የኛ ነገር፡ ከኔ ማዕዘን፡- በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ (ከተ/ሚካኤል አበበ)

የኛ ነገር፡ ከኔ ማዕዘን፡ ክፍል 13

በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ

ከተክለ ሚካኤል አበበ

1-      ይህ ጽሁፍ ዓላማው አድናቆት፡ ትችትና ግብዣ ነው። የአንድነት ምሽት በቶሮንቶ ግብዣ። ከአድናቆትና ከግብዣው በፊት ስለፖለቲካ መሪዎችና ስለፖለቲካ ተንታኞች አትቶ፤ የብርሀኑ ነጋን (ዲባቶ) አቀራረብ ይተቻል። የሰማያዊ ፓርቲን ርምጃ ያደንቃል። የአንድነት ዘመቻን ስለማገዝ ያሳስባል። እንደው ተገጣጥሞ ነው እንጂ፤ አንዱን ለማሞገስ ሌላው መኮሰስም መከሰስም የለበትም። ግን አንዳንዴ ደግሞ፤ በጊዜ ያልተተቸ፤ ይለመዳል። አጉል ልማድ ይሆናል። ሁሉንም ለያይቶ ለመጻፍ ደግሞ፤ ጊዜ የለም። ስለዚህ ባንድ ወንጭፍ ሶስት ወፍ ነው ለመማረክ የምጥረው። ከሀተታ ልጀምር።

የፖለቲካ ተንታኝና የፖለቲካ መሪ

2-      የፖለቲካ መሪ ከፖለቲካ ተንታኝ መለየት አለበት። የፖለቲካ መሪ የፖለቲካ ተንታኝ ሲሆን፤ የጋዜጠኞችንና የፖለቲካ ተንታኞችን/የምሁራንን ስራ ይጋፋል። ያ ብቻም አይደለም። መምራት አቅቶት፤ ወይም መምራት ጠፍቶት፡ በአካልና በስም የፖለቲካ መሪነቱን ወንበር ተቆናጦ፤ በግብር ግን የፖለቲካ ተንታኝነትን ቦታ ይዞ፤ የፖለቲካ መሪነትን ስራ በፖለቲካ ትንታኔ ሊያካክስ ይሞክራል። ያም ብቻ አይደለም፡ የፖለቲካ መሪነት ሚናን ከፖለቲካ ተንታኝ ጋር ያደባለቀ መሪ፤ የያዘውን የፖለቲካ መሪነት ሀላፊነት ከተንታኝነት ሲለሚቀይጠው፤ ትንታኔው ንጹህ አይሆንም። ስለዚህ የፖለቲካ ትንታኔውን መቀበል ይከብዳል። ባይከብድም ትንታኔው ጎዶሎና ወደሁዋላ የሚጎትት፤ ወይንም ወደፊት የማያራምድ ይሆናል። ወይም ትንታኔው ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የሚደረግ ጥልቅ ያልሆነ ትንታኔ ይሆናል።

3-      ለምሳሌ ብርሀኑ ነጋ ባለፈው የኢሳት ስብሰባ ላይ ያቀረበውን የንግግሩን ገጽ 16 መጨረሻና ገጽ 17 መጀመሪያ ብንመለከት ሀሳቡ ጥልቅ ወይም ሀቀኛ አለመሆኑን በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል። https://zehabesha.info/archives/6563 ለዚህም ነው ምሁር ፖለቲከኛ መሆንን ከመረጠ፤ ምሁርነቱን ቀንሶ መሪነቱን እንዲያጠብቅ ግድ ነው የምንለው። ኦባማን ውሰዱ። ኦባማ ሲመረጥ ምሁር ነበር። ከአራት አመት በሁዋላ ግን ምሁርነቱ እየቀነሰ፤ ወደቡሽነት እየተጠጋ መጥቷል። የኦባማ የሶሪያ አቋም፤ ከቡሽ የኢራቅ አቋም ብዙ አይለይም። አሳድን እንበለው ወይም እንብላው እያለ ነው። ኢሳት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ብርሀኑ ነጋ (ዲባቶ) ያንን መለየት ነው የተሳነው። በፖለቲካ መሪነት መጥቶ (በግንቦት ሰባት ሊቀመንበርነት) የፖለቲካ መሪነቱን ግን ትቶ፤ ምሁር ለመሆን ሞከረ። ተንታኝ። የፖለቲካ ተንታኝ በመሆን የጋዜጠኞችንና የምሁራንን ስራ መሻማት ብቻ ሳይሆን፤ ሁለቱንም ሳይሆን ቀረ። በዚህ ረገድ ጃዋር ይሻላል። እንደተንታኝ በደንብ ይተነትን ነበር። የተንታኝነቱን ሚና ትቶ ባለፈው ሰሞን የራሱን የፖለቲካ አቋም ሲያንጸባርቅም፤ ብዙ ሰዎችን ቢያበሳጭም፤ እቅጩን ነው ያስቀመጠው። ብሬ አድበሰበሰው። በእስር ላይ የሚገኙትም ይሁኑ በነሱ የተተኩትን ከነሱም የቀደሙትን ሙስሊሞች አካሄድና እንቅስቃሴ የሚጠራጠሩ ካሉ፤ ጥርጣሬያቸው በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ነው የተፈጠረው ለማለት ይከብዳል። በወያኔ ፕሮፓጋንዳ የማይበገሩም ከተጠራጣሪዎቹ ተርታ ውስጥ አሉበትና።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሁለት መነጽሮች ወግ - አስቻለው ከበደ አበበ ሜትሮ ቫንኩቨር ካናዳ

4-      የዲባቶ ብርሀኑ ነጋ ያልጠራ ትንታኔ የመነጨው፤ ፖለቲካዊ መሪ መሆንና ፖለቲካዊ ምሁር/ተንታኝ መሆንን አጣምሮ ለመሄድ ከመሞከር ነው። የፖለቲካ ተንታኝ የምለው፤ በፖለቲካ ውስጥ በቀጥታ በአድራጊ-ፈጣሪነት ሳይሳተፍ ወይም መሳተፍ ሳይጠበቅበት፤ የአንድን ፖለቲካዊ ስብስብ/ማህበረሰብእ ፖለቲካዊ ሁኔታ እየቃኝ፤ ከአካባቢያዊና አለማቀፋዊ ሁነቶች ጋር እያጣቀሰ፡ የሁነቶቹን ምክንያት የሚያብራራ፤ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮችን የሚጠቁም፤ አደጋዎችን የሚተነብይ፡ ተመልካችና ተናጋሪ ማለት ነው። የፖለቲካ መሪ የፖለቲካ ተንታኝ ሲሆን፤ አደናጋሪ ነው የሚሆነው። የፖለቲካ መሪዎች የፖለቲካ ተንታኝ መሆን የለባቸውም እያልኩ አይደለም። እኔ የምለው፤ አንደኛ ፖለቲካ መሪዎች የፖለቲካ ትንታኔ ችሎታቸው የሚገለጸው በፖለቲካዊ አመራራቸው በሚወስዱት ፖለቲካዊ እርምጃ ውስጥ መሆን አለበት ነው። ሁለተኛ፡ ፖለቲካን መተንተን የፖለቲካ መሪዎች ዋና የአደባባይ ስራ መሆን የለበትም ነው። እዚያው ድርጅታቸው ውስጥ እንደፍጥርጥራቸው። ይፋዊ ፖለቲካዊ ስራቸው ግን፤ መምራት እንጂ መተንተን አይደለም። አቶ መለስ ከሞቱ በሁዋላ ብቻ ያለውን ሁኔታ እንኳን ብንለመከት ግን፤ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ብርሀኑ ነጋ፤ ከሲሳይ አጌና ጋር ያደረጋቸውን ቃለምልልሶች ወይንም ያለፈው ሰሞንን የኢሳት መድረክ ጨምሮ፤ በቀረበባቸው መድረኮች ላይ የሚናገራቸወን ስንለመከት አድራጊ የፖለቲካ መሪ ሳይሆን፤ ተንታኝ ጋዜጠኛ ወይንም እዚህ አገር እንደሚሉት ጠቢብ ምስክር ለመሆን ነው የጣረው።

5-      ያ ብቻም አይደለም፤ አሁን በእመ-ብርሀን፤ ሰላሳ ድርጅቶች የኢትዮጵያን እጣፈንታ ከህዝብ ጋር ሊመክሩ በተሰበሰቡበት መድረክ ላይ ለመነሻ የሚሆን የአስር ደቂቃ ንግግር አድርጎ የተቀረውን ሰዓት ለህዝብ ውይይት መተው እንጂ፤ የ55 ደቂቃ ድርሳን ማንበብ ምን የሚፈይደው ነገር አለ? ብርሀኑ ነጋ ባለፉት ሶስት ወራት በኢሳትም ይሁን በተለያዩ መድረኮች ያገኘውን እድልና ሰዓት ስንመለከተው ደግሞ የንግግሩ መርዘም ስህተትነትና አበሳጭነት ይጎላል። ያ ብቻም አይደለም፤ ሶስት ሺህ ምናምን አመት፤ መጀመሪያ በጸሀዩም በጨረቃውም በማምለክ፤ ከዚያ ብሉይን በመቀበል፤ ከዚያ ክርስትናን፤ ከዚያ እስልምናን፤ ከዚያ ካቶሊክን፤ ከዚያ ፕሮቴስታነንስዝምን፤ በመቀበልና በማቻቻል ለኖረች አገር፤ የሊበራሊዝምና ዴሞክራሲ መፍትሄ ለሀይማኖት ነጻነት የሚል የአንድ ሰዓት ስብከት ያስፈልጋታል? ቢቀርብንስ?

ተጨማሪ ያንብቡ:  የታላቁን ወር ረመዳን መግባት አስመልክቶ ከታሳሪ ጀግኖቻችን የተላለፈ አጭር የ‹‹እንኳን አደረሳችሁ›› መልእክት - ከድምጻችን ይሰማ

