September 17, 2013
11 mins read

የኛ ነገር፤ ከኔ ማእዘን፤ ክፍል 14 (ከተክለሚካኤል አበበ)

ከተክለሚካኤል አበበ

የግንቦት ሰባት ርእሰ-አንቀጽ
1. ከግንቦት ሰባትና የግንቦት ሰባት አመራር አባላት የማደንቅላቸው ድንቅ ነገር ቢኖር ሌሎችን ያለመተናኮስ ባህርያቸው ነው። ሌሎች ቢተነኩሷቸውም እንኳን፤ ምንም ምላሽ ያለመስጠት አቋማቸውን አደንቅላቸዋለሁ። እስካለፈው ሁለት ሳምንት ድረስ። ባለፈው ሁለት ሳምንት ግን፤ በራሳቸው አነሳሽነት አገር ቤት ያሉትን ድርጅቶች ወደመተንኮስ ያዘነበሉ ይመስላል። በተለይም ሰማያዊ ፓርቲን። ስለዚህም ጥያቄ ተነሳብኝ።
2. ግንቦት ሰባት፤ ነሀሴ መጨረሻ ላይ፤ http://www.ginbot7.org/2013/09/02/በሰማያዊ-ፓርቲ-አባላት-በደረሰው-ወያኔያ/ አንድ ርእሰ አንቀጽ ጽፏል። ርእሰ አንቀጹ የሚቆጣም የሚያላግጥም ይመስላል። ድሮ ልጆች ሆነን አባቶቻችን የሚሉንን አይነት ለዛ አለው። “ሀሳብህ ጥሩ ነው፤ ጥረትህንም እናደንቃለን፤ ነገር ግን ልጅ ስለሆንክ ነው” አይነት ነገር።
3. የኢህአዴግ አገዛዝ የሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰልፍ ሲዘጋጁ በነበሩ አባላት ላይ ያደረሰውን ድብደባ ያወገዘው ግማሽ ገጽ ርእሰ አንቀጽ፤ በግማሽ ገጽ ላይ ሰባት ግዜ “ወጣቶች ወጣቶች” እያለ ወርዶ (ትንሽ አጋንኜ ነው እንጂ አምስት ግዜ ብቻ ነው)፤ ወጣቶቹን ተስፋ ለማስቆረጥ የታለም የሚመስል መልእክት ይሰነቅራል። እንዲህ ይላል።

