የቦምብ ጥቃት በሐሮ ወንጪ ቅ/ገብርኤል ገዳም ላይ መፈጸሙ ተዘገበ

(የፎቶ ምንጭ ሐራ ተዋሕዶ ድረገጽ)በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት ወንጪ ወረዳ ሐሮ ወንጪ ቀበሌ በሚገኘው የሐሮ ወንጪ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙን ሐራ ተዋሕዶ ድረ ገጽ ዘገበ። እንደ ድረ ገጹ ዘገባ “ጥቃቱ የተፈጸመው ጳጉሜ 4 ቀን 2005 ዓ.ም ምሽት 5፡00 ላይ ወደ ገዳሙ ቅጽር በተወረወረው ቦምብ ነው፡፡”

በገዳሙ የኪዳነ ምሕረት፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ዑራኤልና ቅድስት አርሴማ ታቦታት መኖራቸውን የገለጹት የገዳሙ አበምኔት መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር ኣብርሃ፣ የተወረወረው ቦምብ በገዳሙ ቅጽር ውስጥ ቢፈነዳም በመነኰሳቱ ላይ ያደረሰው ጉዳት አለመኖሩን ለዜና ሰዎች ተናግረዋል ያለው የድረ ገጺ ዘገባ “የአንድነት ገዳሙ አስተዳደር በቁጥር 17/2005 በቀን ፭/፲፫/፳፻፭ ለሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ለወንጪ ወረዳ መስተዳደርና ፖሊስ ጽ/ቤት በጻፈው የድረሱልን ጥሪ÷ ከዚህ ቀደም የገዳሙን ይዞታ በመጋፋት፣ መነኰሳቱና መናንያኑ ገዳሙን ለቀው እንዲሄዱ ተደጋጋሚ ዛቻና ስድብ በማሰማት የሚታወቁ 18 ግለሰቦችን በስም ለይቶ በመዘርዘር በጥቃቱ አድራሽነት እንደሚጠረጥራቸውና በቁጥጥር ሥር ውለው ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል፡፡ በስም ከተዘረዘሩት 18 ግለሰቦች መካከል ጌቱ ታደሰ እና መኰንን ካሳ የተባሉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የኾኑ የቀበሌው ነዋሪዎች በዋና አስተባባሪነት ተጠቅሰዋል፡፡” ብሏል።

ሀራ ጨምሮም “ደብዳቤው ‹‹ፀረ ሃይማኖት የኾኑ ግለሰቦች›› ሲል የገለጻቸውና በቡድን የሚንቀሳቀሱት እኒህ አካላት፣ በገዳሙ ላይ ከዘጠኝ ጊዜ በላይ የተለያዩ ጥቃቶችን በገዳሙና በገዳማውያኑ ላይ በማድረስ ንብረት ማውደማቸውንና መነኰሳቱን ማሳደዳቸውን ጠቅሷል፡፡ ‹‹ለቀበሌው ብዙ ጊዜ አመልክተናል፤ ከአቅሜ በላይ ነው በማለቱ መፍትሔ ሳናገኝ እስከ አሁን አለን›› በማለት ከግለሰቦቹ ጥቃት ባሻገር አስተዳደራዊ በደልም እየተፈጸመ እንደሚገኝ ደብዳቤው አጋልጧል፡፡” ብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ የውይይትና መፍትሄ መድረክ (ኢውመመ) በኢትዮጵያ ላይ ስለሚካሄደው ሕዝባዊ እምቢተኛነትና የገዢው ፓርቲ የጭካኔ እርምጃዎች ያወጣው መግለጫ

እንደ ድረ ገጹ ዘገባ የወረዳውና ቀበሌው ባለሥልጣናት በተገኙበት ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከነዋሪው ጋራ በተደረገ ውይይት ሕዝቡ በቡድን እየተንቀሳቀሱ በገዳሙ ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ግለሰቦችን የጠቆመ ቢኾንም ተገቢው ርምጃ ባለመወሰዱ÷ ግለሰቦቹ ገዳሙ በሚገለገልበት የውኃ ታንከርና የሶላር ቴክኖሎጂ ላይ ባደረሱት ጉዳት ሲስተሙ ለብልሽት ተደርጓል፤ መነኰሳቱ በሱባኤ ላይ ባሉበት ቀን ለቀን ወደ ገዳሙ ክልል ገብተው በይዞታው ላይ ችግኝ ከመትከል፣ የገዳሙ መውጫና መግቢያ በኾነ ቦታ ላይ አጥር ከማጠር አልተከለከሉም፤ ገዳማውያኑንም ‹‹ከዚህ ቦታ ባትመጡ ይሻል ነበር፤ ለዛሬ ብቻ ነው የምትኖሩት፤ ብትውሉ አታድሩም›› እያሉ በስልክና በአካል በተደጋጋሚ ዛቻና ስድብ ከማስፈራራት አልታቀቡም፡፡ ‹‹በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየዕለቱ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚሰነዘርብን ጥቃት በዘመናዊ የጦር መሣርያ ጭምር የታገዘና በቀጣይም እየተጠናከረ እንደሚሄድ ያሳያል›› ያለው የገዳሙ አስተዳደር÷ ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከሌሊቱ 7፡40 ዘመናዊ የጦር መሣርያ ታጥቀው ወደ መናንያኑ መኖርያ የመጡት ግለሰቦቹ በመናንያኑ መኖርያዎች ላይ የድንጋይ ውርጅበኝ ማዝነባቸውን፣ ጥይት መተኰሳቸውን፣ ገዳሙን በጥበቃ እንዲያገለግሉ የተቀጠሩ የአካባቢው ተወላጆች ሥራቸውን እንዲተዉ ያልተሳካ ሙከራ ማድረጋቸውን አስታውሷል፡፡