6-      በዚህ ኢሳት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ፤ ግንቦት ሰባትን ወክሎ ንግግር ካቀረበው ብርሀኑ ነጋ ይልቅ፤ የሽግግር ምክርቤቱ እጥር ምጥን ባለች ባለአራት ገጽ ወረቀቱ፤ የተሻሉ የሽግግር ሀሳቦችን አቅርቧል። http://etntc.org/ENTC/wp/wp-content/uploads/ESAT-Presentation-0818.pdf። እነሱ የሚመኟት ኢትዮጵያ ምን መምሰል እንዳለበት፤ ሽግግሩ ምን እንደሚመስል፤ የሽግግር ሰነድ የሚያረቅ ኮሚቴ ስለማዋቀራቸው፤ አለማቀፍና አገርአቀፍ የእምቢተኝነት ቡድን ስለማቋቀም፤ ድርጅታቸው ምን እየሰራ እንደሆነ ተናግሯል። ከሽግግር ምክርቤቱ አራት አመት ቀደም ብሎ የተቋቋመው ግንቦት ሰባት ግን ጥምረት ከተቋቋመ ከሶስት አመት በሁዋላ፤ የከማል ገልቹ ኦነግ ከተመለሰ ከሁለት አመት በሁዋላ፤ ገና ስለድርጅቶች አንድነት፤ በጋራ ትግል ወያኔን ስለማስወገድ አጣዳፊነት ይሰብካል። የዛሬ አመት፡ የዛሬ ሁለት አመት፡ የዛሬ ሶስት አመት ከነበርንበት ብዙም ፈቀቅ አላልንም።

7-      ኢሳት ይሄንን ስብሰባ ማዘጋጀቱ ይደነቃል። ይሁን እንጂ፤ የኢሳት አስተዳዳር የሆነው ወዳጄ ነአምን ዘለቀ የዛሬ አመት አካባቢ እንዲህ ያለው ተመሳሳይ ስብሰባ ሲዘጋጅ፤ (ያኔ ስብሰባው የተዘጋጀው በኢሳት ሳይሆን በግንቦት ሰባትና በነኑሮ ደደፎ (ዲባቶ)/ከማል ገልቹ ኦነግ ነበር)፤ እባክህን መሪዎቹ ንግግር ያሳጥሩና ለሰዉ እንዲተነፍስ ግዜ ይስጡት ብዬ አሳስቤው ነበር። ነአምን አንዳንዴ አይሰማም። ወይም ቢሰማም አያደምጥም። እነሆ፤ ባመቱ፤ ሌላ ውድ መድረክ ባከነ። የብርሀኑ ነጋ ጽሁፍ፤ የመጀመሪያው አስራሶስት ገጽ ለዚያ መድረክ አስፈላጊ አልነበረም። ነገር መቁረጥና ማሰጠር፤ እንዲሁም መድረክ ላይና ምድር ላይ የምናቀርበውን መምረጥ አለብን። ያለበለዚያ ትክክለኛና ውጤታማ ሚናችንን መለየት አለብን።

ተስፋ፡ አድናቆትና፤ ግብዣ

8-      መቼም ተቃጥላችሁ አትሙቱ ያለን ፈጣሪ መጽናኛ አያሳጣንም፤ በግንቦት ሰባት ሊቀመንበር አቀራረብ ብንበሳችም፤ አላህ የሚያጽናናን አላሳጣንም። የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ እኛ በምናደርገው ነገር ምንም ቀስቀስ በማይልበት፤ ፖለቲካዊ አየሩ ጸጥ ረጭ ባለበት ሁኔታ ነው፤ የዛሬ ሶስት ወር አካባቢ፤ ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የተሳካ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ። ላለፉት ስምንት አመታት ሰልፍ አይታ ለማታውቀው አዲስ አበባ ሀያ መቶም የሁን ሀያ ሺህ ሰው ያስወጣ ሰልፍ ተከሰተ። ያ ያጽናናል። እነሆ ያኔ በያዙት ቀጠሮ መሰረት፤ ሁለተኛው የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በመጪው እሁድ ይቀጥላል። መቼም ብዙዎቻችን ፈሪዎችና ሸሺዎች በሆንበት ሁኔታ፤ ጥቂት ዠግኖች አልጠፉምና፤ የሰማያዊ ፓርቲዎች ድፍረትና ቁርጠኝነት የሚያስደንቅ ነው። የህወሀት ኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር በኩል ሰልፉ ህገወጥ ነው ቢሉም፤ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ግን ሰልፉ ህጋዊ ነው፤ እንገፋበታለንም እያሉ ነው። የመጪው እሁድ ትልቅ ተጋድሎ ዋዜማ ላይ ነን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከዕዉነት ሽሽት…አስከ የት ? - ማላጂ

9-      እንዲህ ያለውን ትእይነት ቆሞ መመልከት ብቻ ግን ነውር ነው። መቼም አንዴ ሸሸተን ወጥተናል፤ በወጣንበትም ቢሆን ግን፤ የምንችለውን እንኳን በማድረግ ተዋናይ መሆንም አለብን። የኛ የተቀናቃኙ/ተፎካካሪው/ተቃዋሚው ጎራ፤ በተለይ በውጪ የምንኖረው ተቃዋሚዎች ትልቁ ችግር፤ ማድረግ የምንችለውን እንኳን ማድረግ አለመቻላችን ነው። በሰላማዊም ይሁን ደማዊ መንገድ፤ በአመጽም ይሁን በጸሎት ለሚታገሉት ስንቅና ትጥቅ ማቀበል። ስንቅና ትጥቅ ላለማቀበል ብዙ ምክንያት መደርደር ይቻላል። ምንም ምክንያት ግን አጥጋቢ አይሆንም። ቅዳሜና እሁድ የዱለትና የቁርጥ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን ጉዳይ እያብራራ የሚተነትነው፤ የምእራባዊያንን ሴራ የሚመሰጥረው ወዳጄ፤ የኢሳት ዝግጅትን የ20 ብር ትኬት ስሰጠው ፊቱን እንዳጨፈገገው መሆን የለብንም። ለሰማያዊ ፓርቲ ሁለተኛ ሰልፍ መሳካት እንጸልያለን። በጸሎት ብቻ አናበቃም። በግብርም እንከተላለን።

