easy to criticize the work of others, but the difficult thing is to be part of the solution. Before, denouncing their strategy, you had to know how they arrived on such kind of strategy. I think, they have analyzed different alternatives before arriving on this strategy. So, it would be advisable if you mentioned another way of struggle other than the one they are doing now. But when you mention the best option, you have to convince the readers by telling the advantages as well as the disadvantages the selected option and the one you prefer should have higher benefit than its cost. I hope they will accept your advice if you do this properly.

  10. This is a coffee house cadre of some kind of political organization. A sick person with a never ending poltical wish.

  11. Wedednm telanm be ahun seat le ethiopia hizb weyannen emiakl aremene telat yelewm. weyanen be ager bet tigil lemasweged betam aschegari yehonu nebegeroch alu kezih befitm temokro taytual. bichegnaw amarch ye titik tigil new bilen kaln demo ke Eritrea yebelete amechi menderideria linor aychlm. Zuriachinn yekebebun ageroch betekilala ye weyanne tikimegnoch silehonu beminm melku yetitik tigliun liagzu aychlum. MR BOGALE minalbat ante emitilew neger enkuan lik yihonal bilen binikebelh ena ye G7 amarach sihtet new binil MIn yeteshale amarach Hasab aleh. Leloch balachew akm le hager ena le wegen bemaseb emiserutn hasab sitichefelek andit mesmer enkuan amarach lihon yemichl hasab alakerbkm. silezih esti ebakh ebakh yeteshale new emitilew menged kaleh tekumen

  12. This guy is clearly one of woyanne cadres. The reason I say that is not because he has disagreements about Ginbot 7 getting help from the Eriterian government but because he is trying to discredit Ginbot 7 by making personal attacks against Ginbot 7 leaders. If he had a doubts about Ginbot 7’s strategy of getting help from Eriteria, he could make a genuine argument why Ginbot 7 shouldn’t receive help from Mr Esayas and state his reasons why he disagree with Ginbot 7’s leadership. He should also propose an alternative to that. But making personal attacks in such away will definitely create suspicion on the person’s motives. We all might have questions about the nature of relationships between Ginbot 7 and the Eriterian government and the motives behind Eriterian’s willingness to provide help to opposition groups like Ginbot 7. It is also expected from Ginbot 7 answer the questions and give assurances that they will not bargain the future of Ethiopia and Ethiopian people with any one.

  13. we have to evaluate the consequence what happend Tplf were friend with Shabia,we lost one big state (Eriteria) then we become landlocked! what will happen the friend ship of Genbot 7 and Shabia? we most probably lose some part of ethiopia…Bademe? Ogaden? the whole Oromia (if this happen,no more Ethiopia)…
    we all know that to remove Eprdf there must be some support,but we should ask serious questions abt in return that supporter what he need?

  14. “ይዘገያል እጂ አህያ የጅብ ነች”
    asebin yaskemane erasu ahun yalew geዢው party mehonu emaykadi ነbarawi haki new

  15. Tigre people liberAtion front is the brain child of Isayas Afeworki. TPLF were escorted to Addis Abeba by Shabia. TPLF were trained, conceived, and were serevants of Shabia. Do these TPLF cadres forget where they came from.

  16. ከስራ ሁሉ የመጨረሻው ቀላል ስራ ሌሎች የሰሩትን መገምገምና መተቸት (review) ነው፡ ምክንያቱም ገምጋሚው ስራውን የሚገመግመው ስራውን በተሰራበት ሁኔታ ላይ ሳይሆን ሁሉ ነገር በተሟላበት እሳቤ ነው (Reviewer reviews document or some once work in the assumption of the ideal conditions). ገምጋሚዎች ብዙ ጊዜ የሚያቀርቡት ትችት እንጂ የመፍትሄ ሃሳብ ወይም አማራጭ፤ አይደለም፡ ምክንያቱም የትችቱ መነሻ የተለፋበትን አድንቆ ጉድለትን አስተካክሎ ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ታስቦ ሳይሆን ከጥላቻ፤ ከንቀት፤ ራስን አንቱ ከማለት መነሻነት ስለሆነ ያልተመቻቸውን አካሄድ የመናድ የማፈራረስ ግብ ስንቀው ነው፤ የሳይበር አለም ደግሞ ለሚጻፉትም ሆነ ለሚነገሩት ነገሮች ከሃላፊነት ነጻ ስለሚያረግ የሌላውን ስራ እንደፈለጉ መገነጣጠል ይቻላል፡ ይህ ደግሞ ለማንም ለምንም አይጠቅምም፡
    ግንቦት 7 የተሳሳተበትን ዝርዝር ከማቅረብ ሊሻሻል የሚችልበትን፤ ሊታረም የሚገባውን፤ አማራጭ መንገዶችን የጠቆመ አስተያየት ቢሆን ኖሮ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፤ ነገር ግን ለዚህ ገና የበቃን አይመስለኝም።

Comments are closed.

Share