ሀራ ዘገባውን ቀጥሎ “ገዳሙ ይዞታውን በሕግ ያረጋገጠበት ደብተር እንዳለው የጠቀሰው አስተዳደሩ የሹራብ ሽመና፣ የዶርና እንስሳት ርባታን ጨምሮ ራሱን የሚያግዝበት የልማት ጅምሮችና ዕቅዶች ቢኖሩትም ፍትሕ እያጡ በሚሰደዱት መነኰሳት ምክንያት ጥረቱ እየተሰናከለ ነው፤ በገዳሙ ምሥረታ ከነበሩት 15 መነኰሳት መካከልም ጸንተው የቀሩት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ ወረዳው በተለይ ከ፳፻፬ ዓ.ም ጀምሮ ከገዳሙ ለሚቀርቡለት አቤቱታዎች ሁልጊዜ ተስፋ ይሰጠናል እንጂ የተጨበጠ ነገር አላስገኘልንም፤ ትኩረትም አይሰጡትም ያለው አስተዳደሩ÷ ‹‹መንግሥት ለሃይማኖታችንና ለገዳማችን ልማት የማይተኙልንን ፀረ ሃይማኖት የኾኑ ግለሰቦች›› በአስቸኳይ በቁጥጥር ሥር እንዲያውልና ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስድባቸው ጠይቋል፡፡ ብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ተከታታዮች በሙሉ: እንኳን ከ2014 ዓ.ም ወደ 2015 ዓ.ም በሰላም አሸጋገራችሁ

6 Comments

  1. this is weyanes divide and rule system they wanted christians to disappear from the face of ETHIOPIA but it won’t happen instead weyane will be destroyed by the power of GOD

  2. በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ። ( 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3 ቁጥር 12)
    ከቦምብ የባሰ ጥቃት ቢሰነዘር እንኳን ቁምነገሩ በጽድቅ መኖር መቻል ነው እንጂ ጉዳዩን የማንፈልገውን አካል ለመምታት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮፖጋንዳ ማዋል ክርስቲያናዊ መርህ አይደለም። ለእግዚአብሔር ቤት ከእግዚአብሔር በላይ መቆጨት ግብዝነት ቢሆንም ጥንቃቄ ይጠብቃል ማስተዋልም ይጋርዳል። ጥላቻና አካላዊ አፀፋ ፅዩፍ ናቸው። ያሁን ዘመን ጴንጤና ኦርቶዶክስ ከጭፈራቸው ውጪ አንድ ናቸው። የተመሰረቱበትን አለት ረስተው ለምድራዊ ጥቅማቸውና ክብራቸው የተጉ፣ ዘላለማዊ አጀንዳቸውን የረሱ፣ ንፁሁን ወንጌል ከማሰማት ይልቅ ተፈለጥኩኝና ተቆረጥኩኝን ብቻ የሚጮሁ፣ እርስ በርስ የሚነካከሱ፣ በአስተዳደር ላይ የፅድቅ ተፅእኖ ማምጣት ሲኖርባቸው የፖለቲካ ወጥመድ ታናቂዎች፣ ተረትና ፍልስፍና አንጋሾች፣ ከፍቅርና አንድነት ይልቅ ጥላቻና ልዩነትን ሰባኪዎች፣ የስህተት ትምህርትን ከመከላከልና ተኩላውን ከመመንጠር ይልቅ እርስ በእርስ መናፍቅ በመባባል ተወናያጆች፣ ከመንፈሳዊ እሴቶች ይልቅ ቁሳቁስንና ለፅድቅ የማይሆን ስርአቶችን ያስቀደሙበት ዘመን ነው።
    ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን
    የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ። ( ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ቁጥር 18)
    አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን
    ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥
    አገልግሎትህን ፈጽም። ( 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4 ቁጥር 5)

  3. Ahee! ene enkuan protestantoch telatachin sew aydelem yemnwagawm keseytan gar new silu new emawkew yhen wshet keyet ametachihut tewu ebakachu yihe esat hulunm new yemibelaw behuala be esat atchawetu ebakachu weyanewoch lerasachum asbu.
    CHEW BITETAFIT TAFIT ALEZYA DENGAY NEW BILEW YWEREWRUHAL

  4. Confused and desperate Woyane is running out of divide and kill recipe.they failed miserably with their plan which they tried to make a rift between Muslims and orthodox.now,they came up with this plan.what a loser.time is running out on them.it is a matter of time.they will go for good once for all.

Comments are closed.

Share