August 4, 2013
16 mins read

ልዩነታችን ውበታችን ነው ! የሚሊዮኖች ድምጽ በጂንካ

ግርማ ካሳ

ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ.ም

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ ሥር፣  ታላቅ ሕዝባዊ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ መጀመሩ ይታወቃል። በደሴና በጎንደር በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የሰላም፣ የመብት የእኩልነትና የነጻነት ጥያቄዎቻቸውን አስምተዋል።

በፊታችን እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም፣ የአንድነት ፓርቲ በአራት  ከተሞች  ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው። በመቀሌ፣ በባሀር ዳር፣ በአርባ ምንጭና በጂንካ ። በወላይታ ሶዳ ደግሞ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የዛሬ ትኩረቴ ጂንካ ላይ ይሆናል። ምናልባትም ብዙዎቻችን ስለጂንካ ላናውቅ እንችላለን።  «የት ነዉ ጂንካ ? ደግሞም ብዙ የማይታወቅ ከተማ አንድነት ምን ያደርጋል ? » የሚሉ ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ። እስቲ ስለጂንካ ትንሽ ላውጋችሁ።

ጂንካ በደቡብ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን ዋን ከተማ ናት። ከአርባ ምንጭ ወደ ታች ወረድ ብላ የምትገኝ የምታምር ከተማ። የደቡብ ኦሞ ዞን አርቦሬ፣ አሪ፣ ዳሰነች፣ ናያንያቶም፣ ሃመር፣ ማሌ፣ ሙርሲ ፣ ጸማይ፣ ቤና፣ ካሮ ፣ ቦዲ፣ ዲሚ የተሰኙ ብሄረሰቦች በብዛት የሚኖሩበት ዞን ናት። በዞኑ ዋና ከተማ ጂንካ፣  ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከነዚህ ብሄረሰቦች የተወጣጣ ነው። ደገኞች የሚባሉ አማርኛ ተናጋሪዎች ወደ 5% ብቻ ነው የሚጠጉት። ጂንካ እነዚህ ሁሉ ብሄረሰቦችን አንድ ላይ አድርጋ፣  በሰላም የምትኖር ከተማ ናት። ጂንካዎች ልዩነቶቻቸው ውበታቸው ሆኖ፣ ተፋቅረው፣ ተከባበረው የሚኖሩ፣ አንድነት ምን ማለት እንደሆነ  በኑሯቸዉ ያስመሰከሩ ናቸው።

በቀዳሚነት፣ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት፣ ወደ ጂንካ ያቀኑት፣ ሕዝቡን ስለ አንድነትና ስለኢትዮጵያዊነት  ሊያስተምሩት ሳይሆን፣ ከሕዝቡ አንድነትን ሊማሩ ነው።

አንድነት በቁጥር ትንሽ የሆኑ ብሄረሰቦች መብትን እንደሚያከብር፣ ማንም የማህበረሰብ አባል መደመጥ አለበት ብሎ የሚያምን፣ አንዳንዶች እንደሚሉት፣  የአዲስ አበባ ኤሊቶች ወይንም ነፍጠኞች ስብስብ ሳይሆን፣ አዲስ አበባ የሚኖሩትን ጨምሮ፣ የሃመሮች፣ የአሪዎች፣ የአርበሬዎች የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድርጅት መሆኑን ሊያሳይም ነው።

የሰላም፣ የእኩልነት፣ የዴሞክራሲ፣ የመብት ጥያቄ፣  የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነው። የሁሉም ብሄረሰቦች ጥያቄ ነው። ለዚህም ነው በደሴ ፣ በጎንደር የተሰማውን የነጻነት ደውል፣  በመቀሌ፣ በባህር ዳር፣ በአርባ ምንጭ ፣ በሶዶና እንዲሁም በጂንካ የሚኖረው ሕዝባችን እንደገና ሊያቃጭለው እየተንቀሳቀሰ ያለው።

ከሌሎች እያየን ያለነው በዘር የመከፋፈል ፖለቲካን ነው። «ከዚህ ዘር ካልሆንክ እኛ ድርጅት ዉስጥ አትገባም። ከዚህ ጎሳ ካልሆንክ የኛን መሬት ለቀህ ውጣ። እኛ ለዚህ ብሄረሰብ ብቻ ነዉ የቆምነው። የኛን ቋንቋ ካልተናገርክ ከኛ ጋር መስራት አትችልም..» የሚል፣ የጥላቻና ኋላ ቀር ፖለቲካን ነው። ለብሄረሰብ መብት ቆመናል ይሉናል። ግን በብሄረሰብ መብት ስም በደልና ግፍ በዜጎች ላይ ሲፈጸም ነዉ እያየን ያለነው።

የአንድነት ፓርቲ ፍቅርን፣ መቻቻልን ፣ አንድነትን ይዞ ተነስቷል።  እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በፈለገው ቦታ የመኖር፣ የመስራት፣ የመነገድ፣ የመምረጥ፣ የመመረጥ መብት አለዉ ብሎ ያምናል። ማንንም ኢትዮጵያዊ እንደጠላት አያይም። የአገዛዙ አገልጋዮችም እርሳቸው ነጻ መዉጣት ያለባቸው ናቸው ይላል። እነርሱን ነጻ ለማውጣትም ይታገላል።  ለነርሱም አበባን ያበረክታል። ማንንም በእምነቱ፣ በዘሩ፣ በሚናገረው ቋንቋ አይለይም። ሁሉንም ኢትዮጵያዊ፣ ኢትዮጵያዊነት በምትባል  ድንኳን ዉስጥ  ለማሰባሰብ እየሰራ ነው።

አንድ ተብሎ ነው ወደ ሁለት የሚደረሰው። እርግጥ ነው ከዚህ በፊት ወድቀናል። በስድሳ ስድስቱ ወቅት፣ የቆሰልነው ቁስል ጠባሳ አሁንም አለ። በዘጠና ሰባት በቅንጅት ጊዜ የተፈጠሩት ስህተቶች፣ አንገቶቻችንን አስደፍተውናል። ገዢው ፓርቲ ሕወሃት/ኢሕአዴግም  የትላንቱን  ስህተቶቻችን ላይ እያተኮረን፣ ወድቀን እንድንቀር ነው የሚፈልገው። በራሳችን እንዳንተማመን፣ በተስፋ መቆረጥና አይቻልም መነፈስ እንድንሞላ ለማድረግ እየደከመ ነው።  የምናደርጋቸውንም  ጥረቶች በማጣጣል፣ ርካሽ የፖለቲካ ጨዋታ ጀምሯል።

እንግዲህ ከባህር ዳር፣ ከጂንካ፣ ከመቀሌ፣ ከአርባ ምንጭና ወላይታ ሶዳ ወገናችን ጎን እንቁም። በቦታዉ ያለን ሰልፉን እንቀላቀል። በሩቅ ያለን፣ በአካባቢው የምናውቃቸው ወገኖችን በስልክ በኢሜል በፌስቡክ በመሳሰሉ እያገኝን ወደ ሰልፉ እንዲወጡ እናበረታታ። ያ ብቻ አይደለም የተዘጋጁ ፔቲሽኖችን በመፍረም፣ የገንዘብ እርዳታ በማድረግ ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን !

Go toTop