“ወጣቶች ምን ትላላችሁ? ጥንካሬያችሁን እናደንቃለን፤ ሆኖም የያዛችሁት መንገድ የባላንጣችንን ባህሪይ እግምት ውስጥ ያስገባ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አለን። … ባርነትን ትቀበላላችሁ ወይስ አማራጭ የትግል ስልቶችን ለመመርመር ትደፍራላችሁ? ባዶ እጆቻችሁን እያሳያችሁት እየረገጠና እያዋረደ “መንግሥት” ነኝ ብሎ የሚኮፈስ እኩይ ጋጠወጥ ጋር ሰላማዊ ትግል ያዋጣል ትላላችሁ?”
4. ርእሰ አንቀጹ ሀቀኛ አይደለም። ርእሰ አንቀጹ፤ መልሱን ለናንተ እንተወዋለን ቢልም፤ መልሱን ግን ዝቅ ብሎ ይመልሰዋል። መልሱ፤ ባንድ በኩል “የሰላም ትግል ከእኛ ወዲያ አልቆለታል” የሚል መልእክት ያለው ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ “ሁለቱም ተያይዘው ይሄዳሉ” የሚልም ለዛ አለው። አንዱ ያላንዱ፤ ሰላማዊው ከአመጽ፤ የአመጹም ከሰላማዊው ተለይተው ህይወት ይላቸውም ይላል። አንዱ መንገድ ያለሌላው ህይወት ከሌላቸው የራሳቸውን ጠበቅ አድርገው ሌሎቹም የራሳቸውን ጠበቅ እንዲያደርጉ መምከር ሲገባ፤ ወያኔ ከዚህም የከፋ ድብደባና ውርደት ስለሚያከናንባችሁ፤ መንገዳችሁን መርምሩና፤ ዛሬውኑ ወስኑና እኛን ተቀላቀሉ ምን የሚል ግብዣ ነው ያቀረቡት።
5. እነሱማ ወስነዋል። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወስነው፤ የለም ጠብመንጃ መሸከም አንችልም፤ ዳገት ቁልቁለቱን መውረድ፤ እሾህና ጋሬጣውን መቋቋም፤ አውሬውንና መከራውን እንደምን መሸከም አይቻለንም፤ መሸከም ብንችልም፤ የትጥቅ ትግል ተገቢ አይደለም ብለው በሰላም፤ ነገር ግን በመጋፈጥ እዚያው አገር ቤት ሊፋለሙ ወስነዋል። ግንቦት ሰባት አንዳቸው ያላንዳቸው ህይወት የላቸውም ካለና፤ የራሱ የመለመላቸው ጫካ የገቡ ሀይሎች ካሉት፤ ለሰላሙ የቆሙትን ደግሞ ባላችሁበት በርቱ ማለት ሲገባው፤ እንደገና ደግሞ ከወያኔ ጋር የሰላማዊ ትግል አያዋጣምና እኛን ተቀላቀሉ ምን የሚሉት ጅልኛ አነጋገር ነው።
6. የዚህ ርእሰ አንቀጽ መንሸዋረሩ ብቻ ሳይሆን የታሪክ ድግግሞሹም የሚገርም ነው። የዛሬ ዘጠኝ አስር አመት ሰላማዊ ትግል ብቸኛው ምርጥ መንገድ ነው የሚሉት የግንቦት ሰባት መሪዎች ነበሩ። እነ ኢህአፓ አገር ቤት በሰላም የሚታገሉትን ድርጅቶች ወያኔዎች ናቸው ወይም ለወያኔ ህጋዊነት ያሰጡታል እያሉ ሲከሱ ሁሉ ብርሀኑ ነጋ (ዲባቶ) አውሮፓና አሜሪካ መጥቶ በፍጹም ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ መንገድ ነው እያለ ይሰብክ ነበር። የዛሬው ርእሰ አንቀጽ ግን ልክ እነሱ ከአገር ሲወጡ የሰላማዊ ትግል ከነሱ አብሮ እንደተሰደደ ነው የሚነግረን። የሰላማዊ ትግል ከነሱ መሰደድ ጋር እንዳበቃለት ይሰብካሉ።
7. እንደኔ እንደኔ አስተያየት፤ የግንቦት ሰባት ርእሰአንቀጽ፤ በሰላም እንታገላለን የሚሉትን ሁሉ እነሱን እንደሚያሳጡ አድርገው ከማሰብ የመነጨ ይመስላል ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ፤ የዛሬው የግንቦት ሰባት አቋም፤ ትናንት እነሱ ቅንጅት በነበሩበት ግዜ፤ ኢህአፓና ወዳጆቹ ሲያራምዱት የነበረውና እነሱ የግንቦት ሰባት ሰዎች ሲዋጉት የነበረው አቋም ነው። ርእሰ አንቀጹ፤ “ያለን ምርጫ ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው ሲል የደነገገልን ማነው?” ብሎ ይጠይቅና፤ ሰላማዊ ትግል ከትጥቅ ትግል በላይ መስዋእትነት ሊያስከፍል እንደሚችል፤ እንደውም ሰላማዊ ትግል ብቻውን ድል ማቀዳጀት እንደሚችል ማረጋገጫ እንደሌላ ይናገራል። እንዲህ ያለው ያልጠራና የተደባለቅ አካሄድ ነው ቀደም ሲልም በቅንጅት ዘመን ድል ያሳጣን።
8. ግንቦት ሰባት የሚያዋጣውን መንገድ መርጦ ከገባ በሁዋላ፤ የሌሎችን መንገድ ባደባባይ መተቸትና መጠየቁ አግባብነቱ አይታየኝም። የራስን የትጥቅ መንገድ መተንተን አንድ ነገር ነው፤ የሌሎችን የሰላም መንገድ ማጣጣል ደግሞ ሌላ ነገር ነው። ይሄ ርእሰ አንቀጽ፤ ቀደም ሲል ግንቦት ሰባት የተናገረውን፤ በምንም መልኩ ሌሎችን አንነካም የሚል መርህ የሚጣረስም ነው። በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የደረሰውን መከራ ማውገዝ አንድ ነገር ነው። ከዚያ አልፎ ግን ይሄ የደረሰባችሁ ሰላማዊ ትግል የሚባል የፖለቲካ ደዌ ስለአዛችሁ ነው ብሎ በሌሎች መንገድ ላይ መፈትፈትና ማላገጥ ፋይዳው አይታኝም። ስለዚህ ግንቦት ሰባት ርእሰ አንቀጹንም፤ ርእሰ ነገሩንም ይመርምር።
9. በመጨው አርብ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቃለምልልስ ላይና፤ ብርሀኑ ነጋ (ዲባቶ) ጎበዝ የዴሞክራሲ ጊዜ መሪ ስለመሆኑ፤ በምንም መልኩ ግን ውጤታማ የትጥቅ ትግል መሪ ሊሆን ስላለመቻሉ እጽፋለሁ። የማደንቀውና የማከብረው የግንቦት ሰባት ዋና ጸሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ እኔ አምስት ስድስት አመት በተደጋጋሚ የጻፍኩበትን ከኤርትራ በቅርበት የመስራት ነገር ደግፎ መናገሩ ቢያስደስተኝም፤ ያቀረበት መንገድና ትንተናው በጣም የሚዘለዘል ነው። ባለፉት አራት ቀናት በቶሮንቶና ኦታዋ ስለከረመው አቶ ግርማ ሰይፉም ትንሽ እቀዳለሁ። ከአቶ ግርማ ጋር ያደረግነው ይፋ ህዝባዊ ስብሰባ በቪዲዮ ስለተቀዳ፤ ለኢሳት እንልከውና ኢሳት ካልገገመና መልካም ፈቃዱ ከሆነ በኢሳት ትመለከቱታላችሁ። በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ በግልና በቡድን ከአቶ ግርማ ጋር ስለተጫወትናቸው አንኳር ጨዋታዎች እጽፋለሁ። ኢንሽ አላህ አለ ሀሰን ኡመር አብደላ። እግዚአብሄር ያውቃል እንደማለት ነው።
እኛው ነን፤ ከቶሮንቶ፤ ካናዳ፤ መስከረም፤ 2006/2013

24 Comments

  1. ተክሌ ልክ ነህ። የግንቦት 7 ርዕሰ አንቀጽ ቅን አይደለም። እርስ በርስም ይቃረናል በትክክል እንደጠቆምከው። በአንድ አፉ ለስልጣን የሚደረግ የእርስ በርስ ጦርነት እንጂ ሰላማዊ ትግል አይሰራም ይላል ጽሑፋቸው። በሌላ አፉ ደግሞ የእርስ በርስ ጦርነት ትግል ከሰላማዊ ትግል ጋር ካልተቀናጀ (ካልተጋገዘ) ብቻውን ፋይዳ የለውም ይላል። ምን ያህል ግልጽ የሆነ ግንዛቤ እንደሊላቸው በትክክል አሳይተሃል። የዛሬዎቹ ግንቦት 7 ልክ ያኔ ቅንጅቶች በነበሩበት ጊዘው እንደዞረባቸው ናቸው። ያኔ የተጀመረውን ወጣት ሰላማዊ የነፃነት ትግል አስመቱት። በተለይ ብርሃኑ እና አንዳርጋቸው። ዛሬ ግን የፈለጉትን ቢያወሩ አይችሉም። ኢትዮጵያ ብዙ የበሰሉ እና በመብሰል ላይ ያሉ የሰላም ትግል ተንታኞች አፍርታለች። አንዳርጋቸው እና ብርሃኑ ጋሬጣ ሆነዋል ግን ለጊዜው ነው!

  2. የግንቦት 7 ርዕሰ አንቀጽ እንደሚለው ሳይሆን ሰላማዊ ትግል እና የትጥቅ ትግል (የርስ በርስ ጦርነት) እሳት እና ጭድ ናቸው። ይጠፋፋሉ። ጦርነት የሶሪያን ሰላማዊ ትግል ድራሹን እንዳተፋው በአይናችን ያየነው ነው። ትጥቅ ትግል አምባገነን ይሰጥሃል። ሰላማው ትግል ግን ዴሞክራሲን ይሰጥሃል።

  3. የዛሬ 8 አመት ብርሃኑ እና የዛሬዎቹ ግንቦት 7ቶች ትጥቅ ትግል (የእርስ በርስ ጦርነት) አይሰራም። መንገዱ አንድ እና አንድ ብቻ ነው። እሱም ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው። እናንተ ግንዘብ ብቻ አምጡ። ይሉን ነበር። ዛሬ ደግሞ አንዴ ትጥቅ ትግል ነው መንገዱ እናንተ ገንዘብ ግፉ ይላሉ። ሌላ ግዜ ሁለቱ መተጋገዝ አለባቸው ሰማያዊዎች ግን ጫካ ግቡ ይላሉ። እስከዚህ ድረስ ለ9 አመቶች ይኽ ግሩም የነጻነት ትግላችን ላይ ውሃ ሲጨምር መቆየቱ አይረሳም። በታሪክ ይጠየቃል። ጥሩ ዜና ግን ዛሬ ኢትዮጵያ የጅን ሻርፕ ሰላማዊ ትግል ተማሪዎች ማፍራቷ ነው። በዚህ እንጽናናለን። እነ ብርሃኑ ሁሉንም ብለው ጨርሰዋል። የሚተፉበት እየመጣ ነው። ብርሃኑ ያውቃል። ለዚህ ነው ብርሃኑ ጡረታውን የሚያስጠብቅለት ቋሚ ስራ የጀመረው።

  4. ትክሌ ባልከው ብዙ እስማማለሁ። ትንሽ ልጨምርበት ፍቀድለኝ። የብርሃኑ ሰላማዊ ትግል እውቀት ሌኒን በአንድ ገጽ ላይ ዱማ ውስጥ ገብቶ ስለመታገል የጻፈው እንጂ የዘመኑ የሰላም ትግል ጠበብቶች እነ ግን ሻርፕ በጻፉት ላይ መሃይም ነው። ሌኒን ሰላማዊ ትግል እና አመጽ ይተጋገዛሉ ይል ነበር። የግንቦት 7 ረዕሰ አንቀጽ እንደሚለው። ባጭሩ ብርሃኑ እና አንዳርጋቸው ፋይዳ የላቸውም። አት ኢሳይስ ለእኛ (ለኢትዮጵያኖች) ሲል መከረ እንደበላ እና እየበላ ሰለመሆኑ የሚያወራ ሰው አያስደነግጣችሁም? እሱ ይምራን? ኢሳያስ ደግሞ በቀደም ኢትዮጵያ የምትባል አገር በታሪክ እንደሌለች ነገረን አንዳርጋቸው እንደሚለን ከሆነ ኢሳያስ ይኽንንም ያለው ለእኛ (ለኢትዮጵያውያን ሲል) ነው። ያሳዝናል።

