በዋሽንግተንና አካባቢዋ ለምትገኙ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በሙሉ
የስብሰባ ጥሪ፤
የኢትዮጵያ ጥንታዊት እናት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬም ከችግር ውስጥ ነች ያለችው። የአዲስ አበባው ሲኖዶስ እጅግ የሚያሳዝንና ቤተ ክርስቲያናችንን ከመሰረቷ የሚያናጉ ተግባራት እየተፈጸመባት መሆኑን በሀዘን እናስበዋለን። ይህ ከመንፈሳዊቷ ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያናችን ስርዓትና ቀኖና በወጣና በማንለአብኝነት ስድስተኛ የፓትርያርክ ምርጫ በሚል የተያዘው ህገ ወጥ ሩጫም ለሕዝባችን የተሰወረ አይደለም።
ይህንን በተመለከተ ህጋዊው ስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈውን ውሳኔና የኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ተዋህዶ ምዕመናን ሀላፊነትን የሚያስገነዘብ መንፈሳዊ መመሪያ ለመስጠት ለመጪው ማርች 3 ቀን 2013 ብጹዕ አቡነ ሳሙኤል የዋሽንግተንና አካባቢዋ ሊቀ ጳጳስ መንፈሳዊ ስብሰባ
ጠርተዋል። በዚሁ መንፈሳዊ ሰብሰባ ላይ በመገኘት የብጹዕነታቸውን መመሪያ እንዲቀበሉ በአክበሮት ተጠርተዋል።
ቦታው – 1611 16ኛው መንገድ ኖርዝ ዌስት ዋሽንግተን ዲሲ – የቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፤
ሰዓት፦ የዕለቱ መንፈሳዊው ስነ ስርዓት ከተጠቃለለ ከ11 ኤኤም በሁዋላ ይሆናል።
ቀኑ – ማርች 3 ቀን 2013 /እ.ኤ.አ/።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ።