“ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ወያኔን እናስወግድ” – ግንቦት 7

(ዘ-ሐበሻ) ግንቦት 7 “ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ወያኔን እናስወግድ” ሲል ጥሪውን አቀረበ። ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው “በአገራችን ሰላም እንዲሰፍን እና መሠረታዊ መብቶቻችን ተከብረውልን መኖር እንድንችል ወያኔን ለማስወገድ ቆርጠን እንነሳ።” ብሏል።
“ወያኔ ወገኖቻችንን እየገደለ፤ አገራችንን እና ሕዝቧን በሽብር እያመሰ ነው። ከአርብ ሐምሌ 26 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ በአገራችን የተለያዩ ክፍሎች የወያኔ ሠራዊት ባልታጠቁና ባልተዘጋጁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥይት እያዘነበ ይገኛል። እስካሁን የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ማወቅ ቀርቶ መገመት እንኳን አዳጋች ነው። ሞስሊም ወገኖቻችን፣ በሕጋዊ መንገድ ለውጥ እናመጣለን ብለው የሚያምኑ ሰላማዊ ታጋዮች፣ ሕፃናትና አዛውንት የጥቃቱ ሰለባ ናቸው። ” ያለው የግንቦት 7 መግለጫ “የወያኔ ግንባር ቀደም የጥቃት ሰለባዎች ሰላማዊነታቸው ለማሳየት እጆቻቸውን አስረው ፍትህ ሲማፀኑ የነበሩ ዜጎች ናቸው። ሕግ የማያውቀው ወያኔን በሕጋዊ መንገድ ታግለን መሠረታዊ መብቶቻችንን እናስከብራለን ያሉ ወገኖቻችን በግፍ ተግደዋል፤ ተደብድበዋል፤ ተግዘዋል። የምዕራብ አርሲ ከተሞችና መንደሮች በአጋዚ ጦር ተወረዋል። አዲስ አበባም ውስጥ ዋይታ በርክቷል።” ሲል ይተነትናል።
“ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወያኔ ፋሽስታዊ እርምጃ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች ሁሉ የተሰማው መሪር ሀዘን ይገልፃል። እንደዚሁም ለአካል ጉዳት ለተዳረጉ፣ ለተዋከቡ፣ ለተረገጡ፣ ለጅምላ እስር ለተዳረጉ ወገኖቻችን ሁሉ በደረሰባቸው በደል መቆጨቱን ይገልፃል። ” የሚለው ግንቦት 7 ‘ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ የእምነትም ሆነ ሌላ ማናቸውን ነፃነት ሊኖር እንደማይችል የትናትናና የዛሬው ድርጊት አንድ ተጨማሪ ማስረጃ ነው። ወያኔ በሥልጣን መንበር ላይ ውሎ ባደረ መጠን እንዲህ ዓይነቱ መርዶ መስማታችን የማይቀር ነው ብሎ ግንቦት 7 ያምናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ መከራ እንዲያበቃ ወያኔ ከሥልጣን መወደግ አለበት፤ ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።” ብሏል።
የንቅናቄው መግለጫ በማጠናቀቂያው ላይም “ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሰላማችን ዋስትና የወያኔ መወገድና በምትኩ የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት መተካት ነው ብሎ ያምናል። ስለሆነም በአገራችን ሰላም እንዲሰፍን እና መሠረታዊ መብቶቻችን ተከብረውልን መኖር እንድንችል ወያኔን ለማስወገድ ቆርጠን እንነሳ።” ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰላማዊ የመብት ጥያቄ በሠለጠነ ውይይት እንጂ በአፈናና ግድያ መቼም ቢሆን አይፈታም!

5 Comments

  1. How are you are going to do it Dr. Berhanu? you are teaching in a University and living comfortable life with your family in USA? but the poor people to kill each other ? then be girgir you want to grab Arat kilo? I do not think it will work that way. It is very selfish of you Dr. I am hating your PHDS now. You do not think you are using your education to think analytically. But Good luck with your cyber army and cyber war. Mengedun cherq yargelwot, siltan must be given to selfless servants instead of to power thirsty people like you. Is it not enough 200 people you killed in 2005? you wanted more ?

  2. No Dr Brhanu is not Selfish do you think weyane is good for killing peaceful Ethiopians do you think Ethiopians are only tgray people God created us different but to live in that country equally. I guess you are weyane and you are selfish.
    I just pray that let we see the judgment of God come to our country oh God peace forgive us hating each other

Comments are closed.

Share