10-   መቼም በየከተማው ብዙ የማይደክማቸው ሰዎች አሉ። እነሆ በመጪው ቅዳሜ ማታ፤ በዚህ በኛ ከተማ ትንሽ ተንፈስ እንላለን። ተሰብስበን ኢህአዴግን ከመዘልዘል ባሻገር፡ የትግሉ በረከት እንጥፍጣፊ ይደርሰን ዘንድ የአንድነት ምሽት ያዘጋጁ አሉ። “የአእላፋት ድምጽ ለነጻነት” የተሰኘውን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ዘመቻ በመደገፍ እዚህ ቶሮንቶ ከተማ፤ እንደፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር፤ ቅዳሜ ኦገስት 31 ማታ ከ6ሰኣት ጀምሮ’፤ 2050 ዳንፎርዝ ጎዳና በሂሩት ሬስቶራንት የቤተሰብ አዳራሽ የእራት ምሽት ተዘጋጅቷል። በሰሀን $ 50 ብቻ። ለጥንዶች $ 60። ለኔቢጤው ደሀ ደግሞ $ 30 ብቻ። ገቢው፤ ከወጪ ምላሽ ለአንድነት ፓርቲ የሚሄድ ነው።

11-   እነሆ፤ በአካል ከግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይል ጋር ላንዘምት እንችላለን። በአካል ከሰማያዊ ፓርቲም ጋር አንሰለፍ ይሆናል። ከአንድነት የነጻነት ድምጾች ጋር ለመጮህ ግን አይሳነንም።ለሚጮሁት ጉልበት፤ ለሚሰለፉት ብርታት፤ ለሚዘምቱትም ጽናት ልንለግስ እንችላለን። በያለንበት አካባቢ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች እንርዳ። እዚህ ቶሮንቶ ያለን፤ ቅዳሜ ሂሩት ሬስቶራንት ብቅ እንበል። ቅዳሜ እንኩዋን፤ ላሊበላና ብሉናይል፤ ዞብልና ራንዴቩ ይቅሩብን። ቅዳሜ ማታ፤ ሂሩት ጋር እንገናኝ።

እኛው ነን። ከቶሮንቶ። ነሀሴ፡ 2005/2013።

51 Comments

  1. You are a sick man I think you have something wrong? Go Hospital and check your self.you have mental problem Lij Tekle .

    • Tekle,Are you sick? I know you . You were desturbed whe we were in Kenya refuge camp.still you are childishe behavior. Are you writing comment or insulting? who are you? we know you, your comment is always a raw rotten dog meat.I think It is better not to write on line , you can write your self and read yourself . we do not have read your madness behavior. You are always tried to blamed some people. please stop this type of idomatic idea, This is non sens and stupied comment. we need to fight TPLF. If you want to make friendship with them, you can go and serve them as soon as possible.

  2. ለተቀማጭ ሰማይ ቅርብ ነው ዶክተርን ብርሃኑን እንዳንተ በየመንገዱ ሽንቱን እየሽና አይደለም እዚህ የደረስው የሚያደርገውን ጠንቅቆ የሚያውቅ አላማ ያለውና ለዛች ምድር ዋጋ የክፈለ መሪ ነው በጣም የገርማል ኢሳት ላይ ብዙ ሰዓት ተጠቀመ ብለህ ወይንም በኢሳት የአየር ሰዓት በዙ ለዶክተሩ መሰጠቱ መታመምህ ይገርማል ሊላው አንተ ዶክተቱን ለመተቸት ሞራሉም የለህም ተክሊ አስታውሳለው ኢሳት ውይይት ላይ ከነ ሲሳይ ስተወያይ ምን ያሃል እንዳሳፈረክን በዙ በስለት የቀረሃል የጽፍክውም ከአንዱ ወያኒ ዊብ ሳይት ቀንጭበህ ነው ንግግር የማትችል መሆንህን በተደጋጋሚ አይቻለው በሽተኛ ነህ

    • ተክሌ- ድፍረትሽን አደንቃለሁ ድድብናሽን ሳልረሳ። የ ዶ/ር ብሬ አምላኪ አይደለሁም፦ ያነሳሀው አመንክዮ ደደብነትህን ስላሳበቀብህ እንጅ። I KNEEW YOU IN ESAT “የእሁድ ወግ” ስትቀርብ። ወያኔ ለ ሰማያዊ ስለፈቀደ ሊመሰገን ይገባዋል ስትል ማንነትህን አሳብቆብሀል። TEKLIS… PLEASE DON’T BE ARROGANT!!!

  3. Who are u and what are u doing and who gave u the licence for critisism and appreciation? This is fruit salad article. When are these so called woyane opposing groups going to stop to disagree and bite each other? This is good, that is bad; bla bla… Does it matter which one is which now? Like child game we construct and deconstruct; appreciate and depreciate!! Hell with it. What matters is, I don’t even care re-incarnating derg or even the devil himself coming, getting something someone that can undo all the vices of TPLF/Woyane/ and give us back a country where we all will have opportunity and say. This article must have gone to awramba time, I guess because it gona make woyanes happy!
    We have writers but we miss people with action! God help us.
    Tigre sifak woyane kehone, andandu amara sifak degemo tigre yihonal!!

  4. Although I personally appreciate Dr.Berhanu Nega for his commitment for Ethiopia, I share your comment on his presentation. No matter how important the message of the piece was, it shouldn’t take that much time. If I were the moderator of the conference, I would have stopped him on the 15th minute of his allocated time. I think he is influenced by his profession (professor). whenever he comes to a meeting a speaker, his presentations are always GOOD but TOO LONG. I know and everybody knows that Dr.Berhanu is one of the best and outstanding economists. But the problem is we don’t have time or patience to listen lengthy lectures, Sorry!

    Hey man (Kebede), Listen Tekle is not a sick man. He is exercising one of his RIGHTS (freedom of expression). This is ——

  5. ጋሽ ከቤ ተክሌ ጥሩ አስተሳሰብ ያለው ልጅ ነው ቅኒው አልገባህም መሰለኝ

  6. Tekele, you are sick person, we like it the way Dr, Birhanu brief that. Dr. Berhanu teach us, I read isit twice. what is your problem? tekele creat new party and show us , how to rid of woyane. I know you need attention .

  7. i endorse your article Lij Tekle, thank you. offffffffff Dr brehanu’s 54 minutes speech was so boring plus the same shit.

  8. Tekle the great …I rally admire you , u are telling the truth which are on the table … Yes we hate woyane !!!!! But we are against extremist . We don’t have to support akraries by saying my enemies enemy….. Because Ethiopia is zelalemawe….koy ene emlew docteru lemera new demsachen yesema ( if woyane is down)????? Good job Tekle !!

  9. wow really me like hem .ልጅ ተክሊ ሰውን አያምልክም ስለዚይ ካልመስለው የፈለገውን ይጹፋል፣ እዲይውም ብዙዋቻችን ከሶ ልንማር ይገባናል. God beluss u bro pls keepit up

  10. I don’t understand Tokelau if they don’ t do anything why TPLF worried ?do you think TPLF worried for nothing?Semayaw and and andenet are legal party that’s why you see every thing front I think you forget this minor different!I think you write this to show that you are alive! Thank-U

  11. Thank you Teklem,

    yes you are right somebody has to tell Dr. Berhanu to do more practical thing other than talking and commenting to each political events. He has to work hard and do effort to be successful in his goal. We need to see at list one thing on what he promised us. Tekle you are practicing your right and he has to be accountable and to be asked on what he has been doing.

  12. Tekle what happen to you? You become some thing sensetive or unmatured let you change the poletical leaders how much you are enough strong? “Letekemach Semay kirbu new” alu. Gera tagabaleh You are confusing the Ethiopain.

  13. ተክሌ ሳስብህ ወሬ እየለቀምክ የምትጽፍ እንጂ የራስህ የሆነ ብስለት ያለህ አትመስለኝም እዚ ላይ በእርግጥ አንድ ቁም ነገር ተናግረሃል ለተሳታፊ ምን እነደሚሰማው እንዲተነፍስ መድረክ ሊሰጠው ይገባል ይሄንን ለማለት ግን ዶ/ር ብርሃኑን ይሄን ያህል መጨፍጨፍ አስፈላጊ አልነበረም አንተ እራስክን እንደአወዛጋቢ ጋዜጠኛ የምትቆጥር ይመስለኛል ያ ግን ፈጽሞ ሰው ላንተ ካለው ግምት ጋር የሚጣረስ ነው ከዛሬ ነገ ታድጋለህ ብለን ብንጠብቅም አድሮ ቃሪያ እየሆንክብን ተችገርን ዶ/ ር ብርሃኑ እጅግ ውስብስብ በሆነው የኢትዮጲያ ፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት የሚታገል ሰው በመሆኑ ያለበትን ጫና እንዳንተ ገና ጨቅላ የሆነ ሰው ቢረዳው ነበር የሚገርመኝ!!!

  14. tekle, if i were you,i would try to stop my ego before i comment such controversial statement .this kind of critisism is not help us to fight against dictator accept woyane

  15. Let me say first that Tekle’s appreciation for what Semayawi and UdJ are doing and the call for extending our support in practical terms is not only the right thing to do but a must to do if we want to make a difference .
    His comment on the style of Dr.Behanu’s presentation can be taken and should be taken as constructive way of looking at it if it is expressed in a genuine and respectful manner. The problem with Tekle in this regard sounds disingenuous and disrespectful. And by doing this, Tekle looks “smartly “cynical . I have to say that this kind behavior or mentality is not good for himself leave alone for being part of a big national issue and contribute to the consorted efforts in moving in the right direction and make a difference. I have observed Tekle’s very silly and negative way of expressing himself about people who he personally is not happy. I do not know why he chose that kind of way of highly negative and introverted expression to comment that it is better for Dr. Brhanu to consider making his speech shorter and give participants a chance to say their opinions.
    I do not know from what kind of epistemology and theory that say a politician cannot and should not have an analytical approach or should not be an analyst too. I do not know why Tekle wants to see things unnecessarily and destructively that way.
    I hope he will be courageous enough to minimize, if not get out of this kind of very difficult behavior to deal with.

    • Ato T. Goshu, Stop intimidating people like Tekle! He is among the few voices we have among us who can talk to the power. Mind your message! This is clear intimidation, like it or not!

      Bravo Tekle!

      Although I have not seen a convincing argument that the muslim question is wrong headed, I have series doubts it will stay like this (or is sincere). Before it is too late to steer the wheel, we need to be cautious.

      On Dr. Berhanu’s presentation, although I have high respect for what he has done, his long lecture was not value adding to the current struggle.

      I commend your support of Semayawi and UDJ, our hopes for creating the Ethiopia we want to see tomorrow.

      Berta Tekle, and don’t listen to the bad comments. Some of them are hired to do just that!

  16. Lij Tekle

    We know that you do not support the Ethiopian Muslim movement. You pray day and night so this movement becomes unsuccessful. Last time you wrote saying muslim movement is becoming a strong force. Your stand is not based on reason but hate. You just hate to see muslims whose right respected. Your muslims brothers are just asking basic right. They are not asking to make Ethiopia a muslim state. But you do not want believe that you just want follow your ego.

    Now you start insulting Dr Berhanu because he came up with detailed explanation that every Ethiopians should support this movement. It is very long because there are dull people like you who need very detail points to delete their unfounded ego so that they they become part of struggle against weyane/EPRDF.

    When I see your article I thought you are going to give us evidence based article against his speech note at the meeting. But you keep on telling us 16 pages are too much… Come on LIj (Kid)….. You are crazy and full of hate… you hate Dr Beranu because he told you that you are stupid with evidence and explanation and you do not want to accept.

    Dr Berhanu and Jewar are not comparable. You are so confused….

    You

  17. I am sure Tekle is gonna be woyane very soon. Tekle wants to go to Ethiopia (like Solomon Tekalign) and he is now insulting true oppositions. Shame on you Tekle!

  18. Teklea ,I am glad that you are out from esat .but there are steel some there like u who are under cover Weyanes .i do not really understand why esat is opening the door for such kind of people .specially those who are coming strate from addis Abeba and now trying to take over esat which is the people media.when you we come to tekla he is a well known under cover weyane who travell from Canada to USA and different part of the cantry even when he was a student to divide and destruct the opposition and all his expense was cover by weyane.so it is not a big surprise for most of us who know this tplf thugs.finally my advice to esat management is that there are steel some Weyanes specially around the radio area which weyane try to plant inside.so we need to watch them very carefully.

  19. Tekle is far from being adro tija or adro qaria!!!!…He is a crook!!!…he is woyane/shaabia in ‘ Ethiopian’ cloth!!!!!

  20. Tekle you must see doctor. Did you read your article before you post online .
    Do you want advice please change your profession and do some thing tottaly different please stay away from computer.

  21. ተክሌ፤ ዶ/ር ብርሃኑ ላይ ተንጠልጥለህ፣ ንግግሩን እየጠበቅህ የምታወጣው ጽሑፍ አላማው ምን ይሆን? ዶ/ር ብርሃኑ የያዘውን ቦታ በትክክል ጠየቅሞ መሪ ሆኖ ያሳዬን–ያኔ እኛም እንጽናናለን ትላለህ፤ አንተ ግን ኢሳት ላይ ብቅ ያልክባትን የ“ጋዜጠኛነት“ ስራ በምን ያህን ፍጥነት ጥለሃት ወደ ነበርህበት ጉንተላህ እንደገባህ፤ ያደባባይ ሚስጥር ከሆነ ቆይቷል። አንተ ማድረግ ያልቻልኸውን፣ ሌላው ሰርቶ (በአንተ አመለካከት መስራት የሚገባውን ካልሰራ) እንዲያሳይ መጋበዝ ቂልነት ነው። መጀሪያ ራህን ጠይቅ–ምን ሰራህ? ምን መሬት ላይ የሚውል ነገር አመጣህ? “አሳራ ጎሪጓሪ ዘንዶ ያወጣል፤“ ይላል ያገራችን ሰው!

  22. This is democracy in practice. Tekle wrote his opinion and that is his right. Most commentors try to silence Tekle because he criticized their idol Dr. Berhanu. I appreciate Dr. Berhanu but he should be open for criticism. Otherwise, what would be the difference with Woyane, if you deni his Rght

  23. Lij Tekle you read the messege all Comment that is for you. if i am you I don’t want to see anyone but still you have plan to go Ethiopian meeting please shut your mouth and stay far go to mole & find like you. “Adro kareya”

  24. I don’t know why most of the comments have ‘you are sick’ kind of comments. I think maybe someone is submitting comments again and again?? Just because someone wrote what he/she thinks does not deserve to be called ‘sick’…in fact the person who is thinking that himself is sick! Coming to Tekle’s article, I think he has very good points and I agree with him. ESAT’s platform on that day was well intended but useless because of time management. As Tekle put it nicely, we Ethiopians do not want to hear past history, analysis of problem, etc. we had those upto our neck. What is clearly needed from political parties and other groups is leadership and solutions. I believe there were some groups who had presented tangible proposals and solutions, others were blah blah..I think ESAT had learned its lesson and will correct its problems going forward.
    Other than that, people who are outraged when Dr. Berhanu’s is criticized, you should think twice…even God has His share of criticizms let alone a person who has shown literally nothing…G7 should have been in a better position to fight the tyrant TPLF as they have more support and resources than the other political groups in the diaspora. Too bad it hasn’t shown anything so far!