  5. የግንቦት 7 ርዕሰ አንቀጽ እንደሚለው ሰላማዊ ትግል እና ትጥቅ ትግል (Civil War) አይተጋገዙም። ተቃራኒ ናቸው። ለምሳሌ በከተሞች የምናካሂደው የእኛ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል በጫካ ትጥቅ ትግል ቢጀምር ኖሮ በአሁኑ ጊዜ ሰላማዊ ትግል ተደምስሶ ነበር። በአሜሪካም የእነ ማርቲን ሉተር ትግል ትጥቅ ትግል ቢያጣምር ኖሮ ጥቁሮች ዛሬ የደረሱበት ደረጃ አይደርሱም ነበር። የማርቲን ሉተር ጉዋደኛ የሲቪል ራይት መሪው አንድሬው በቀደም በዋሽንግተን ህዝባዊ ስብሰባ ላይም ይኽንኑ ነበር ያለው። እነብርሃኑ ተራ እየሆኑብኝ ነው የመጡት። ይገርማል። እኒ እንደሚመስለኝ ትግሉን ዛሬ ብቅ ብቅ በማለት ላይ ላሉት የጅን ሻርፕ አይነት አስተሳሰብ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ትተውት ቢሄዱ ይሻላል። የሌኒንዝም የማኦኢዝም የተደበላለቀበት አስተሳሰብ የኢትዮጵያን የትግል ሜዳ ለቆ ቢወጣ እመኛለሁ። እነ ብርሃኑ እና እን አንዳርጋቸው የምርጫ 97ን ድል አሳጡን። አሁንም ችግር እየሆኑብን ነው። እባካችሁ ሂዱልን።

  6. I am suprising that all of you dislike to fight TPLF. do you want to be colonized for ever by TPLF? Tekele , why did you run to America through Kenya.you know me , I know you since we were in one tent.allof your coments are Trash. I am tired .

  7. አስተያየት ስትሰጡ ቅንነት ያለው ቢሆን ምናለበት? የተናዳፊ አስተያየት ምንጩ ከየት ወገን እንደሆነ…

  8. አቶ ተ.አበበ በተለያዩ ወቅት ይምትጽፋቸው ስሁፍ እትዮጲያ አሁን ከአለችበት የፖለቲካ ውጥንቅጥ አንዳትወጣ ይተቃዋሚወችን ስነልቦና ሊሸርሽር የሚችል አና የግለሰቦችንም ስብእና የሚንካ መሆኑን በግልጽ ያሳየ ነው፤ባለፉት ዓመታት ኪኒያ በነበርክበት ወቅት እና አሁን ያልሀ አመለካከት እየተጣረሰብኝ ይገኛል ምናልባት ፖለቲካው አንተን አያውቅህም ወይም አንተ ፖለቲካውን አታውቀውም ለማለት ዳዳኝ ስለዚህ ወንድም የገደል ማሚቱ ሆነህ የተቀዋሚን ጉድፍ አየነቀስክ በኢትዮጲያ ህዝብ ላይ ተጨማሪ የስቆቃ አመት አትጨምርበት ካለው ጋር ተስማምቶ መስራት ወይም መኖር ጥበበኝነት ነውና መቻቻልን አወቅበት፤ከግንቦት ስባት ጋር ሳይሆን መጅመሪያ ከራስህ ጋር ታረቅ ከልብህ ሁን ግንቦት ስባት የራሱ መስመር አና የትግል ስልት አለውና፤ልብ ይስትህ፡፤

  9. Poisonous Woyanes can you stay away from our indispensable comrades? No one has expected a chicken from snake egg, this literally applies to you guys. Dr Birhanu has paid an utmost scarification for his mother land and he knows the behaviour of wild woyanes more than any of us. So he is suppose to share his ordeal that he had endured in Ethiopia to members of semeyawi party. Peaceful struggle doesn’t work out in countries like ours where there is no rule of law but rule of jungle prevails. Your motive behind all these rhetoric is to keep woyanes on power by waging smear campaign against brave Ethiopians committed to engage in armed struggle. Tigre is Woyane and Woyane is Tigre after all.

  10. tekle kenya hielhu fufu yemibal megeb selemitebela chewa neberk .haun gen hamberger hiebelah chiklati abete.gudenoch kalachew ye leg sew ager hono endayebed senlebonaw miker yesfelegewal bene gemet, he tekele ahuns deberken-

  11. I am really amazed by Ginbot 7. Berhanu is calling on Semayawi Party to to jungl and die for him while he is living in the USA in comfort. He is an immoral person.

  12. Wow, We are even questioning why we died for TPLF. We Arenas are now struggling against TPLF and against our past. we brought the worst type of Dictatorship. Learn from us!

  13. Guys, have you noticed the arrogance of Berhanu. He is just as arrogant as Melese was. So he is an other worst potential dictatorship. Fight him.

  14. Berhanu, do you understand Semayawi party is an election party not a gurrela fighter. please stay away.

  15. Bravo Tekle,

    If we don’t correct the mistakes that are made by any political opposition then we are doomed. What is wrong with crticizing G-7 or any other political opposition? they have to use to it because it is part and parcel of politics. People have a right to critcize anyone as they have a right to support. The main idea here is it is constructive criticizim.

  16. ato tekle, now i stopped to comment on your nonsense garbege, instead i suggest you to see a psycatrist before its too late as you seem that you are suffering with paranoia, shit head wake up and run to see a doctor rahter than flooding all website with your nonsense garbege, of course the only people who are dancing empty dance are the weyane evil members and anti ginbot 7 elements who cant do anything except dancing all over the planet, regardless of your empty echo, ginbot 7 is a head ache for weyane and a true path to freedom and democracy, MAFERIA

  17. Tekle!

    Yebabin merz yawm kemot keterefe yemyawk yetenedefew bicha new yeselamawi tglen kekinijit belay yemyawk lasar new, ahunm yenesemayawi partin mechersha enayalen weyane zim kalachew geen aydelem weyane lesimu sil new selfun yemifekdew kezia tinsh kef silu melso ybelachewal ,yeweyanen chekagninet liasay yichlal beselamawi tgle mesewat mechereshaws? ene samora eshi blew siltan ysetalu yemaytaseb new.

    • @Eyob
      Either write in English or Amharic or Oromgna or Tigrigna. Do not waste out time with this gibrish.

  18. tekele chiras eyebasebeh metah, lemin tebel atetemekim, i am tired of your nonsense attack against ginbot 7, of course those enemies of ginbot 7 are celebrating as they are worthless , but for true ethiopians your attack is a pain and you are a true MORON, edegmewalew, YOU ARE UNKNOWING MORON

  19. Tekele I respect your writing but for G-7 it is not the first time to call to be with them what happen to you now they call muslim ,Amhara, and so .even Amhara youth start struggle with gun .are they wrong then why don’t write for the Amhara youth to put their gun ? do you think the people who wrote comments the supporter of idea think theater Way!

  20. Tekle stands out among those who frequently like to degrade and attack people in leadership role, without lifting a finger to help the group they are a part of. His relentless demand to be in the lime light is a constant issue which causes problem for him to get along with members he is supposed to collaborate with.

    Constructive criticism should be welcomed as a growth promoter and a moral booster for an organization. But one shouldn’t resort to personal attack and defamation, there by serving as hatchet man for Woyane, when giving feed back. People who struggle for the same cause may yet differ in their strategy of how to achieve their goals. It is also acceptable for the leaders to change the mode of struggle as conditions change. They are not liable for blame as long as they seek sincere feed back and their explanation is accepted by their followers. This however does not immune them from criticism, from friends and foes,in and outside the organization.

    If Tekle is attempting to assert that Dr. Berhanu has not been true to the cause or has not made his share of contribution for the democratic struggle of Ethiopia, let him openly declare this with tangible proof. Otherwise, cutting down the leader(s) of Ginbot-7 with a distorted here say is not only an intentional destruction of this opposition group but may also be construed as a mission of a Woyane stooge.

    Tekle, look up into the clear September sky and you may hear Melese from Hell saying to you, ” Thank you for a good job”.

Comments are closed.

Previous Story

በ6 ኪሎ አንበሳ ግቢ አንበሳ ሰው ገደለ

mental
Next Story

በቻድ አንድ የስነ አእምሮ ሐኪም ብቻ በኢትዮጲያስ? (ክፍሉ ሁሴን)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop