ሰመረ አለሙ
ቀደም ሲል ዳግማዊ ጉዱ ካሳ በሚል ስም ለልጂ ተክሌ የጻፈዉን ከግምት በማስገባት እሱ በጠቃቀሳቸዉ ጉዳዮች ላይ መጠነኛ ግንዛቤ ለመስጠት ብእር መምዘዝ ግድ ብሏል።
በመጀመሪያ ደረጃ ጸሀፊዉ ቋንቋዉ ላይ ያለዉን የበላይነት ለመግለጽ እወዳለሁ (ሃሳቡን አላልኩም ልብ በሉልኝ) ወረድ ብዬ ደግሞ ጽሁፉን በስሱ ሳጠናዉ ጽሁፉ በቀጥታ የተነጣጠረዉ ልጅ ተክሌ ላይ ሁኖ ዶ/ር ብርሀኑን አስመልክቶ ልጂ ተክሌ የዘገበዉ በእጅጉ እንዳበሳጨዉ ከጽሁፉ ለመረዳት ከመቻሉም በላይ የጉዱ ካሳ ጽሁፍ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ላይ የተመዘዘ ሰይፍ ነዉ ተብሎ ቢነገር ለክርክር አይዳርግም የሚልም አመለካከት አለ። ጉዱ ካሳ ዲማቶ ከመዉደቃቸዉ በፊት ዘሎ መሀል ገብቶ የቁርጥ ቀን ወዳጂ መሆኑንም አሳይቷል ለዚህም አድናቆት ይቸረዋል።
ብቻ ሲያመጣዉ አንዴ ነዉ የጉዱ ካሳንና፡የልጂ ተክሌን ጽሁፍ ካነበብን በሗላ ደግሞ በጥሩ ኢትዮጵያዊ አቀራረብ ስለ ዶ/ር ብርሀኑ ሌላዉ እንደ ልጂ ተክሌ አንጀቱ የበገነ አንድ ጽሁፍ አስነበበን። አዎ ዶ/ር ብርሀኑ እና አቶ አንዳርጋቸዉ ሊሸፈኑ የሚችሉ ካለመሆናቸዉም በላይ ሊሸፈቱም ግድ ይላል ሁኔታዉን እስከዛሬ በቅርብም በሩቅም ስንከታተለዉ ነበር። መለሰ ዘራዊ በህይወት ቢኖር እና ቢፈልግ እነዚህን ሰዎች የሚፈልጉትን ሰጥቶ ይመልሳቸዉ ነበር ይጠቅማሉ ብሎ ከገመታቸዉ ይህም ግለሰቦቹ ላይ ካለን ጥላቻ ሳይሆን የህይወት ታሪካቸዉን በሚገባ ከመበርበር የተወረወረ አስተሳስብ ነዉ።
ወደ ጉዱ ካሳ ሌላዉ ክፍል ስንሸጋገር ዶ/ር ብርሀኑ ስለ ዋሂቢሰቶቹ ያላቸዉን አመለካከት አስመለክቶ በመደገፍ “ኢትዮጵያዉስጥ የሸሪያ ህግ ተቋቁሞ ኢትዮጵያ የእስላም አገር ትሆናለች የሚል እብድ ነዉ” የሚለዉን የሀጂ ነጂብን ማረጋገጫ ሰጥቶናል። እዚህ ላይ ጉዱ ካሳ እስላም ይሁን ሌላ እርግጠኛ ባንሆንም ይህን ማረጋገጫ አምነን ዶ/ር ብርሀኑን እንድናምን የተፈለገበት ምክንያት ግን ግልጽ አይደለም። እዉነታዉ ግን ሓጂ ነጂብ በጣም ጥበበኛ እንደኛዉ አገላለጽ ደግሞ ጩሉሌ ብለዉ ሊጠሩ የሚገቡ ሰዉ ናቸዉ። ብዙ ንግግራቸዉን ባለፈዉ አምስት አመት ተከታትለነዋል አንዳንድ ስብሰባቸዉንም ተሳትፈናል። ሐጂ ነጂብ እስላሞች ስብሰባና ሌሎች ስብሰባዎች ላይ የሚያወሩት የተለያየ ሃሳብም ነዉ። የህዋትንም መንግስት እንደዛሬዉ ከመጣላታቸዉ በፊት መንግስታችን ነዉ በማለት ሙሉ ድጋፋቸዉን ሲሰጡ የነበሩም ሰዉ ነበሩ። የሀጂ ነጂብ ሚስት ወ/ሮ ዘይነብ ይባላሉ እሳቸዉ የተናገሩትን ሙሉዉን ቃልም ቀድተነዋል “ኢትዮጵያ የእስላም አገር ትሆናለች ማሺ አላህ; አቶ መለሰ ወደ እስልምና ቢመለሱ ይሻሎታል ኢትዮጵያ በሸሪያ ትተዳደራለች” ይላል ቅንጫቢዉ ከዚህም የባሰ አባባል ታክሎበታል። ወ/ሮ ዘይነብ እና ሀጂ ነጂብ አንድ ሀይማኖት አንድ እምነት አንድ የኢስላም አይዲዮሎጂ የሚጋሩ ባልና ሚስት ናቸዉ በየስብሰባዉም ተከታትለዉ የሚሄዱ ናቸዉ።የሚለያዩት ሐጂ ነጂብ እንዲህ ያለ ቋንቋ የሚናገሩት በእስላሞች ዝግ ስብሰባ ነዉ እነ ጁሀርን የመሳሰሉ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎችን በክብር ሲጋብዙ።
