ቀነኒሳ በቀለ ያሸነፈበት ቪድዮ – Video

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ድሃውን በማፈናቀል ላይ የሚገነባ ከተማ ‘ስማርት’ ሳይሆን የሰይጣን ከተማ ነው።” ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ [ኤኮኖሚስት]

2 Comments

  1. መቼ አቅም አነሰን__አጥተን እንጂ ዳኛ
    በሩጫው ብንሄድ ጠላት ብንዋጋ
    ለሰላም ዘብ ብንቆም ለእርቅ ብንተጋ
    ኩራት ነበርን ለአለም_ ክብራችን ተዋርዶ
    እህት ወንድማችን_ ከሀገር ተሰዶ
    ባንዲራችን ረክሶ_ ድንበራችን ጠቦ
    በዘረኛ አገዛዝ_ ህዝባችን ተርቦ
    አንገት አቀርቅረን ቅስማችን ተሰብሮ
    በሀዘን ውስጥ ከርመን በዝቶብን እሮሮ
    ተስፋችን ተሙዋጦ_ እንዳይሆኑ ሆኖ

    ድንገት ይመጡና_ በአለም አደባባይ
    ባንዲራ አንስተው_ ከፍ አርገው ወደላይ
    ኢትዮጵያን ሲያሳዩኝ_ አውጥተው ከሰማይ
    አንገቴን አቅንቼ_ ማንነቴ ሳሳይ
    ተስፋዬን መልሰው_ ቅዠቴን አባረው
    ያስፈነድቁኛል ያጣሁትን_ ፍቅር በኩራት አድሰው

    ግጥሙ መታሰቢያነቱ ለአትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ለሻለቃ ሀይሌ ገብረ ስላሴ መታሰቢያ ትሁንልኝ።

  2. መቼ አቅም አነስን_ጉልበት አጣን እኛ
    ፍትህ አደላዳይ_አጥተን እንጂ ዳኛ
    በሩጫው ብንሄድ_ጠላት ብንዋጋ
    ለሰላም ዘብ ብንቆም_ለእርቅ_ብንተጋ
    ኩራት ነበርን ለአለም የሰላም ወታደር

    ዛሬ ሰላማችን ጠፍቶ _ክብራችን ተዋርዶ
    እህት ወንድማችን_ከሀገር ተሰዶ
    ባንዲራችን ረክሶ_ድንበራችን ጠቦ
    በዘረኛ አገዛዝ_ህዝባችን ተርቦ

    አንገት አቀርቅረን_ቅስማችን ተሰብሮ
    በሀዘን ውስጥ_ከርመን_በዝቶብን እሮሮ
    ተስፋችን ተሙዋጦ_አንጀታችን ደብኖ
    አርሮ ከስሎ ጨሶ_እንዳይሆኑ ሆኖ

    ድንገት ይመጡና_ በአለም አደባባይ
    ባንዲራ አንስተው_ከፍ አርገው ወደላይ
    ኢትዮጵያን ሲያሳዩኝ_አውጥተው ከሰማይ
    አንገቴን አቅንቼ _ማንነቴን ሳሳይ
    ተስፋዬን መልሰው_ቅዠቴን አባርረው
    ያስፈነድቁኛል ያጣሁትን ፍቅር_በኩራት አድሰው።

    በትክክል የጻፍኩት ግጥም አንዳንድ ስንⶉች ስለተዛቡና ስለጠፉ ደግሜ ጻፍኩት

Comments are closed.

Share