    • Why do not join G7 and show us how we topple TPLF/EPRDF, Tekele did not critisiz Dr Berhanu article he rather complain about time management. He should critically tell us where Dr Berhanu analysis gone wrong.

  25. I guess this guys lost the plot , I have seen his writing couple of times. Now it looks like he has got personal issue . We saw him reading news and interviewing people on Esat tv , after he left he start criticising Esat .Now as we see instead of commenting the issue , he just start Blaming other individuals . What is his issue , what is his offering for ? Tekle and Dawit awramba they have issue with Esat and Dr Berhanu , don’t know why ? If anyone know please comment about it

  26. lij tekle, sayiqemetu igir mezergat mefengel newu. ante Dr. birhanun lemetechet ye moral biqat yeleshim. yeneza wushoch dollar begish geba mesel. yateratiral. bizu yalhone neger kemawurat tebabiren ethiopian enadin. ye weyane anti viruse tablet enditwosid emekrih alehu. aweku aweku mechereshaw DIT.

  27. If the lengthy speech made by Dr. Berhanu had been made by another individual with no stature as Berhanu, then most of us would not have problem with Tekle’s critical opinion. We always have the tendency to worship personalities and thus become very protective of them from any criticism. We love and respect Dr. Berhanu for what he has been doing for our country. The best help we can offer is to render our honest assessment regarding the performance of him and the party he is chairing. In doing so, we are sharpening him like a knife. For what it is worth, i agree with most of the critical opinion of Tekle on this one. There are lots of issues i do not agree with Tekle, but not on this one. I hope we learn to think of leaders as ones who serve the people, and not the reverse.

  28. Ewket malet Yemetsaf agatami silagegne bicha mastwek mehone yelebetim. Ye balager neger mechereshaw yihe new.

  29. I’m sure this guy is confused or has hidden mission sponsored by Woyane.I’ve read
    his previous articles criticizing about an outstanding effort by Ginbot 7 to bring to
    together all ethnic politic based movements to an all inclusive united movement
    that I gave 5 stars for G-7 for this effort. And on his other article he was not comfortable to see Ethiopian Muslims scholars lecturing about Globally known
    Ethiopian Muslims peaceful movement on ESAT’s fundraising events.Tekle,by looking your resume, you are well qualified to be a journalist for Aiga forum or others Woyane sponsored media outlet.I want you to focus on Woyane’s evil action at this critical time. If you need more let me know.

  30. Your commentary in respect of timing flawless.

    1. I knew Dr. Birhanu went far beyond the limit. Was this his fault? No way, not at all. The organizer (ESAT) has to take the blame for they may let him stop on time.

    2. Your critic lack credibility in the sense that instead of focusing on blaming time use you focused on the paper and tried to butcher Birhanu’s presentation in the ugliest way I ever saw. Please read the first two or three lines of #3, #4, and #6. It totally was insult.

    3. You tried using some jargon (new words) like “Dibato” which I didn’t understand. This kind of jargon may have connotations of closeness or contempt between the writer and the Panelist. For me because of the aforesaid points (3,4,6) I found it more of contemptuous than cordial.

    Don’t give up expressing your feeling; I like the way you exercised freedom of expression lest think of empirical facts surrounding Ethiopian politics for you may consequently be the subject of failure in opposition camp.

  31. Dear Tekle

    First learn how to write an article, why you do not have ”introduction” ….. ”conclusion” etc….not just numbers.

  32. Lij tekele ewnetem eyader lij eyhonkenew yawem metfolij yemayafer yemayefera hi beluit enQwan yemasefera lij endayetnew bekerbu hakem ayetohe yehone? estibetseb endalhe wede ayemero hakem yewesedohe endew netsawe yemtsfeya menged temchegh belhe senti amet mulu lezhe hezebe setaser sefeta yenorewein seweya letechet bedege belhe tewetabetalhe telat keruk ayemetam ezawe ategeb yegheghal esu antenehe gen gen yehaye neger yetnenet almeselghem ena temremer aleyam wedetsbel Gora Bele memeher Girema wendemu ga 2===7 betetemeke betam terunew enaye wegenhe ethiopiaweit seleasazenkegh yechen azezekulhe.kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk

  33. hi tekila menew edzh jezbki keniya setnor ekan tishal nber nesant yalew haGER SITGEB MINE NEKAH WEYANE FESBH ENDA YQIRI YEBLH BETAM AZENKU EWDH NEBRENA

  34. Tekle we know that there is problem with you and Esat but you can do it proftoinaly
    doing this pubelcely is not good shame on you Ethiopians in South Africa

  35. A littel knowledge is very dengerous!tekle u know what the problem is the more u read the less u understand.are u switching aba mela or what?

  36. This article should be a wake up call to the managment committe of ESAT to launch an investigation on political background of ESAT crews presently working either in the radio or TV channels. I think we should never been surprised with what Tekle had said about Dr Birhanu. All Tigrians all over the planet including the writer of this article (Tekle), Dawit Awramba, Mesfin Negash and others in diaspora who are involced in the media are waging any knid of smear campaign against ESAT and prominant political figures like Dr Birhanu Nega as much as TPLF has been doing. Tekle would like to show his ingenuine support for political parties only committed to peaceful struggle because he make sure that woyanes are armed to crackdown if things go ouit of their grip. As has been said earlier by one commentator he is very cynical and should be banned from ESAT for ever. He will do more harm to the people of Ethiopia if he is given any more chance. I remember when he went into fierce argument with Sisay Agena in one of current political discussion via ESAT-tv. He is absolute Woyane. Enough is enough. We must say a spade is a spade. Now not later.

    • Hi Lij weym jill Tekle Minn taregale Canada kamenk beselamawi tigll.Ante you have to go Ethiopia and steragl with b selamawi tigll k mitaglut gar!I rispect in Ethiopia steragl peacefully not for you and the others they living abroad only they saying Selamawi tigll Selamawi tigll you have to go Ethopia weregna Jill Tekle!!!!

  37. ሰላም ተክሌ ያንተን ጽሁፍ ከማንበቤ በፊት መጀመሪያ ርዕሱ የጽሁፍህን ይዘት ቁልጭ አድርጎ ነገረኝ ከዚያ ህዝብ ምን እንደሚል ወረድ ብዬ ማንበብ ጀመርኩ ይህንን አስተያየት በምጽፍበት ጊዜ 44 አስተያየቶች ተቀምጠዋል ከነዚህ አስተያየቶች ቢያንስ 38 ስለጽሁፍህ ከፊሉ ስላንተ መታመም የሚያወራ ስለሆነብኝ ከማነበው በዚሁ ልተወው ብዬ አለፍኩት። መልካም ተክሌ ቀና ጽሁፍ ለመጽሃፍ ያብቃህ።

  38. ሰላም 1 ሙርሲ ከግብጽ ሲመረጥ የወጣዉ መራጭ 33% ነበር 33% ከ 80 ሚሊዮን ህዝበ ወደ 24 ሚሊዮን ይሆናል ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሀል ሙስሊም ብራዘር ሁድ ህዝቡን አዋክቦም ሆነ አስፈራርቶት ሙርሲ አንድ 10 ሚሊዮን ህዝብ አግኝቶ ይሆናል ከዚህ አንጻር ከላይ የጻፍከዉን እንዴት ታየዋለህ? ወይም ደግሞ ሙርሲ በዲሞክራሲ የተመረጠ ነዉ ብለህ ታምናለህ?

  39. ፖለቲካችን እዉር ድምብሩ የጠፋዉ ለልጂ ተክሌ ስድብ ባወረዱ በተደራጁ ብሄረተኞችና ኢዝላሚስት ሃሳባቸዉን ለማሰረጽ በሚያካሂዱት ትግል ነዉ። ይሳደባሉ፤ያሸማቅቃሉ ይገድላሉ ባመዛኙ እነዚህ አጥፍቶ ጠፊዎች የጁዋርና የአህመዲን ጀበል ምልምሎች ናቸዉ። ይህን እዚህ ላይ በእንጥልጥል ትተን ዶ/ር ብርሀኑ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ መሳተፋቸዉ ለሳቸዉም ሆነ ለፖለቲካዉ መልካም አይመስልም አቅሙም የላቸዉም። ግለሰቡ ቀደም ባለዉ ጊዜ ኑሯቸዉ አሜሪካ ሁኖ ከተክለ ሰዉነታቸዉ ጀምሮ አሜሪካዊ ሁነዋል እሳቸዉ ዉጭ ሀገር እያሉ ከተወለዱ ልጆች ጋር ፖለቲካ ዉስጥ እሰጥ አገባ ታች ላይ ማለት ለጤንነታቸዉም ጥሩ አይመስለኝም። በየቦታዉ ቃለምልልስ ሲያደርጉ ምን ያህል እንደሚጨነቁ መገንዘብ ይቻላል።
    አንዳርጋቸዉም ሆነ ዶ/ር ብርሀኑ የሰለጠኑበት ፖለቲካ ከጊዜዉ ጋር ትቷቸዉ ሂዷል ፖለቲካም የእድሜ ገደብ አለዉ አረጋዊ በርሄ፤ዲማ ነገዎ፤ሌንጮ ለታ የነሱ ዘመን ሰዎች ቆም ብለዉ ቢያስቡ መልካም ይመስለኛል እንዴት ነዉ ይህን ነበልባል ትዉልድ እንደነዚህ አይነት ሰዎች የሚመሩት። ። ዶ/ር ብርሀኑ ተከታዮቻቸዉ ስለሳቸዉ ከሚያወሩት በስተቀር አንድም የሚናገሩት ልብ አይደርስም እዉነት ለመናገር በሃሳብ የተጎዱ ሰዉ ናቸዉ። አቅሙ ካላቸዉ ዝባዝንኬዉን ትተዉ አነድ ቢሮ ከፍተዉ ፕሮፌሰር የሚለዉን ማእረግ አስቀድመዉ አንድ ኮንሱልታሲ ግሩፕ ቢያቋቁም መልካም ይመስለኛል ሀብት አላቸዉ ይባላል ከሆነም አንድ በጎ አድራጎት ነገር ክፍተዉ አገር ይርዱ ፖለቲካዉ አልሰራላቸዉም። በተግባር ያልታየ ምሁርነት ማእረግ ብቻ ነዉ።

Comments are closed.

Share