በጉዱ ካሳ ጽሁፍ አቶ አንዳርጋቸዉ ተደጋግመዉ ተነስተዋል እዉነታዉ ግን አቶ አንዳርጋቸዉ ህወአት ሲደናብር እጅ እና እግር ቀጥለዉለት ነብስ ዘርተዉበት ተሸልመዉ ተሸኝተዉ የሚኖሩ ሌላዉ ጩሉሌ ሰዉ ናቸዉ። አቶ አንዳርጋቸዉ ሕወአት ኢትዮጵያን ሲወርር የፕሮፓጋንዳ ሀላፊ ሁነዉ የሰሩ የህወአት የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸዉ እንዲህ ያለዉ ስልጣን ለትግሬዎችም ቢሆን ለመስጠት ደጋግሞ ማሰብን የሚጠይቅ ነበር ለትግሬዉ ድርጂት። ዶ/ር ብርሀኑን በተመለከተ የህወአት ልዩ አድናቂ ከመሆናቸዉም በላይ ለመለስ፤ ለበረከት ስምኦን ለሰየ አብረሀ ልዩ አመለካከት የነበራቸዉ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵየ በነበሩበት ጊዜ ከፕራይቬታይዜሺን ፕሮግራም ምን ያህል ሊያተርፉ እንደሚችሉ ሲያሰሉ የነበሩ ግለሰብ ናቸዉ። ታዲያ ሁኔታዉ ይህ ሁኖ ሳለ እነ ጉዱ ካሳ በ ኢቫንጀሊካን ሰበካ መንገድ ተጉዘዉ ኢሳትን፤ ከረንት አፌይርስን እና ሌሎች ደካማ የሚዲያ ተቋማትን በመጠቀም ግንቦት 7ን ከምንም በላይ አገዝፎ ለኢትዮጵያ አሳቢ አስመስሎ መሪዎቹ አንዳርጋቸዉ ጽጌና ብርሀኑ ኢትዮጵያን ካለችበት የሚያድኑ አድርገዉ አቅርበዉልናል። ይህ እንዴት ይተገበራል? ቀላል ነዉ ጸረ ኢትዮጵያን ሀይሎችን አስተባብሮ ኢትዮጵያ ላይ መዘመት (ኦነግ፤ኦብነግ፤ሻቢያ፤ግብጽ………………) እንግዲህ እነዚህ ሀይሎች ናቸዉ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ሊያደርጉ የሚችሉት ጎበዝ ተደፍረናል ትዉልዱን እያዩም መቀለጃ አድርገዉናል ቀደም ያለ ጊዜማ ቢሆን እንዲህ ያለ ቀልድ ለ አሳቢዉም ያስፈራ ነበር።
እንደእዉነቱ ከሆነ አንድን የሚዲያ ተቋም ተቆጣጥሮ እንደ ሂትለር ፕሮፓጋንዳ ህዘብን አደንዝዞ አማራጭ አሳጥቶ ህዘብን ዉዥምብር ዉስጥ መጨመር ለአንድ ህዝብ አማራጭ አይሆንም አለፍ ሲልም ወንጀል ይሆናል። ዛሬ ሁኔታዎች ተለዉጠዋል በኢትዮጵያ ስም ተቋቁመዉ ከላይ የተመለከትነዉን አይነት የተወላገደ አስተሳሰብ እኛ ዉሰጥ ፈጥረዉ የራሳቸዉን እቅድ ለሚያሳኩ ዜጎች ወገን ዞር በሉ ብሏል። ይህን ክስረት የተረዱ የዜና ድርጅቶችም ከሉበት ከፖለቲካ አቅዋም እና ትርፍ ሊያመጣልኝ ይችላል ከሚለዉ አመለካከት ተላቀዉ በመጠኑ በራቸዉን ከፍተዋል መሆንም ያለበት ይኸዉ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ በሚደረገዉ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ጥቃት የሚመለከትን ዜጎች ሁሉ ያገባናል። አለም አቀፍ የፖለቲካ ተልእኮ ያለዉ የዋሃቢስቶች እንቅስቃሴ በማጭበርበር ፖለቲካ ኢትዮጵያዉያንን ሲያምስ ይህ ነገር ሊታሰብበት ይገባል እያልን በጽሁፍም በቃልም ሀሳብ ስናቀርብ ከወያኔ በላይ ወያኔ ተብለን ዉርጅብኝ ቀርቦብናል። ይህ ማንንም አይረዳም እዉነት ከአጀማመሯ ብትቀጥንም በሗላ ግን እየገዘፈች እንደምትሄድ የተፈጥሮ ህግ ያሳያል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ይህ የአዲሱ እስላም እንቅስቃሴ ያደረገዉን የቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ፤ የንብረት ዉድመት፤አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ዜጎችን መግደል ነጻ የሆኑ የሚዲያ ተቋማት ዘግበዉታል ታድያ እነሱን ኪሳራ ዉስጥ የሚከት ሁኔታ ሲፈጠር ወያኔ ነዉ ያደረገዉ የሚለዉ የፌዝ አነጋገር እየተለመደ መጥቷል። እነዚህ ማስረጃዎች ህዝቡ ዘንድ እንዳይደርሱ ቢደረግም፤የኢትዮጵያ ሚዲያዎችን በማጭበርበር እና ግፊት በማድረግ ህዝቡ ዘንድ እንዳይደርስ ጫና ቢደረገም ለሀገራቸዉ በጎ የሚያስቡ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ለእይታ አቅርበዉታል አንባቢ በጉግል ከተመለከቱት ከብዙ በጥቂቱ ተመልካቹን የማያሳቅቀዉን ብቻ መርጠን አዉጥተነዋል ቀሪዉን ብርታት እና ጥናቱ ያላችሁ ዜጎች የዚህን ኢሰብአዊ ስራ መመልከት ትችላላችሁ።1.
እዚህ ላይ እነዚህን ሰዎች ኮትኩቶ እዚህ ያደረሳቸዉ የህወአት መንግስት መሆኑን አንባቢ እንዲረዳዉ ያስፈልጋል ሆኖም የህወአት ትግራይ ቢኮተኩታቸዉም አድራጊዎቹ እነሱ በመሆናቸዉ ለዚህ ወንጀል በህብረት ተጠያቂ መሆናቸዉም ሊሰመርበት ይገባል። እዚህ ላይ ታማኝ በየነም ምንም እንኳን ቀደም ባለዉ ጊዜ ለሀገሩ ብዙ ዉለታ የዋለ ዜጋ ቢሆንም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በነ ዶክተር ብርሀኑ ተጋልቦ የኦነግ ወዳጂ ሁኖ ወደ ኢትዮጵያን መንደር የተኮሰዉን ሳናነሳ ልናለፍ አንፍለግም።ይህንን ነገር አስመልከተዉ ታማኝ በየነን አንዳንድ ጥንቃቄና ትምህርት የሚያስፈለገዉን ጉዳይ የዘገቡ ወገኖች (ዲ/ን ሙሉጌታ) በመኖራቸዉ ታማኝ በየነም ከዚህ ይማራል ብለን እንገምታልን ሌሎች ታማኝ በየኖችም ጥንቃቄን ያደርጋሉ ብለን እናምናለን።
ዛሬ ነገሮች ተለዉጠዋል ኢትዮጵያን የሚጎዳ ማንኛዉም አይዲዮሎጅ፤እምነት፤እይታ የሚዲያ ተቋማትን በሞኖፖሊ ይዞ ኢትዮጵያዊነትን የማፈን እንቅስቃሴ ጊዜዉ አልፎበታል ተጎጂዎቹም ከማንም በላይ የሚዲያ ተቋማት እና ይህን የሚያራምዱ ድርጂቶች እና ቡድኖች ይሆናሉ። በጊዚያዊ ጥቅም ተገፋፍተዉ ታላቁን ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያን ማጣት ከጥቅም ጉዳቱ ስለሚያመዝን ቆም ብለዉ ማሰብ ይጠበቅባቸዋል። ይህንን ኪሳራ በብዙ የኢንተርኔት የዉይይት መድረክም ጭምር ተመልክተናል በብዙ መቶዎች ያስተናግዱ የነበሩ በወረደና በጸረ ኢትዮጵያ አቋማቸዉና ተልእኮዋቸዉ ዛሬ ክፍላቸዉን ሬሳ የወጣበት ቤት አስመስሎታል። ህዝቡ የሚፈልገዉን ስለሚያዉቅ ዛሬም ተቋማት በጊዜያዊ የቴርሞ ሜትር መለኪያ ብቻ ሳይወሰኑ የረጅም ጊዜ እይታችሁን መዝኑ እንላለን።
እንግዲህ መባል ያለበት ተብሏል ካጠፋሁም በዚህ ተቆጡኝ [email protected]
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር